ETHIOPIA:

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 1 гру 2024
  • #ETHIOPIA #ኢትዮጵ #EthiopTube ቅዱስ ሚካኤል ️ ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ ሚ-መኑ’ ካ-ከመ’ ኤል አምላክ ማለት ሲሆን በአንድነት ሲነበብ መኑ ከመ አምላክ (እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው) ማለት ነው፡፡ ይህ ታላቅ መልአክ ዮሐንስ ወንጌላዊ በራዕዩ ‹‹በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ›› ብሎ ከተናገረላቸው መላእክት ውስጥ የሚመደብ ሲሆን የሰባቱም ሊቃነ መላእክት አለቃ እንዲሆን እግዚአብሔር መርጦ ሹሞታል፡፡ ይህ ታላቅ መልአክ ያደረጋቸው የሠራቸው እጅግ ብዙ የሆኑ ተአምራት አሉት፡፡ ️በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ። በፊቱ ተጠንቀቁ፥ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት። ( ኦሪ ዘፀ 23፥20-21)በትህትናው ልዕልናን ያገኘው ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠው ክብር ከማንኛውም መልአክ የበለጠ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ አስቀምጦታል፡፡ ሚካኤል ማለት “ከመ እግዚአብሔር እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው?” ማለት ነው፡፡ ይህም የእግዚአብሔርን ገናንነትና እሱን የሚመስል አምላክ እንደሌለ የሚያመለክት ነው እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ ንጹሕ ርህሩህ ኃይል ረቂቅ ማነው? መልሱ የለም ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል የስሙ ዘርፍ ሆነው የሚጨመሩ መጠሪያዎች አሉት እነዚህም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠውን የባለሟልነት ክብር የሚገልጹ ናቸው፡፡ ይኸውም መልአከ ኃይል ፣መጋቤ ብሉይ፣ መልአከ ምክሩ ናቸው፡፡️መልአከ ኃይል የተባለው እግዚአብሔር በሱ አማካይነት ታላላቅ ሥራዎችን በመሥራት ኃይሉን ስለገለጸ፣ ዲያብሎስን ከነሠራዊቱ ስላሸነፈ ነው፡፡ ️ መጋቤ ብሉይ የተባለበት ምክንያት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከእግዚአብሔር እየተላከ ብዙ ታላላቅ ሥራዎችን የሠራ በመሆኑ ነው፡፡ መልአከ ምክር ወይም የእግዚአብሔር የምክሩ አበጋዝ የተባለበት ምክንያት እግዚአብሔርን በምክሩ ይረዳዋል ለማለት ሳይሆን እግዚአብሔር የሚሠራውን ሥራ ለወዳጁ ለቅዱስ ሚካኤል ይገልጽለታል በሱም አማካኝነት ይሠራል ለማለት ነው፡፡የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ! የተጨነቁትን ዘወትር እንደምትረዳቸው ሁሉ እኔንም ለመርዳት ክንፍህን ዘርግተህ ፈጥነህ ድረስ። ቅዱስ ሚካኤል ሆይ! ለሰው ልጅ ይቅርታን ለማስገኝት ወደ ልዑል እግዚአብሔር አሻቅበው ለሚማልዱ ዓይኖችህ ሰላምታ ይገባል።የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ፣ጸሎትና ጥበቃው ከሁላችን ጋር ይሁን። አሜን !!

КОМЕНТАРІ • 10

  • @Teka-n9z
    @Teka-n9z 11 днів тому +3

    አቤቱ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ
    ምልጃህ ይጠብቀን አሜን
    አሜን አሜን 🙏🙏🙏🙏🙏
    🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲

  • @elizabethyimer237
    @elizabethyimer237 11 днів тому +2

    ቃለ ህይወትን ያሰማልን

  • @happyhappy5826
    @happyhappy5826 11 днів тому +1

    Amen Amen Amen🙏🙏🙏

  • @Arar-i1m
    @Arar-i1m 11 днів тому +2

    እንኳንአደርሰንአደርሳችሁ

  • @yonasnegash340
    @yonasnegash340 11 днів тому +1

    አንኩአን አደረሰሽ አህቴ ቃለ ሂወት ያሰማሽ

  • @abebahagos5208
    @abebahagos5208 11 днів тому

    Amen Amen Amen K/Micheal kifuwen hulu yeshefnelen. Kekefu yeseweren. Amen Amen Amen 🙏🙏🙏

  • @habtamu4106
    @habtamu4106 11 днів тому +1

    እህታችን እንኳን ደህና መጣሽ አንቺ ስታቀርቢው በጣም ጥሩ ነው አንቺው ቀጥይበት እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል አደረሳችሁ።❤❤❤🎉🎉🎉

  • @alemitujabi5671
    @alemitujabi5671 11 днів тому +1

    እንኳን አደረሰን!!!!

  • @girmamang3797
    @girmamang3797 6 днів тому

    Keep it up . Berchi❤

  • @AsedeMariam
    @AsedeMariam 11 днів тому

    የጀመርሽውን ድርሣን እስከመጨረሻው ለምን አላነበብሽም።ድርሣን አይቋረጥም።