የስህተት ት/ት...ዜማው አንድ አይነት ነውእኛ ራሱ ስህተት ሆነን ነበር❗️❗️ PROPHET_ZENEBE_GIRMA Nikodimos Show - Tigist Ejigu

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 8 вер 2024
  • የተወደዳችሁ የኒቆዲሞስ ሾው ቤተሰቦች፡ ከታች ያለውን link ላይክ በማድረግ facebook ገፃችንን እንድትቀላቀሉ በታላቅ አክብሮት እጋብዛለሁ፡፡ 👇👇
    / nikodimosshow
    ፕሮግራማችንን እየተከታተላችሁ ገንቢ አስተያየታችሁን ሁል ጊዜ ስለምትለግሱን እጅግ አድርገን እናመሰግናለን፡፡ ሰብስክራይብ ያላደረጋችሁ አዳዲስ ቪዲዮ እንዲደርሳችሁ ሰብስክራይብ ማድረግ አትርሱ፡፡
    This Video Clip is Dedicated Only to Nikodimos Show Channel /Tigist Ejigu/!
    Subscribe today for latest Videos Here:- / nikodimosshow
    Facebook:- / nikodimosshow
    Instagram:- / tigisttg
    Awtaru Kebede,Ethiopia,Ethiopian Gospel Song,Amharic Gospel
    © Copyright:- #Tigist Ejigu /Nikodimos Show/ 2024

КОМЕНТАРІ • 360

  • @tigi886
    @tigi886 6 місяців тому +39

    የስህተት ትምህርት እንደሆነ ያወቅነዉ እኮ ስንማር ሳይሆን ስንሆን ነዉ ያልከዉ አስተማሪ የሆነ ገላጭ አባባል ነዉ። እራሳችንን ከምንሰማዉ ስብከት ከሚመስል ነገር ሁሉ እንድንነቃ እና ስተን እንዳንጠፋ ያደርገናል። ዘመንህ ይለምልም።

  • @redietlemma7878
    @redietlemma7878 6 місяців тому +28

    አሜን! ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ ኢንተርቪው ሰማሁ።ገዢ እርጋታና ትህትና ከመንፈሳዊ ቅናት ጋር የምናይባቸውን እንደ ዘኔ አይነት ሰው አያሳጣን።

  • @surafelabebe8678
    @surafelabebe8678 6 місяців тому +14

    እንደእነዚህ አይነት ጌታን ወዶ እንድንወደው የሚያደርጉ ጥቂት ስዎች መካከልአንዱ አንተስለሆንክ ትምህርትህን እከታተላለሁጌታ ይባርክህ እወድሀለሁ❤❤❤❤

  • @mishameyohannesloveneverfa5384
    @mishameyohannesloveneverfa5384 6 місяців тому +16

    አቤት እንዴት አይነት ድንቅ ቃለ መጠይቅ ነው። ዘኔ በእውነት ዕውቀት፣ ትህትና እና ጥበብ የሞላብህ ወንድም ነህ። እግዚአብሔር ዘመንህን ሁሉ ይባርክ! ትጂዬ እንዲህ ዓይነት የበሰሉ አገልጋዮች ስለምታቀርቢ ዘመንሽ ይባረክ! በጣም ተባርኬበታለሁ።

  • @user-ju9xu3xp7j
    @user-ju9xu3xp7j 6 місяців тому +8

    ትዝ ይለኛል ድሬደዋ መሉወንጌል ሲኔማ ኤንፓየር ስናመልክ መጥተው ይረብሹ ነበር ነብይ ዘኔ አንተ ግን በጣም እድለኛ ነህ እግዚአብሔር ይመስገን ዛሬ ላይ መድረስህ ብዙዎች እንደ ጠፉ ቀርተዋል በእውነት ስላን ጌታ ኢየሱስ የተባረከ ይሁን አሜን

  • @user-pp1wh1ff4f
    @user-pp1wh1ff4f 6 місяців тому +7

    ሰው መንፈስ ነው የሚለው ት/ት በጣም ስህት ነው ሰው የእግዚአብሔር ጥገኛ ነው አንቺስ ሚናሽን ለይ ጌታ ይርዳሽ ተባረኪ !!!

    • @tesfahungebregiorgis
      @tesfahungebregiorgis 6 місяців тому

      እና ሠው ምንድነው?

    • @henokmehari822
      @henokmehari822 6 місяців тому +2

      ​@@tesfahungebregiorgis'ሰው' ከምድር አፈር የተበጀ የእግዚአብሔር እስትንፋስ እፍ ተብሎበት ህያው የሆነ 'ሰው' የተባለ ፍጡር ነው።

