ቅዱስ ቁርባን | የጌታ እራት| የካቶሊክ እና የፕሮቴስታንት መሰረታዊ ልዩነት ምንድን ነው?

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 7 січ 2025

КОМЕНТАРІ •

  • @TseganeshWadu
    @TseganeshWadu День тому +1

    ተባረክ ወንድሜ በርታልኝ!

  • @Antmen1
    @Antmen1 2 дні тому

    እጅግ በጣም ጥሩ እይታዎችን ማሳያና እንደገና ይህንን ድንቅ ሚስጥር እንደ ቃሉ በመመርመር ገብቶን በተገቢው ሁኔታ እንድንካፈል የሚረዳ ትምህርት ነው። ይህንን በረከት ማካፈል እንድትችል ለረዳህ እግዚአብሔር ክብር ይሁን። የጌታ ጸጋ ይብዛልህ ያበርታህ። ተባረክ።

    • @gratiaethiopa
      @gratiaethiopa  2 дні тому

      አሜን ወንድም የእግዚአብሔር ቃልን መስማት ግዴታችን ነው!

  • @user-vh6ig3vb
    @user-vh6ig3vb 2 дні тому

    ተባረክ በጣም አመሰግናለሁ
    ጌታ ይባርክህ❤❤❤❤

  • @mesimatyos8137
    @mesimatyos8137 2 дні тому

    ተባረክ የእኔ ወንድም!

  • @MogosKebede
    @MogosKebede День тому

    ተባረክልን ውንድም ቀጣይ ስለ ዎችማን ኒ እና ዊትነስ ሊ ሚኒስትሪዎችን ስራልን።

    • @gratiaethiopa
      @gratiaethiopa  День тому

      እሺ እግዚአብሔር ይረዳኛል!

  • @lilytekleab1577
    @lilytekleab1577 17 годин тому

    እናመሰግናለን በጣም ጠቃሚ ነገሮችን እያስገነዘብከን ነው🎉በነካ እጅህ በነዚህ ቤተ እምነቶች መካከል ያለውንም የጥምቀት ልዩነቶች ጀባ ብትለን?ተባረክ❤❤

    • @gratiaethiopa
      @gratiaethiopa  9 годин тому

      አሜን! በሚቀጥለው ለስራት እሞክራለሁ።

  • @adamababu4129
    @adamababu4129 День тому

    Tebarkehal wendeme❤

  • @reformedtheology9064
    @reformedtheology9064 2 дні тому

    ተባረክ! ሪፎርምድ መሆን መሰጭ ነው!🤩🤩🤩😍😇😇

  • @Chere1992
    @Chere1992 2 дні тому

    ተረክ ወድሜ!

  • @HabtamuTilahun-t9o
    @HabtamuTilahun-t9o 2 дні тому

    Tebarek kirstinan menor yihunilin

    • @gratiaethiopa
      @gratiaethiopa  2 дні тому

      አሜን ለአንተም እንደቃሉ መኖር ይሁንልህ!

  • @theman1234-y4u
    @theman1234-y4u День тому

    ተባርከሃል! ፊደል አጻጻፍ ላይ ግድፈቶች አሉ ኣስተካክላቸው። እና ምንጮችህን ከስር በlink ኣስቀምጥልን። በርታ

    • @gratiaethiopa
      @gratiaethiopa  День тому

      እሺ በሚሞጥለው ለማስተካከል እሞክራለሁ ወንድሜ

  • @sagnidereje2358
    @sagnidereje2358 День тому

    በጣም አናመሰግናለን በርታልን አግዚአብሔር ይባርክህ ጥምቀት ላይም ቢሰራልን ምን ይመስልሃል 🙏

    • @gratiaethiopa
      @gratiaethiopa  День тому

      እሺ እሰራለሁ ያው ኮሜንት ላይ መጨቃጠቅ ግን አይፈቀድም 😂

  • @Ayele-Rodamo
    @Ayele-Rodamo 2 дні тому +1

    እግዚአብሔር ይባርክህ ። ቀጣይ ቪዲዮችህ ላይ ስለ ጥምቀት ከድነት ጋር ስላለው ግንኙነት እንዲሁም እንደየዲኖምኔሺን ያለውን ምልከታ ታነሳለህ ብዬ አስባለሁ ። አንዱ ሌላውን ደግሞ ማጥመቅም እንዴት እንደሚታይ እንሰማለን ብዬ እጠብቃለሁ ። ቡሩክ ሁን።

