I am deeply blessed and encouraged by your presentation. May God continue to use you mightily for His glory. Please keep sharing more of these messages-they are touching lives and spreading His light!
Greetings, I was very interested in this and wanted to listen to it. I’m commenting here because there was no other way of reaching you directly. Please stop the music while you speak. It is very distracting and unnecessary!! 5 minutes into this video and I couldn’t take it anymore. There is NO need to let the music run while you are speaking and this was way too loud! Sorry brother but there was no way of contacting you directly.
The Nicene Creed and the Filioque Clause: The original Nicene Creed, formulated at the First Council of Nicaea in 325 AD, did not include the phrase "and the Son" (Filioque in Latin). The original wording concerning the Holy Spirit stated: “We believe in the Holy Spirit, the Lord, the giver of life, who proceeds from the Father.” The Filioque clause ("and the Son") was later added to the Creed in Western Christianity during the Third Council of Toledo (589 AD) and became a point of contention between the Eastern (Orthodox) and Western (Catholic) Churches. The Eastern Churches maintain the original version of the Creed without the Filioque, emphasizing the procession of the Holy Spirit from the Father alone. It is essential to be accurate when presenting historical or theological matters. Including the Filioque in a context about the Council of Nicaea is historically incorrect and can lead to misunderstanding about the original formulation of the Creed. Orthodox Tewahedo Church and Miaphysitism: The Orthodox Tewahedo Churches (e.g., Ethiopian, Eritrean, and Coptic) adhere to Miaphysitism, not Monophysitism. Miaphysitism: This teaching asserts that Christ’s divine and human natures are united in one composite nature, "without confusion, change, division, or separation." Monophysitism: Often inaccurately attributed to Miaphysite Churches, it claims that Christ has only one nature, usually divine, with the human nature being absorbed. Labeling the Orthodox Tewahedo Church as Monophysite is a significant theological error. My Recommendation 1. For the Nicene Creed: Remove the Filioque from discussions of the Council of Nicaea (325 AD) and clarify that it was a later addition by the Western Church. 2. For the Orthodox Tewahedo Church: Accurately describe its teaching as Miaphysitism to avoid misrepresentation and ensure theological correctness.
@@gratiaethiopia Where do you live homie? I assume you reside in the US, as I do - I like your attitude. I just encountered limitations on UA-cam and am being forced to restrict the length of my comments - sorry for repeated short responses. Study more on this topic - I've conducted extensive research on it, drawing upon over 20 scholarly sources. Through the grace of God, I've successfully defended the Miaphysite Christology of the EOTC against several Diaphysite apologists in recent debates. You do know St. Cyril is a Miaphysite. I encourage you to explore the provided links below, where you'll discover an eight-part defense of OO Christology by the Lion's Den brothers, which extensively references the early church fathers. ua-cam.com/video/VlSqTTsGneQ/v-deo.html
@@gratiaethiopia Additionally, please peruse the links below, where you'll encounter Agen of the Apostolic Orthodoxy offering a splendid elucidation of the Oriental Orthodox Christology. ua-cam.com/video/SH5Y2nUYR5c/v-deo.html Also refers to Sam Shmoun's contents on various theological topics, including: the Divinity of Christ, responses to Muslim arguments, the role of early Church Fathers, the concept of intercessory prayer by saint etc.... ua-cam.com/video/P9JHSQibXC0/v-deo.html
@@gratiaethiopia If you reside in the D.C., MD, VA area, I highly recommend a visit to the Manuscript Division of the Library of Congress, renowned for its extensive collection of rare books. Additionally, the Semitics/ICOR Library in Washington D.C. is known for its exceptional resources.
ፀጋው ይብዛለህ ወንድሜ ❤❤ ጥንታዊ መፃፎችን ማንበብ በጣም ነው ምፈልገው እና በጌታ ፍቅር ተባበረኝ ከታላቅ ፍቅር ጋር❤
ተባረክ ወንድሜ ፅጋ ይብዛል 🌹🌹🙏🙏
እናመሰግናለን👏👏👏👏
ዘመንህ እና ዘርህ ትዉልድህ በኢየሱስ ክር ስቶስ አባትና አምላክ ስም ለዘለአለም የተባረከይሁን በሚገባ አድርገህ አቅርበኸዋልና ተባረክ
አሜን! ይሄን የበረከት ቃል በሰማሁ ሰአት ልጅ እንዲነረኝ ተመኘሁ!