    • @tesfahungebregiorgis
      @tesfahungebregiorgis 6 місяців тому

      @@henokmehari822 ኦ ነዉ እንዴ እንደዛማ ከሆነ በእግዚአብሔርም ማንነት ዉስጥ ምድራዊ (ተፈጣሪ የሆነዉ) አፈር አስተዋፅኦ አለዉ ማለት ነዉ፤ ምን ለማለት ፈልጌ ነዉ በዘፍጥረት መፅሐፍ ላይ ሠዉን በመልካችን እንደምሳሌያችን እንፍጠር አለ - ሠዉንም በመልክና ባምሳሉ ፈጠረዉ፤ ካለ በኋላ ወርዶ ሠዉንም ከምድር አፈር አበጀዉ ይላል፤ እንደሚገባኝ በመፍጠር እና በማበጀት መካከል እጅግ ሰፊ ልዩነት አለ፡፡ ፈጠረዉ ሲል ምንም ካልነበረ ነገር ሠዉ የተባለዉን እንደ አምላኩ ወይም ሰሪዉ ያለ ማንነትን ሰራ ሲሆን፤ አበጀዉ ሲል ደግሞ ፊዚካል ለሆነችዉ መሬት ፊዚካል የሆነ እና ኦፕሬት የሚያደርግበት ስጋዊ (አፈራዊ) አካልን አበጀለት ማለት ነዉ፡፡ ስለሆነም ነብዩን ብወደዉምና ባደንቀዉም፤ እሱን በጣም መዉደዴ ግን የሠዉን አምላካዊ ገፅታ አይቀይረዉም፡፡ በጣም በሚገርም ሁኔታ ሠዉ አፈር ቢሆን ኑሮ መንፈሳዊነት በጣም አስጠሊታና ተስፋ ቢስ ይሆን ነበረ፤ ሐዋሪያቶቹም ለዛነዉ ስጋዊ ኪሳራና ሞትን እጅግ የናቁት - ምክንያቱም ሰዉየዉ ከዚያ ሌላ ስለሆነ፡፡
      በእነ እዮብ መፅሐፍ የጭቃ ቤት፣ በሐዋሪያቶቹ በእነ ጳዉሎስ አንደበት ድንኳን እና በራሱ በእግዚአብሔር አንደበት የእግዚአብሔር መቅደስ የተባለዉ ይህ ስጋችን እዉነተኛ ማንነታችን አይደለም፤ ነዉም የሚል የመፅሐፍ ቅዱ አንድም ክፍል የለም፤ ለዛ ነዉ ሠዉ ዳግም ካልተወለደ የዘላለም ሕይወትን የማያየዉ ሲል ዳግም መወለድ ለዉስጠኛዉ ሠዋችን (ትክክለኛ ማንነታችን) የተሰጠዉ፡፡ ለዛም ነዉ አዳምን ከዚህ በበላህ ግዜ ሞትን ትሞታለህ ብሎት በበላ ግዜ ሞትን የሞተዉ አፈር ስጋዉ ግን ይመላለስ ነበር - የሞተዉ ከአምላኩ ጋር ይገናኝና ይነጋገር የነበረዉ መንፈሱ ነዉና፡፡ ስለሆነም ሰዉ መንፈስ ነዉ፣ ነፍስ (ዕዉቀት + ፍቃድ አለዉ) እንዲሁም በስጋ ዉስጥ ይኖራል፤ አንድም ቀን ጠቢቡ እንዳለዉ ስጋም ወደመጣበት ወደመሬት፣ ነፍስ (መንፈስም) ወደፈጣሪዉ ይመለሳል፡፡

  • @AddisKenNew
    @AddisKenNew 6 місяців тому +8

    እኔም በጣም በብዙ የእንባ ስሜት በተሰበረ መንፈስ ነው እንድሰማ የሆንኩት በብዙ ጌታ ይባርክህ ❤ ቲጂዬ በጥሩ የመንፈስ ቅዱስ ምሪት ነው ሰዎችን የምትጋብዥልን እና ወደፊትም እንዲሁ እንድትቀጥይ ተስፋ አደርጋለሁ "ጥርት እና ጥልል ያሉ" እንዳለው ዘኔ ማለት ነው

  • @yandabatlijochshow
    @yandabatlijochshow 6 місяців тому +6

    ዘኒ አንተ በዚህ ዘመን የተሰጠኸን ስጦታችን ነህ። ተባረክ

  • @sanialula1174
    @sanialula1174 6 місяців тому +3

    ለመጀመሪያ ጊዜ ቃለ ምልልስ ስሰማ አንተ የተወደደክ የእግዚአብሔር ሰው ዘርህ ይለምልም ስፋ ብዛ ተከናወን ❤❤❤

  • @zewdiea
    @zewdiea 6 місяців тому +5

    Focus ከሌለን ሁሉ ነገር focusአችን ይሆናል የሚገርም አገላለጽ ነው።ጌታ ይባርክህ።

  • @meseretyirgu3211
    @meseretyirgu3211 6 місяців тому +4

    አቤት እርጋታ ! አቤት ትህትና ! እኔም የቴሌግራሙ ተጠቃሚ ነበርኩ ነብይ ዘኔ በብዙ ተባረክ ! ትግስትዬ አንቺም የምትጋብዢአቸው ሁሉ በጣም የተረጋጉ ናቸው አመሰግንሻለሁ ተባረኪ 🙏😇🥰

  • @SenaitSeni-pi7ps
    @SenaitSeni-pi7ps 6 місяців тому +29

    ሶፎኒያስ ና ከእዚ ሾዉ ተማር
    ቲጂዬ እግዚአብሔር ይባርክሽ
    አንተን የሰጠን ጌታ ይባረክ

    • @melkam1502
      @melkam1502 6 місяців тому +1

      ሰኒዬ ኧረ በናትሽ ፣ ይሄን ስም በቅዱሳን ጉባኤ ባይጠራ ደስ ይለኛል አሃሃሃሃ ሱፍ የለበሱ እብዶች መች ናፈቁን፣ መፅሐፍ ቅዱስ የሚቆረጣጥሙ እውነት እውነት እላችኋለሁ አላውቃቸውም።

