የብቃት ደረጃ ላይ ለመድረስ የሚታለፉ የቅድስና መአረጋት ( በመምህር ተስፋዬ አበራ)

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 15 січ 2025

КОМЕНТАРІ • 284

  • @hareggetaneh4075
    @hareggetaneh4075 4 роки тому +48

    መምህር እኔ ሲከፋኝ በጸሎት መልኩ እንባየን አፈሳለሁ ደስ ሲለኝ ደግሞ በደስታ የደስታ እንባ አፈሳለሁ አንድም ቀን እግዚአብሔር ለምኘው ያጣሁት ነገር የለም ምን አልባት የጠየቅሁት ነገር ማያስፈልግ ቢሆን እንኳን እግዚአብሔር ቀይሮ የሚያስፈልገኝን ነው ሚሰጣኝ እንጂ ጠይቄ በንባየ ያጥጣሁት ነገር የለም ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን

    • @twerkkeskes4661
      @twerkkeskes4661 4 роки тому +3

      ቃለሕይወት ያሠማልን መምሕር በዉነት እንዴት ተመሥጨየ እንደሠማሑት ከልብ አመሠግናለሑ እንባአ ዋጋአ አለዉ እኔ ብዙነገር አግኝቻለሑ እግዜአብሔር ይመሥገን

    • @edenaraya6643
      @edenaraya6643 4 роки тому +2

      እባካችሁ እህቶቼ ወለተሚካኤል ብላቹ በፀሎታችሁ አስቡኝ

  • @solnetu1260
    @solnetu1260 4 роки тому +35

    እውነት ነው እኔም አልቅሼ ለምኜ ፅሎቴ ተሰምቶልኛል እግዚአብሔር ይመሥገን ድንግል ትክበርልኝ። አሜን

  • @Adne_
    @Adne_ 4 роки тому +7

    አዎ መምራችን በእንባ እኔ አምላኬ መልስ ሰጥቶኛል አንድ አመት ሙሉ በትዳሬ ምክኒያት በጣም አለቅስ ነበር በጣም አስቸጋሪ ስጥ ነበርኩ ችግሬን ቀርፎልኛል በእውነት ክብር ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁን እናቴ ድግንግል ማርያምን በጣም እለምናት ነበር ስሚኝ እያልኩ እሷም የለመንኳትን ሞልታልኛልች ወይም አድርጋልኛለች ምን ያላለቀስኩበት ቅዱሳን አለ ለማውቃቸው ቅዱሳን መላእክት ወቅዱሳን ሰማእታት ወጻድቃን አለቅስባቸው ነበር በጣም ይከፋኝ ስለነበር አሁን ግን ይሄው ዘጠኝ ወር አስቆጠርኩ ሰላም ካገኘሁ ስለሁሉም ነገር ልኡል እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን ምስጋናም ይድረሳቸው ለቅዱሳኑ እንደየክብራቸው የተጨነቃችሁ የተቸገራችሁ፣እንደኔ፣እግዚአብሔር፣ይድረስላችሁ፣ ለምኑት አልቅሱበት ለቸሩ መድኃኒዓለም ይመልስላችኋል

  • @burtekanamin9065
    @burtekanamin9065 4 роки тому +3

    ከዚህም በላይ ፀጋህን ያብዛልህ

  • @ሐናየማርያምልጅልጅድንግል

    በእውነት መምህር ባንተ አድሮ የሚያስተምረ የሚገፅፀን ልኡል እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን
    አሜን (፫)
    ቃለ ህይወት ያሰማልን ተስፋ የምናደርጋትን መንግስተ ሰማያዊይ ያውርስልን በእድሜ በጤና ይጠብቅልን ያገልግሎት ዘመንክን ይባርክልን
    መምህር ያንተ ትምህርት ማዳመጥ ከጀመርኩ በኅላ እራሴን ዞር ብየ ሳይ በስመ ክርስቲያን ነበርኩ
    መምህር ላስቸግርህ ወለተ ጊዮርጊስ እባላለሁ ከአረብ ሀገር ለቤቱ ያበቃኝ ዘንድ በፆለትህ አስበኝ ።

  • @በአብፀጋ
    @በአብፀጋ 4 роки тому +19

    አሜን !! መምህሬ እውነት ነው እንባ መልስ አለው የእርሶን ትምህርት ካዳመጥሁ በሃላ ብዙ ለውጥ አለኝ እግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጦት እልፍ ሺ አመት ኑርልኝ

  • @ቅዱስገብርኤልድረስልኝ

    በእግዚአብሔር ፊት አልቅሼ ለምኜ ያልተመለሰልኝ ነገር የለም ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን። በእመቤታችን ስእል በቅዱስ ገብርኤል በቅዱሳን ስእል ፊት እምባዬን አፍስሼ ከጸለይኩ የቅዱሳን ምልጃ ይረዳኛል እንዳንድ ቀን ውዳሴ ማርያም ውዳሴ አምላክ ሰይፈ ስላሴን ሳነብ በእምባ ሆኜ ነው በተለይ ጾም ከሆነ ምግብ በልቶ እንደጠገበ ሰው ነው የሚሰማኝ ሸክሜ ሁሉ ይቀልልኛል እግዚአብሔር አምላክ ክብሩ ይስፋ። ነገር ግን እንደ እኔ ሀጥያተኛና በደለኛ የለም ቸርነቱ የበዛ የድንግል ማርያም ልጅ ቅዱስ አማኑኤል በጸጋው አቁሞኝ በህይወት አለሁ። የቅዱሳኑ አምላክ የተባረከ ይሁን።

