" ኮሜዲያን እሽቱን ሆቴል ያሳደረው ታሪክ " ክፍል - 01

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 12 січ 2025

КОМЕНТАРІ •

  • @hanaethiopia1059
    @hanaethiopia1059 2 роки тому +111

    አቤት የሃገሬ ህዝብ ያለበት አበሳና መከራ ተወርቶ አያልቅም:: እግዚአብሄር ሆይ ሕዝብን አስብ እርስትህንም ባርክ::🙏🏽🥲

  • @ሰላምሐበሻ
    @ሰላምሐበሻ 2 роки тому +177

    አሼ አንተ ቅን ልጅ እንደ አንተ አይነት ሰዎች በእትዮጵያ ምድር ይብዙልን😍🙏💚💛❤

  • @etsefews-sm
    @etsefews-sm 2 роки тому +113

    እሼ መልካም ሰው አንተን በጣም አደንቅሀለሁ በቀን ውስጥ 24 ሠዓት እንዴት እንደምትጠቀምበት ነው ይህን ሁሉ ተግባር ማከናወን ከፈጣሪ እገዛ ካልሆነ በስተቀር አይሳካም። ኅያሉ አምላክ ብርታቱን ይስጥህ።

    • @ambesajrsemere723
      @ambesajrsemere723 2 роки тому

      ከፈጣሪ ደገፍ ራስህን ማሳመን ነው በቃ busy መሆን

    • @etsefews-sm
      @etsefews-sm 2 роки тому +1

      @@ambesajrsemere723 እሱም ትክክል ነህ እችላለሁ ብሎ በራስ መተማመን ቁልፉ ጉዳይ ሆኖ ግን እንድትበርታ አቅም የሚሰጥህ ለሰኬት የምትበቃው እግዚአብሔር ሲጨመርበት ነው።

    • @ambesajrsemere723
      @ambesajrsemere723 2 роки тому +1

      @@etsefews-sm እሱማ ግዴታ ነው ብያለሁ'ኮ፡

  • @abiyefekadu9125
    @abiyefekadu9125 2 роки тому +21

    እሼ አብዬ ፍቃዱ እባለላሁኝ የልጁ ታሪክ እየለቀስኩኝ ነው የሰማሁት ምክንያቱም የገጠር ልጅ ስለሆንኩኝ ተመሳሳይ ህይወት ስለሆነ የኢትዮጵያ የገጠር ኑሩ ልክ እንደአበራ ነው እኔም አንደኛ ክፍል የገባሁት በ8-9 ዓመት ሲሞላኝ ነው ምክንያቱም ቤተሰቦቼን ስለምረዳና የመጀመሪያ ልጅ ስለሆንኩኝ፡፡ በ1989 ዓ.ም 1ኛ ክፍል ገባሁ ነገር ግን ልቀጥል አልቻልኩኝም በዛው ዓመት አቋርጬ አንደኛ ክፍል ልጨርስ 2 ወር ሲቀረው ቀንጃ እንድሄድ ተደርኩኝ በሰዓቱ በዓመት የሚከፈለኝ 120 ብር ነበር አባቴ ከባለቀንጃው ጋር ተሰማምቶ ላካኝ ጉዞየን ቀጠልኩኝ ነገር ከቤት ስወጣ እናቴ እያለቀሰች ነበር እንድሄድ ፈቃደኛ አልነበርችም እያለቀሰች ግን አንድ ሚስጠር ነገርችኝ አባትህ ቅር እንዳይለሁ ባለቀንጃው ቤቱ ድረስ ሂድና አልተመቸኝም ብላህ ተመልስህ ና አልችኝ እሺ አልኮት ጉዞየን ቀጠልኩኝ ቤቱ ስደረስን የሰውየው ሚስት/ባለቀንጃው እመጫት ነበርች ቤቱ ሁሉ ሰው ነው ቡና አለ ጠላ አለ አርቄ አለ ዳቦ አለ ሰው እየጠጣ እየበላ ነው ለእኔም ምግብ ተሰጠኝ ቡናየንም ጠጣሁ፡፡ ቡናው ካለቀ በኋላ ሰው ተበተነ እኔም እመጫት ጋር ቆየ ተባኩኝ ነገር ግን አበበ የሚባል ከአንድ በላይ ከባለቀንጃው አባት ጋር የቆየ የሰፈሬ ልጅ እንዳለ አውቃለሁ ግን አልተገኛኝም አበበ የት ነው አልኮቸው አለ ሥራ ነው አሉኝ እሺ ወጥተህ ተጫወት አለችኝ እመጫቷ እሺ ብዬ ወጣሁ ሰዓት አለኝ ልክ 11፡30 አካባቢው ነው መንገዱ ቢያንስ በወጣት አራማመድ ከ 2፡00 በላይ ይወስዳል፡፡ እደጃፍ ማንም ሰው የለም ባለቀንጃው ሽንኩርት እየኮተኮተ ነው ደስስ አለኝ እናቴ የነገረችኝ ትዝ አለኝ ጉዞየን ቀጥለኩኝ ከ20 ደቂቃ ጉዞ በኋላ የበግ ነጋዴዎችን አገኘኋቸው ወደየት እንደሚሄዱ ግን አላውቅም ተከተልኮቸው የመጣሁበት መንገድ ኮረኮች ሆኖ የመኪና መንገድ ነው 50ደቂቃ-1፡00 ጉዞ በኋላ ከተማ ገባን ከተማዋን አወቃለታለሁ እድገቴ ገጠር ነው ወደ እኔ አካባቢ መውጫ ግን ጠፋብኝ አሁንም የመኪና መስመር ይዤ ተጎዝኩኝ አካባቢው አዲስ ሆነብኝ ከባለቀንጀው ጋር የመጣንበት መንገድ ለማስታወስ ሞክርኩኝ አልቻልኩም ወደ ኋላ ተመልሼ መሐል ከተማ ገባሁ ከዛ በኋላ ግን እንዴት መውጫ እንድአገኘሁ አላውቅም በግ ነጋዴዎች ጋር መውጫ በር ተገናኝ ተከተልኮቸው ልክ 12፡ 30 አካባቢ እቤቴ ስገባ እናቴ እያለቀስች ነበር እኔን ስታየኝ ደስ አላት አባቴ ለምን መጣህ አለኝ ልብስ ና ብሎኝ አልኩት ዝም አለኝ በነጋተው አልሄድም አልኮቸው ወደ ትምህርቴ ተመለስኩኝ፡፡ አሁን በ2003 ዓ.ም የመጀመሪያ ዲግሪ አዲስ አበባ የኒቨርሲቲ በስታትስትክስ ተመርቄ በኢንዱስትሪ ሚኒስተር ስር ባለው የኢትየጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከፍተኛ የጥናትና ምርምር ባለሙያ ሁኜ በመንግስት ሥራ ላይ እገኛለሁ እሼ፡፡ ታሪኩ ብዙ ቢሆንም ከሞላ ጎደል ይህንን ይመስላል፡፡ ግን ብዙ ታሪኮች አሉኝ በመፅሐፍ መልክም ባይሆን ሌሎች እንዲማሩ በቃለ መጠየቅ መጋራት ይቻላል፡፡0900067950 መደወል ትችላለህ እሼ፡፡ በጣም እውድህአለሁ እግኢአብሔር ጤናና እድሜ ይስጥህ እሼ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡ እግዚአብሔር ሀገራችንን ሰላም ያድርግልኝ፡፡