  • @bornagain2024
    @bornagain2024 6 місяців тому +6

    ውይ ውይ ውይ ዘኔ የጌታ የልብ ሰው ነህ እኔ ያለሁት ሲያትል ነው ትምህርቶችህን እከታተላለሁ ጌታ ረድቶኝ ኢትዮጵያ ስመጣ ቸርች ይምካፈለው እናንተ ጋር እንደሚሆን አምናለሁ። የልብ የልቤን አወራኸው ውስጤ በጌታ ፍቅር እየነደደ ነው የሰማሁት። በርግጥ ጌታ እንዳንተ ያሉን ያብዛልን። ነብይ ጥሌንም በጣም አከብራለሁ። ቲጅዬ ተባረኪ እውነተኞችን ብቻ አቅርቢልን አንዳንዴ የምታቀርቢያቼው ሰዎች ላይ ተጠንቀቂ ለእየሱስ ክብር የማይሆን ሁሉ ናቂው በተለይ አስተምሮ ላይ የሚታሙ ትን አታቅርቢ ሚዲያውን እንደ ዘኒ ላለ ሞቲቭ ብቻ ተጠቀሚበት። አሜን ምርቃቱን ተቀብለናል ነብይ ዘኒ። እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ።

  • @user-tf2kx4dc6d
    @user-tf2kx4dc6d 6 місяців тому +4

    ከዛ ስህተት መንገድ የመለሰህ ጌታ ይባረክ እግዚአብሔር አይጥልም

  • @tsegageremew2551
    @tsegageremew2551 6 місяців тому +4

    ለዘመኑ ቤተክርስቲያን እና ቅልብልብ አገልጋዮች ለምትቅበዙ ህዝቦች የሰውን ገመና ለምታሰጡ ሚዲያዎች ትልቅ ትምህርት ተገኝቶላችኋል እባካችሁ ቤተክርስቲያንን ወደ ክርስቶስ አሳድጓት። ዘኔ ተባረክ በዚሁ መንፈስ ዝለቅልን 🙏❤ቲጂ እወድሻለሁ ❤

  • @meseretegrace4793
    @meseretegrace4793 6 місяців тому +5

    በቅድሚያ ስለኡሉ እግዚአብሔር ይመስገን!!!!!!ቲጂዬ ለአድማጮችሽ ተጠንቅቀሽ ብዙ የምንማርባቸውን የእግዚአብሔር ሰዎች ስለምታቀርቢልን እናመሰግናለን!!!!!!ፓስተር ዘኔ ብሠማው ብሠማው የማልጠግበው የእግዚአብሔር ሠው!!!!ክርስቶስን በሙላት የማይበት ለብዙዎች አስተማሪ የኦነ የህይወት ምስክርነት ያለው በጣም ነው ስላንተ ፈጣሪን አመሠግናለሁ!!እንዳንተ ያሉ የተሠጡ ክርስቶስን የሚሸቱ በምድራችን ላይ ያብዛልን!!!!!መልኸክተኛ ነን በዚህ ምድር❤❤❤❤❤❤❤❤ሶሻል ሚዲያ በትክክል ከተጠቀምንበትን ወንጌልን የምንደርስበት ፕላት ፎርም ነው!!የተሠጠንን ዕድል በአግባቡ እንጠቀም!!!ወደማስተዋል እንምጣ ዘንዬ እውነት አንተ ትለያለህ

  • @user-yb3zd8sj7i
    @user-yb3zd8sj7i 6 місяців тому +6

    አሜንንንንንንንንን በጌታ በኢየሱስ ስም ተባረክ ለበረከት ሁኑ❤❤❤

  • @user-kj8gx3ls1n
    @user-kj8gx3ls1n 6 місяців тому +4

    የሚገረም ቆይታ ጌታ ዘመንህን ይባረከው
    ነብይ ዘኔ ነብይ ጥሌ ፍፄ ጌታ ለምድራችን ለወጥ ለወንጌልን በአለም ሁሉ ሊያዳረስ ያስነሳቸዎ አረበኞች ናቸው ጌታ በደሙ ይሸፍናችሁ እድሁም ሚዲያ ላይ ያልወጡ ጌታ በሀይል የሚጠቀምባቸው ህይወታቸውን ሙሉ ለጌታ ስራ የሰጡ አሉና በድራታችሁ ከላይ ነውና እንወዳችሁአለን

    • @user-kj8gx3ls1n
      @user-kj8gx3ls1n 6 місяців тому

      አሜን አሜን አሜን
      ባረኮትህን ተቀበልን
      ትጅዬዘመንሽ ይለምልም ብሩክ ነሽ❤

  • @azitieyesuse1145
    @azitieyesuse1145 6 місяців тому +2

    አቤት ንግግር እኮ ዘኔዋ በእውነት ብዙ ቀርቶልኛል ተባረክ በብዙ ፀጋ ይብዛልህ ቲጂዬ አንቺም ተባረኪልን ጥሩ ነገር የምንማርበትን ስለምታቀርቢልን ፀጋ ይብዛልሽ🙏🙏🙏❤❤

  • @deboamare5171
    @deboamare5171 6 місяців тому +7

    የዲላው ምስክርነት. ልብ ነኪ ነውና አይ መንፈስ ቅዱስ 😮😮❤❤ ላለቅስ ስል መዳንዋን ሰማሁ።

  • @user-fx3xm4we2h
    @user-fx3xm4we2h 6 місяців тому +3

    ዘኔ የጌታሰው መንፈስ ቅዱስ ከአንተጋርእንዳለ በብዙ ታስታውቃለህ ዘመንህ። ይባረክ ከነቤተሰብህ እድሜእናጤና ይብዛላችሁ❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @heeryyee2062
    @heeryyee2062 6 місяців тому +2

    የሚገርም የሚደንቅ እየሱሰን እየሱሰን የሚሸት ማንነት እኔ በብዙ ተምሬሀለሁ ተባርኬሀለሁ ነብይ ዘኔ ተባረክልን ሰፋ ብዛ!!!!! ባርኮቱንማ እያለቀሰኩ ነው የተቀበልኩት ውይ እንዳት እንደረሰረሰኩ !!!!! ቲጂዬ ተባረኪ ለምልሚ ቃላት የለኝም ሰለዛሬ ቃለመጠይቅሸ ዋው ዋው !!!!!!!!!!!!!!!