  • @سعدسعد-ت2ز
    @سعدسعد-ت2ز 4 роки тому +2

    መምህ እግዚአብሔር እድሜህን ያርዝምልን በርታ ምን አይነት ቦታ ሆነን እደምናዳምጥህ ብታውቅ መምህር ከዚህም በለይ ትትጋለህ ብዙ ሰው እየቀየርክ እደሆነ እዳትዘነጋ በርታ

  • @ergoyeali30
    @ergoyeali30 4 роки тому +5

    መምህር እመብርሀን ፍቃዳ ሁኖ ከዝሙት መንፈስ የተላቀቅሁት በእንባና በስግደት ነው ይህን ስፀፍ ያሳለፍኩትን እያሰብኩ በትምርትህ ሆነ በገጠመኝ የምታቀርባቸው ልቤን የሚነካኝ ከያዳንዱ ትምህርት ጥቅም ያገኘሁበት ነው እባክህ ዎድሜ ቅዳታቆም እደራ ስለመብርሀን ብለህ እደኔ ባጋንንት አሰራር የተያዙ ብዙ ይኖራሉ መምህር ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይጠብቅህ አሜን።

  • @ሳምራዊትነኝ
    @ሳምራዊትነኝ 4 роки тому +32

    ቃለ ህይወትን ያሰማልን ፀጋዉን ያብዛለዎት መምህር ከይቅርታ ጋር ድምፅ ትንሽ ጨምሩልን የመዳም ሸቃላዎች ቻርጅ አድርገንም እየበላንም ስለሆነ የምንሰማዉ ድምፅ ይጨመርልን🙏

  • @ቲጂኢትዮጵያ-ጸ4ቘ
    @ቲጂኢትዮጵያ-ጸ4ቘ 4 роки тому +7

    ተራ ቁጥር 4 ላይ እንደተገለፀው የእንባ ፀሎት ያዋጣል ምክንያቱም እኔ ከአለሙ ሁሉ 1ኛ ሃጢያተኛ ስለሆንኩኝና ያንን ሃጢያቴን ተሸክሜ ከመዳህኒያለም፣ ከእመቤቴ ማርያም ፣ከመላእክቶችና ከፃድቃን ሰማእታት ስእለአድኖ ፊትስር ሳይገባኝ መንበርከኬና የሃጢያቴ ብዛት /ክብደት ፊቴ ላይ ድቅን ሲል ገና ተንበርክኬ ፀሎት ስጀምር እንባዬ ዱብዱብ ይልና ከጉንጬ ወርዶ መሬት ይንጠባጠባል, እና በማለቅስበት ጊዜ ፀሎቴ 100% ይሆናል እና በፀሎት ጊዜ እንባ ያዋጣል, የውስጥ ሰላም፣ በረከት፣ ጤና ወዘተ አግኝቼበታለሁ እግዚአብሔር ይመስገን!

  • @yeshigoshu3716
    @yeshigoshu3716 Рік тому

    እውነት ነው እንባ ሀይል አለው ወንድማችን የእግዚአብሔር በረከት
    አይለይህ እድሜና ጤና ይስጥህ ብዙ ነገር እራሴን የጠየኩበትና
    ይተማርኩበት ነው:
    🙏✝️🙏✝️🙏✝️

  • @ቃልኪዳንወሎየዋየድንግልል

    እግዚአብሔር ይመስገን ውድ መምህራችን በእውነት ቃለህይወትን ያሰማልን እስከ ዳግም ምፃቱ በቤቱ ያፅናህ እኔ የምገልጽበት አንደቨት የለኝም እግዚአብሔር አምላክ በጥበብ ያኑርህ አሜን አሜን አሜን🌾🌾🌾🌿🌿🌿🌿🌿🌾🌾🌿🌿💒 💠

  • @tube4569
    @tube4569 4 роки тому +12

    መምህር ሰለ እንባ በጣም አለቅሳለው ድንግል የኔ እናት ያረገችልኝ ቤተሰቦቼ ተለያይተው ነው የሚኖሩት ሁላችንም በየቦታው ተበታትነን የምኖንረው ፪፲፲፲አካባቢ ሞጆ ገዳም ኪዳን ምህረት ስቅል ስር ነበር እባዬን ያፈሰሱኩት ብዙም ስልቆይ ለስራ ከሀገር ወጣው በውጣው ሶስት ወሬ ቤቴስቤ ተሰባስበዋል ተባልኩ እመብረሀን ምን ይሳናታ የደስታዬ ብዛት ባለውበት ነበር ተበርኪከ ያመሰገንኩት ሰለሁሉም የእግዚአብሔር ስም የተመሰገን ይሁን ።
    መምህር እርሶንም የሰጠ እግዚአብሔር የተመሰገን ይሁን ባገኙት ደስ ባለኝ

    • @bezaabebe6689
      @bezaabebe6689 4 роки тому

      አሜን እግዚአብሄር ይመስገን

    • @Kibrekidusan...888
      @Kibrekidusan...888 4 роки тому

      እኔንም ይስማኝ ሐጢአቴን ይቅር እንዲለኝ ወልደ መድህን ብለሽ አስቢኝ

  • @asniasni7529
    @asniasni7529 4 роки тому

    Amen amen amen Kal heyoten yasmlen mamerachen amen amen amen 👏👏👏👏👏🕊️🕊️🕊️🕊️🕊️🕊️🕊️🕊️

  • @ኤልሻዳይነውጌታ-ጸ9ጐ

    መምህር ቃለ ህይውት ያሰማልን እግዚአብሔር ፅጋወን ያብዛልህ ከዚህ በላይ ዕውቀቶን ያብዛልህ እግዚአብሔር ይጠብቅህ እዳይነቱን ሺ ሺ ሺ ያብዛልን መምህር