ድንቅ ነው።
ጥራት ባለው መንገድና ቀለል ባለ ሁኔታ በምታዘጋጃቸው ትምህርቶች በጣም ተጠቀሚያለሁ፤ እግዚአብሔር ይባርክህ።
የእግዚአብሔር የሆኑትን ማገልገል እንዴት ነፍስን ደስ ያሰኛል መሰለህ። በጣም ደስ ብሎኛል ስለተጠቃማቹ! ተባረክ!❤
I am deeply blessed and encouraged by your presentation. May God continue to use you mightily for His glory. Please keep sharing more of these messages-they are touching lives and spreading His light!
በጣም አመሰግናለሁ አሳብ እና አሴታየታችሁ የበለጠ እንድተጋ ያደርገኛል ተባረኩልኝ!
Egziabher yibarkih.... Bertalin.... Ahunim tsega yibzalih!!!
አሜን ወንድሜ!
በጣም ግሩምና ድንቅ መገለጥ ነው ወንድሜ ጌታ ፀጋውን ያብዛልህ
አዎ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን የመሰረተበት ግሩም መገለጥ! አሜን!
በርታ ወንድሜ በጣም ጥሩ አቀራረብ ነው።👏👏 እግዚአብሔር ይባርክህ!
አሜን! ወንድሜ በየፊናችን ስለመንግስቱ መስፋት እንደ ጸጋው ልግስና እንተጋለን!
Woo ድንቅ አቀራረብ እግዚአብሄር አብዝቶ ይባርክህ🎉🎉🎉🎉🎉
አሜን!❤
ጌታ አብዝቶ ይባርክህ። ሰሞኑን የድሮዋ ቤ/ክ ምን ትመስል ነበር ሚለውን ነገር በደምብ ሳሰላስል ነበር እናም ይሄ ቪዲዮ በጣም ነው የጠቀመኝ። በተጨማሪም ስለ ጥምቀት, ቁርባን, የጳጳሱ infallibility, በአጠቃላይ ስለ sacraments የድሮ አስተምህሮ እና አሁን ላይ እንዴት evolve እንዳረጉ/እንደተቀየሩ በዛ ላይ ደሞ ትክክለኛው የሃዋርያት ትምህርት እንዴት በሌላ የስህተት ትምህርቶች ሊበረዝ እንደቻለ እና ከዚህም ጋር በተያያዝ የprotestantism reformation እንዴት እንደተጀመረ ብትሰራልን ደስ ይለኛል።
እግዚአብሔር ይረዳናል በታቻለን መጠን በጣም በጥልቀት ጊዜ ወስደን ሁሉም ላይ የምንሰራ ይሆናል።
በጣም የበሰለ ጥልቅ እና ጥሩ አቀራራብ ነው። በርታ ተባረክ ፀጋ ይብዛልህ ❤👏🙏😇
አሜን!❤ ተባረክልኝ!
Dedeb sew y orthodoxyn temhirt lerasu yawral dedeb. Pente amalaj yilal
በጣም ደስ በሚል መልኩ አቅርበከዋል። ተባረክ
አሜን!
ተባረክ! እጅግ ድንቅ ትምህርት!
አመሰግናለሁ! ተባረኩ
It was great, and be the grace and peace of God upon you.
አሜን!
ዋው ወንድሜ ጌታን በጣም ግሩም ትምህርት ነው ተባረክ!
አመሰግናለሁ ተባረኩ❤
ድንቅ ትምህርት ነው!😇❤️
❤❤
በርታ!
በብዙ ተባረክ
አሜን!
ድንቅ ማብራሪያ ተባረክ በርታ ቀጥታ 😊
አሜን
Woow ጌታ ይባርካችሁ በርቱ 🙏🙏
አሜን!
Tsega Yibzalih !!!
አሜን!
ወንድምአለም ተባረክልኝ ከዚ በበለጠ ደግሞ ጥሩ video እንደምትሰራ እጠብቃለሁ።
እሺ ወንድሜ!
Wow Tebarek geta Tsagawun yabizalk
አሜን!
ቴሌግራም group ካለህ ብትሰጠኝ በጣም ያስፈልገናል አሪፍ ትምህርት ነው የምታስተምረውና ❤❤
ግሩፕ እከፍታለሁ እሺ።
ጌታ ይባርክህ ወንድሜ! ጥልቅ የሆነ የስነ_መለኮት እውቀት እንዳለህ ይገባኛል። የምትሰራቸውን ቪድዬዎች በጣም ነው የምወዳቸው።
አሜን! ወንድሜ!