  • @alazartesfamichael1740
    @alazartesfamichael1740 6 місяців тому +2

    አቤት እንዴት ውልቅልቅ ስብርብር ድቅቅ አድርጎ ደግሞ እንደሰራህ መንፈስ ቅዱስ በጣም ይገርማል :: ወድንሜ ነብይ ዘነበ እንዴት እንደቀናሁብህ አትጠይቀኝ ምን አይነት የእግዚአብሔር ምህረት ነው የበዛልህ :: እንደ ባህር አሽዋ ያብዛህ የተወደድክ ነህ ዘንዬ::

  • @semeresibhatu8691
    @semeresibhatu8691 6 місяців тому +5

    በድጋሚ እድል ሰጥቶ የሚመራ ኣምላክ ስሙ ይባረክ።

  • @Eyu_channel
    @Eyu_channel 6 місяців тому +5

    Please, please, please, we love how you teach the Bible Zene. This generation needs more of you. Don't change. God is using you mightily, and everybody with the right mind and eye can see that. !!!

  • @20204606
    @20204606 5 місяців тому +1

    በእውነት እግዚአብሔር ይባርክህ። ለብዙዎች መጽጽናናት ሆነሀል። ብዙ ነብይ ነን ባሉ ልባችን ቢሰበርም ባንተ እግዜር አጽናንቶናል።

  • @bechobeti2008
    @bechobeti2008 6 місяців тому +2

    በጣም ከምወዳቸው እና ከምሰማቸው አስተማር አንዱ መምህር ዜኔ ነው ተባረክ ::

  • @LED_PICTURES
    @LED_PICTURES 6 місяців тому +3

    What a charismatic person. Now I know why I love him. This interview is full of wisdom and knowledge. God Bless you Zennye.
    I watched both parts but too short 😌
    Best interview ever by Nikodimos Show, Thank You TG

  • @Dinksiraw
    @Dinksiraw Місяць тому

    ነቢይ ዘነ በሰማው ጊዜ ሁለ አድስ ትሆንብኛለ ተባረክ እኔ ተባርክሃለሁ❤❤

  • @misrakasfaw9519
    @misrakasfaw9519 5 місяців тому

    በጣም የምትወደድ ወንድም ዘኔ በአምላክህ ላይ ስትጓደድ ስታስቀና ተባረክ አንቺም እህታችነ ዘመንሽ ይባረክ

  • @sitotayohanis1847
    @sitotayohanis1847 6 місяців тому +6

    የአማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን ከላይ እስከ ታች ድረስ ያለው structures አንድ አይነት የሚናፈቅ ነው ዘኔ ጸጋ ይብዛልህ ከዲላ አከባቢ 😍🔥😍🔥

  • @Canada404
    @Canada404 6 місяців тому +2

    ዋው እግዚአብሔር ዘመንህን ይባርክ ውድ ወንድማችን የእግዚአብሔር ሰው ነብይ ዘኔ በጣም በጣም በመገረም ነው የሰማሁት የቲጅየ የአጠያየቅ ዘይቤ ከርጋታ ጋር ያንተ እርጋታ ና ትህትና በዕውነት ትልቅ ትምህርት ነው ያገኘሁበት እግዚአብሔር ዘመናችሁን አገልግሎታችሁን በብዙ እጥፍ ይባርከው ካስማችሁ ይስፋ የበረከታችሁ መጠን ዳርቻ አይኑረው 🥰✝️

  • @Hiwotdesta-iu3wl
    @Hiwotdesta-iu3wl 6 місяців тому +2

    ዘንዬ እንዳንት ያለ መሪ ሰላለኝ እግዚአብሔር አመስግናለሁ ተባረክልኝ

  • @ananakebede5398
    @ananakebede5398 6 місяців тому +4

    የኔ ወንድም በእንባ ነው የሰማሁህ። ጌታ እንዴት ቸር ነው። የመለሳችሁ መንፈስ ቅዱስ ይባረክ።

  • @eyerusalemabebe3051
    @eyerusalemabebe3051 6 місяців тому +4

    ዘኔ የአገሬ ልጅ በውኑ ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ ይችላልን?
    ብሎ እንደጠየቀ በውኑ ከሐረር ከዚች ጣኦት ከሚመለክባት ጥልቅ የሆነ ከዘመና ዘመናት እየተቀባበሉ ያመጡት ጅብ መንፈስ የድግምት አሰራር አዚም ወጣቱን ያደነዘዘ ጫት እረ ምኑ ቅጡ ከሰለጠነባት ከዚህ አገር እንዲህ አይነት አገልጋይ በመገኘቱ አምላኬን እባርካለሁ 🤲🙏🏾
    👉አሁንም ጥለሀት የወጣሀት
    👉ከአፍህ የማትነጥላት ሐረር እጅግ ብዙ ፀሎት ያስፈልገናል ፀልይልን እንወድሀለን♥️♥️♥️🙏🏾🙏🏾🙏🏾