  • @bx395
    @bx395 4 роки тому +3

    ቃለሕይወትያሠማልን ፀጋውን ያብዛልሕ በእድሜ በበረከት ያቆይህ አሜን

  • @filmwedajtubee
    @filmwedajtubee 4 роки тому +13

    መምሕራችን እንኳን ደህና መጣህ ፤ የምትሰጣችው ትምሕርቶች ደስ ይላሉ ፤ ትውልዱን ማንቃት አለብን
    ሶሻል ሚዲያን ለበጎ ነገር መጠቀም እንችላለን ፤ እኔም የሀገር በቀል እውቅት በቻናሌ እያስተላለፍኩ ነው በርታልን እግዚአብሔር ያበርታህ ..............…

  • @የስላሴባርያየማፊቅርልጅ

    በትክክል ተለውጪበታለው በእውነት ልዑል እግዚያብሂር ይመስገን በመለወጢ ብዙ ነገር ተጠቅምያለው

  • @mebratseifelddin7710
    @mebratseifelddin7710 4 роки тому +1

    Kale Hewot yasemalen memher🙏💚💚💚💛💛💛❤❤❤

  • @mrkbemrkbe6748
    @mrkbemrkbe6748 Рік тому

    መ ምኽራችን ቃለኽይወት ያሰማልን በረከትክ ይደርብን💚💛❤️አሜን ❤❤❤

  • @tariquamelaku1251
    @tariquamelaku1251 4 роки тому

    አሜን አሜን አሜን
    ቃለ ሂውት ያስማልን በእድሜ በጤና ይጠብቅልን ፅጋውን ያብዛልን ያገልግሎት ዘመንህን እግዚአብሔር ይባርክልህ

  • @sltanmehari1720
    @sltanmehari1720 4 роки тому +6

    ክፉ መንፈስ በጨጓራ ህመም ተመስሎ ያሰቃየኛል። የበላሁት ምግብ ወደ አሲድነት እየቀየረ ያሰቃየኛል። ሲያመኝ ኃጥያቶቼ እያስታወስኩ ስቅስቅ ቢዬ ሳለቅስ በሆዴ የተነሳብኝ እሳት ወዲያውኑ ይጠፋና እያገሳሁ በአረፋ መልኩ አሲዱ ይወጣልኛል። አሁን እንባ ለኔ የማስታገሻ መድኃኒትና ነው፤ ወደ ህክምና እየሄድኩ anti-acid(አሲድ መቀነሻ) ክኒን መግዛት ትቼ ሲያመኝ ፀሎት ቤቴ ውስጥ ገብቼ አለቅሳለሁ። ይህን የምላቹ ግን የእንባ ኃይል ለማመግለፅ እንጂ የብቃት ደረጃ ከተባለው የሚያገናኘኝ የለም እኔ እልም ያልኩ ኃጢአተኛ ነኝ።

    • @zigeredagerelase2220
      @zigeredagerelase2220 4 роки тому +2

      Ayzoh wendmachn tages bzu tagegnaleh!!! Egziabher mahari new 🇪🇷

    • @sltanmehari1720
      @sltanmehari1720 4 роки тому +2

      @@zigeredagerelase2220 አሜን በጣም አመሰግናለሁ እህቴ። አሁንማ እየቀጠቀጥኩትም ነው መሸኘቱ አይቀርም በቅርብ ከእግዚአብሔር ጋር።

  • @bx395
    @bx395 4 роки тому +4

    ሠላም ለእናንተ ይሁን በሞላው አለም የምትገኙ ቤተሠቦቼፍፁም የእግዚአብሔር ሠላም ከእናንተ ጋር ይሁን መምህር በእውለት የቅዱሣን አምላክ ከዚሕበላይ የምታሥተምርበት እውቀቱን ሚሥጥሩን ይግለፅልሕ አሜን

  • @AsmeretMeresa
    @AsmeretMeresa 4 роки тому +8

    እሜቤቴ ድንግል ማርያም, ኪኪዳነምሕረት እናቴ ከልጇዋ አማለደችኝ, እኔ ሃጢአተንኛ ለጇዋን እምባየን አበሰችልኝ! እምባ ሃይል አለው!🙏

  • @robeltekle8754
    @robeltekle8754 4 роки тому +1

    Amen amen amen memihir tesfaye thanks God

  • @ጎዶልያስጎዶልያስ-ረ6ኸ

    አሜን አሜን አሜን እኳን ደህና መጣህ መምህር

  • @ዮዳሄዮዳሄ-በ8ፈ
    @ዮዳሄዮዳሄ-በ8ፈ 4 роки тому +12

    እውነት ነው መምህር እንባ ሀይል አለው እኔም በብዙ ነገር በፀሎት መልስ አግኝቻለሁ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን

  • @ወለተፃዲቅ-ዸ5ቐ
    @ወለተፃዲቅ-ዸ5ቐ 4 роки тому +3

    መምህር ቃለሕወት ያሰማልን ፀጋውንያብዛልህ

  • @እግዚአብሔርመልካምነዉበመ

    እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን መምህራችን እኔ በጣም ሀጥያተኛ ና ቆሻሻ ቢሆንም ቸሩ መድሃኒአለም በእንባ የጠየቁትን ሁሉ ሰጥቶኛል አንድም ያጎደለቢኝ ነገር የለም መፅሓፍ ይዜ ከመፀለይ ይልቅ የቅድስት ስላሴ ስእለ አድህኖ ከፍቴ አርጌ ማልቀስ ይቀድመኛል እኛ ነዉ የራቅነዉ እንጂ እግዚአብሔር የኛ ጥያቄ ለመመለስ በጣም ቅርብ ነዉ። መምህራችን ፀጋዉ ያብዛልህ እግዚአብሔር ባንተ ላይ አድሮ ልጆቹን እያስተማረ ነዉ

