What is the meaning of (dink sirota) my wife is pregnant and will soon put to bed, I'm naming my baby with a beautiful Amharic name, suggest three, like praise, God fearing, love, thanks
I was high school student 15 years back. I can't understand Amharic by then. They used to open this song again and again in Our NGO Library ( CMF Library ) . I fell in love with this song by that time and really wished if I one day understand what it really meant! Now, I sing it for my friends and family joyfully. God bless you more for this generational gift, Azebiye. Kahine ❤️❤️❤️❤️.
ዴቭ ግን የእውነት ትውልድ አፍርተሃል። በጣም ድንቅ እና ጥርት ያለ ስራ ሰርታችኋል ማዳመጥ ለማቆም ተቸግሬ አለሁ። What a cross generational blessing it is....!!! sad for not attending the concert.
ከነ አሮን ክነት የኢየሱስ ይበሌጣል🎉🎉❤❤
እነዚህን የመዝሙር ቪዲዮዎችን የተመለከታችሁ፣ባርኮታችሁንና ፍቅራችሁን በፅሁፍ ለነገራችሁኝ ሁለ እግዚአብሔር አምላክ ይባርክልኝ ።በጣም አመሰግናለሁ!! እወዳችሗለሁ
Amen
ua-cam.com/video/AWGjpVBNY5s/v-deo.html
Azebye, wedededded....my sister in Christ.
I am listening your song for thanks giving day while I am giving thanks to Gid fir all he does to me!!!!
መልካም የምስጋና ቀን
I'm a Muslim but I love your songs Azeb. Stay blessed!
❤❤❤❤
እኛ ወንጌላውያን ዓይመማኖታችን ይሄ ነው….ኢየሱስ ካህነናችን ነው! ኢየሱስ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው! በእግዚአብሔር ፊት ያቆመን ያከበረን የበዛው የእግዚአብሔር ፀጋ እና በእኛ ላይ የገነነው ምህረቱ ነው የምትል ናት ስብከታችን!
ከወንጌል ዓይማኖት ውጪ ያላችሁ በመልካም ሥራ ብዛት ለመጽደቅ ምታትሩ ወደ ፀጋው ወንጌል ፈጥናችሁ ምጡ …”የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የህግ ፍፃሜ ነው።”
I'm Orthodox
ለመጀመሪያ ነው ሳይሽ።ለመጀመሪያ ነው ስሰማ የመጀመሪያውን መዝሙር ።በእውነት ውስጤ ሃሰት ተሞላ ። መዝሙር እጽፋለሁ እና ስለ ክህነቱ እና ስለ አንድ ጊዜ በደሙ ገብቶ በአብ ቀኝ እንደተቀመጠ የሚያስረዳ ነው ...የእግዚአብሔር ፍቃድ ከሆነ እኮ አንድ ቀን እንዘምራለን አብረን ኣ የጌታ ታዓምር አያልቅምና።
ተባረኩ
ሊቀ ካህናችን ጌታ ከፍ ይበል።
እውነቱ በርቶልሻል ዳስ ይላል ተባረክህ
❤❤❤❤❤❤❤getaa yi wedishali ihete iheni getaa taqabayi
@@fenetbedo3224 ሶስት ጊዜ ተቀበልኩት ግን back አደረኩ ሰላሜ ግን የለም ደስታም የለም ያለሁበት በጣም ከባድ ሁኔታ ውስጥ ነው ።one day you will hear my story !😢pray for me
Kiristose Hiwote mangade ena birhane nw
Getaymsgn
ተባረኩ አለማት ላይ ያሉ ሰዎች በጌታ ስም ይገዙ ኑሩልኝ❤❤❤
በሞት ያልተሻረ በሞት ያልተገታ
በሰማይም ቀጥሏል ክህነቱ የጌታ
ሌሎቹ እንዳይኖሩ ሞት ከልክሏቸዋል