  • @emebettsegaye5940
    @emebettsegaye5940 27 днів тому +1

    ዘኔዋ ባንተ እጅግ ተጠቅሜአለሁ እሰከሁን ተባረክልኘ 🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @HALELUYA62
    @HALELUYA62 6 місяців тому +4

    Oh prophet ዘኔ በጣም ነው ምወድህ ተባረክልኝ አንድ ቀን በአካል ካንተ እንደሚማር አምናለሁ 🙏🙏🙏🙏🙏

  • @teshome7693
    @teshome7693 6 місяців тому +3

    አሜንንንን ተቀብያለሁ በረከትህን ጌታ የረዳህ ሰው ነህ ለዚ ጊዜ ለዚህ ዘመን አስቦህ ነው የመለሰህ ተባረክ ፀጋ አሁንም ይብዛልህ ለእህት ቲጂ እኔ ጥያቄ አለኝ ኒው ክሬሽን አንቺ ያለሽበት ቸርች አደለ እዴ ሰው መንፈስ ነው የሚል የስተት ትምርት ያለው??? ለሐዋርያ ጃፒም ይሄ ጥያቄ ምላሽ ይስጥበት ስተት ስተት ነውና

  • @user-nu5ix1pw9f
    @user-nu5ix1pw9f 6 місяців тому +3

    ኡፍፍ የኔ ወንድም ተባረክ ትልቅ ነገር ነው ለእኛም ለልጆቻችንም ትምህርት ነው የኔ ትሁት ደስስትል ግልፅ ነክ

  • @alemayhutilahun2368
    @alemayhutilahun2368 6 місяців тому +3

    መጋቢ ዘኔ ተባረክ!
    ቲጂ ጌታ ይባርክሽ!

  • @mikiyasbiruk9779
    @mikiyasbiruk9779 6 місяців тому +1

    This is the real Christianity, stay blessed 🙏❤

  • @tsiyonyegetatsiyonyegeta8094
    @tsiyonyegetatsiyonyegeta8094 6 місяців тому +3

    እኔ ቃል የለኝም ነብይ ዘኔ ዘመንክ በክር ይለቅ ያከበርከው እሱ በሀል ክብሩን ይግለጥልህ እወድሀለው❤❤❤❤ቲጂዬ አድናቂሽ ነኝ ብሩክ ነሽ እወድሻለው❤❤❤❤

  • @mesaygudina2658
    @mesaygudina2658 6 місяців тому +5

    ነብይ ዘኔ በጣም እንውድሃለን።አንተን እና አንተ የምትመራት ቤ/ክርስቲያን ሞዴላችን ናችሁ።እኔ በግሌ ባለፈው አንድ አመት ተኩል በብዙ ከእናንተ እየተጠቀምኩኝ ነው
    በስስት ነው የምውድህ❤❤

  • @hewanmekonnen2501
    @hewanmekonnen2501 6 місяців тому +3

    እኔ በእንባ ነው የሰማሁት ቲጂዬ ጌታ ይባርከው ነብይ ዘኔ

  • @fasikaaddis9385
    @fasikaaddis9385 6 місяців тому +1

    ጌታ ይባርክህ ትልቅ ሰው ነህ ስህተትን ማመንና መመለስ:: በጣም በጣም ትልቅ ሰው!

  • @hannaatena7844
    @hannaatena7844 6 місяців тому +2

    Tgya እዉነት ነዉ እኔ ምስክር ነኝ ተባሪኬአለሁ ።
    አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን 🎉🎉🎉🎉🎉❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @EtsegenetAbebe-jf1ed
    @EtsegenetAbebe-jf1ed 6 місяців тому +3

    የኔ ጨዋ መሪ አንተ መሪዬ ስለሆንክ በጣም ደስተኛነኝ ካንተ ብዙ ተምሬያለው ተባረክልኝ ፀጋው አሁንም ይጨምርልክ ለምድር ትረፍ እንወድሀለን❤❤❤❤❤ቲጂዬ ተባረኪ❤❤

  • @jesusisalive4337
    @jesusisalive4337 6 місяців тому +2

    አምላካችን እግዚአብሔር ሊመለስ ለወደደ ሁሉ ለካ እንዲህ ለበረከት ያደርጋል ጌታ ኢየሱስ ይባርክህ ወንድማችን ተባረኬ ትጄ

  • @kibebew
    @kibebew 6 місяців тому +1

    አሜን በእየሱስ ስም🙏እኔም ልባርክህ ጌታ በነገር ሁሉ ይባርክህ፣ ድንበርህ ይስፋ፣ በመውጣትህና በመግባትህ ሁሉ ተከነወን ።

  • @kameth423
    @kameth423 6 місяців тому +2

    አሜን የመረከን አንዱም ጠብ አይበል የመረከን ይጽናብን በርክትልን ከልቤ ነው የማከብርህ የምወድህ እንዲሁ ቀጥልልን እውነት ነው አትደባለቅ ከሀሳውያን ጋር እግዚአብሔር ይጠብቅህ❤❤❤❤❤❤❤

  • @Mercy2Mee
    @Mercy2Mee 6 місяців тому +2

    34:40 ነብዬ ዘኔን በጣም የምወደው ለዚህ ነው. Wow amazing testimony and interview. Learned so much.