    • @የማርያምልጅነኝ-ዠ6ፀ
      @የማርያምልጅነኝ-ዠ6ፀ 2 роки тому +3

      ማንኛውም ሰው በብዙ ውጣ ውረድ መንገድ ያድጋል ፈተናዎችም አሉ ግን ጠንካራ ከሆንክ ሁሉም ያልፋን እና ያን ሁሉ ውጣ ውረድ አይቶ እዚህ ለመድረስህ ፈጣሪን አመስገን

    • @ashagregessesse1596
      @ashagregessesse1596 2 роки тому

      Wow wenedme dese yelale.....

  • @ekarmenderrssi4290
    @ekarmenderrssi4290 2 роки тому +144

    ያረብ ሀገር ታሪክ ተወርቶ አያልቅም ያሣለፈው ያቀዋል ብቻ ለሀገራችን ሠላም ያብቃን

  • @የማርያምልጅነኝ-ዠ6ፀ
    @የማርያምልጅነኝ-ዠ6ፀ 2 роки тому +19

    የናቴ ልጅ ወንድሜ ማንኛውም ሰው በችግርና በመከራ ያልፋን ግን ጠክረው ከሰሩ የማይቀየር ነገር የለም ያሁሉ አልፎ ዛሬ ሌላ ሰወች ሁነናል ግን ክብር ምስጋና ለድንግል ማርያም ልጅ ወንድሜ ኑርልኝ

    • @aberanigus2856
      @aberanigus2856 2 роки тому +5

      የኔ ውድ እህት ሁሉም ባንች ነው የሆነው

    • @የማርያምልጅነኝ-ዠ6ፀ
      @የማርያምልጅነኝ-ዠ6ፀ 2 роки тому

      @@aberanigus2856 በርታልኝ ጠንክር ከዚህም በላይ ታድጋለህ 💖💖💖

    • @tadelatube4375
      @tadelatube4375 2 роки тому +2

      ሁላችንም ብዙ ፍተና አልፈናል እንኳን በባህር በአየር የመጣንም ስንቶን አሳልፈናል ብቻ ለሀገርህ ስለበቃህ አምስግን እኛም ፅልይልን ስድት ክፎ ነው

  • @abenitubekobo9014
    @abenitubekobo9014 2 роки тому +26

    የሚገርም ታሪክ ነው ባያልቅስ ነው ያልኩት ደስ ብሎኝ ነው ያዬሁት እሼቱ መለሰ ምርጥ ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ኮሜንት ሰጠሁህ ሁሉን ተቀባይ ነህ እግዚአብሔር ይባርክህ

  • @tiruworkeshetu3544
    @tiruworkeshetu3544 2 роки тому +8

    እሸትየ ተባረክ እድሜ ይስጥህ አንተን የወለደች እናትህ እድለኛ ነች እኮ
    የወድማችን አበራ ታሪክ ከእኔ ወድም ጋ ተመሳሳይ ነው የኔ አባት ሲያሳዝን

  • @እግዚአብሔርጠባቂየሚካኤል

    የሚገረመው ነገር እኔም ሴቴ ልጅ ልክ እዳታ በበረሀ ነበረ የመጣሁት የምሄደውም ቤሩት ነበር እዛ ለመድረስ 17 ቀን ነበር የፈጀብኝ አቤት ፈተና አቤት ስቃይ አቤት እረሀብ አቤት ጥማት 😭😭😭😭😭 እዲት ብየ ልገራቹሁ ደስ የሚለው ነገር ደሞ በኔ ላይ ምንም አይነት ጥቃት አልደረሰበኝም ፈጣረየን በጣም አብዝቼ አመሰግነዋለሁ ነገር ግን ጠካራ ሴት ነበርኩኝ የተሰደድኩትም በጣም እደ አይኔ ቢሌን የምሳሳለትን አባቴን በህይወት ማለትም በመተት ስለገደሉብኝ በዛ እልህ ደሞ እናቴን ላለማጣት ነበር ያሰብኩትም ተሳካልኝ እህቴን ይንበረስቴ እያስተማረኩ ከጎን ደሞ የናቴን ሄወት ማትረፍ ነበር እቅዴ እግዚአብሔርን እመኖ እጅ ሁሉም ነገር ይሳካል እኔም ከዛ ሄወት አትረፈት አሁን በደስታ ትኖራለቹ እህቴንም አስመረቄ አስጨረስኩኝ እና ወድሚ የኔና ሄወት ካተጋ ተመሳሳይ ነው መፈተን ለበጎ ነው ብላቹሁ የወጣቹሁበትን አላማቹሁ እዲሳካላቹሁ እመኝለሁ

    • @saratsegay6095
      @saratsegay6095 2 роки тому

      Amen 🙏❤️

    • @hcjth1747
      @hcjth1747 2 роки тому +4

      እግዚአብሔር አምላክ አሁንም ያሰብሽውን ሁሉ ያሳካልሽ የሞላው ቤተሰቦችሽን ሰላም ጤና አብዝቶ ይስጥልሽ እህቴ በእግዚአብሔር ያመነ እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማሪያምን የአምላክን እናት የያዘ ወድቆ አይቀርም እማምላክ ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማሪያም አትለይሽ አሜን 🙏💝