Wow its amazing!🎉🎉🎉❤
Thank you! 😄
wow, grace up on you brother
አሜን!
17:50 ላይ ኦንሊ ጂሰሶች የኢየሱስን አምላክነት ይክዳሉ ያልከው ትክክለኛ ሰላልሆነ ኤዲት ብታደርገው። ኢየሱስ አምላክና የዘላለም አምላክ አዳኝም መሆኑን ጠንቅቀው ያምናሉ። አንድ አካል አንድ ዙፋን አንድ ገዝ አንድ አምላክ ብለው ነው የሚያምኑት ያም የእውነተ መሰረት ነው።
የሰላሴ አማኝ በነበርኩበት ጊዜ ለማን እንደምፀልይ ግራ ይገባኝ ነበር ሳመሰግን እራሱ አብን ካልኩ ወልድን እንዳላሳዝን ወይ መንፈስ ቅዱሰን የሚል አለመመቸት ይሰማኝ ነበር። ሰሙ ይክበር አሁን አንድነቱን ተረድቼ አምላኬ እጅግ ቀርቦኛል። እንደልቤ ጌትዬኮ አዳኜና ወዳጄ ምህረትህ አይለየኝ ሁሌ ምራኝ ተመሰገን ማለቱ እጅግ ቀሎኛል።
የወልድን አምላክነት አጥብቀው ይክዳሉ! የእግዚአብሔር ቃል አምላክነት ክደው ወደ ሚሞት ሥጋና አጥንት ተለወጠ ይላሉ። ከዛ እዚያ ስጋና አጥንት ውስጥ አብ ተገለጠ ይላሉ። ስለዚህ ወልድ ወይም የእግዚአብሔር ቃል እግዚአብሔር አይደለም የሚል ጠንካራ ትምህርት አለቸው። ወልድ የአብ ስጋ ብቻ ነው ብለው ያስተምራሉ። እንደውም ከጆቫ የከፋ ትምህርት ነው።
የኦልኒጂሰሶች ትምህርት በ20ኛው ክፍለዘመን የተጀመረ እንግዳ ትምህርት ነው። ኢየሱስ የመሰረታት የጋሀነም ደጆች የመሰረቷት ቤተክርስቲያን የአንተ ሐይሞኖት በሰዎች እስኪመሰረት ድረስ የት ነበረች?
4:40 ፈጽሞ ተሳስተሀል። ያልተማረን ሰው ልትሽውድ ትችል ይሆናል። የአሁኑ ትውልድኮ በስክሪን ላይ ሁሉን ፈልጎ እውነቱን ከመጽሐፋ የሚያገናዝብ ትውልድን በጭፍን ውሸት ልታደናግረው አትችልም። ኦንሊ ጂሰቦች በክርሰቶስ አምላክነት ያምናሉ አብም ወልድም መንፈስ ቅዱሰም የአንዱ መገለጫው እንደሆነ ያምናሉ። ሰጋው ከሰማይ ሰለመጣ ሰማያዊ ነው ሲጀምርም ብለው ከትንሳኤ በኃላ ወደ ነበረበት ሰማይ ማረጉንም መንገሱንም ያምናሉ። እኛም ይሄንኑ እናምናለን ትክክል ነውና። ከእነርሱ ጋር በትንሽ ሚለየን እኛ ሰለጌታ በ70AD ላይ ዳግም መመለሱን ማመናችን ነው። አቤት እሄን እውነት ቢረዱልንና አብረናቸው ማምለክ ብንችል ምኞታችን ነበር። እውቀት ያድጋል በፀሎት በተከፈተ ልብ በብሩህ አይምሮ ሁሉን አገናዝቦ ወደ እውነት መጠጋት በረከቱ ለራስ ነው በምድርም ሆነ በሰማይ።
እንደው ሰለ ሞናርኪያን ተመልክተህ የጥንት ክርሰትያኖችን አሰተምህሮ ለመረዳት በመከርክ ከአንድ አምላክ ውጭአያቁምም አያሰቡትምም ሰላሴ አደለም ሁለት አምላክ አይደለም ሊያሰቡት አሰበውትም አያውቁትምኮ። በብሉይ ዮናስ እራሱኮ እኔ እብራዊ ነኝ ሰማይንና ምድርን የሰራውን አንድ አምላክን አምናለሁ እኮ ነው ያለው።