ከነአሮን ክህነት የኢየሱስ ይበልጣል
ካህኔ እንደመልከጼዴቅ
ካህኔ ለዘላለም ሹም ነህ
ካህኔ ለኔም ሕይወት መዳን
ካህኔ ምክንያቱ አንተ ነህ
ካህኔ በማይጠፋው ክህነት
ካህኔ በማይሽረው ሞት
ካህኔ የምትማልድልኝ
ካህኔ ቆመህ በአብ ፊት
ምን እላለሁ ከምስጋና ሌላ
ምን እሰጣለሁ ከማመስገን በቀር
በማለዳ በቀትር በማታ
አምላኬ ሆይ ልበል ክበር ክበር (2x)
ካህኔ በአብ ቀኝ ያለሀው
ካህኔ የነፍሴ ጠበቃ
ካህኔ መከራዬ እንዲቆም
ካህኔ ሀዘኔ እንዲያበቃ
ካህኔ የጥልን ግድግዳ
ካህኔ በሞት አፈረስህ
ካህኔ ለበደሌ መስዋዕት
ካህኔ ደምህን አፈሰስህ
በሞት ያልተሻረ በሞት ያልተገታ
በሰማይም ቀጥሏል ክህነቱ የጌታ
ሌሎቹ እንዳይኖሩ ሞት ከልክሏቸዋል
ከነአሮን ክህነት የኢየሱስ ይበልጣል
የካህናት አለቃ የበጎች እረኛ
የእውነተኛዋ ድንኳን መካከለኛ
በኔ ፈንታ የሞተ የሆነልኝ በዛ
ነፍሴ በጣም ረክታለች ለእርሱ ስትገዛ
መድህኔ የመቀበርያዬን
መድህኔ ጉድጓድ የደፈንከው
መድህኔ የሕይወቴን ጨለማ
መድህኔ ገለል ያደረከው
መድህኔ በሞትና በኔ
መድህኔ መካከል ገብተህ
መድህኔ ሕያው አደረከኝ
መድህኔ አንተ ተችሎህ
ምን እላለሁ ከምስጋና ሌላ
ምን እሰጣለሁ ከማመስገን በቀር
በማለዳ በቀትር በማታ
አምላኬ ሆይ ልበል ክበር ክበር (2x)
መድህኔ ዛሬስ ብርሃን ነው
መድህኔ ቀን ሆኖ ለነፍሴ
መድህኔ ባንተ ተሰበረ
መድህኔ ለቅሶና ትካዜ
መድህኔ ፍጻሜዬ እንዲያምር
መድህኔ የመጨረሻዬ
መድህኔ አንተን መጠጋቴ
መድህኔ ልክ ነው ምርጫዬ
ምን እላለሁ ከምስጋና ሌላ
ምን እሰጣለሁ ከማመስገን በቀር
በማለዳ በቀትር በማታ
አምላኬ ሆይ ልበል ክበር ክበር
Tebareki
Thank you
Tebareki azu ❤❤❤
❤❤❤❤❤
እግዚአብሔር ይባርክሽ:: በዝማሬዎችሽ ሁላችንም ተባርከናል! ካህኔ my favorite song! 💜
Fenu yet teftesh new kingdom sound atetayem
ፍና እንቺም በጌታ በረዳሽ ፀጋ የአዘብ ፍለግ በመሆንሽ እግዚአብሔር አመሰግናለሁ ።God bless you
My favorite song too! Bless you both!
አንቺንም እንወድሻለን
@@tinsaetariku9489 fsltljj
ይህን መዝሙር ስሰማ ነፍሴን የሚሞላትን የሐሴት ብዛት ለመግለጽ ይከብዳል። 😭
ካህኔ .... በአብ ቀኝ ያለኸው፤
ካህኔ .... የነብሴ ጠበቃ፤
ካህኔ .... መከራዬ እንዲቆም፤
ካህኔ .... ሀዘኔ እንዲያበቃ፤
ካህኔ .... የጥልን ግድግዳ፤
ካህኔ .... በሞትህ አፈረስክ፤
ካህኔ .... ለበደሌ መስዋዕት፤
ካህኔ .... ደምህን አፈሰስክ፤
ሀሌሉያ ሀሌሉያ ሀሌሉያ !!!! 🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌😍😍😍😍❤❤❤❤ my favorite song!
አዚቲ ስላንቺ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን!!
we love u😘😘😘😘😘
God bless you 🙂🙂
@@muluayele8381😮😮 no I'm mm hmm FM en ok rlc RV ex ex TN RV be GM TN GM TN um hmm hmm TN um I'm hmm TN TN
RV to um RV um um hmm in I'm😮😮😢😮
What is the meaning of (dink sirota) my wife is pregnant and will soon put to bed, I'm naming my baby with a beautiful Amharic name, suggest three, like praise, God fearing, love, thanks
@@davouboniface3449misgana (praise), fikir (love)
@@davouboniface3449(Dinik sitota) means in English special gift.