    • @eduyedingillijedu2494
      @eduyedingillijedu2494 2 роки тому

      አሜን

    • @rabiasaid9888
      @rabiasaid9888 2 роки тому +1

      አብሺሪ አላህ ካችጋ ነው ጀግና ነሺ

    • @Mነኝየበረሀውመናኝልጅ
      @Mነኝየበረሀውመናኝልጅ 2 роки тому +1

      አንቺ አስራሰባት እኔ ፡3 ወር ነው የፈጀብኝ ሊውም በቁስልና በንዳድ ሰውነቴ ትል እየፈላ እስኪወጣ እህህህህ አረ አላስታውስው

  • @naimaanaimaa2416
    @naimaanaimaa2416 2 роки тому +62

    ዛሬ የሁላችን ታሪክ ተፃፈ😥😥 ኮሜት እዳየሁት ሁሉም ያረብ ሀገር ስደተኛ ነው 😭

  • @ቅድስትብርቁ
    @ቅድስትብርቁ 2 роки тому +30

    ገራሚ ገጠመኝ ነው የስደት እሮሮ መቼም አያልቅም ብቻ ተከድኖ ይብሰል እሸየ እግዚአብሔር እንዳንተ አይነት ቅን ሰወችን ያብዛልን

  • @ሀሊማነኝከወደወሎ
    @ሀሊማነኝከወደወሎ 2 роки тому +27

    አይይይ😢 ኢትዮጵያ ሀገራችን ከፍፍፍፍፍ ብለሽ
    ዜጎችሽ በሀገራችን ላይ የደስታ ጊዜ የምናሳልፍበት ቀን
    ናፈቀኝ ኢትዮጵያዬ ምን ጊዜም ሰላምሽ ሞልቶ ይፍሰስ
    ሁሉም አልፎ ታሪክ መሆኑ ደስ ይላል ወንድም🙏🇪🇹🕊🇪🇹

  • @fakraeabte7010
    @fakraeabte7010 2 роки тому +16

    እሼ ምን ልበልህ ጀግና ነህ እመቤቴ ማርያም ከዚህም በላይ በሰው ዘንድ እንድትወደድ ምኞቴ ነው❤❤❤❤ ገራሚ ታሪክ ነው አይ ስደት ብዙ ያሳያል

  • @tigistmolla30
    @tigistmolla30 2 роки тому +18

    እሼዋ በእመብርሃን እመ ሕይወት በፍቅሯ ተሸፍነህ የምትኖር ድንቅ ሰዉ ኢትዮጵያዊ ቀና ልብ ትግስት እጅግ ታከብርሃለች ጌታ ጠብቆቱ ያብዛልኝ💜💜

  • @kedirraya2949
    @kedirraya2949 2 роки тому +4

    ጀግናው እና የፀባይ አባት የሆንከው ውድ ጓደኛየ አበራ ንጉስ አጅግ በጣም አሳዛኝ እና አስተማሪ ሀሳብ ነው! ያካፈልከን አሸም በጣም ጀግና የታሪክ ፅሀፊ ሁነህልናል
    የሰዉ ልጅ ትልቅ ቦታ ለመድረስ ብዙ ውጣውረድ ይገጥማል ግን ብዙ ሰዎች ካንተ ታሪክ ይማራሉ አበራ ንጉስ

    • @aberanigus2856
      @aberanigus2856 2 роки тому

      ከድሬ የምወድህ ወንድሜ

    • @asugualkeshi2082
      @asugualkeshi2082 2 роки тому +1

      @@aberanigus2856
      እኔም የመጀመርያ ልጅ ነኝ እና ታርኬ ከታሪክህ ይቀራረባል ገና ከስደት አልተመለስኩም ያለሁት ሰላማችን ይመልስልን ልዑል እግዚኣብሄር

  • @sarasayalewu4249
    @sarasayalewu4249 2 роки тому +16

    በጣም በሚገርማችሁ ሰራ ነበረኝ ያዉም አስቸኮይ ነበር ግን ማየት አለብኝ ብየ ቁጭብየ ነዉ የሰማሁት በተመስጦ ቀጣይ በጉጉት እንጠብቃለን እሸ እግዚአብሔር ይባርክህ ወንድማችን የሚገርም ታሪክ ነዉ የምር

  • @moamnamoha9270
    @moamnamoha9270 2 роки тому +6

    አባቴ እውይይይ እስኪ ልስማ ጨርሼ. እመለሳለው እሽየ ምን ልበልህ እረጅም እድሜ ከጤና ጋ ያሰበከው ሁሉ ይሳካልህ. ሌላ እምለው የለኝም ልዩ ሰው ነህ

  • @medinamohmmed6096
    @medinamohmmed6096 2 роки тому +4

    የስደት ነገር ከተነሳ ሁሉም ታሪክ አላው
    ብቻ እድሜ የሰጠው ታሪኩን አእምሮ ለለው ይደርሳል እዛው ለተቀጩት የት እንዳሉ ላልታወቁት ምህርትን ለቤተሰቦቻቻው ፅነትን አላህ ይስጣቻው

  • @SaeedMohammed22
    @SaeedMohammed22 2 роки тому +21

    ብጣም ይገርማል እስከ አሁን…
    ይህ ታሪክ ግን በፈልም ቢተሰራ ይበልጥ ይሻላል ነበር ።

  • @anteshtube8249
    @anteshtube8249 2 роки тому +27

    እሼ መልካም ሰው እንደ አንተ አይነት ሰዎች በእትዮጵያ ምድር ይብዙልን:: ሰላም ለሀገራችን ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር💖🇪🇹💖💕🇪🇹

    • @nigestadmase6358
      @nigestadmase6358 2 роки тому

      ክፍል ሁለት የት ላግኘው😥😥😥 ላኩልኝ ከተለቀቀ

  • @sifenshume7726
    @sifenshume7726 2 роки тому +7

    የሚገርም ታሪክ ነው ወንድሜ ወይ ስደት እስኪያልፍ ያለፋል የሰው ልጅ መከራው ብዙ ነው
    እሼ መልካም ሰው ውድድ ❤️❤️

  • @ስለሁሉምነገርእርይመ-ሠ8ኘ

    እሚገርም ታሪክ ይህ የሁሉም የብሶት ታሪክ ነው እሽቱ ደም ያለፍቃድ ታናግራለህ እግዚአብሔር ይባርክህ የልጅ አዋቂ ከፍገግታ ጋር ስውችን ማዳመጥ ስችልበት አቤት መመርቅህ እግዚአብሔር ይባርክህ

  • @beletemuleta1356
    @beletemuleta1356 2 роки тому

    የዚህ ልጅ ታሪክ ሰማሁትና ከእኔ ጋራ ሳመዛዝነው የፈረስና የአህያ ያህል ልዮነት አለው እኔም እንደ እሱ ገጠረ ነው ትውልዴ እስከ 14 ዓመቴ ገጠር ነው ያደኩት ከ14 ዓመት ቦኃሏ ወደ አአ ገባሁት አሁን ያለሁት ጀርመን ሀገር ነው ብቻ ከገጠረ እስከ ጀርመን ድረስ የገጠመኝ ነገሮች ባወራ ሰውም እንደዚህ ያሳልፋል ይባል ይሆናል አሁን ፈጣሪ ይመስገን ጥሩ ህይዎት ላይ ነኝ ያለሁት ግን ያሳለፍኩት መከራ ይከብድ ነበረ ብቻ ሁሉም ያልፋል ከፈጣሪ ጋራ ከታገዙ ዋና ተስፋ አለመቁረጥ ነው