  • @netsanetsoimon8355
    @netsanetsoimon8355 3 роки тому

    እግዚአብሄር ይመስገን ቃለ ህይወት ያሰማልን መምህራችን አሜን አሜን አሜን

  • @werkiyewonde4310
    @werkiyewonde4310 4 роки тому +7

    መምህር ተሰፍ ሰላሴ ቃለህይወት ያሰማልን በእድሜ በጸጋ ይጠብቅልን ሰለ እንባ የተደረገልኝን ከብዙ ብትንሹ አንደኛ እና በጨሌ ታመልክ ነበር እኔ ሁል ጊዜ አለቅሰ ነበር አሁን ግን እግዚያብሔር ይመሰገን ባአድ አምልኮቱ ቀረ መንፈሱም በጸበል ተያዘ እኔም እጅግ በጣም ብዙ ችግሮችን በእንባ ተፈጸሞልኛአል የሚገርማችሁ አልቃሻ ከመሆኔ የተነሳ አይኔ በጣም ያነሰ እና የደፈረሰ ነው እና በንጹህ ልብ ከሆነ እንባ ትልቅ ዋጋ አለው የድንግል ማሪያም ልጅ ለሁላችንም ንጹህ ልብ ይሰጠን።

    • @addseketemaw5549
      @addseketemaw5549 4 роки тому +1

      አሜን

    • @mrkbemrkbe6748
      @mrkbemrkbe6748 4 роки тому +1

      አሜን👐👐👐አሜን አሜን

    • @bezaabebe6689
      @bezaabebe6689 4 роки тому

      አሜን እህቴ በድንግል ማርያም ይዤሻለው በጣም በስጋም በነብስም በጣም ችግር ውስጥነው ያለሁት ስትጸልይ በጅሽ እህተ ሚካኤል ብለሽ በጸሎትሽ አስቢኝ እህቴ

    • @mrkbemrkbe6748
      @mrkbemrkbe6748 4 роки тому

      Beza Abebe እግዚአብሔር ይርዳሽ እኽት አለም

  • @betanyabiruk3091
    @betanyabiruk3091 4 роки тому +1

    ምስጋናውን እግዚአብሄር ይውሰድ ብለሀል እኔም ይህንኑ እየደገምኩ።
    ቃለህወት ያሰማልን።
    ተባረክ እጅግ ጠቃሚ ትምህርት ነው ሰምቶ በተግባር ላይ ማዋሉ ነው ባለድል የሚያደርገን።
    አንተስ የድርሻህን እየተወጣህ ነው ፍጥረታትን ወደፈጣሪ ማቅረብ። ተመስገን ፈጣሪያችን።
    በርታልን መምህራችንም በአንተ አገልግሎት
    የመንፈስ እርካታ እንደሚያገኙ እርግጠኛ ነኝ የስራቸው ውጤት ነህና።
    ድንቅ ነው።

  • @hiwotfekadufekadu4724
    @hiwotfekadufekadu4724 4 роки тому +2

    አሜን ቃለሂወትን ያሰማልን መምህር በእውነት በተመስጦ ነው ያዳመጥኩት በጣም ደስ የሚል እራሴን እንድጠይቅ ነው ያደረገኝ በእውነት እግዚአብሔር አምላክ በቅድስና ህይወትእንድንኖር እግዚአብሔር ይርዳን

  • @ሩሀማነኝየድንግልማርያምል

    እኔ ከአንድም ሁለት ሶስቴ አልቅሼ ለምኜ እግዚአቤሄር መልሶልኛ ያውም እኮ እጅግ በጠም በሰዘንኩት ማግስት ነው የመለሰልኝ ስሸሸው ፍቅሩ ይበልጡኑ ይጨምረል የእውነት እግዚአቤሄር እኔን እጅግ ተግሶኛል ጠጥቦ ጭቃ ነኝ ማልለወጥ

  • @tamanechayza2972
    @tamanechayza2972 3 роки тому

    መምህራችን እመብረሃን ፀጋው ታብዛለክ በርከትህ ይድረሰን::

  • @godisgreat1630
    @godisgreat1630 4 роки тому +3

    በመጀመሪያ መምህር ስላንተ ምንም የምገልፅበት ቃላት የለኝም ብቻ ቸሩ መድሃኒአለም ፀጋውን ደርቦ ደራርቦ ያብዛልህ ቤተሰቦችህን ይጠብቅልህ ይባርክልህ እኔ በንባ ብዙ ነገር አትርፊያለሁ ቢያንስ ስቅስቅ ብዬ አልቅሼ ገፀለይሁ በቃ በጣምም ቀልል ይለኛል አንድ ጊዜ ደግሞ በስደት እያለሁኝ በጣም በሰውኔቴ ላይ ቁስል ይወጣ አስቸገረኝ በጣም ያማል ብዙ ቦታ ነበር የሚወጣብኝ በጣም መግል ያወጣል ለሰዎቼ መንገር ፈራሁኝ በቃ ከልቤ አለቀሼ ለአምላኬ ነገርኩት በቃ ምንም መሄጃ የለኝም ብዬ ነገርኩት ወደዛው ጠፋልኝ ግን ያው ከንቱ ነኝ አሁን ትዝ ያለኝ ስታስተምር

  • @hannadesta382
    @hannadesta382 4 роки тому +1

    የሚገርም ትምህርት ነው መምህር ኣብዝቶ ይባርክህ

  • @askalabrahamsaldosry1110
    @askalabrahamsaldosry1110 4 роки тому +1

    ቃለ ሂወት ይስማል ኣሜን

  • @ፀጌማርያምa
    @ፀጌማርያምa 4 роки тому +1

    እኔ በመምህር ብዙ ተምራለው ሃይማኖቴ በይበልጥ እዳውቅ የረዳኝ እግዚአብሔር መምህር እድሜ ይሥጥልን

  • @hannaathuniya9335
    @hannaathuniya9335 Рік тому

    አሜን አሜን አሜን በረከታቹሁ ይድርብን❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @ephremabera2395
    @ephremabera2395 3 роки тому