አንድ ቀን በአካል እንደማገኝሽ እርግጠኛ ነኝ...ከዚህ በፊት በአካል ከአንቺ እና ከባለቤትሽ ጋር 1995/96 ጋር በSIM Ethiopia በኩል ላንጋኖ ለአስራ ምናምን ቀን እኛን አገልግላቹናል እኔን ጨምሮ ብዙቻችን የጌታ እየሱስን መንገድ አልጀመርንም ነበር...ነገር ግን ብዞቻችን አሁን አብዛኞቹ በጌታ ቤት አለን...በእናንተ አገልግሎት ተባርከናል...ደሞ እኛ ቤት ውስጥ ማንም በጌታ ሳይሆን ካሴትሽ ተገዝቶ ይደመጥ ነበር...አሁንም ከምርጦቹ መዝሙር ሊስቶች ውስጥ ያንቺ ካሴቶች አሉ...ከላንጋኖ ስንመለስ አቃቂ አካባቢ ስትወርዱ ከባለቤትሽ ባርች ጋር በፍቅር ነበረ የተለየናቹ... እህታችን አዜብ ኃይሉ ባንቺ የሚሰራው ጌታ ብዙዎችን አስመልጣል 😇😇😇
❤
❤❤❤
❤
ሊቀ-ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ለአንተ ብቻ ይሁን 💜💜💜
❤❤❤
ፀጋህ በዝቶ ከብርያለሁ
ዘመን መቶ ታስብያልሁ🎵🎶❤
እልልልልልልልልልልል ካህኔ ኢየሱስ አንተ ነህ
አዙዬ ተባረኪልኝ 🙏🙏💎💎💎💎🥰🎸🎻🎬🎤🎹🎼🥁
ሱሬ እንወድሀለን!!!
ይህን መዝሙር ከሰማሁ ሁሌ በልቤ የመዳኔ ነገር እና የመነቃቃት መንፈስ ይመጣል😊 ይህን የምታነቡ የጌታ የመስቀሉን ፍቅር ፣ ከነበርንበት ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ብርሃን የማውጣቱን እና በእውነተኛ ፍቅሩ እኛን የመዉደዱ በቃ በፅሁፍ የመግለጽ አቅምም የለኝም ይህን ሁሌ በልብችን እያሰብን ይህን ጌታ እናመስግነው 🙏🙏 መድህናችን ኢየሱስ ❤ ብቻ አዚ ተባረኪልኝ❤🙏🙏
❤❤❤
አሜን
ይሔንን መዝሙር የሰማችሁ ዘመናችሁ ይባረክ አሜን 💚💚💚♥️♥️♥️♥️
amen bro
Amen 🙏
Amennnnnnnn
Amen
አሜን
I am ortodox but this song❤❤ keber hulem legeta le eyesus chrstos geta yebarkesh ehetachen😊
ዕብራውያን 7
²² እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል።
²³ እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለ ከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤
²⁴ እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤
²⁵ ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።
ሊቀካህናት ኢየሱስ ክብር ላንተ ይሁን 🙏🏿
ቢኒ ወንድማችን ተባረክ
“የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ወደ ሆነው ወደ ኢየሱስ፣ እንዲሁም ከአቤል ደም የተሻለ ቃል ወደሚናገረው ወደ ተረጨው ደም ደርሳችኋል።”
- ዕብራውያን 12፥24 (አዲሱ መ.ት)
ቢኒ ጌታ በረዳንክ ፀጋ የአዘብ ፍለግ ተከታህ በመሆንክ እግዚአብሔር አመሰግናለሁ ።God bless bro
9
@@efoyafrica-psychologistama2633 ።።።ለቸለደፀፀፀፀፀፀፀፀ
ሁሌም ልዩ ፀጋ አለሽ ተባረኪልን እንወድሻለን❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
የማይሻር ክህነት የኢየሱስ ክህነት ነው!
ሊቀ ካህን ኢየሱስ.
amen ዉዴ በምትወጃት እናትሽ subscribe አርጊኝ በቅንነት፣ጀማሪ ነኝ
ዕብራውያን 7
²² እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል።
²³ እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለ ከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤
²⁴ እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤
²⁵ ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።
ሊቀካህኔ ኢየሱስ ክብር ላንተ ብቻ ይሁን 🙏🏼 ባንተ በኩል ወደ አብ መግባት ሆነልን 🙏🏼🙏🏼
(ወደ ዕብራውያን ምዕራፍ 7)
----------
24፤ እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ #ክህነት አለው፤
25፤ ስለ እነርሱም #ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ #ሊያድናቸው ይችላል።
26፤ ቅዱስና ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት ከኃጢአተኞችም #የተለየ #ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ #ካህናት ይገባልና፤