  • @afomiyatadese8387
    @afomiyatadese8387 2 роки тому +2

    ሁሁሁሁሁሁሁ በጣም ያጓጓል መች ይሆን ቀጣይ
    እግዚአብሔር እንኳን ለሀገርህ አበቃህ

  • @እሙዩምና
    @እሙዩምና 2 роки тому

    አይ ስደት የያየው ያቀዋል ስለሁሉም ነገር አልሀምዱሊላህ እሽየ አላህ ይጠብቅህ እዳንተ አይነቶችን አላህ ያብዛልን ቅን ሰው ነህ በጣም ነው የምወድህ

  • @እግዚእኃረያሁሉባንተነውየ

    እሸቱ፡ሠላምህ፡ይብዛ፡ድን፡የዚህ፡ዘመን፡ወጣት፡የልብንጭንቀትና፡የምታዳምጥ፡አስተዋይ፡በዚህ፡ዘመን፡ለምንድ፡ነው፡ወጣቱ፡የረዘመሠላምታንና፡መልክትን፡በዋትሳብ፡መስማት፡ይሰለቻሉ፡፡እባካችሁ፡ከእሸቱ፡ቅንነትንና፡አስተዋይነትን፡እንማር፡፡ስልቹ፡አትሁኑ፡የሠውን፡ሀሳብ፡እንረዳዳ፡

  • @አስኩፍስሀሀገሬንናፋቂ

    ውይ ወንድሜ ህይወት እንዲህ ውጣ ውረድ ናት የሚገርም ታሪክ ነው

  • @Nùh4424
    @Nùh4424 2 роки тому +10

    የኛ የስደተኞች ተስፋ ሁሉም ያልፋል ነው
    አዎ ኢንሻ አሏህ ሁሉም ያልፋል ታሪኩን ልስማው
    የስደት ታሪኬ ቢወራ የኔ የግሌ 3 አሳዛኝ እና ገራሚ ፊልም ይወጣው ነበር
    የአረብ ሀገርን ኑሮ የኖረው ያውቀዋል አልሃምዱሊላህ ይህም ያልፋል

    • @ahhs9393
      @ahhs9393 2 роки тому +1

      😀😀እዉት ነው

  • @kdejaadres5875
    @kdejaadres5875 2 роки тому +9

    በጣም ገራሚ ታሪክ ነወ ቀጣዩን በጉጉት ነው የምጠብቅ

  • @dulmannerriyyatt4109
    @dulmannerriyyatt4109 2 роки тому

    እሼ በጣም ምርጥ ሰዉ ሰዉአክባሪነተህ ስነምግባርህ ሁሉም ነገሬህ የማወደድ ነዉ ምን ላርግህ በጣም እወድሀላሂ ከኔ የበለጠ ፈጣሪ ይዉደድህ

  • @rukitube8634
    @rukitube8634 2 роки тому +27

    ቀጣዩን በጉጉት እሽዬ ኑርልን ምርጡ ወንድማችን 🍓🍓🍬🍬🍬🥰🥰

  • @asefumoges2997
    @asefumoges2997 2 роки тому +6

    አይይይ😭😭😭ድህነት የኔ ታሪክ ሣውዲ አረቢያ ያለን ,ልጆች በብዛት በዚህ መንገድ ነው የመጣነው
    በብዛት የምንገኝበት የወሎ ክፍለ ሀገር ልጆች በተለይ ራያ ቆቦዎች ሣውዲ ላይ በብዛት እንገኝበታል እኔም ታሪኬኝ እስፈዋለሁ በሠላም ለሀገሬ ያብቃኝ 😭😭

  • @Dinamohamed2235
    @Dinamohamed2235 2 роки тому +15

    ታሪኩ በጣም ውስጤን ተሰማኝ እባ ተናነቀኝ😭 እሼ መልካም ሰው ቀጥልበት ይህንን መልካምነትህን

  • @bezuyefanta896
    @bezuyefanta896 2 роки тому +3

    ምሥኪን የኔወድም በጣም ተሣዝናለሕ አይሥደት

  • @elsashume9747
    @elsashume9747 2 роки тому

    ወይ ፈጣሪ እያዳዳች ያየነው አበሳና መከራ ወይ ድህነት ያልፍል እያሉ መባተት ብቻ ጤና ጌታ ሆይ ሁሉ ለአንተ ይቻልሃል

  • @molumulo570
    @molumulo570 2 роки тому

    እሄ ህይወት ማርያምን የእኔ ህይወት ነው ሁሉም በስደት ያለነው የመጀመሪያ ምክንያታችን የቤተሰብ ህይወት ለመቀየር ነው እኔም እኛ ቡዙ ቀን ተርበናል እህቶች ወንዱሞች ያን ህይወት እንዳይደግሞት እኔ ተሰደደሁ ግን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን ለእራሴ የሆነ ነገር ባይኖረኝም ቤተሰቦችን ቀይሪልሁ በህወቴ እስካሁን ደረሰ የማይጠፈኝ ነገር ቢኖር አንድ ቀን አመት ባህል ሆኖ ዶሮ ወጥ ሠረተን በምን እንበለው የዶሮዉን ሥጋ በልተን ወጡን ጠጥተን ያደርነበትን ቀን ሳስበው መቸም አረሰዉም💔💔💔💔

  • @addisdemeke1472
    @addisdemeke1472 2 роки тому +2

    ውይ እሸቱ ወሬ አታቆርፍድ እስኪ አሸዋ ድንጋ እያልክ ለማንኛውም ስቀልድ ነው ተባረክ አክባሪህ ነኝ

  • @zelalemaweke3807
    @zelalemaweke3807 2 роки тому +2

    እሼ መልካም እና ኣስተዋይ ሰው ነህ እመብርሀን ትጠብቅህ ቀጣዩ በጉጉት እጠብቃለው

  • @ነጁየናዝሬቷሽቅርቅር

    እሼ መልካም ልጅ ቃላት አጣሁልክ ውይ የኔ ወድም በጣም የሚያሳዝን ታሪክ ነው የኛ የስደተኞች ሂዎት ቢወራ ማለቅያውም የለም ኡፍ አስለቀሰኝ ወድሜን ነው የመሰለኝ 😭😭😭😭😭😭

  • @Degsewtube
    @Degsewtube 2 роки тому +23

    ገራሚ ነው ልዑል እግዚአብሔር ሀገራችንና ህዝቦቿን መረረጋጋትን አንድነትን ፍቅርን ይላክልን ሰው ለሰው አለልኝ እንጅ አለብ እምንልበትን ጊዜ ቀይሮ አሉልኝ እምንባል ያርገን ኢትዮጵያዬ ሰላምሺ ይብዛ💚💛❤️

  • @አልሀምዱሊላአንተሳእ-ኰ3ቈ

    የስደት ታሪኩ ብዙ ነው አልሀምዱሊላ አላህ ላገራችን ያብቃን የወጣነው ያልወጡትም አላህ ባገራቸው ይረዝቃቸው መሳጪ ታሪክ

  • @mikimiki7194
    @mikimiki7194 2 роки тому +7

    ሰላም እሼ ምርጥ ሰው ነህ ውድድድድ..

