"…ጎንደርዬን እንዴት እንደምወዳት! የጎንደር ዩኒቨርስቲ ምሩቅ መሆኔንማ..."@yehewanua Eyita@Nahoo Television

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 15 жов 2024
  • "…ጎንደርዬን እንዴት እንደምወዳት! የጎንደር ዩኒቨርስቲ ምሩቅ መሆኔንማ..."@yehewanua Eyita@Nahoo Television
    For more :
    ቴሌግራም :- t.me/NahooTele...
    ፌስቡክ፦ / nahooethiopia
    ዩትዩብ፦ / nahootvethi. .
    Web-Site :- nahootelevision...

КОМЕНТАРІ • 9

  • @tinsaetesfaw9088
    @tinsaetesfaw9088 5 місяців тому +1

    Thanks to Dr melat who gave a clear and matured explanation for every question.

  • @TheTesemahb
    @TheTesemahb 6 місяців тому +2

    You're Amazing, Doctor God bless you!

  • @berhanea3798
    @berhanea3798 6 місяців тому +2

    Dr. Melat, you have achieved so much at such young age! You’re so smart and talented, may God help you grow further into your education and career! 🥰🥰🥰🥰

  • @teddyselassie9955
    @teddyselassie9955 6 місяців тому +1

    Great interview the journalist and Dr Melat I love you guys

  • @EliasGetachew-y6g
    @EliasGetachew-y6g 6 місяців тому +2

    ❤❤

  • @seifutilahun1204
    @seifutilahun1204 6 місяців тому +2

    የምትወደጂዶ/ርነሽ እግዚአብሔርም ይባርክሽ

  • @ffm377
    @ffm377 6 місяців тому

    ❤bravo

  • @serguteselassiekebebushelw7559
    @serguteselassiekebebushelw7559 6 місяців тому +1