    • @gratiaethiopa
      @gratiaethiopa  2 дні тому

      አስቢያለሁ ግን ሰላማዊ ይሆናል ብዬ አላስብም ኮመንት ሴክሽኑ።

    • @DawitNigussie-p1k
      @DawitNigussie-p1k 21 годину тому

      @@gratiaethiopa its ok just do it

  • @MesayMge
    @MesayMge 2 дні тому

    ዮሐንስ 6
    ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
    ⁵³ ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም።
    ⁵⁴ ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።
    ከዚህ መልህት ከንፃር የጌታ ስጋና ደም ህይወትን የሚሰጥ ነው?
    በተረፈው ተባረክልኝ ውንድሜ❤❤

    • @gratiaethiopa
      @gratiaethiopa  2 дні тому

      ዮሐንስ 6
      ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
      ⁶¹ ኢየሱስ ግን ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ እንዳንጐራጐሩ በልቡ አውቆ አላቸው፦ ይህ ያሰናክላችኋልን?
      ⁶² እንግዲህ የሰው ልጅ አስቀድሞ ወደ ነበረበት ሲወጣ ብታዩ እንዴት ይሆናል?
      ⁶³ ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።
      ኢየሱስ ካረገ በኋላ ጌታ መንፈስ ቅዱስ በሰማይ የአብ ቀኝ የተቀመጠውን ስጋ ይመገብናል።

  • @nanon-ed
    @nanon-ed 2 дні тому

    Anabaptistቶች መታሰቢያ ብቻ ነው ብለው አያምኑም መሰለኝ እንደማቀው ግን ደሞ እንደ denomination ይለያያል እንጂ መታሰቢያ ብቻ ብለው የሚያምኑ ያሉ አይመስለኝም

  • @Jopprince
    @Jopprince 2 дні тому

    የኔ ጥያቄ ምን መሰለህ
    1. የጌታ እራት ለድነት ያለው ፋይዳ ምንድን ነው ? ስጋውን እና ደሙን በመብላት ውስጥ ነው ወይንስ በእምነት ብቻ ድነት

    • @gratiaethiopa
      @gratiaethiopa  2 дні тому +1

      በጌታ ራት ዳግም አትወለድም ዳግም ሥለተወደክ ግን የጌታን ራት ትበላለህ ስለዚህ በእምነት ብቻ ትምህርት ጥብቅ አቋም ያላቸው አባቶቻችን ሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ በጌታ ራት ዳግም ልደት ይከናወናል ብለው አላስተማሩም። ያመነ ሰው የጌታ ራት ሲካፈል በጾሎት እና ቃሉን በማንበብ ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት እንደሚያደረገው እውነተኛ ህብረትን ያደርጋል። በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀቀት ከክርስቶስ ጋር አንድ አካል የሆነ አማኝ በህይወቱ እንዲያድግ ክርስቶስን ይመገባል፤ የጌታ ራት ካልወሰድክ ደህንነት የለህም የሚል ትምህርት የለንም ግን ደግሞ ከዳንክ የጌታን ሥጋ መብላት ወዴታህ አይደልም አንተ የክርስቶስ አካል ስለሆንክ ደሙ በደምህ ውስጥ ስጋው በሥጋው ውስጥ በእውነት ይገኛል። ይህ ከክርስቶስ ጋር የሚደረገ ዘላለማዊ ህብረት ደግሞ የዘላለም ህይወት ይገኝበታል። አንድ ሰው የሚያምነው ወደ እግዚአብሔር መንግስት አካል ለመሆን እና ህብረት ለማድረግ ነው። የጌታ ራት ደግሞ አንድ የምንሆንበት ህብረት ምናደርግበት ሚስጥር ነው። ምልክት ብቻ አይደለም! እግዚአብብሔር በዚያ ውስጥ ለዳኑ ቅዱሳኑ የሚያካፍለው ትልቅ በረከት አለ።

  • @teklumark4122
    @teklumark4122 День тому

    የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ቋንቋ ላቲን ነው:: transubstantiation እንግሊዘኛ በመሆኑ እምነቱን አይገልፅም::