    በትዳር ጉዳይ በባለቤቴ የምፈተንበት ጊዜ ነበረኝ ለፃድቃኔ ማርያም አልቅሼ ነግሬያት ዛሬ ነገሮች ሁሉ ተስተካክሎልኛለል አሜን

  • @NaomiBerhe
    @NaomiBerhe 4 роки тому

    ቃለ ሂዎትን ያሰማልን መምህር ብሰማው ብሰማው አልጠገብ አለኝ እህት ወንድሞቼ እሂን ትምህርት ደጋግማችሁ አዳምጡት

  • @אווגובריהון
    @אווגובריהון 4 роки тому +3

    አሜን አሜን አሜን መምህረ ተሰፍየ

  • @tsagae6563
    @tsagae6563 4 роки тому +6

    ትምህሩቱ ስሰማ እንዴት ልስማ እንቅልፉ ተጫጫነኝ እራሴ ሸክም የተሸከምኩ ያክል ከበደኝ ውይ የቅድስና መአረጋት በጣም ጠቃሚ ነው በውነት መምህራችን ቃለይዎት ያሰማልን አሜን ከሞት የተነሳችሁ ልጅ አስለቀሰችኝ ደሞ የፀለየችላት ልጅ አቤት መታደል በውነት

  • @ወለተኢየሱስወለተጊዮርጊስ

    ሰላም ለአንተ ይሁን መምህር

  • @da_blu_noodle2142
    @da_blu_noodle2142 4 роки тому +9

    እውነት ነው መምህር ተስፋዬ እንባ ያለው
    ፅሎት ቶሎ ነው መልስ የሚያገኝው።
    እኔ በራሴ በደካማው አቅሜ አይቸበታለው።

  • @ህይወትኃይሌ
    @ህይወትኃይሌ 4 роки тому +3

    እግዚአብሔር ይመሰገን መምህር ቃል ህይወት
    ያሰማልን በእድሜ በጤና ይጠብቅልን
    የሰማነውን በልባችን ይፃፈልን በእውነት ፀጋውን
    ያብዛልህ 🙏 ጌታ ሆይ ንፁህ ልብ ፈጠርልኝ
    አረ እኔሰ የናፈቀኝ ንስሐ የምገባበት ቀን😢🙏

  • @sosainasosi3951
    @sosainasosi3951 4 роки тому +8

    መምህር እውነት የማእቱ ሳላን እድሜ ይስጥልን በጣም እየተለወጥን ነው እኔ በራሴ እውነት በቃ ህይወት እየተቀየረ ነው

  • @helenbultum3600
    @helenbultum3600 4 роки тому

    እግዚአብሔር ይመስገን ባንተ በመምህራችን ላይ አድሮ የሚያስተምረን እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው ላንተም ልፕወንድማችን ተስፋ ሥላሴ የሚፈታተነውን ፀላየ መንፈስ ቅዱሳን መላህክትን ልኮ ይጠብቅህ እንዲሁ የቅዱሳን አባቶች አብተ በረከታቸው ፅጋቸው ዙቶሪያክን ከፀላየ መንፈስ እንደ አጥር አጥሮ ይጠብቅህ.
    ስለእውነት ከሆነ እኔ በእንባ እጅግ ብዙ ነገ መልስ ከአምላክ ከድንግል ማርያም ልጅ መልስ ተሰጥቶኛል ለዚህ ሁሉ ድንቅ ረቂቅ ተመርምሮ የማይደረስበት እፁብ ድንቅ አሰራሩ አልፋና ኦሜጋ የድንግል ማርያም ልጅ የተመሰገነ ይሁን አሜን ፫

  • @ቲጂኢትዮጵያ-ጸ4ቘ
    @ቲጂኢትዮጵያ-ጸ4ቘ 4 роки тому +1

    ለመምህራችን ቃለ ህይወትን ያሰማልን የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክልን አሜን. መምህር አስተማሪ ገጠመኞች ስላለኝ በኢሞ መልእክት አስቀምጬአለሁ ገጠመኞችህ ሁሉ ሃገር ውስጥ ስላሉት እህት ወንድሞች ብቻ ነው እኛስ ውጪ በስደት የምንሰቃየው ማን አለን የኛንም አቅርብልን የሚገርም የሚገርም ገጠመኞች አሉን.

  • @ምስጢርቲዩብ
    @ምስጢርቲዩብ 4 роки тому +4

    መምህራችን እድሜና ጤናውን አብዝቶ አትረፍርፎ ይስጥልን👏👏🙏

  • @mihreteabalemu8010
    @mihreteabalemu8010 4 роки тому +19

    መምህር ምን ብዬ እንደማመሰግንህ አላውቅም ብቻ ዛሬም እመቤታችን ፀጋውን ታብዛልህ
    አንብሀ ንስሐ ላይ እስቲ አቁማችሁ እናንተ አልቅሳችሁ እግዚአብሔር እንባችሁን አይቶ ቆጥሮ ላልከው በዙም መናገር ባልችልም
    እኔ ዛሬ ላይ በህይወት መኖሬ እንደዛ በሃጢአት ቆሽሼ ገምቼ ግን ዳግም በፊቱ ወድቄ ስቅስቅ ብዬ ሳለቅስ በቸርነቱ ቆሚያለሁ ከሞት አትርፎኛል ይዞሀል የተባልኩት በሽታ ያለምንም ምልክት ያለምንም ህመም በእመቤታችን ምልጃ በእርሱ ምህረት ዛሬ ቆሚያለሁ
    ይህን ሳወራ በጣም እያዘንኩ ነው ምክንያቱም ለኔ አይገባኝም ብቻ ምን እላለሁ ዘወትር ከማመስገን በቀር
    ውዳሴ ከንቱን መድሀኒአለም ያርቅልኝ