  • @HagereTashenif-zk9kg
    @HagereTashenif-zk9kg 6 місяців тому +1

    ድንቅና ሁሉን ሀሳብ ለጌታ ክብር የሰጠ ቃለ ምልልስ ነው፣ ነቢይ ዘነበ የቤተክርስቲያንንና የወንጌልን ዓላማና አሰራር በግልፅ የገለጠ መሪ ነው፣ ለክርስቶስ ታማኝ ምስክር በመሆን የክርስቶስን ወንጌል ከፍ ስላደረክ ከዚህ በላይ አብዝቶ ልዑል አምላክ ይባርክህ።

  • @user-pp1wh1ff4f
    @user-pp1wh1ff4f 6 місяців тому +1

    ጌታ ማስተዋል ስለሰጠልን ስለተመለስክልን ስሙ ይባረክ መጨረሻህ ይመር ሁላችንም ጌታ ይርዳን !!!!

  • @Jesusislord-th8ze
    @Jesusislord-th8ze 6 місяців тому +1

    ጌታ ኢየሱስ አብዝቶ ይባርክህ ነብይዘኒ የእግዚአብሔር የልቤ የሚልህ ድንቅ አገልጋይ ነህ እንወደሃለን ቲጅ አንች ጥበበኛና አስተዋይ የእግዚአብሄር ባረያነሽ ብል አላጋነንኩም ምክንያትም ጠቃሚ ትምህረት የምሰጥ interview ስለምታቀርብ በእውነት የጌታ እየሱስ ሚርጥ ጋዘጠኛ ነሽ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

  • @haimyhabte1680
    @haimyhabte1680 6 місяців тому +2

    አሜን አሜን አሜን 🙌🙏
    ለምልምልን ነብይ 💙
    ቲጂዬ ጌታ አብዝቶ ይባርክሽ 💓

  • @abbyabunetizale7824
    @abbyabunetizale7824 6 місяців тому +3

    Praise God and thank you both so much!!! Way to go🙏🙏🙏🙏

  • @rahelworku6710
    @rahelworku6710 6 місяців тому +1

    አሜን አሜን አሜን አሜን ጌታ ኢየሱስ ይባረክ።
    ታማኝ የጌታ ባሪያ ዘኔዋ❤❤❤ በአገልግሎቱ ታማኝ ነው!!!!

  • @JeryyKastro-ro1rb
    @JeryyKastro-ro1rb 6 місяців тому +1

    ወይ ዘኔ የምር ድሮም ወድካለው አሁን የባሰ ውድድድድ አደረኩ ስለ አንተ ጌታን አከበረኩ ረጅምም እድሜ ኑርልን አባቴ

  • @johnnati-yh2cl
    @johnnati-yh2cl 6 місяців тому +1

    ዘኔ ጌታ ይባሪክእ ድንቅ ምስክሪነት በዚእ ዘመን እንተን የሰጠን ጌታ ይባረክ ቲጂይ ተባረኪ😊😊😊😊

  • @banchibeyene3085
    @banchibeyene3085 6 місяців тому +2

    ቲጂዬ ተባረኪልኝ በጣም ተጠቅሜያለው ዘንዬ ተባረክልን።

  • @lemi520
    @lemi520 6 місяців тому +1

    አሜን !!!ተባረክ ዘመንህ ይባረክ online ባለው ፕሮግራም እጅግ የተጠቀምኩ ፈውስም ያገኘሁ ትንቢትም ሰምቼ የተከናወነልኝ ሀሉንም ቀን በናፍቆት የምጠብቅ ነኝ አሁንም ብዙ መከናወን ይሁንልህ ሁለቱም interview አይቼ እንዲህም አለ ያልኩብህ ነህ ተባረክ!!!!!!!!!!

  • @hanaayele247
    @hanaayele247 6 місяців тому +2

    እፎይ ደስ አለኝ በቃ ተደስቻለሁ ተባረክ

  • @user-rh7zm4hc9j
    @user-rh7zm4hc9j 6 місяців тому +1

    ዘኔ ዘመንህ፣ሕይወትህ፣ቤተሰብህ፣
    አገልግሎትህን እግዝአብሔር ይባርክ! ትህትናህን፣ይዋህነትህን፣አስተዋይነትህን ፣ታታርነትህን ወደድኩ ለምልምልን።

  • @tiruneshbelachew6452
    @tiruneshbelachew6452 5 місяців тому

    የኔ ውድ እህት ተባረኪ የተረጋጋሽ ጌታ በውቀቱ የሞላሽ ተባረኪልኝ። ነቢይ ዘኔ እግዚአብሔር ይባርክህ ለጌታ ያለህ ፍሽር ያስቀናል ደግሞም ከሳትክበት ጌታ እንኳን መለሰህ ዛሬ ለብዙዎች የምትጠቅም ሆንክልን ያዳነህ ጌታ ይጠብቅህ ይጋርድህ በጌታ ጸጋ በርታ ❤

