የኢትዮጵያ መንግስት 1,500 ብር የሚከፈላቸው ሰራተኞችን ደመወዝ በ300 ፐርሰንት ሊጨምር ነው | Abiy Ahmed | Ethiopia | Salary| News

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 16 вер 2024
  • የኢትዮጵያ መንግስት ለደመወዝ ጭማሪ ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ እንደመደበ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። በቅርቡ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚቀርበው ተጨማሪ በጀት የሚካተተው የደመወዝ ጭማሪ በዋናነት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የመንግስት ሰራተኞችን የሚመለከት እንደሆነ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “ተሿሚዎች ብዙ ላያገኙ ይችላሉ” ብለዋል።
    ጠቅላይ ሚኒስትሩ የደመወዝ ጭማሪን ጉዳይ ያነሱት፤ ከክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ከፌደራል መንግስት ባለስልጣናት እና ከግል ባንኮች ፕሬዝዳንቶች ጋር በተደረገ ውይይት ነው። ከሁለት ሰዓት በላይ የፈጀው ውይይት፤ የኢትዮጵያ መንግስት የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ ቢሆንም በገበያ ላይ ወደ ተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓት የተደረገው ሽግግር ዋነኛ ትኩረት አግኝቷል።
    ከውይይቱ አንድ ሰዓት ከ20 ደቂቃ ገደማ ወስደው ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፤ “በስንት ልመና፣ በስንት ጭቅጭቅ የመጣ” ያሉትን “ድል”፤ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት መያያዙ ቅር አሰኝቷቸው ታይቷል። ተሳታፊዎች ካቀረቧቸው ጥያቄዎች በኋላ ረዘም ያለ ጊዜ ወስደው ምላሽ የሰጡት አብይ፤ የመንግስታቸውን ውሳኔ በተደጋጋሚ ሲከላከሉ ተደምጠዋል።(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
    ተጨማሪውን ለማንበብ ይሄን ሊንክ ይጫኑ ethiopiainside...
    -------------------------------------------------------------------------------------------
    የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
    ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider...​
    ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
    ትዊተር (ኤክስ) ፦ / ethiopiainsider
    ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaI...
    ቲክቶክ፦ / ethiopiainsider

КОМЕНТАРІ • 153