  • @youhalayyouhalay6597
    @youhalayyouhalay6597 4 роки тому +5

    *መምህር ቃለህወትን ያሠማልን በድሜ ከፀጋጋ ያድልልን*

  • @abatlhaymanottsshaynefsenw9165
    @abatlhaymanottsshaynefsenw9165 3 роки тому

    Amen 🙏 Amen kale hiwot yasemalen

  • @meseretdaka2069
    @meseretdaka2069 4 роки тому +9

    አሜን እግዚሀብሄር ይመሥገን መምህራችን ሠላምህ ይብዛ ከነ መላው ቤተሠብህ

  • @salamsalam8060
    @salamsalam8060 4 роки тому

    እግዝአብሔር ይመሰገን ብዙ ተምሬአለሁ ቃለህይወት ያሰማልን

  • @yetenaytyeteye4153
    @yetenaytyeteye4153 3 роки тому

    Amen Amen Amen kelyewet yasemalin wedemachin balkebet selamek yebezalen❤

  • @ወለተማርያምወለተማርያም

    በውነት መምህር ብዙነገር ተምራልው ፀጋውን ያብዛልክ እረጅም እድሜና ጤና ይስጥህ ምናለበት ሀገሬ ብሆን ነው ያልኩ ይህን ለመተግበር መምህር በስልክ አድቀን ባገኝ ይበልጥ መፍትሄ አገኛለው ብዬ አስባለው ትምህርትህ አብዛኛው የኛ የሂወታችን ታሪክነውና ፀጋውን ያብዛልክ

  • @bekelechbalcha8309
    @bekelechbalcha8309 4 роки тому +2

    መምህር እኔ አምላኬን ከማመሰገን ሌላ ቃላት የለኝም።በየጊዜው እኛን ክፉ ልጆቹን ለማሰተማር መልክተኛ ይልክልናል።ለኛ ወደፈጣሪአችን መመለሰ ሌላመንገድ ሊኖር አይችልም።
    ለርሶም ፀጋውን አብዝቶ ይስጦት።

  • @tsigeredawerku2149
    @tsigeredawerku2149 4 роки тому +1

    አዉ መምህር እንባ በጣም ጥቅም አለዉ እኔ አልቅሼ የምፀልየዉ ፀሎት የደርስልኛል ዉስጤም ደስስስስስይለዋል አልቅሼ በምፀልይ ስአት

  • @dtdtdyfy492
    @dtdtdyfy492 4 роки тому

    መምህር በእውነቃለህይወት ያሰማልን ግዴለም እኛ አይሰለቸንም

  • @expo3491
    @expo3491 4 роки тому +3

    መምህራችን እግዚአብሔር ይመስገን ቃለ ህወሃት ያሰማልን

  • @እመቤትጉግሳ
    @እመቤትጉግሳ 4 роки тому +4

    እውነት ነው መምህር እንባ ትልቅ ዋጋ አለው እኔ ገና ልጅ እያለው እናቴና አባቴ ተለያይተውብኝ በጣም እዝኚ ታናናሽ ወንድሞች ና እህቴ. የትም ሲንክራተቱብኝ በጣም አዝኚ ለምን ብዬ አልቅሺ ነበር እግዚአብሔር ይመስገን አሁን ታርቀው በስላም በፍቅር እየኖሩልኝ ነው እና እውነት መምህር. ብዙ ያልገቡኝ ነገሮችን አስተምርህኛል እግዚአብሄር ፀጋውን ያብዛል መምህር

  • @Tube-if5bz
    @Tube-if5bz 4 роки тому +1

    መምራችን ቃለህይወት ያሰማልን እጅግ በጣም ያስተምራል ፀጋዉን ያብዛልህ እግዚአብሔር ይባርክህ አፀደ ማረያም ብለህ በፀሎትህ አስበኝ

  • @ወንቅሸትሂወቴዮሐንስ-ኰ1ጨ

    እግዚአብሔር ይመስገን ቃለህይወት ያሰማልን መምህራችን በእውነት ፀጋውን ያብዛልህ እግዚአብሔር ከነቤተሰብህ ይጠብቅህ በቤቱ ያጽናህ

  • @tsedilove4731
    @tsedilove4731 4 роки тому

    Amen memher kala hiwot yasmelen Kaleb anmsgnalen betam des mil tamrt new egzabhern bamnt banba kaxyqut zema aylem yamlsel yesmanwen belbunchin yasdrben

  • @tsigeredawerku2149
    @tsigeredawerku2149 4 роки тому

    ቃለህወትን ያሰማልን መምህር እኛም የሰማነዉን በልቦናችን ያሳድርብን በምነታቸን የናን በፀሎት የተጋን ለመሆን ያብቃን አሜን

  • @azebgizawe7792
    @azebgizawe7792 3 роки тому

    ትምህርት ህን ስለሰጠን እናመሰግናለን

  • @tsedalegera1434
    @tsedalegera1434 4 роки тому +1

    አሜን ቃለ ሕይወት ያሰማልን መምህራችን እረጅም ዕድሜና ጤና ይስጥልን

  • @yodettareku1738
    @yodettareku1738 4 роки тому +1

    አሜን አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን ፀጋውን ያብዛልን አሜን አሜን አሜን መምህር

  • @ethio540
    @ethio540 4 роки тому +1

    memeher , Thanks very much for everything you are doing for us. May Our lord and God bless you.