ሔለኒዝም ስላሴን አሰፀረስ በመቀጠልም የማርያምንና የመልአክትን አምልኮ ካሌንደር ቀየረ ጂኦግራፊካል ሰም ወዘተ...ተቀበል እያልኩህ አደለም። እኛም እንዳንተው ነበርን ግን ጊዜ ሰጥተህ እየው። በተረፈ ፈጣሪ ይርዳህ።
እርግጠኛ ያልሆንክበትን ማሰተማር ፍርዱ የከፋ ሰለሆ መጠንቀቅ ያሰፈልገናል ምክንያቱም ከእነዚህ ታናሹን ከሚያሰት አንገቱለ ላይ ....ይላልና 4:40 4:40
10፥55 የኣንጾክያው ቅዱስ ኣውጎስቲን የሚለው፡ በቅዱስ ኣግናጽዮስ Ignatius of Antioch ይታረም
አግንጽዮስ የትግርኛ ቃል ነው አግናጥዮስ የአማርኛ ቃል ነው ለማንኛውም አመሰግናለሁ ሁለቱንም እጠቀማለሁ።
ከማስተማር በፊት መማር ይቅደም፤ ሁለተኛው ሰው (ክርስቶስ) ከሰማይ ነው እንጂ ከምድር አፈር አይደለም። በስእል ጋጋታ ሰውን አታወናብድ። ማስተዋል ይስጥህ።
የገኃነም ደጆች የማይችሏት ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብላት የምታም ቤተክርስቲያን እንጂ ኢየሱስ አብ ነው ብሎ የሚስተምር የሰው ሐይማንት አይደለም።
ሲቀጥል የእግዚአብሔር ቃል እግዚአብሔር ነው ብለህ አታምንም። የእግዚአብሔር ቃል ወደ ሥጋ እና አጥንት ተለወጠ ብለህ የምታወናብደው ተክሌ የሚባል ሰውዬ የፈጠረው ሐይማኖት ተከታይ ሆነህ እንዲህ ስትል አታፍርም?
ትናንትና ተክሌ ከእንቅልፉ ተነስቶ ተፈላስፎ ያገኘውን ሐይማኖት ከሐዋሪያት ከዛ ከአባቶቻችን ከተቀበልነው ሐይማኖት ጋር አታወዳድረው።
አንተም የሰው ፍልስፍና ጠጥተህ "መማር ይቅደም" ምናምን ከምትል እስኪ 1 ዮሐንስ 4፥1 የተፃፈው ለማን ነው? ኢየሱስ ማንን እየተቃወመ ነው? ምን የሚያስተምሩትን እየተቃወመ ነው? ብለህ ተማር! አቃለሁ ድርጅትህ ከነገረህ ውጪ ምንም የማታወቅ መብት የሌለህ ጨለማ የዋጠህ መሐይም እንደሆንክ፤ ዘመኑ የቴክንሎጂ ነው። መረጃ ቅርብ ነው እስኪ ለ 1ዮሐ 4፥1 ከበቂ ታሪካዊ መረጃ ጋር ማብራሪያ ስጥ! ደመነፍሳዊ አትሁን!
👏👏👏👏
ብሮ በርታ!
እሺ ወንድም!
እኔ ወደ ፊት ለማድረግ የምመኘውን በአንተ ስላየው ደስ ብሎኛል እናም አንድ ቀን በአካል እንደማገኝህ አልጠራጠርም። ወንድሜ😊
ጌታ ይፈቅዳል!
ድንቅ ነው ወንድሜ
አመሰግናለሁ ወንድሜ!
yezarew degimo liyu new wow
አርፍና ግልፅ የሆነ አቀራረብ ነዉ ጌታ ይባርክህ❤❤🎉😊
በቀጣይ ስለ ጌታ እራት
(ቅዱስ ቅዱስ ቁርባን) ሰዎች ስለሚያስተምሩት ትምህርት እና ህፃናትን የሚያጠምቁ ሰዎች ማስረጃቸዉ ምንድን ነዉ ?ሕፃናትስ ሳያምኑ ተጠምቀዉ ቅዱስ ቁርባን መዉሰዳቸዉስ ትክክል ነዉ???
የሚለዉን ብትመለከተዉ please ??