27፤ እርሱም እንደነዚያ #ሊቃነ #ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና።
Geta yebarkeh. Thank you for sharing this verse 🙏🏽
geta ybarkh wendme❤❤❤❤❤❤❤❤😮
ከን አሮን ክህነት የኢየሱስ ይበልጣል 🙌
❣❤❤
አዜቢና ብሩክ ሴት ባንቺ ላይ ስላለው ፀጋ እግዚአብሔር ይባረክ ሁሌም ዘምሪ ለምልሚልኝ የኔ ውድ ❤️❤️🙏🙏
Dear ❤❤❤
ካህኔ
በሞት ያልተሻረ በሞት ያልተገታ
በሰማይም ቀጥሏል ክህነቱ የጌታ
ሌሎቹ እንዳይኖሩ ሞት ከልክሏቸዋል
ከነአሮን ክህነት የኢየሱስ ይበልጣል
ካህኔ እንደመልከሰደቅ
ካህኔ ለዘላለም ሹም ነህ
ካህኔ ለኔም ሕይወት መዳን
ካህኔ ምክንያቱ አንተ ነህ
ካህኔ በማይጠፋው ክህነት
ካህኔ በማይሽረው ሞትን
ካህኔ የምትማልድልኝ
ካህኔ ቆመህ በአብ ፊት
ምን እላለሁ ከምስጋና ሌላ
ምን እሰጣለሁ ከማመስገን በቀር
በማለዳ በቀትር በማታ
አምላኬ ሆይ ልበል ክበር ክበር (2x)
ካህኔ በአብ ቀኝ ያለሀው
ካህኔ የነፍሴ ጠበቃ
ካህኔ መከራዬ እንዲቆም
ካህኔ ሀዘኔ እንዲያበቃ
ካህኔ የጠመድ ግድግዳ
ካህኔ በሞት አፈረስህ
ካህኔ ለበደሌ መስዋዕት
ካህኔ ደምህን አፈሰስህ
በሞት ያልተሻረ በሞት ያልተገታ
በሰማይም ቀጥሏል ክህነቱ የጌታ
ሌሎቹ እንዳይኖሩ ሞት ከልክሏቸዋል
ከነአሮን ክህነት የኢየሱስ ይበልጣል
የካህናት አለቃ የበጎች እረኛ
የእውነተኛ መካከለኛ
በኔ ፈንታ የሞተ የሆነልኝ በዛ
ነፍሴ በጣም ረክታለች ለእርሱ ስትገዛ
መድህኔ የመቀበርያዬን
መድህኔ ጉድጓድ የደፈንከው
መድህኔ የሕይወቴን ጨለማ
መድህኔ ገለል ያደረከው
መድህኔ በሞትና በኔ
መድህኔ መካከል ገብተህ
መድህኔ ሕያው አደረከን
መድህኔ አንተ ተችሎህ
ምን እላለሁ ከምስጋና ሌላ
ምን እሰጣለሁ ከማመስገን በቀር
በማለዳ በቀትር በማታ
አምላኬ ሆይ ልበል ክበር ክበር (2x)
መድህኔ ዛሬስ ብርሃን ነው
መድህኔ ቀን ሆኖ ለነፍሴ
መድህኔ ባንተ ተሰበረ
መድህኔ ለቅሶና ትካዜ
መድህኔ ፍጻሜዬ እንዲያምር
መድህኔ የመጨረሻዬ
መድህኔ አንተን መጠጋቴ
መድህኔ ልክ ነው ምርጫዬ
ምን እላለሁ ከምስጋና ሌላ
ምን እሰጣለሁ ከማመስገን በቀር
በማለዳ በቀትር በማታ
አምላኬ ሆይ ልበል ክበር ክበር (2x)
Geta yibarkeh wodeme 🙏🙏
Thank you;God bless you.
10q dave
10q
ተባረክ!!
ምን እላለሁ ከምስጋና ሌላ ❤ተመስገን ሊቀካህኔ❤
Eu sou de Moçambique, mas gosto muito de ouvir músicas de Azeb. Essas músicas me inspiram muito. Que Deus lhe abençoe, a todos irmãos...
ለካህናት አለቃ ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ሁሉ ይገባዋል
ይህ መዝሙር ሰምቼ አልጠግብም ኑሪ ለዘላለም ❤❤😊😊
እዉነትም መዝሙር ከጌታ ጋር የመገናኛ ቋንቋ ነው ሲባል ። በዚ መዝሙር ልባችን በሃሴት ሶሞላ ታወቀን እኮ ኣባቴ !! መቼም ሁልግዜ ለጌታ ክብር ስትዘምሪ ኑሪ ኣዜ 1ኛ ነሽ ........
🇪🇷🇪🇷🇪🇷🇪🇷🇪🇷
መዝሙሮችሽ ድርሰቶች አይደሉም ጌታዬ መንፈስ ቅዱስ የሰጠሽ ናቸዉ ።ካህኔ የሚለውን ዝማሬ በመሰማሁ ቁጥር በመንፈስ ቅዱስ እጥለቀለቃለሁ ጌታ 100 እጥፍ ይባርክሽ።
ሰምቼ ኮ አልጠግብም ኮ መዝሙሮችሽን ተባረክልኝ
We love you siz here in kenya plz translate your songs so that we can also be blessed more God bless you more
አዚ ለበጉ ክብር የሚሆን አዲስ ቅኔ ከአንደበትሽ አይታጣ። ጌታ ኢየሱስ አብዝቶ ይባርክሽ🙏‼️
I was high school student 15 years back. I can't understand Amharic by then. They used to open this song again and again in Our NGO Library ( CMF Library ) . I fell in love with this song by that time and really wished if I one day understand what it really meant! Now, I sing it for my friends and family joyfully. God bless you more for this generational gift, Azebiye. Kahine ❤️❤️❤️❤️.