  • @Abiyot_Gurasho
    @Abiyot_Gurasho 6 місяців тому +1

    wooow...ድንቅ ኢንተርቪው ነው። ነብይ ዘኔ አና አህታችን ቲጂ ጌታ አብዝቶ ይባርካችሁ።

  • @deboamare5171
    @deboamare5171 6 місяців тому +3

    ተፅእኖ ፈጣሪ እንድትሆኑ ይርዳችሁ። ጨውና ብርሀን😮😮ተባርኬያለሁ❤❤❤ ሁለታችሁም ተባረኩ

  • @hanaayele247
    @hanaayele247 6 місяців тому

    እግዚአብሔር ቤቱን መስራት ያውቅበታል ደስ አለኝ ጌታ ስሙ ይባረክ ❤❤❤❤❤❤

  • @user-cx9rh3od8x
    @user-cx9rh3od8x 24 дні тому

    ትጅዬ ብዙ ፀጋው ይብዛልሽ የተበራክሽ ነሽ
    ከቸልሽ ደዊት ፋስልን ቀለ መጠየቅ አርግልን❤

  • @Mamite926
    @Mamite926 6 місяців тому +2

    Wow! What a blessing! God bless you too.❤❤❤

  • @mahlethailu119
    @mahlethailu119 6 місяців тому +1

    you are blessed Zenye ❤❤❤ ሁሌም ባንተ ደስተኛ ነኝ እግዚአብሔር ጤና እድሜ ይስጥ ለትውልድ ትረፍ ተባረክልኝ

  • @emebetbrussow5398
    @emebetbrussow5398 6 місяців тому +1

    አሜን ፣አሜን ፣አሜን ዘንዬ እኛን በባረክህበት ባርኮት በእጥፍ አንተና ቤተሰብህን እግዚአብሔር ይባርክ !! ❤❤❤ ዘንዬ አብረውህ የሚያገለግሉ ሁሉ ይባረኩ !! ትጊ እግዚአብሔር ይባርክሽ !!❤❤❤

  • @user-lt4kr8kp3j
    @user-lt4kr8kp3j 6 місяців тому

    ቲጂ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክሽ በጉጉት እያየሁት ያለቀ ቃለመጠይቅ ነው ባርኮቱ ደግሞ ቃል የለኝም ነብይ ዘኔን ከልብ እናመሰግናለን አንተን የሰጠን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን አሜን

  • @assefaamanuel
    @assefaamanuel 6 місяців тому

    እህት ትዕግሥት በብዙ ተባረኪ እናመሰግናለን.....ወንድም ዘኔ ዘመንህ ይባረክ ከዚህ በላይ ተከናወን እንወድሃለን ያንተ የሆነው ሁሉ ጌታ ይባርክ ይጠብቅ

  • @user-xs5zd6zw1w
    @user-xs5zd6zw1w 4 місяці тому

    እግዚአብሔር ይባርክህ የተወደድህ የእግዚአብሔር ሰው አንተን ሳይ ጳውሎስን አያለሁኝ አትያዝ እግዚአብሔር ጥላ ከለላ ይሁንህ እኔስ ነፍሴ አንተ ውስጥ ባለው ጸጋ ሁልጊዜ ትጠማለች በርታ እውድሃለሁኝ❤

  • @salameskyes7240
    @salameskyes7240 6 місяців тому +3

    አሜን አሜን አሜንአሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜነ አሜን አሜን አሜን አሜን አሜነ አሜን አሜን አሜን አሜን,አሜን,አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አልኩ በኢየሱስ ስም አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን እልልልልልልልል🙏🙏🙏🙏🙌🙌🙌🙌🙌🔥

  • @user-yj7ye7hh7j
    @user-yj7ye7hh7j 6 місяців тому +2

    Powerful message thank you ❤

  • @itsmee5496
    @itsmee5496 6 місяців тому +2

    Amen amen amen amen amen amen amen amen amen amen amen amen amen amen. Amen amen amen amen amen amen amen amen amen amen amen amen
    Bless you Zenewa ❤❤❤

  • @HalemaS-ww3kk
    @HalemaS-ww3kk 6 місяців тому +2

    የስህተት ትምህርት ስንማር ሳይሆን ስንኖር ነው ያወቅኩት ያልከው እኔም አጋጥሞኝ ህይወቴን አይቸ ነው የተመለስኩት ። የመለስኝ ጌታ ይመስገን

  • @rahelasefa9045
    @rahelasefa9045 6 місяців тому

    አምላኬ እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡ በእውነት በጣም እንወድሃለን የውስጥህን ቅናት በቅዱስን ላይ ሁሉ እንዲሁን በረከን፤ ነፍሴ ሃሴት አደረገች ተባረክ፤ ቲጄ አንቺም እግዚአብሔር አምላክ ይባርክሽ ስትጠይቂ ለጠየቅሽው ጥያቄ መልስ ሲሰጥ እርግት ብለሽ በማስተዋል ስትሰሚ ይህ በራሱ ዕረፍት ያለው ሰው ማንነት ነውና አሁንም ዘመንሽ የሰላም የጤና ይሁንልሽ ተባረኪ፡፡

  • @user-mn5bo9ej8q
    @user-mn5bo9ej8q 6 місяців тому +3

    አሜንንንንን! አብዝቶ ይባርክህ

  • @user-yf5ry3cz9v
    @user-yf5ry3cz9v 6 місяців тому

    ነብይ ዘነበ እኔ እገር ቤት ብገባ እናንተ ቸርች ነኝ በጣም በጣም አውነተኛ የጌታን ድምጽ የሚሰማና የሚያገለግል አገልጋይ ነው ጌታ ዘመንህን ይባርክ ይህንን አይቀይርብህ ዘመናዊ አገልጋይ አያድርግብህ

  • @salameskyes7240
    @salameskyes7240 6 місяців тому +2

    የኔ አባት ዘኔዋ የከበደሽ ይቅለልሽ ያከኝ ቀን ተፅናናው እወድአለው❤

  • @mahletbetemariam1264
    @mahletbetemariam1264 6 місяців тому

    ዘኔ እንደአንተ አይነት መሪ ጌታ ስለሰጠኝ አመሰግናለሁ። ትሁት ነህ፣ ሁሌ በትምህርቶችህ እየሱስን ነዉ የምታሳየን ጌታ ይባርክህ ፀጋዉንም ይጨምርልህ🙏 ቲጂዬ የምትጋብዣቸዉ እንግዶች ሁሉ አስተማሪዎች እና እየሱስን የሚያሳዩ ናቸዉ ተባረኪ 🙏

  • @mekdeseshetudejene9750
    @mekdeseshetudejene9750 6 місяців тому +2

    በጣም አስተማሪ ነው እግዚአብሔር ይባርካችሁ።

  • @abebaabuhay7805
    @abebaabuhay7805 6 місяців тому

    ስላንተ እግዚአብሔርን አመሰግናለው እግዚአብሔር ይባርክህ ሮሆባት ያርግልህ !!!!!