    • @gratiaethiopa
      @gratiaethiopa  День тому

      አዎ ግን በውስጠ ተዋቂነት ይለወጣል የሚለው ትምህርት የካቶሊክ ነው። ትምህርቱ ከአርስቶትል ፍልስፍና የተወሰደ ነው ።ከቃሉ በላይ ቁስ የሆነው ወይን እና ህብስት ሥግው ቃል ወይም መለኮት ወደ ሆነው የእግዚአብሔር ቃል ተለወጠ የሚለውን ተለወጠ የሚለው ትምህርት መጽሐፍቅዱሳዊ አይደለም። ክርስቶስ በህብስቱ ይገኛል ነገር ግን ህብስቱ ህብስትነቱን አቶ ክርስቶስ አልሆነም። ስንቃውም ትምህርቱን እንጂ ቃሉን መርጠን አይደለም። የምስራቅ ኦርቶዶክስንም የተለወጠ ትምህርት አንቀበልም ካትሊክን ለይቼ የገለጽኩት ሲጀመርም የተለየነው ከካቶሊክ ክርስቲያን ወንድሞቻችን ጋር ስለሆነ የጌታ ራት ትህርታችንን አውድ በሚገባ ለማብራራት ነው። እና ተሳሴቼ ከሆነ ወደ ፊት ሰፊ ቪዲዮ መስራቴ ስለማይቀር በሚገባ አጥቼ አርመዋለሁ ላቲኑንም ካቶሊካዊያኑ እንዴት እንደሚተረጉሙ ማለት ነው። ላቲን ባልችልም😂።

  • @AbelKahsayChristian
    @AbelKahsayChristian 2 дні тому

    1, መታሰብያ ብቻ ሚል ሃሳብ ፅንፍ ነው ኣልከን ማስረጃ ኣለህ? ከ መፅሐፍ ቅዱስ ኣንፃር ወይን ና ህብስቱ ለመታሰቢያ ነው ከዛ ውጭ ለመዳን የኢየሱስ ደም ና ስጋ በእምነት ወደ ውስጣችን ገብታል ።

    • @gratiaethiopa
      @gratiaethiopa  2 дні тому

      “የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን?”
      - 1ኛ ቆሮንቶስ 10፥16

  • @TsegayeZenebe
    @TsegayeZenebe 2 дні тому

    ከመካነ ኢየሱስ ስለሆንኩ በግሌ የሉተራን ምልከታ ነው ያለኝ። ሁሉም ሰው ይኸው ተመሳሳይ ምልከታ ቢኖረው ምኞቴ ነው። ግን ማጠቃለያ ላይ ያነሳኸው ሀሳብ ላይ አንድ ነገር ለማለት ያህል። በተለያየ የቅዱስ ቁርባን አስተምህሮ ውስጥ ሆነን በየሄድንበት ህብረት ውስጥ ቅዱስ ቁርባን መውሰድ ያስኬዳል እንዴ? በግሌ ከመካነ ኢየሱስ ወይም ሌላ ሉተራን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ካልሆነ መውሰድ ትክክል መስሎ ስለማይታየኝ ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ከተገኘሁ ስርዐቱ ሲጀመር ትቼ ነው የምወጣው። ይህን የማደርገው ተጠያቂነትም ስላለበት ነው። ኮንቴንቱ ግን ግሩም ነው። እግዚአብሔር ይባርክህ። ጸጋውን ያብዛልህ።

    • @gratiaethiopa
      @gratiaethiopa  2 дні тому

      የሉትራን እና የሪፎርምድ ምልከታ አንድ አይነት ነው። ልዩነታቸው በአካል ተገኘ ወይም በመንፈስ ተገኘ የሚለው ላይ ነው። አብረህ ከዘመርክ አብረህ ከጸለይክ ህብረት እያረክ ነው። ለምሳሌ እኔ በግሌ "የነቢያት" ቤተክርስቲያን አልሄድም ከእነሱ ጋር ፈጽሞ አላመልክም ከእነሱ ጋር ሙሉ ህብረት የለኝም። ግማሽ ህብረት ስሌለ በአምልኮ ከእነሱ ጋር ህብረት ካረክ በዚህም ማድረግ ይኖርብካል። ልክ እንደ LCM ሉትራኖች ለሌቹ መዳን እውቅና ሰተህ ከሌሎች ጋር ህብረት አለማድረግም ትችላለህ። ግን ህብረት አላመድረግ ከውግዘት የሚነሳ ነው መሆን ያለበት ያው ሉተር ዝዊንግሊን ስላወገዘው "መታሰቢያ ብቻ ነው" ከሚሉ ጋር ህብረት ባለማደረግህ አጠፋህ ለማለት አልችልም። ያው እንደ አባትህ አልዳናቹም ብለህ አታሳቃቸው እንጂ።😂 እና ልጠይቅህ በተቦቱ ጋር በማመሳሰሌ የሚያስቆጣ ነገር አላረኩማ?