Blessed
❤❤❤❤❤❤ካህኔ❤❤❤❤❤❤ የነብሴ ጠበቃ ።ምን እላለው ከማመስገን በቀር ❤❤❤የ5 ዓመት ታላቅ ሴት ልጅ አለችኝ ስመሽ ካህነ መዝሙር ትላለች በማለዳ ካህነ የምለውን ክፈት ትላለች ጌታ ይባረክ አሁን ሙሉ መዝሙሩን እኩል ትዘምራለች ።ተባረክ የጌታ ባሪያ ዘማሪት አዘብ ❤❤❤❤❤❤ ልጄ በዝሁ ሞገስ እንድትገለጥ ፀልይላት ❤❤❤
አስረግጣ ዘመረች ጌታ ይባርካት አዜብን
አሜን አሜን አሜን እየሱስ ጌታ ነው ክብር ሁሉ ለእየሱስ ክርስቶስ ይህን ካህኔ እየሱሴ ሃሌሉያ ክብር ጌታ እየሱስ እልልልልልል በእየሱስ ስም ትባርክህ ❤❤❤
አዜብ ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የተሰጠች በረከት ነች እኔ መዝሙሮቻን ሰስማ ውዬ ባድር ሰብከት እኮ ነው ውሰጡ የመንፈሰ ቅዱሰ ህልውና አለው ሁለመናዊ ወርሸፕ ነው አልጠግበውም አዜብዬ የጌታ ባሪያ ጌታ እየሱስ አብዝቶ አብዝቶ ይባርክሸ ! የክርስቶስ ሌጀንድ ብዬሻለው !
በተከታታይ ሁለት ሳሚንት ሲሰማና ስዘምር ነበር አሁን ዩቱብ ስገባ ተለቆ አገኘሁ በጣም ምወደው ዝማሬ ነው አዚዬ የተባረክሽ ሴት በረከታችን ከዚህ በላይ ፀጋ ይብዛልሽ እወድሻለሁ❤🥰
ሊቄ---ካህኔ በአብ ቀኝ ያለሄዉ ካህኔ የነብሴ ጠባቅ!
ሊቄ-ካህኔ መከራዬ እንድቆም ካህኔ ሀዜኔ እንድያበቃ!
ሊቄ-ካህኔ የጥልን ግድግዳ ካህነ በሞት አፈረስህ!
ሊቄ-ካህኔ ለበደለ መስዋት ካህነ ደምን አፈሰስህ!
ምን እላለሁ ከምስጋና ሌላ ?
ምን ሰጣለሁ ከማመስገን በቀር ?
ሀለሉያ!!!!!!!!!
የተከበርሽ ውድ
ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ
ሊቀ ካህናት፣ የእግዚአብሔር አብ ልጅና ቃል፣ መንገድ፣ እውነት፣ የዘላለም ሕይወት፣ ትንሣኤ፣ የጌቶች ጌታ የነገሥታት ንጉሥ፣ አልፋና ዖሜጋ፣ ድንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል፣ ተስፋ፣ እምነት፣ ፍቅር፣ ወዳጄ ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል፣ በቅርቡም ይመጣል!
ጌታችን ይክበር! ሃሌ ሉያ!