  • @abitiaderajew7178
    @abitiaderajew7178 2 роки тому +9

    የኔ አባት ፀጥ ብየ ነው ያዳመጥኩት አንደበቱ ደስ ሲል😍😘😘ቀጣዩን በጉጉት እንጠብቃለን የሚገርም ታሪክ ነው👌👌

  • @አይንዬየራያዋ
    @አይንዬየራያዋ 2 роки тому

    በዚህ ታሪክ በተለይ የራያና የአካቢበወች ሴት ወንዱ በጣም ትንሽ ልጆችነን የምንሰደደዉ በጣም ስቃይ ነዉ የምናሳልፍ ቡዙ ወንድሞቻችነን የጥይት እራት ሁነዉብናል እፍፍፍ ሳስበዉ ያመኛል ደበር ላይ ያጣናቸዉ ከሚስ ምሽት እሪያድ ያጣናቸዉ ወንድሞቻችን እህቶቻችን ብቻ ለሞቱት ነፍሳቸዉን ይማርልን ላለነዉ በቃይበለን ለሀገራችን ያብቃን እፍፍፍፍፍ ብቻ ያማን የማቅህ ይመስለኛን አድሴ አደለኸም መጨረሻህ ደስይላል ወንድሜ

  • @maryetube14585
    @maryetube14585 2 роки тому +2

    ሡበሀንአላህ ትምህርት ሣይገባ በፊት ያለውን ህይወት ያሣታውሳል እኔም የልጅነቴን አረሳም ስምንተኛ ክፍል ስደርስ ግን ጉዞ ወደ ሥደት

  • @genetgenifitwi5760
    @genetgenifitwi5760 2 роки тому +12

    ፈጣሪ በቃችሁ ይበለን ይስህን ስደት በጣም የሚገርም ታሪክ ነዉ

    • @ሠአዳ.ወሎየዋ
      @ሠአዳ.ወሎየዋ 2 роки тому

      @@comedianeshetu
      እሸ.ምንልበልህ.እኔዱባይ.ነውያለሁት.ከሀገሬተወጣሁ.7.አመትሆነኝ.እናትናአባትየለኝም.አልሀምዱሊላህ.በጣምከህይወቴበላይየምወዳቸው.ወድሞችአሉኝ.
      ግንግን.የወድልጅ.ስቃይስሰማ..እናቴስትሞትብኝእዳለቀስኩትነውየማለቅሰው.
      የሰው.ብሶትችግርታዳምጣለህ.ላተደግሞ.ፈጣሪ.ሙሉጤና.ከሀብትጋርይለግስህ.
      እዳተአይነትሰውነው.ኢ.ቶ.ሀገራችንየምፈልገው....ሰላሙንሁሉተመኘሁልህ..

  • @ለይላኡምጁናይድ
    @ለይላኡምጁናይድ 2 роки тому

    ህልማችንን እዉን እናዲርግ ያ ጄመአ አባታችን ከብት ሽጦ እናታችን ተቸግራ አረብ ሀገር ልከዉን እዚህ ከመጣን በሁዋላ አላማችንን አንሳት አትትፊ የዛሬዉ ታሪክ ይለያል አሹ በርታ ይገርማል

  • @kedesrzegene1704
    @kedesrzegene1704 2 роки тому +15

    እሼ መልካም ሰው ነህ ሰውን እዴት እደምትረዳ ታውቃለህ የእውነት ተመስጬ ነው ያዳመጥኩህ ቀጣዩን ለመስማት ጒጉቻለው

  • @Sara-nh3zg
    @Sara-nh3zg 2 роки тому

    እሸቱዬ የኔ መልካም ትለያለክ እግዚአብሔር ይጠብቅህ የልጁ ታሪክ ልብ አንጠልጣይ
    ነዉ እንጠብቃለን

  • @ወለተማርያምሀብተሚካኤል

    ክፍል ሁለት እጠብቃለን እሼ መልካም ሰው ❤🕊 ፍቅር የሆንክ ሰው ነህ አንተ የምታገባ ምነኛ የታደለች ሚስት ነች ❤ ፅናት ትግስት ጥበብ ብቻ እግዚአብሔር ሿሞሐል 🙌

    • @beckydd8865
      @beckydd8865 2 роки тому

      እግዚአብሔር እንደአንተ የተባረከች የትዳር ጎደኛ ይስጥህ ምን እንደምልህ አላውቅም ብቻ እረጅም እድሜና ይስጥህ ቀሪ ዘመንህ ይባረክ የኔ ደግ

  • @salilishbira7480
    @salilishbira7480 2 роки тому

    እሼቱ እግዚአብሔር ይስጥህ ምን አይነት የተባረክ ልጅ ነክ ሰለቸኝ የማትል ብሩክ ብሄካለው እግዚአብሔር ጨምሮ ጨምሮ ይስጥክ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳንተ አይነት የተባረከ ሚዲያ ያለው አላየሁም የምታቀርበው ነገር ሁሉ ታይቶ የማይጠገብ ነው በርታ

  • @kushland4761
    @kushland4761 2 роки тому +1

    እኔ በበኩሌ 12 አመት አካባቢ ውጭ ሀገር ኖሬያለሁ ግን እስካሁን ይህ ታሪክ የተለየ ነው ስለዚህ በግርምት እያዳመጥኩኝ ነው
    አስተማሪና አሳዛኝ ታሪክ ነው።

    • @ethiopia3929
      @ethiopia3929 2 роки тому

      ታድለሃል እኔስ ያለው ሁሉ ታሪክ ታሪኬ ነው የሚለየን እርሱ ወንድ ነው እኔ ሴት ነኝ ብቻ እግዚአብሔር ይመስገን

  • @serklmal6341
    @serklmal6341 2 роки тому

    በሕይወት ኑረህ እዚህ በመድረስህ እግዚአብሔር ይመስገን

  • @feteletilahun1013
    @feteletilahun1013 2 роки тому

    እሼ በጣም የምትወደድ ሠው ነህ
    ያለህ ቅንነት ጥሩ ልብ አለህ እግዚአብሔር እድሜ ይስጥህ

  • @ኤካቦድዘኢትዮጵያ
    @ኤካቦድዘኢትዮጵያ 2 роки тому

    እሽ በእውነት የሚያስለቅስ ታሪክ ነው፡፡ እውነት ለሀገርና ለእንዲህ ዓይነት ቤተሰብ ማሰብ ችግር መቅረፍ የሚችሉ ተቋማትን መገንባትና መመስረት ወጣቱ ላይ ትልቅ የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት የሚችል ስራ መስራት ያስፈልጋል፡፡