  • @user-qg1ff9mi8i
    @user-qg1ff9mi8i 6 місяців тому +1

    እግዚብሂር ይባርክቨ እንደነዚህ አነቶች የወንጌል አርበኛች እየጋበዝቨህይ ወተችንሰለሚረሰርሰ

  • @giftiadam7406
    @giftiadam7406 6 місяців тому

    በለቅሶ ነው የመጀመሪያውን ምስክርነት የሰማሁት😢 አቤት የእግዚአብሔር እጅ ዛሬም ህያው ነው!! እግዚአብሔር ይባርክህ ነብይ ዘኔ

  • @liyameko8897
    @liyameko8897 6 місяців тому

    የሚገርም ፕሮግራም ነበር ዜኔዋ በብዙ ተባረክ እንወድሀለን ❤❤ እኔም በቴሌግራም ትምህርትና በማለዳው ፀሎት በኮቪድ ውቅት በጣም ተጠቅሚያለው ተባረኩ ሀልዎት ውስጥ ምታገለግሉ በሙሉ ❤❤❤ አሜን አሜንንንን ❤❤ቲጂዬ ብሩክ ነሽ

  • @birukshimelis-xu7zq
    @birukshimelis-xu7zq 6 місяців тому +2

    T G የምከፍለው ቢሆን ከፍዬ ባየሁ
    ተባረኪ አንች መልካም ሴት
    Zeniye ❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @meheratmatiku8053
    @meheratmatiku8053 6 місяців тому +1

    እግዚያአብሔር አምላክ ይባርክህ ደግሞ ተባርከሀል ያብዛልህ እንዳንተ አይነት አገልጋዮች ያብዛልን እረጋ ብለህ ሁሉንም እውነት የሆነውን ፍንቱ አርገህ ሰለገለፅከው አመሰግንሀለሁ ትግዬ የንቺ የተወደድሽ ነሽ በጣም ነው የምወድሽ ዘመንሽ ይለምልም

  • @alemseifu1556
    @alemseifu1556 6 місяців тому +1

    ዋው ቲጂዬ ኢንተርቢዪሽን አያለሁ የዛሬው ይለያል ጌታ ብርክ ያርግሽ ወንሜ ጌታ ከዚህ የበለጠ ፀጋውን ይስጥህ ምርቃትህን በደንብ አፈስኩት ጌታ አብዝቶ አብዝቶ ይባርክህ ተከናወን❤❤❤ 🎉

  • @user-ki1sf9hn9z
    @user-ki1sf9hn9z 6 місяців тому +2

    ዋው ገበያ መር ያልሆነ አገልግሎት ዋው

  • @BinyamT-kf7rx
    @BinyamT-kf7rx 6 місяців тому

    Zena
    You are the real Men of God and I appreciate you.
    You are blessed .

  • @winydemssie
    @winydemssie 6 місяців тому +1

    ነብይ ዘኔ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ በረከትህን ተቀብለናል በጣም ነው የምንወድህ የአንተን ትምህርቶች ሁልግዜም በጉጉት ነው የምንጠብቀው ከዚህ በላይ ፀጋ ይብዛልህ 🙏💐💐ቲጂዬ ተባረኪልን ደስ የሚል ጥያቄና መልስ ብዙ እውቀትን ነው ያገኘነው ተባረኩ 🙏♥♥😘

  • @MihretShewnngzaw-dz7rn
    @MihretShewnngzaw-dz7rn 6 місяців тому

    አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን ዘኒየ ከመረከው አንድም አይለፈኝ በኢየሱስ ስም አሜን❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @tsiontemesgen2195
    @tsiontemesgen2195 6 місяців тому

    ቲጂዬ በመጀመሪያ አንቺም ተባረኪ ጌታ እየሱስ ይባርክሽ ደስ ስትይ እኮ አጠያየቅሽ እራሱ ይማርካል ተባረኪ ይህ ቃለመጠይቅ ሁሉም አገልጋይ ቢያየው ብዙ ይማርበታል ነብይ ዘኔ ተባረክ ይህ መንፈስ አይወሰድብህ ትድባረክልን።

  • @user-tf2kx4dc6d
    @user-tf2kx4dc6d 6 місяців тому +2

    አሜን አሜን ባርኮትህ ያግኘኝ 🎉🎉

  • @TizitaAbera-fu1uf
    @TizitaAbera-fu1uf 6 місяців тому +1

    አሜን አሜን አሜን ።ጌታ ይባርክ።

  • @user-dl4oq4wd5w
    @user-dl4oq4wd5w 6 місяців тому +1

    እግዚአብሔር ይባርክህ ደስ የሚል ልብ የሚደርስ ምልልስ።

  • @user-mo6vs4sk3v
    @user-mo6vs4sk3v 6 місяців тому +1

    ትክክል አሁንም ኢየሱስ ለጥቅቶች ሞቷል የምባል ሰይጣናው ትምረት መቷል በጣም ትብተኞች ናቾ