ካህኔ በሞት ያልተሻረ በሞት ያልተገታ በሰማይ ቀጥሏል ክህነቱ የጌታ እንደዚህ እየዘመርን የመንግስቱ ወራሽ ያርገን ❤️🙏
ሊቀ ከህናት ኢየሱስ ክበር ላንተ ይሁን 🙌
ጌታ ኢየሱስ ሆይ ተመስገን አንተን እንዳዉቅ ስለ እርዳህኝ ሁሌም አመሰግናንሀለዉ🙏🏻🙏🏻🙏🏻
ሊቀካህናችን ኢየሱስ🙏💥
አዚቲ ብሩክ ነሽ ወድሻለው😍
ካእኔ የጥልን ግርግዳ ካእኔ
በሞት አፈረስህ ካእኔ
ለበደሌ መስዋዕት ካእኔ
ደም አፈሰስህ እልልልልልል
ጌታ አብዝቶ አዜብዬ ይባርክሽ
👏👏👏👏❤️❤️❤️❤️❤️
Powerful You are Blessed
WoW👏👏👏❤️❤️❤️❤️
አሜን አሜን ይህን መዝሙር በህይወቴ አይቼዋለሁ። የጌታ ስሙ ይክበር።
ካህኔ .... በአብ ቀኝ ያለኸው፤
ካህኔ .... የነብሴ ጠበቃ፤
ካህኔ .... መከራዬ እንዲቆም፤
ካህኔ .... ሀዘኔ እንዲያበቃ፤
🙏🙏🙏
ሞት ያልከለከለው ካህኔ
ኢየሱስ ነው ለኔ
አዚቲ በረከታችን ነሽ ይብዛልሽ😍
ክዛሪ 19 አመት በፊት አዜብ ሃይሉን የማየት አድል አጋጥሞኝ ነበር። አኔ ከ 8 አመታት የአሜሪካን ሀገር ቆይታ ቡሃላ ሀገር ገብቼ ጉዳይ ኖሮኝ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ሄጄ ነው በአጋጣሚ ያየዋት። ቀጠነ ብላ አረዘም ያለች ልጅ አግር ነበረች። ነጭ የሚያንጸባርቅ አና አረጅም ቀሚስ ለብሳ ነበር። በሰዎች ተክባ ነበር። ፊቱዋ ላይ ደስታ አና ፈገግታ ይነበብ ነበር። በአጋጣሚ ስንተያይ ፈገግታዋ አልተለያትም ነበር። አሁን ሳስበው አሷ በዛ ግዜም ታዋቂ ነበርች አኔ ውጭ ስለነበርኩ ያው ነገሩን አላወኩም። ሁኔታዋ፤ አለባበሷ፡ ሰላሟ፤ ፈገግታዋ ሁሉ ልክ ትናት አንደሆነ ሁሉ አይኔ ላይ ድቅን ብሎ ይታየኛል። ይህን መዝሙሯን ሳዳምጥ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ይወርዳል።
21 እነርሱም ያለ መሐላ ካህናት ሆነዋልና፤ እርሱ ግን። ጌታ። አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ ብሎ ማለ አይጸጸትም ብሎ በተናገረለት ከመሐላ ጋር ካህን ሆኖአልና ያለ መሐላ ካህን እንዳልሆነ መጠን፥
22 እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል።
23 እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለ ከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤
24 እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤
25 ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።
(ዕብራውያን - ምዕራፍ 7)
ካህኔ የጥልን ግድግዳ ካህኔ በሞትህ አፈረስክ፣ ለበደሌ መስዋዕት ደምህን አፈሰስክ፣ ተባረኪ አዜብ
ሀሌሉያ ኢየሱስ እናመሰግንሀለን ለዘላለማዊው ሊቀ - ካህንነተህ።
እውነት ነው መተማመን መጔደድ ባንተ ነው ሁሉ ባለህ ሁሉን በፈጠርከው ኢየሱስ
የዘለአለም ካህነ ኢየሱስ ክብር ለአንተ ይሁን 🙏🙏🙏🙏
ገታ ይባርክሽ አዝቡዋ
እሰይ የተወደደሽ በጌታ እህቴ እንኳንም መዝሙሮች በራስሽ እደገና በመዘመሩ ተደስቼአለሁ ልዩ መስዋአት እንከን የሌለው የሚለውን ዝማሬሽን እባክሽ ዘምሪው በብዙ የተባረኩበት ነው በተረፈ ዘመንሽ ልጆችሽ ትዳርሽ እየሱስ ዳግም እስኪመጣ ድረስ ተባረኩ ሻሎም
ዘመን ተሻጋሪ ዝማሬ ቢኖር !!ይኸው ነዉ ጌታ ዘመንሽን አገልግሎትሽን ይባርክ
Ooooo geta hoyi simih biruk yehun getan yeteqebelkubat ehe. Mulu mezmur new ehewu zare 8 amet honeng bageta kahonkugn geta yibarek sela zemarit azebiye getan ejig arige akebralwu hulem malselechish zamari kebizochun anduwa nesh uuuffff birrrrrrkkkkk bay we love you ❤❤❤❤ halelujaaaaa elililili
ተባረኪ ከዚህም በላይ ለምልሚ
በአብ ቀኝ ያለውን ልጁን ኢየሱስን አሳይቶኛል ❤ አዜብዬ infact You are a blessing for us we love you so much
ካህን ሊቀካህኑ እሱ ብቻ የምን የሃይማኖት ቀሳውስት ውሽት አምልጡ ሃይማኖተኞች ካህን ጌታ ሊቀካህኑ እየሱስ ተባረኪ
ዕብራውያን 7
²² እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል።
²³ እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለ ከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤
²⁴ እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤
²⁵ ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።
አዜብዬ አመለጥኩት3 መሐላውን ቃልኪዳኑን አፈረስኩት የሚለውን መዝሙር እናቴ ን አስታውስበታለሁ ጌታ ዘመንሽን ይባርከው የለምልምሽ
ምን እላለሁ ከምስጋና ሌላ
ምን እሰጣለሁ ከማመስገን በቀር
በማለዳ በቀትር በማታ አምላኬ ሆይ
ልበል ክበር ክብር 🙏🙏🙏🙏
Azebye our blessing ❤️❤️❤️በብዙ ተባረኪ❤️❤️❤️
አዜብዬ ቀሪ ዘመንሽ ሁሉ የተባረከ ይሁን።
ያነሳሽው ጉዳይ የደህንነታችን መነሻ የሆነውን የአዲስ ኪዳን መሰረት ነው።
መንፈስ ያለበት ዝማሬ።
You are a blessing for this generation.