  • @weleteeyesusweleteeyesus6243
    @weleteeyesusweleteeyesus6243 4 роки тому +1

    እግዚአብሔር ይመስገን መምህር ቃለ ህይወት ያሰማልን አሜን

  • @sanaitoqbay7156
    @sanaitoqbay7156 4 роки тому +1

    ቃለ ሂወት ያሰማልን ምህር

  • @mariahanf9675
    @mariahanf9675 4 роки тому +1

    ቃላህይወትያሰሜልን

  • @ngsitweldebrhan7845
    @ngsitweldebrhan7845 7 місяців тому

    ቃለ ህይወት ያሰማልን❤❤❤

  • @wubetsemawu6697
    @wubetsemawu6697 4 роки тому +3

    የህይወት ቃል ያሰማልን መህምራችን ፀጋ እግዚአብሔር ያብዛልህ በረከትህ ይደርብን

  • @ኤፍታህብዬጀመርኩ
    @ኤፍታህብዬጀመርኩ 4 роки тому +1

    መምህር ቃለህይወትን ያሰማልን የጸጋው ቀለበት ፀጋውን ያብዛልህ በእውነት ውስጥን ሰርስረው ነው ትምህርቶችህ የሚገቡትና ማንነትን የሚመረምሩት ኑርልን ።

  • @ብንያም
    @ብንያም 4 роки тому +5

    መምህር እንባ እንደጠቀመኝ የተገነዘብኩት በእርሶ በሚሰጡት ትምህርት ላይ ነው። ይሄው እግዚአብሔር ይመስገን ከትክክለኛው ከቅዱስ ወንጌል መምህራን ጋር በሱ ፍቃድ እየተማርኩ ነው።

  • @classiphone5329
    @classiphone5329 4 роки тому +2

    Amen Amen Amen kale hiwotin yasemalen wandemachin

  • @ጓልቅዱስጊዮርጊስ
    @ጓልቅዱስጊዮርጊስ 4 роки тому

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ሂወት ያሰማልን መምህሪችን እግዚአብሔር ፀጋው ያቡዙሎት

  • @haileleulwoldemariam5529
    @haileleulwoldemariam5529 4 роки тому

    Kalehiwet yasemalin memehir.......ewnet ewnet emesekeralehu. eyalekesku be emebete seel ser yelemenkutin hulun agegnchalehu. egzabher yemesgen.

  • @የማረያምልጅአዲሰአለም

    ቃለሕይወት ያሰማልን🙏

  • @hellenabrha4205
    @hellenabrha4205 4 роки тому +3

    ወንድሞቼ፣እህቶቼ በእግዚአብሔር ፍፁም ሰላም እንደምን ቆያችሁ፣ መምህር እንዳሉት የንስሐ እንባ ታላቅ ሐይል አለዉ

  • @semuyemednanialemlij8291
    @semuyemednanialemlij8291 4 роки тому

    Egziabher ymesgen sladereklgn neger Hulu 🙏🙏🙏 Be enbaye ke metifo hiywet wetchalehu

  • @mariyammg9866
    @mariyammg9866 4 роки тому

    Kalewet Yasemaln tesfamegstesmayat yawarsiln memihirachin Amen Amen Amen

  • @sraself7813
    @sraself7813 4 роки тому +1

    Amen amen amen 😭😭👏👏👏👏🌾🌾🌾🌾🌾🌾💞💞💞💞💞💞💞

  • @lailallla2709
    @lailallla2709 4 роки тому +2

    አሜን አሜን አሜን

  • @aresamwmeftahgetahoye6275
    @aresamwmeftahgetahoye6275 4 роки тому

    Amen amen Amen Kali yasimalin memehire🙏🙏🙏🙏

  • @ድንግልማርያምየፈጣሪየእና

    ቃለህይወት ያሰማልን መምህራችን

  • @desstayrga2780
    @desstayrga2780 4 роки тому +2

    ቃለህይወት ያሰምልን መምህሬ

  • @addseketemaw5549
    @addseketemaw5549 4 роки тому +3

    ቃለህይወትን ያሰማልን መምህራችን ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን እኔበጣም ሃጥያተኛ ብሆንምእውነትነው እንባሃይልአለው ቸሩእግዚአብሔር እኔንም እንባዬን አይቶልኛል ይሄውም እንድህነው የምኖረው በሳውድ አረቢያነው መጀመሪያ ስመጣ ስለሃይማኖት ቅጣት እውቀቱየለኝም ማትብያለኝ ክርስቲያንብቻነበርኩ ከዛም ሃይማኖቴን ሳልናገር አድአመት ከመንፈቅ እደአህዛብ ተቀመጥኩኝ ከዛም ከምማረውትምህርት አከማዳምጣቸውስብከቶች ስነሳ እኔማነኝ አልኩ እግዚአብሔርም ባንድት እህቴላይ አድሮ ስራውንሰራ ለዚች እህቴ ታሪኬን ነገርኳት እስዋም እግዚአብሔር ዘመንዋን ይባርክላትና ከአባትጋር ጠየቀችልኝ እኔም እመቤቴሆይ እባክሽን ሃይማኖቴን ተናግሬ ሳልሳቀቅልኑር እያልኩ ሁልጊዜም ስራጨርሸ ከመተኛቴ በፊት አልቅሸ ፀልዬ እማፀናለሁእግዚአብሔርን እናም እኝህ አባት እግዚአብሔር ይስጣቸው አይዞሽ በመጀመሪያ አጥፍተኛል ትልቅ ሃጥያት እግዚአብሔርን መካድ አሉኝእና ፀሎትሽን አድርገሽ እኔ ክርስቲያንነኝ ብለሽተናገሪ እናም ሰዎቹ ምንምአይሉኝ
    ሽ እግዚአብሔር ልቦናይሰጣቸዋል አሉኝ እኔም በጣምፈራሁ እደት ይሆንልኛል በማለት ይችን ካሉኝ ቀንጀምሮ ለቅሶዬ በረታ የኪዳነምህረት ቀን ማታ ልጅቱፊቴን አይታ ሳልጠይቃት ጠየቀችኝምንሆሽ ስትለኝ እኔክርስቲያን ነኝ አልኳት ትንሽ ግር አላትግን እናመብትሽነው ለምንታለቅሽአለሽ አለችኝ ከዛም ሙሉ ቤተሰቡሰማ እሽብለው በሃይማኖቴ ሳልሳቀቅ የራሴን ፆምእየፆሙኩ የራሴንሃይማኖትፀሎትእያደረኩ አለሁኝ እግዚአብሔርስራው ግሩምነው ለሱየሚሳነውምን አለ ማመን አልቻልኩምእኔ ወዳው ይሄው 5ወርሆነኝ እደገና ከተወለድኩ በጣምደስ ብሎኛል ይህን ያነበሁሉ እልልልይበልልኝ ለእግዚአብሔር ክብርምስጋና ለዘላለሙ ይሁን አሜን