    እንዴት ነህ? አዬህ አቶ ጃዋር፣ ወይን ፕሮፌሰር ህዝቃዬል፣ ወይንም ዶር መራራ ጉዲና አልነበሩም በሬቻ ጭፍጨፋ ተመድ ሶሊዳሪት ያሳዩት፣ ለእኔ ሲባል እንኳን በፀጋዬ ራዲዮ ብቻ ለከፈልኩት መስዋዕትነት አንድም የአማራ ልጅ አንድም የተዋህዶ ልጅ ስቃይ ሊደርስበት ባልተገባ ነበር፣ ለዛሬው መንበር የተበቃው በፋንታዚ አልነበርም። ንግሥት ምንትዋብ መከነች አልክን ወንድም ዓለም? ለህሊና ዳኝነት በስሱ እስኪ ……ዛሬ ህሊናዬን የሞገተ ጉዳይ ስላነሳህ መልሱን ልሰጥህ ወደድኩኝ። ዶር ሜላትም ብትመልስልህም። በሌላ በኩል ልዕልቴን ዶር አንጌላ ሜርክልንም ስላነሳህ የኢትዮጵያ እናቶችን ያደመጡ ስለመሆናቸው ልገልጽልህ ወደድኩ። ቅድስቷ ወሮ ሚሺያል ኦባን ጨምሮ። እንደ እኔ ተመድ ቀጣይ መሪውን ከእነኝህ ሁለት ቅድስቶቼ አንዳቸውን ቢመርጥ ምርጫዬ ነው። እቴጌ ኢትዮጵያም ድምጽ ይኖራት ነበር። ጉዳታችን በልኩ ስለሚያውቁ። አንተ ንግሥት ምንትዋብ መከነች ብለሃል። እሷ ብቻ ሳትሆን እቴጌ ተዋቡም፣ እቴጌ ጣይቱም መከኑ የማለት ያህል ነው የተሰማኝ። እቴጌ ጣይቱ ለኢትዮጵያ ምን ነበሩ? ንግሥት ምንቴ መከነች ያሰኝ ይሆን??? ዕድሉን ማጣት አንዱ ነው። ሁለተኛው የቦታው አቀማመጥም ነው። ሁለቱንም ዶር ሜላት መልሳዋለች። ትባረክልኝ። የከፋው ሁሉ ወደዬት ተመመ? ምን ስለሆነ ምቹ ስለሆነ። የከፋው ሁሉ ወደጎንደር መትመሙ ጎንደርን ምን አደረጋት? የጦርነት ቀጠና። ስንት ሳይንቲስት፣ ስንት ፈላስፋ ተቀጬ? በእኔ ዘመንም ጦርነት ዛሬም። ልደተ ክርስቶስ በባሩድና በሬሳ 2016ም። አዬህ ይህን ሙሉ 50 ዓመት እሰበው። ሌላ ያችን ቀንበጥ እሰባት አማራ ተጋድሎን እንዴት እንደመራች ንግሥት ይርጋን። ያ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጃጀት ውጭ አገርስ አይተኽዋልን? ዛሬ ያላትን የፖለቲካ አቋም አላውቅም። ለወቅቱ ግን ፈር ቀዳጅ ነበረች። እና ምንቴ መከነችን? ወደ እኔ ልመልስህ የትኛዋ ሴት ናት የኮሚኒቲ ራዲዮ ስደተኛ ካንፕ ሆና ያደራጀች? የትኛዋስ ሴት ትሆን ኢንተርኔት ሳይኖራት ሆም ፔጅ ያደራጀች? የትኛዋ ሴት ስደተኛ ናት ጠረጴዛ እና ወንበር ሳይኖራት የ20 መፃህፍት ስክርፒት ጨርሳ ሰባቱን ለህትምት ያበቃች? የትኛዋ ሴት ስደተኛ ትሆን ካንፕ ውስጥ ሆና በድህረ ገፆዋ እና በራዲዮ ፕሮግራሟ የልጆች ፕሮግራም መሰናዶ የወጠነች? ልትነግረኝ ትችላለህ? የትኛዋ ሴት ስደተኛ ናት በዬሳምንቱ በቋሚ አምደኝነት ከሊቅ እስከ ደቂቅ በደጉ ዘሃበሻ እና በደጉ ሳተናው እምትጽፍ፣ እምትሞግት? የትኛዋ ስደተኛ ካንፕ ውስጥ ተቀምጣ ህዝባዊ ስብሰባወችን በራሷ ወጪ ተጉዛ የምትዘግብ። ሲዊዝ ብቻ አይደለም ጀርመን፣ ኮፐን ሃገን ይታከል። የትኛው ስደተኛ ሴት ናት ተመድን፣ አውሮፓ ህብረትን የፍቅር ተፈጥሮ እንደ ሂሳብ፣ እንደ ባይወለጂ ካሪክለም ተነድፎለት መደበኛ ትምህርት ይሁን ብላ የሞገተች? የትኛዋ ቀንጣ ሴት ትሆን ያለአንድ አጋዢ አይዞሽ ባይ የፀጋዬ ራዲይን ለ16 ዓመት በስንት ወጀብ እና ክስ፣ ሁለት ዩቱብ ቻናል፣ አንድ ብሎግ፣ አንድ ፌቡ ብቻዋን በራሷ ወጪ የምትመራ? የትኛዋ ስደተኛ ሴት ናት ካንፕ ውስጥ ሆና ኢትዮጵያን ለማስተዋወቅ ለድምፅ አልባ እህቶቿ ድምጽ የምትሆን? በስደተኛ መጋዚን፣ 6 ጊዜ በሲዊዝ ኢንተግሬሽን ቤተመፃህፍት ጉባኤ መፃህፎቶቿ መግለጫ ተሰጥተውባቸው ተሽጠው ብቻ ሳይሆን የአማርኛ ቋንቋ ዲፓርትመንትም ተከፍቶላቸዋል። የ193 አገሮች ገጽ መፃህፍ ህትምት በሲዊዝም ኢትዮጵያም አማርኛ ቋንቋም አልቀረበትም። መቼ ፈልገህን? በአገር ውስጥም አርቲስት ሜላት እና አምለሰትም አሉ። በእኔ በኩል ማን ደፍሮ ሥሜን ያነሳል? የትኛው ደፋር ከጋዜጠኛ ሥሜነህ ባይፈርስ በስተቀር??? ሌላው ጎንደር ሲባል ፀጉሩ የሚቆመው ስንቱ ነው? ለዛውም ሴት? አጭር ፊልም ፕሮጀክት ጀምሬ ሁለት እንደሠራሁ ቲሙን አስቆሙት። ወደ 30 የሚጠጋ ስክሪፕት ጨርሼ ነበር። ከአንተ አገር ለአንዲት እህቴ በራሴ ወጪ 7 መፃህፍት ልኬያለሁ፣ 613 እርዕስ ያላቸው ሦስት የግጥም መፃህፌንም ለአንድ ወንድሜ በራሴ ወጪ ልኬያለሁ፣ አሜሪካ 7 መፃህፍቴን ለሁለት፣ አንድ መጽሐፍ ለአንድ ወንድሜ፣ 7 መጽሐፍ ለአንዲት ኖይዝላንድ ለምትኖር እህቴ ልኬያለሁ። አክሰሱ ያላቸውም በዝምታ አለፋት። ግጥሞቼ በዲዛይን የተሠሩ ናቸው። እርዕሳቸውም ባልተለመደ ሁኔታ ነው በራሴ መንገድ የተሠሩ። እና ምንቴ መከነች ወይንስ አፈራች??? ብዙ የተከደኑ ነገሮችን አልፌ ማለት ነው። የእኛ አገር ፖለቲካ ታውቀዋለህ። እንዳሻህ ካላቦካህ ትገለላህ። ሼር ማድረግ እንኳን አይፈቀድልኝም። አስተያዬት መፃፍም። ፌቡ ዘግይቼ ጀመርኩ። እሱም በስውር ባን ውስጥ ነው። በፈለገው መልክ ቢታገሉኝም ሲዊዝ ውስጥ ግን ቋሚ አሻራ አለኝ። ተመስገን። በሥነምግባር ግድፈት ተወልጄ ያደኩበትን የጎንደርዬን ማህበረሰብ በክፋ አስነስቼ አላውቅም። በጥንቃቄ ገድሜ ነው የምኖረው። ሳጠቃልለው ኢትዮጵያ የከበደችን ለሁላችንም ነው። አቅም ይፈራል። ለዛውም የጎንደር ሳተናአንስት። እግዚአብሄር ይስጥልኝ።