እሺ ጌታ ቢፈቅድ በሚቀጥለው እሱን እሰራለሁ።
ሃዋሪያዊ ቅብብሎሽ ብለው ለሚታበዩብን። ለሀዋሪያው ለጴጥሮስ የተነገረው ለሁሉም ይሰራል ማለት ነው። ቆንጆ አቀራረብ ነው እግዚአብሔር ይባክህ በርታ።
ሐዋሪያዊ ቅብብሎሽ ማለት የሐዋሪየትን ትምህርት ለሐዋሪያዊ አባቶች ከእነሱ ደሞ ለቤተክርስቲያን አባቶቾ ከዛ እስከ እኛ ድረስ ተላልፏል ማለት ነው። ሐዋሪያዊ ሥልጣን እንደተላለፈ አድርገው ሊነግሩን ቢፈልጉም ያ ውሸት መሆኑን ታሪክ ያስረዳናል።
ማቴዎስ 28፥20 ያለው የጌታችን ቃል ስህተት ነው ልትለን ነው እርሱ እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ ሁልጊዜ ከሀዋርያት ጋር እንደሚሆን ተናግሯል ታዲያ ሀዋርያዊ ቅብብሎሽ እንዴት ሊቋረጥ ይችላል?
@@እምነትተስፋፍቅር ሐዋሪያዊ ቅብብሎሹ ወድ ቅዱስ ሊዮን ነው የሄደው ወይስ ወደ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ? እኛ ኢየሱስ ከስሁት ትምህርት ቤተክርስቲያንን እንደጠበቃት እናምናለን አባቶቻችን በመከተል አራቱንም ጉባኤያት ተቀብለናል ይህ ማለት ግን አባቶቻችን ከሐዋሪያት የተላለፈውን እውነት ለመጠብቅ የደከሙ የእግዚአብሔር ብሩካኖች እንጂ እንደ ኢየሱስ እና እንደ ሐዋሪያቱ ሥህተት አልቦ ናቸው እያልን አይደልም። ለአንተ አባ ሊዮን ተሳስቷል ለግሪክ ኦርቶዶሶች ደሞ አባ ዲዮስቆሮስ ተሳስቷል። ሁለቱም ሐዋሪያዊ ቅብብሎሽ አላቸው ሁለቱም ከሐዋሪያት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ወንበር ላይ ተቀምጠዋል ግን ይህ ከመወጋገዝ አላዳናቸውም።
@@እምነትተስፋፍቅር 'ከእናንተ ጋር ነኝ' ያለው ሀዋርያቱን ብቻ ነው እያልከኝ ነው? ወይስ ጥያቄህን አላገኘሁትም? ከሆነስ እነሱ እድሜ ገድቧቸው ሞተው የለም ወይ?
የሱስ የእግዛቤር ልጅ መሆኑ ማመን በቂ ነዉ ኢየሱስ እግዛብሄር ነወ ማለት ነው ኑፋቄነት 1ቆረ 15 ፡ እብ 1 ሌላም ጴጥሮስ እንደመሰከረለት ነወ
1 ዮሐ 1፥1
you did little explanation on (the major distinction between protestant theology and nisteros )
እሺ ወንድም ራሱን የቻለ በጥልቀት የሚያብራራ ቪዲዮ ለመስራት እሞክራለሁ።
ክርስትያን ማለት
ኢየሱስ ብቸኛ አካል (1)ሰው / ሰማያዊ አዳም /ሆነ የተገለጠ ::ቃል ስጋ ሆነ
አብ በኔ እንዳለ እመኑ ( የዘላለም አባት ነው )
አንድ አካል በሶስት ማንነት ተገለጠ እንጂ ሶስት አካል ያለው አምላክ የለም( ስጋ, ነፍስ, መንፈስ ) ሰውን በመልኩ ፈጠረ
ይሄ የሰባሊዮስ ኑፋቄ እንጂ ክርስትና አይደለም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል እግዚአብሔር እንጂ የእግዚአብሔር 1/3 ሥጋ አይደለም።ኢየሱስ የእኛ ተወካይ እና ሊቀ ካህን የሆነው የሞተውም የእኛን ሥጋ የያዘ እውኘተኛ ሰው ስለሆነ ነው። ኢየሱስ እውነተኛ ሰው ነው ልክ እንደማሪያም እውነተኛ አምላክ ነው ልክ እንደ አብ እግዚአብሔር ለዘላለም አባት ነው ምክንያቱም ለዘላለም ልጅ ስላለው። ልጅ ሳይኖረው አባት አይባልም አባት ሳይኖረው ልጅ አይባል። ሦስት ማንነት ሦስት አካል ሦስት ስም ሦስት ግብር ይህ ሐዋሪያት ከዛም አባቶቻችን ያስተማሩን ትምህርት ነው። ኢየሱስ ለ2000 አመት ቤተክርስቲያን ስላልተወ ቄስ ተክሌ የሚባል ሰው መቶ "ሥህተት አልባ" አተረጓገም አመትእእኪተረጉም ቤተክርስቲያን አልነበረችም የሚል የኑፋቄ ትምህርት ነው ይህ ትምህርታቹ!