    • @TsegayeZenebe
      @TsegayeZenebe 2 дні тому

      @gratiaethiopa ብዙ የቲዮሎጂ ዕውቀት ባይኖረኝም ከታቦቱ ጋር ያገናኘህበት መንገድ መልካም ነው ባይ ነኝ። ጥሩ መሳ ለመሳ የሆነ ምሳሌ ነው። ደግሞም በትክክል ጥላ ነው ማለትም ልክ ግዝረት የጥምቀት ጥላ እንደነበረው ሰንበትም የክርስቶስ ጥላ እንደነበር ካለው ምሳሌ ጋር በሚገርም አገላለጽ ነው ያቀረብከው። የውግዘት ነገር ካነሳይ አይቀር የሙሉ ወንጌል ሰዎች እነሱ ጋር ከሄድን አልዳናቹም ድጋሚ ካላጠመቅናቹ ይሉናል እኛ ደግሞ ጥምቀት አንዲት እንደሆነች ነው ምናውቀው። እና ልልህ የፈለክሁት ስለጥምቀት ቪድዮ እንደምትሰራ እጠብቃለሁ። theology መማር እንዳለብኝ እየተሰማኝ ነው።

    • @gratiaethiopa
      @gratiaethiopa  2 дні тому

      በቃጣዩ ስለጥምቀት አወራለሁ ችግር የለውም የተወሰነ መረዳት ታገኛለህ ስለሱም ብዬ አስባለሁ። ማነው እናንተ ደፍሮ አልዳናቹም የሚለው? ድጋሜ ካለጠመቅን ማለት ያው የአናባፕቲስቶች (የዳግም አጥማቂያን) ባህል ነው ግን ጥምቀትን ከደህነነት ነጥለው ሁለት የተለያየ ነገር አድርገው ስለሚያዩ አልዳናቹም ለማለት ብዙ ጊዜ አዬደፍሩም። ሉትራንን አንገሊካንን ወይም ሪፎምድ ክርስቲያኖች አልዳኑም የሚል ቤተ እምነት እርሱ ፕሮቴስታንት አይደለም ሌላ ሐይማኖት መሆን አለበት።

    • @DawitNigussie-p1k
      @DawitNigussie-p1k 21 годину тому

      @@TsegayeZenebe me too we have to learn

  • @nanon-ed
    @nanon-ed 2 дні тому

    Anabaptistቶች መታሰቢያ ብቻ ነው ብለው አያምኑም መሰለኝ እንደማቀው ግን ደሞ እንደ denomination ይለያያል እንጂ መታሰቢያ ብቻ ብለው የሚያምኑ ያሉ አይመስለኝም

    • @gratiaethiopa
      @gratiaethiopa  2 дні тому

      "የአናባፕቲስቶች ነው የሚባለው" የሚለውን ሀረግ የተጠቀምኩት የእነሱ ነው የሚል ብዙ አሉባልታ ስለሚናፈስና የእነሱ መሆኑን በተገለጠ የእምነት መግለጫ ማረጋገጥ ስላልቻልኩ ነው። ግን ደሞ ትምህርቱ ስላለ ትክክል አለመሆኑንም መናገር ስላበኝ ተናግሪያለሁ። በታቻለኝ አቅም ሚዛናዊ ለመሆን ሞክሪያለሁ።

    • @nanon-ed
      @nanon-ed 2 дні тому

      @@gratiaethiopa በጣም ሚገርም አቀራረብ ሚዛናዊ በሆነም መንገድ ነው ያቀረብከው ግን አሳነስከው እንጂ ሌላው ገራሚ ነው 🥰😁