We ❤ u.
አዜብዬ አንቺን ለዚህ ትውልድ በረከት ነሽ ብርክክ በይልኝ 🙏🙏
ካህኔ .... በአብ ቀኝ ያለኸው፤
ካህኔ .... የነብሴ ጠበቃ፤
ካህኔ .... መከራዬ እንዲቆም፤
ካህኔ .... ሀዘኔ እንዲያበቃ፤
ካህኔ .... የጥልን ግድግዳ፤
ካህኔ .... በሞትህ አፈረስክ፤
ካህኔ .... ለበደሌ መስዋዕት፤
ካህኔ .... ደምህን አፈሰስክ፤
ሀሌሉያ ሀሌሉያ ሀሌሉያ !!!!
የብዙዎቻችንን ህይወት የሚነካ ዝማሬ ነው ። በእውነት ተባረኩ ። ፀጋው ይብዛላቹ ።
ጌታ ኢየሱስ ዘመንሽን ይባርክ ክብሩ ለካህንናችን ለመድሃኒታችን ይሁን
እ/ር ዘመንሽን በምስጋና የተሞላ ያርገው ተባረኪልን
ወጣቶች በርቱ በሃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ በመከራ ፅኑ አይተዋችሁም አይጥላችሁም ወጣትነትና ክርስትና የመአበል ጉዞ ነው ብቻ ከመንፈስ፡ቅዱስ ጋራ ሁኑ ወደ ወደቡ ትደርሳላችሁ፡፡❤❤❤❤❤❤❤❤❤
ዴቭ ግን የእውነት ትውልድ አፍርተሃል። በጣም ድንቅ እና ጥርት ያለ ስራ ሰርታችኋል ማዳመጥ ለማቆም ተቸግሬ አለሁ። What a cross generational blessing it is....!!! sad for not attending the concert.
ከነአሮን የሚበልጥ ክህነት ያለው ኢየሱሴ እወድሀለው ተባረክል ህይወቴን ቀለል አረክልኝ ተባረክልኝ እወወወወወወወድድድድድድድድሀሀሀሀሀለለለለውውውውውው
ኡኡኡኡኡ በእውነት ውስጤ በጣም ይቀጣጠላል መዝሙሮችሽን በሰማሁ ቁጥር. አዚዬ እግዚአብሔር ቀሪ ዘመንሽን ይባርከው🥰🥰🥰🥰
በእዳንች ባሉ እህቶች በፊት ለፊት ተገልግለና አሁን ቀጣፊ ሀስተኛ ነብያት ምድሪቱን አስቀየሟት አዜብየ ተባረኪልን።ደሴ ላይ አገልገለሽናል
እህት አዜብ ሀይሉ ጌታ ዘመንሽን ይባርክ መዝሙሮችሽ ውስጥ ጠልቆ የሚገባ ነው ሁሌ እሰማለሁ ጌታ ጨምሮ ጨማምሮ ይባርክሽ!!!