  • @ቅድሰትወልደመድህን
    @ቅድሰትወልደመድህን 2 роки тому +14

    የኔ አባት ታሪክ ነው አሁን ደግሞ በማረፊው😭😭 እስርቤት ነው በቻ ሁሉም ለበጎ ነው

  • @emanbintamena4829
    @emanbintamena4829 2 роки тому +20

    በጣም ያማል ስደት ከምንም በላይ ይከብዳል ለአዱው ሀዘን ለአዱኡ ደስታ

  • @mahletmichale7453
    @mahletmichale7453 2 роки тому

    ውይ ስደት አይኑ ይጥፋ ምናለ ስደት ቢጠፋ ኡፋፋፋ የስደት ስቃይ ሰምሺዋለው እግዚአብሔር አገራች ሰላም ያርግልን በአገራችን እንድኖር ይረዳን።

  • @mekilitkidist1542
    @mekilitkidist1542 2 роки тому +9

    እንደኔ ገና ታሪኩን ሳይስማ ሲያየዉ የሚያሳዝን አንጀት የሚበላ ልጅ እንደሆነ የተስማዉ

  • @እምዮእውድሻለሁ
    @እምዮእውድሻለሁ 2 роки тому +2

    በስማአም ሲገርም እርኝነት እንቅልፍ እህህህ እንደ አንተ ባይሆንም እኔም አንድ በሬ ገደል ገብቶብኛል የአጎቴ ነው ሌሎቻ ደህና ቀሩ መሺቶል ግን ትንሽ ልቆይ ብየ ለሺ አልኮ በሬው እየተንከባላላ ዱዱ እሚል ድምፅ ስሰማ ነው የነቀውት ሁሉም ሂዶ ብቸየን ነኝ አሁን ትዝ ሲለኝ እስቃለው እሚያሳዝናው በገደሉ እየትምጨለጨልኩ ነው ያወርድኩት እኔም እንደበሬው እሞት ነበር የእናቴ ፀሎት አግዞኝ ነው በሬው እንደሞተ ሳይ እንደምንም ዙሬ ወደ ሌሎቹን ይዠ ስሄድ አጎቴ እየመጣ ነበር እኔ ተደበቀውና ሌላ ቤት አደርኩ እግዚአብሔር ይመስገን ትርፍኩ እየው የአርብ ሀገር ሸቃላ ነኝ

  • @neimayusuf5594
    @neimayusuf5594 2 роки тому

    የኔ መልካም እሸቱ አላህ የልቦናህን መሻት ይሙላው የኔ አዳማጭ ስራህ ይባረክ እድሜ ከጤና ይስጥህ

  • @genatgenat7165
    @genatgenat7165 2 роки тому +1

    ድንቅ ታሪክ ተመስገን እንዲህ አልፎ መናገርህ እድለኛ ነህ በርታ አምላክ ይጠብቅህ

  • @fasicamolla7352
    @fasicamolla7352 2 роки тому

    አይ ወንድሜ ሁላችንም ብዙ ውጣ ውረድን አሳልፈን ይኸው በህይወት አለን እሚገርመው ልጁ ፈጣሪ አጥብቆ ይፈልግሀል ምናልባት የስለት ልጅ ትሆናለህ በአንተ አጋንት የተናደደ ይመስላል መንፈሳዌ ህይወትህ ላይ ጠበቅ በል የተሰጠህን ህይወት እንድትኖር አባትህን እረዝም እድሜ እና ጤና ይስጣቸው እላለሁ 🌾💚💛❤️

  • @fikirtemisganaw4388
    @fikirtemisganaw4388 2 роки тому

    እሼየስራ በደረቦችን ጨምሮማሪያምን የኢትዮጳያ ምርጥ ልጆች ናቹ እደናተ አይነት ሰወችን ፈጣሪያብዛልን፡፡እሼ መጥፎ ወይም ስለሀገርፍቅር የማይገባቸውን ሰውች ምንእናድርጋችው ምርርር አደረጉን ፡፡ታሪኩ በጣም አሪፍነው አርብ መቸ ደርሶ

  • @እንደትነሺሀገሬ-ፈ9ተ

    እሸየ የኔየ መልካም ወድም ሁሉን ተቀባይ እረጁም እድሜየ ከጤናጋ ያድልህ ሂወት ብዙ ውጣ ውረድ አላት ነገረ ግን ትግስት ያድለን በሂወት ትልቁ ህመም ተስፋ መቁረጥነው ነገረ ግን ተስፋ ሳንቆረጥ ጠክረን ከሰራን ከታገስን የማያልፍ የለም በፍጣሪይ ፍቃድ አይዞን ወድሜየ ለውድቶ ኢትዬጱያ ሰላም እመኛለሁ ሰደቃላሺ ከፍ ብሎ ይውለብለብ ፍቅረን አድነትን መተሳሰብን መቻቻልን ያድለን💚💛❤️

  • @rahejean4212
    @rahejean4212 2 роки тому +2

    በጣም የሚያሳዝን ታሪክ ነው ክርስታን ቆራጥ ነው
    የመቤታችን የስደቷን እያሰብን እናልፍለን የሚገርመው ግን የበሬ ዋጋ ከአምስት ሺ ወደ መቶ ሐያምስት ሺ መግባቱ ነው ወይ ግዜ ያ ዘመን ይመጣ ይሁን ? አገሬ ልጆች ይብቃ ስደት 💚💛❤

  • @rukitube8634
    @rukitube8634 2 роки тому +22

    እንኳን ደህና መጣቹህ ጥብሱን በልቶ ሽሮ ቤት ወሰደኝ ሲል አሳቀኝም አሳዘነኝም 🤣🤣

    • @madi8643
      @madi8643 2 роки тому

      እና እራሱ እየተናደድኩ ሳቅኩኝ

  • @haymiyutbe6580
    @haymiyutbe6580 2 роки тому

    የዚህ ልጅ ታሪክ የኔም ታሪክ ነው በእውነት እኔም በዚህ ፈተና አልፋለሁ እኔም እሼ ክበርልኝ 1 ቀን ታሪኬን እጽፈዋለሁ እል ነበር ይሄን ልጅ ስሰማው ማሪያምን በጣም ነው ያለቀስኩት

