ከመስከረም ወር ጀምሮ ታሳቢ የሚደረግ የደመወዝ ጭማሪ በሚኒስትሮች ምክር ቤት መጽደቁን የገንዘብ ሚኒስትሩ ገለጹ|salary |zena |ethiopiainsider

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 9 жов 2024
  • ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ ለሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ከመስከረም ወር ጀምሮ ታሳቢ የሚደረግ የደመወዝ ጭማሪ፤ ከትላንት በስቲያ በተካሄደው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ መጽደቁን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ። የደመወዝ ጭማሪው 92 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት መጠየቁንም የገንዘብ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
    ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት፤ ከሁለት ወራት በፊት መተግበር የጀመረውን የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያዎች አስመልክቶ በትላንትናው ዕለት ለመንግስት ቅርበት ላለው ፋና ቴሌቪዥን በሰጡት ማብራሪያ ላይ ነው። ባለፈው ሐምሌ ወር መጨረሻ ይፋ የተደረገውን ይህን የፖሊሲ ማሻሻያ ተከትሎ፤ ኢትዮጵያ “በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓት” ተግባራዊ እያደረገች ትገኛለች።
    የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም አካል የሆነውን የእዚህን የፖሊሲ ለውጥ አፈጻጸም የሚገመግም ስብሰባ በትላንትናው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተካሄዶ ነበር። በስብሰባው የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፤ “ፖሊሲው በስኬታማ አፈጻጸም ላይ መሆኑን ያለፉት ሁለት ወራት አሳይተዋል” ሲሉ በይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።
    የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያው ተፈጻሚ በሆነባቸው ወራት “የተረጋጋ የውጭ ምንዛሬ ከባቢን መመልከት ችለናል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “የገቢ ግባችንም የተቀመጠለትን ግብ በመምታት በታለመለት መንገድ ላይ ይገኛል” ሲሉ የአፈጻጸም ግምገማ ውጤቱን አብራርተዋል። በትላንቱ ስብሰባ ላይ የተሳተፉት እና የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ አህመድ በበኩላቸው፤ የፖሊሲ ማሻሻያው “በጎላ መልኩ ማህበራዊ ጫና እንዳያስከትል” በወጣው እቅድ መሰረት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ለፋና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
    🔴 ተጨማሪውን ለማንበብ ይሄን ሊንክ ይጫኑ ethiopiainside...
    የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
    ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider...​
    ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
    ትዊተር (ኤክስ) ፦ / ethiopiainsider
    ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaI...
    ቲክቶክ፦ / ethiopiainsider

КОМЕНТАРІ • 12

  • @AhmadAbdushakur
    @AhmadAbdushakur День тому

    yes thankyu

  • @TibebuBiruk-nt2nh
    @TibebuBiruk-nt2nh 6 днів тому +1

    Thank you

  • @AdemAmànAdem
    @AdemAmànAdem День тому

    Ok

  • @MHMETHIOPIA
    @MHMETHIOPIA 6 днів тому +3

    እረ የጡረተኞች ችግርና ሰቆቃ እየባሠበት ነው መንግስት አንድ ይበላቸው እኛም ድምፅ እንሁናቸው

    • @samritesfaye8252
      @samritesfaye8252 14 годин тому

      በትክክል ለጡረተኞች በሚገባ ችግር ውስጥ ነው ያሉት እኮ

  • @DestaDogiso
    @DestaDogiso 6 днів тому

    no change will come

  • @moleyibeltal
    @moleyibeltal 5 днів тому

    Ahiya ahiyawn new yemiakew, fandiya gimatam.

  • @MeseretAsefa-v6c
    @MeseretAsefa-v6c День тому

    እውነት አይመስለንም

  • @NardosDemse
    @NardosDemse 5 днів тому

    ከመች ነው እዲሡ የሚጀመረው