    • @ሄኤሜንየማርያምልጅ
      @ሄኤሜንየማርያምልጅ 4 роки тому +1

      አሜን አሜን አሜን እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልእንኳንደህናመጣሺልንእህታችንበርችልን እግዝአብሔር መንገዱ ይምራን ሁላችንም

    • @addseketemaw5549
      @addseketemaw5549 4 роки тому

      @@ሄኤሜንየማርያምልጅ አሜን፫💐

  • @91Millie09
    @91Millie09 4 роки тому +2

    Amen 3

  • @edenmeasho
    @edenmeasho 4 роки тому

    እግዚአብሔር ይመስገን በእንባ መጸለይ ሀይል አለው ወንድሜ 🙏

  • @kiakiya2665
    @kiakiya2665 4 роки тому +1

    እንባ ሃይል አለው አምንበታለው መልስም አግንቼበታለው ለዛም አመሰግናታለው እናቴ ቅድስት ድንግል ማርያም🙏🏻🙏🏻🙏🏻

  • @DawitAdenewKassa
    @DawitAdenewKassa Рік тому

    እንባ ሀይል አለው ስለ ሀጥያታችን ማልቀስ መቻል ትልቅ ፀጋ ነው

  • @ያሬድየኪዳነምህረትልጅ1624

    በረከታቸው ይደርብን

  • @HelenBirane
    @HelenBirane 23 дні тому +1

    Amen amen amen ❤❤❤❤❤❤❤

  • @eskezeyaalena8463
    @eskezeyaalena8463 2 роки тому

    እግዚአብሒር ይባርክህ

  • @hhfj9761
    @hhfj9761 4 роки тому

    እግዚአብሔር ይመሰገን መምህራችን ቃለ ሂወት ያሰማልን የቅዱሳኑ ምልጃና ፆሎት በያለንበት የምድር ዳርቻ ሁሉ ይጠብቀን አሜን
    እንባ በቅን ልቦና ካለቀሱ ሀይል አላት እኔ ፈተናዬ ሲቃዬ በባዕድ አጋር ላይ እጅግ ብዙ ነበር አሁን ግን እግዚአብሔር ይመስገን ምን እከፍላለሁ ቢከፈልስ ስንቱን ጨርሼ እከፍለዋለሁ ከባድ የሆድ ቁርጠት ቁረጥማን እግሬ ምንም ሳይነካዉ ጉልበቴ ላይ ያመኛል ወድቆ እነደተሰበረ ሰዉን ሌላው ሰዉነቴ ይቆነጥጠኝ ነበር እንደ ጉንዳን ተዘርዝሮ አያልቅም ሁሉን ተቋቁሜ በጣም እንዳለቅስ ያደረገኝ ግን በምተኛ ስአት እሚፈትነኝ ጥቁር ነገር ይመጣና ዘፍ ሲልብኝ እጮሀለሁ ደግነቱ ለኔዉ ነው ጩሄቱ እሚሰማኝ ለሌላ አይሰማም ዉዳሴን አነብቤ ነው እምተኛ ግን ምንም ሊለቀኝ አልቻለም ከጭነቀቴ የተነሳ በየቀኑ ነው የሚነስረኝ ይህ ጠላት በዛ ላይ በሰዎ ላይ እያደረ ያጣላኛል አረ ስንቱ የዛሬ ሁለት አመት መፆም ጀመርኩ እየፅምኩ ስፀልይ በፊት አልፆምም ነበር አህዛብ አገር ነኝ እያልኩ እና ዉዳሴን ይወድስዋን አንቀፀ ብርሀንን አንብቤ እተኛለሁ እና እንደለመደዉ ለሊት እየመጣ የሚጫነኝ መንፈስ ሲመጣካነዱ ወገን ጫፉ መስቀል ሌላው ወገን ጦር ነገር ነው እየበረረ በአየር ላይ መጣና አጠገቤ ቆም አለ ከዚያ ወዲህ ጭንቀቱ ቀረልኝ ሰዉየ ነጭ አይደለም የለበሱት ቢጫ ነዉ እና ፀይም ፀጉራቸዉ ረጅም ነበር የሚያሰጠኘንቀኝ ጭስ ነገር ነው የሆነው እኒህም አባት አባ ዩሐንስ ናቸዉ ያወቅኋቸዉ አሁን ነዉ እኔ ከዛሬ ሁለት አመት በፊት ሰልኬ ማዉሪያ ብቻ ነው ትልቁ አይደለም ከሻፍ ነበር እግዚአብሔር ይመስገን አሁን ሰላም እንቅልፍ ሰላምና ኑሮ እየኖርኩ ነው መምህር የምታቀርባቸው ገጠመኞች እነዲሁም መምህር ቀስቀስ ሄኖክ የሚስተምረዉ የኔ ሂወት ነዉ እግዚአብሔር ይባርካችሁ እኛም በሰላም ለአገር በቅተን ለመመስከር ያብቃን !!!!አሜን 🤲🤲🤲