  • @seniseni165
    @seniseni165 2 роки тому +3

    ይሂ ታሪክ የሁላችን ታሪክ ነው እናመሰግናለን እሼ

  • @mohammedabdin8393
    @mohammedabdin8393 2 роки тому

    እሼ በጣም ትልቅ ሠው የኔ ታሪክ ደሞ ከሡ ይበልጣል ይረዝማል ከመተማ በኋላ ነው ሚጀምረው ጉዞ ወደ ሡዳን ሊቢያ ኢታሊ ፍራንሥ ኢንግላንድ በህገ ወጥ መንገድ ልጆቹ ሢታረዱ ሊቢያ ነበርኩ የልጁ ታሪክ ሥሠማ በፓራሥታሞል የሚድነው ከኔው ሢነፃፀር

  • @sarahhalefom4454
    @sarahhalefom4454 2 роки тому +1

    የስደተኞች ታሪካችን ተፃፈ የጅጅጋ ፖልሶች የተደራጁ ሰይጣን ናቸዉ የሴት ብልት ሳይቀር ብር ይፈትሻሉ መናሃርያ ዉስጥ ያለ ብሮ ኣስገብተዉ በጥፍ እየመቱን እየፈተሹን ስድባቸዉ ዱላቸዉ ኣቤት ኣቤት ግን ይሄን ሁሉ ኣለፈና ለምስክርነት ኣበቃን ፈጣሪ የስደት ፈተና ከአድስ ኣበባ ነዉ የምኸምረዉ ሃረር ጅጅጋ ዉጫሎ ሃርጌሳ ሶማልንድ ብርዖ በሳሶ የባሁሩ ማእበል ርቀት የሽፌሩ ጩሀት የረዳቱ ዱላ ጀልባዋ የሆነ ነገር እንዳትሆን ክርስትያኑ ማርያም ማርያም ይላል ሙስሊሙ ያኣልህ ያረብ ሁሉ በውስጡ የመጨረሻውን ፀሎት ያደርሳል የምንተርፍም ኣይመስለንም እዛ ስምጠን የምንቀር ነዉ የምመስለን ይሄ ሁሉ እልፍ የየመን ጉድ ይመጣል ወንድም በወንድሙ ደም እና ስቃይ የምደሰትበት ደላላዉ መንግስት የሆነበት ኣገር የመን ሴት ልጅ በግድ ስትደፈር ለየመኖቹ ስሸጥዋት ለገላዋ እንካን ዉሃ ሳትታጠብ በድካሙዋ በርሃብዋ የዉሃ ጥሙ እስከነጭንቀትዋ ለእናትዋ እንካን ስልክ ደዉላ ባህር በሰላም አለፍኩኝ ሳትል በገዛ ያገርዋ ልጅ ስቃይና መንከራ ታያለች እንደማይደረስ የለም በሰዉ ደም የረጠበች ስንት ወጣት ወድቆ የቀራባት ምድር የስንት ህልምና ወጥትነት በከንቱ እንደዋዛ የሚቀርባት የተረገመች ምድር እንደርሳለን ከዛም ወታደሩም ሽፍታዉም ጥይቱም እዛ ይጠብቅሃል እግርን ኣዉጭኝ ብለህ ወደፍት ትሮጣለህ ከዛ ግን ወይ ትያዛልህ ወይ በጥይት ትመታለህ ወይ ታመልጣለይ ወይ ደሞ ወደ እንዱ ገደል ግብተህ የምረዳህ ኣጥተህ እዛዉ ትሞትና ለአሞራ ሁነህ ትቀራለህ እድልህ ሁኖ ብታመልጥም የምትወደም ጋደኛህ ወይ ወንድምህ ወይ እህትህ ሞተች ሞተኮ ወይ የት እንደገባ የለም የለችም ትሰማለህ ከወራት ወይም ከኣመታት ቡሃላ የኣልጉኝ ፅሁፍ ታያለህ ህልም እንድሆንልህ ትመኛለህ ሳዑዲ ትገባና መጨረሻ ኣብዛሃኛዉ በፖልስ ትያዛለህ እስርቤት ትገባለህ እዛም ዱላዉ ዉሃ ጥሙ ርሃቡ በቃ መከራ ነዉ ስደት ከስንት ኣንድ ግን የመስራት እድል ይኖሮዋዋ ለዚህም እድል ያስፈልጋል ስደት ስደት-----------የስንት ህይወት የበላ

  • @khadijamalki2266
    @khadijamalki2266 2 роки тому +1

    እሸቱመልካም ስዉ አንተስይተለየህነህበእዉነት ፀባይህን አይለዉጠዉ ዉይይወንድማችን ይህታሪክየሁላችንነዉ ከብቶችቤተስብንበመርዳት ማደግ ያንተየሚለየዉጎዝዉወደስደት መሆኑነዉ ዉይዉይዉይ ጭካኔ ፍየልከስዉ ጋር ቀጣዩንእንጠብቃለን

  • @vipx5902
    @vipx5902 2 роки тому

    ሀቢቢዋየ፣የኔቆንጆልጅ፣ውይመንከራተት፣እኔም፣የሀራልጅ፣ነኝ፣ብዙስቃይአሳልፌያለሁ

  • @اللهمَوْجُودٌبِلَاَمَكَان-ب9ح

    ሱብሓነሏህ አጂብ እኮ ነዉ በሰዉ አገር ያለን ሁሉ አሏህ ለአገራችን ያብቃን ያሰቡት ወንድሞቻችን እህቶቻችንም አሏህ ባሰቡት ያድርሳቸዉ

  • @ስላምየማርያምልጅ-ወ9በ

    ውይ በጣም የሚያሳዝን ታሪክ ነው ትንሽ በጅቡቲ ይሻላል መንገድ በቦሳሶ ከባድ ነው

  • @tenshasinaweletweled8632
    @tenshasinaweletweled8632 2 роки тому +2

    እሼ ውይ ዋጥ ላድርግህ አንጀት አርስ እኮን ድንቅ ነው

  • @belayethiopia
    @belayethiopia 2 роки тому +2

    wonderful story i resonate. i cant wait to hear the end. specially the father

  • @tigistalemu7580
    @tigistalemu7580 2 роки тому +2

    ይህ ታሪክ በመፅሐፍ ቢወጣ እና ለልጄ ስጦታ ብሰጣት እንዴት ደስ እደሚለኝ❤❤❤❤❤😭

    • @aberanigus2856
      @aberanigus2856 2 роки тому +1

      እህት ትንሽ ቀን ጠብቂን በቅርብ ቀን ይወጣል

    • @tigistalemu7580
      @tigistalemu7580 2 роки тому +1

      @@aberanigus2856
      አበራ ንጉሥ ስለመለስክልኝ አመሰግናለሁ ልጄ 14 አመቷ ነዉ ከዚህ የሕይወት ታሪክ በተሻለ ሊነቃቃት እና አላማዋን ላይ ትኩረት እዲያረጋት የሚችል ያለ አመስለኝም ።ምክንያቱም ደሞ ድርሰት እድትፅፍ አበረታታታለው የውስጧን ምኞት ለማወቅ ብዬ ታዲያ በገፀባህሪው ላይ የውጪ ሕይወት አቀርም ተተኪው ትውልድ በኢትዮጵያ ተስፋ ሊቆርጥ ነዉ ልክ እደኛ😭