ለክኅነቱ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ ምንም አይነት requirement የማያስፈልገው እውነተኛው ሊቀ ካኅናችን ኢየሱስ❤❤❤❤❤☝✋✋👐👐👐👐
ጌታዬ ሆይ ክበር ክበር መድሀኒቴ ሆይ ክበር ክበር። መድህናችን አየሱስ ብቻ ነው ከምስጋና ውጪ ምንሰጠው የለንም ሚስማማ አለ🥰🙏
ክብር አምልኮ ውዳሴ ለሚገባው ብቻ ክብር ለአንድ አምላክ ክብር ለታረደው መድህናችን እንዴት እጅግ ደስ ያሰኛል አዜብ ዘመንሽ የብርሀን ነው ይብዛልሽ ይጨምርልሽ ዋጋሽ በሰማይ እልፍ ይሁን
እግዚአብሔር ይባርክሽ በዚህ መዝሙር ብዙዎች ተባርከናል ብዙዎች ደግሞ ከጨለማ ወደ ብርሀን ተመልሰናል ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይባረክ::
አሜን አሜን አዜብየ ዜመንሽ ይባርክሽ
መንፈስ የምያርስ መዝሚር አሜንንንን❤
እግዚአብሔር በምህረቱ ባለፀጋ ነው።የእንደገና አምላክ ነው ክብር ከዘላለመ እሰከ እሰከለዘላለም ድረስ ለስሙ ይሁን አሜን።
ሃይ አዜብ መዝሙርሽን ደጋግሜ እሰማለሁ እጅግ ሲበዛ ግሩም ነው :: የድምፅሽ አወጣጠና አወራረድ አንዲሁም ቅላፄሽ ድንቅ ነው ጌታ ይባርክሽ::
ጌታ ይባርክሽ አዜብ ! ኢየሱስን ያለ መጋረጃ በግልፅ ያሳየ መዝሙር ክብር ለጌታ ይሁን ።
በርቺ የጌታ ፀጋ ይብዛልሽ ❤!
የተወደድሽ aziti ጌታ ኢየሱስ ይባረክሽ
ሊቀ ካህናትም ሁሉ ዕለት ዕለት እያገለገለ ኃጢአትን ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን እነዚያን መሥዋዕቶች ብዙ ጊዜ እያቀረበ ቆሞአል፤
ወደ ዕብራውያን 10 : 11
እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፥
ወደ ዕብራውያን 10 : 12
ጠላቶቹም የእግሩ መረገጫ እስኪደረጉ ድረስ ወደ ፊት ይጠብቃል።
ወደ ዕብራውያን 10 : 13
አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና።
ወደ ዕብራውያን 10 : 14
በዘመኔ በረከታችን ነሽ ❤ አዜቤ 😍
በሰማይም ቀጥሏል ክህነቱ የጌታ
ሌሎች እንዳይኖሩ ሞት ከልክሏቸዋል
እሰይእሰይ እልልልልልልልልል ይገባሀልየኛጌታ ተባረኪ የኔውድእህት ላይለቀንየያዘን ያባትነትፍቅሩን ሁልጊዜ የሚያሳየን ይክበርይመስገን እኛምላናፈገፍግ ተከትለነዋል ክብርይብዛለት የረፍታችን ወደብሆይ ተባረክ በእውነት ድቅዝማሪነው
ሊቀ ካህኔ እየሱሴ🥰🥰🥰
ድንቅ አምልኮ ነው ተባረኪ
This is one of the best spritual songs of the century.
እንደንደው አዜብዬ እግዛብሄር ይባርክሽ 3:39 ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊❤❤❤❤❤❤❤❤❤
በጣም የምወደው መዝሙር ነው❣️
#Stay_Blessed😇🙏🙏🙌🙌
ሊሊ እግዚአብሔር ይባርክሽ በጣም ነው መዝ ሞርሽ ይባርከኛል
አዜብ ሀይሉ
ስላም የሀገሬልጆች ባሁኑስአት አገራችን ስላሞን አታለች ሁላችንም በየሀይማኖታችን ዲአ እናዲርግ በጦርነት የስቱ ይወት የስቱ ህፃናት የስቱወጣህ ህይወት ይቀጠፋል ምንይሻለናል ያገራችንን ስላም ይመልስልን
Yene konjo, Geta zemeneshen yibark! Endanchi Yale yibzalen.
Amen egizihabiher ulun chay new esu madireg yichilal
እኔ እኮ ዜማ ትርጉም ያለው ሲሆን ዘመናትን እየዋጀ ቀጣይነቱን ሲይዝ በህቴ ያለው የፀጋ ውበት ይደንቀኛል በምድራዊ እውቀት እና ችሎት ብቻ ያልተዘመረ ዘመንሽ የልምላሜ ይሁን።
ቃላት ያጥሩኛል አዚዬ፣ ጌታ ኢየሱስ አብዝቶ ይባርክሽ፣ ፀጋውን ያብዛልሽ
የተወደድሽ የእውነት ዘማሪ ፀጋ የበዛልሽ የአባቴ ልጅ ደሞም የሰፈሬ(የአቃቂ) ልጅ ተባርከሽ ባረክሽን!!!!!❤❤❤❤❤❤
አሜን ክብር ለእርሱ ይሁን ሊቀካህናች ኢየሱስ ነው በአብ ቀኝ ያለው ተባረኪ አዚዬ
ጌታ ይባርካችሁ አሜን ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ውስጤ በዚህ መዝሙር ደስ ብሎታል ተባረኪ 😊😊😊😊😊❤❤❤❤