Reyot Kin: ገጣሚና ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ ሲተዘት፡፡ በቴዎድሮስ ጸጋዬ፡፡

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 10 вер 2024
  • ገጣሚና ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ ሲተዘት፡፡ በቴዎድሮስ ጸጋዬ፡፡
    ቀንን ካልወጡት ጤዛ እየላሱ፣
    ማጣት ስለት ነው ጥንድ ምላሱ፡፡
    ሙሉጌታ ተስፋዬ ወልድያ ሙጋድ በሚባል አካባቢ በ1946 የተወለደ፣ የተባ ብእር፣ የተዋበ ቋንቋ፣ የጠለቀ ሀሳብ ባለቤት የነበረ ገጣሚና ባለቅኔ ነበር፡፡ በህይወት በኖረባቸው 50 አመታት እጅግ በርካታ ውብና ጠሊቅ ግጥሞችን ጽፏል፡፡ እውነት ከመንበርህ የለህማ፣ ምነው አንተ ሙሽር፣ ደስ ይላል መስከረም፣ የባለቅኔው ምህላ፣ ስምአኒ ከጌቴሰማኒ፣ ወደሚቀጥለው፣ ከወገብ በላይ ታቦት ከወገብ በታች ጣኦት፣ ዳብሬ ምንህ ክፉ፣ የሰከነች ሰፊና፣ ከሰው መርጦ ለሹመትና ሌሎች የበዙ ግጥሞቹ በስነጽሁፍ አፍቃርያን ዘንድ ልዩና ትልቅ ስፍራ አላቸው፡፡ግጥሞቹ በቅርቡ በስንዱ አበበ አሰባሳቢነት የባለቅኔው ምህላ በሚል ርእስ ለገበያ ቀርበዋል፡፡
    ሙሉጌታ ተስፋዬ እጅግ የተወደዱ የዘፈን ግጥሞችን ለተለያዩ ድምጻውያን ሰጥቶ ተጫውተውለታል፡፡ አበበ ተካ፣ ብጽአት ስዩም፣ አህመድ ለጋስ፣ ታምራት ደስታ፣ ዣንስዩም ሄኖክ፣ ሀና ሸንቁጤ፣ ጸደንያ ገብረማርቆስ ግጥሞቹን ካቀነቀኑ ድምጻውያን መሀል ይጠቀሳሉ፡፡ ገጣሚና ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ ወፍዬ ለተሰኘችው በአበበ ተካ ለተዘፈነች ግጥሙ ከሁሉ የተለየ ግምትና ፍቅር እንዳለውም ገልጽዋል፡፡ “ወፍዬን” ይላል ሙሉጌታ፡፡ “ወፍዬን፣ አማርኛ ቋንቋ በህይወት እስካለ ድረስ፣ አማርኛ የሚችል ሰው በህይወት ዘመኑ ሁለቴ ባይሰማት፣ ቢያንስ አንዴ ሊሰማት ግድ አለበት”
    ሙሉጌታ ተስፋዬ ምንም እንኳ ለቁጥር የበዙ ድንቅ የጥበብ ውጤቶችን ቢቸረንም፣ ብርሃኑን ሳንመለከትለት፣ እውነቱን ሳናጎላለት፣ እሳቱን ሳንሞቅለት፣ ህመሙን ሳንጋራለት፣ እንደሚገባ ሳናከብረው ያለፈም ባለቅኔ ነው፡፡
    ቴዎድሮስ ጸጋዬ ገጣሚና ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬን እንዲህ ይተዝታል፡፡

КОМЕНТАРІ • 30