    • @BbBb-rg8ry
      @BbBb-rg8ry Рік тому

      እኔም

  • @mekides
    @mekides 2 роки тому +79

    ሰላምህ በክርሰቶስ ይብዛልህ እሸቱ ወንድማችን እንኳን ደህናመጣህልን በእውነቱ ሰራየን አቁሜ ነው የሰማሁት ቀጣዩን በጉጉት እጠብቃለን 💚💛❤️

    • @madinamadina7888
      @madinamadina7888 2 роки тому +1

      ለምን በሰመአ አታዳምጪም ስራሑንም እድጨርሺ

    • @mekides
      @mekides 2 роки тому +1

      @@madinamadina7888 አዳምጣለሁ እያዳመጥኩ ነው

    • @nigestadmase6358
      @nigestadmase6358 2 роки тому

      አረ ክፍል ሁለትን አጣሁት ላኩልኝ

  • @aminauae1063
    @aminauae1063 2 роки тому

    ገራሚታሪክነው እሼየ አላህ ይጠብቅህ የኔመልካም ሠው ቀጣይ እጠብቃለን አይ ሥደት እዳው መቸነው የሚልፍልን

  • @ቅድስትአርሴማእናቴ-ከ6ሠ

    ክፍል 2 እንጠብቃለን እሼ የሚገርም ታሪክ ነው

  • @tube-ii9kv
    @tube-ii9kv 2 роки тому +2

    ውይ እሸ እዳአተ አይነቱን ያብዛልን ቃአላአጠው እፉ

  • @mimegirma251
    @mimegirma251 2 роки тому

    እሼ ማሪያምን አንተ ልዩ ሰው ነህ እግዚአብሔር እረጂም እድሜ ይስጥህ

  • @tubitubi8818
    @tubitubi8818 2 роки тому

    ወይኔ ወንድሜ ተሰቃይቶዋል በዚህ አይነት ፈተና ያሳለፍኡ ብዙ ስደተኜች አሉ ተከታታይ ብታቀረብልን ለሁሉም ትምህርት ይሆናል እሸቱ እናመሰግናለን

  • @juharabamilke8942
    @juharabamilke8942 2 роки тому

    ደሰ የሚል ገጠር አኗኗር አሰታወሰከን ምርጥ አሰተመሪነው

  • @peacelove5040
    @peacelove5040 2 роки тому

    Egziabhier Ethiopian tabetsih. Amen!

  • @redataberam6980
    @redataberam6980 2 роки тому

    የሚገርም ታሪክ ነው አሼ ፈጣሪ ይባርክህ የመዳምን ስራ ትቼ ነበር ስሰማ የነበረ ቀጣይ ይለቀቅልን ግንንንንንን ለምን ታቋርጠዋለህ ሻይ ቡና እያልክ እደኛ እእእእ ብታዳምጠው ብዙዙዙዙ ይወጠዋል እባክህን ክፍል ሁለትን እዳታቋርጠው አይ ስደት ፈተናዋ ብዙነው

  • @shgawbirhanu8142
    @shgawbirhanu8142 2 роки тому +2

    esh betam betam lehager tasfelgaleh bertalen enwodehalen

  • @rigbelemlem3909
    @rigbelemlem3909 2 роки тому

    Esheyuye mirt ethiopiawi endante aynetu yibza. Tebarekilin

  • @فوزىسرج
    @فوزىسرج 2 роки тому

    እሼ በጣም እወድሀለዉ ላንተ ምመኝልህ ምርጥ ትዳር በቶሎ እንዲሰጥህና ሴኬትን ከጤና ከበረከት ጋር የታደለ ቤተሰብ እንዲያረግህ ነው እኔ የልጆች አባት ነኝ

  • @አቤቱደካማባሪያህነኝናከኔ

    አይይይ የስደት ታሪክ ምን ያልቃል ብቻ ፈጣሪ በሰላም ለሀገራችን ያብቃን ኢትዮ ለዘላለም ትኑር😭😭😭😭😭💘💘💘💘💘💘💘🙏🙏🙏🙏🙏🙏

  • @ስደተኘዋነኝ
    @ስደተኘዋነኝ 2 роки тому +1

    የሚገር ነው የስደት ታሪክ አያልቅም ቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር ስደትን በቃ ይበለን ሀገራችንን ኢትዮጵያን በበረከት ጎብኚቶ አብባ እድትኖር ያድርግልን

  • @shewangizawtekest1324
    @shewangizawtekest1324 2 роки тому

    እሸቱ አተመልካም ሰዉ ልጁ ደስ ሲል

  • @rhamethabtemuyoutube7632
    @rhamethabtemuyoutube7632 2 роки тому

    ምርጥልጅ ምርጥ አባት

  • @נגסומלסה
    @נגסומלסה 2 роки тому

    አቤቱ አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይጠብቅ ህዝብህን አድን የአለነበትን አገርን ጠብቅ

  • @tigstshewafra7683
    @tigstshewafra7683 2 роки тому

    የኔ ወንድም😥😥😥😥😔❤🙏💚💛❤እሼ የኔ ሀበሻ ትለያለህ የልብህን መሻት እግዚአብሔር አምላክ ይፈፅምልህ❤🙏

  • @sisayassefa7272
    @sisayassefa7272 2 роки тому

    endeza akabdeh jemreh, mnm adis neger alsemawm, endelelochu Ethiopiawyan betam asazagn tarik

  • @desaletegegne4846
    @desaletegegne4846 2 роки тому

    ወይ አበራ: ላንተ መጥፎ ታሪክ ቢሆንም ለሰሚው ጥሩ ታሪክ ነው። መጥፎውም በመልካም ሲቀየር እጅግ ደስ ይላን። ብርታትንም ያስተምራን።

  • @sebletube6489
    @sebletube6489 2 роки тому

    አሁንም ይህ ልጅ መማር አለበት ያባቱን አላማ ማሳካት አለበት እግዚአብሔር ከብዙ ፈተና ያወጣው ልጅ ነው

  • @sarass2644
    @sarass2644 2 роки тому

    እሽቱ ትለያለህ የልጅ አዋቂ ሰላማቹ ይብዛ የእውነት የሚገርም ታሪክ ነው ወንድሜ እንኳን ከጅቦቹ አፍ አተረፈክ አይ ስደት ብዙ ፈተናዎች አሉባት ፈጣሪ ይመስገን ከሁሉም ነገር በጤናክ ተገኝተህ ታሪክህን ስላካፈልከን እናመሰግናለን 😥😥😍💚💛❤🙏