ከወልድ በሚሠርጽ የሚለው ቃል የጉባኤ ቁስጥንጥንያ ምስክር አይደለም ።
እሱ በካቶሊክ እና በኦርቶዶክስ ሙግት ላያ ያለ ስለሆነ እንደ ፕሮቴስታንት ትውፊትም የካቶሊክ ትምህርት ስለቀጠለ አካትቸዋለው። ኦሮቶዶክስ ክርሰቲያን የሆኑ ወገኖች ደሞ ስለማይቀበሉት በቀይ ለይቸዋለሁ ምናልባት ቪዲዮ ላይ አስተውለህ ካየኸው።
ወቀሳ 2:-- ስጋ በመለኮት ተውጧል የሚለውን የአውጣኪን Monophysite Christology ቅዱስ ዲዬስቆሮስ ተቀብሎ አውጣኪን በ2ተኛው የኤፌሶን ጉባኤ ከግዝቱ ፈታው ያልከው የተሳሳተ ነው። እውነታው ግን:- አውጣኪ ከግዝቱ የተፈታው Chrystologyዬ የቅዱስ ቄርሎስ (Miaphysite) ነው በማለቱ ነበር። ነገር ግን አውጣኪ ወደ ቆሻሻው Monophysite Christologyው ሲመለስ፤ በዲዬስቆሮስ መሪነት፤ ኢትዬጽያን ጨምሮ 6ቱም የOriental Orthodox አብያተ ክርስትያናት አውግዘውታል፤ አሁን ድረስ የተወገዘ ነው።
እንደዛ ያሉት የኬልቄዶን ጉባኤ ላይ የተሰበሰቡ ሰውች እንጂ ኦረንቲያሎች ወይም አባ ዲዮስቆሮስ አውጣኪያዊ አለመሆናቸውን ተናግሪያለሁ እሳቸው ግን አውጣኬን ከውግዘት መፍታታቸው (በተሳሳተ መረጃ ላይ ተመስርተውም ቢሆን) በእሳቱ ላይ ቤንዚን የማርከፍከፍ ያህል ነበረ። የምዕራባዊያ ጽሁፎች የኦረንቲያል ትምህርትን አውጣኪያዊነት ነው የሚሉት ያ ግን የውሸት ክስ ነው። ያ እናንተም የግሪክንና የካቶሊክን ብሎም የፕሮቴስታንት ትምህርት ሆኖ የቀረውን የሊዮን ጦማር ንስጥሮሳዊ ብላቹ እንደምትከሱት ሁሉ ማለት ነው። አሳታዬቶችህ ገንቢ ናቸው፤ በጣም አመሰግናለሁ ወንድሜ!
Still ale
Greetings, I was very interested in this and wanted to listen to it. I’m commenting here because there was no other way of reaching you directly. Please stop the music while you speak. It is very distracting and unnecessary!! 5 minutes into this video and I couldn’t take it anymore. There is NO need to let the music run while you are speaking and this was way too loud! Sorry brother but there was no way of contacting you directly.
እሺ በጠም ለመቀነስ እሞክራለሁ ሙዚቃ ሐሳብን የመሰብሰብ ባሕሪ አለው ብዬ አስቤ ነው ያረኩት እሺ አስተካክላለሁ ወንድሜ!
የኬልቄዶንን ጉባኤ በትክክል፣ የሊዬንን ጦማር በሚገባው ጠቅሰሀል። Generally የሁሉንም fair በሆነ መንገድ ለማቅረብ የጣርከው ጥረት ያስመሰግንሀል። ከፕሮቴስታንት የማይጠበቅ ነው፣ እንደሌሎቹ አይደለህም፤ ፊደል መቁጠርህ ያስታውቃል። 3 ወቀሳና 1 አስተያየት ግን አለኝ።
ምናልባት በተለያየ መንገድ ተቃወምነው እንጂ የፕሮቴስታንት የኦረንቲያሎች ተቃውም የሮም ጳጳስ ሊሳሳት አይችልም የሚለው የካቶሊክ ትምህርት ነው። ለአሳታዬትህ አመሰግናለሁ ፕሮቴስታንትን ነቆር ብታደርግም😂።
Not like that ,the pope is only infallible when he speaks from the see,ex cathedra@@gratiaethiopia
ልጁን አድንቀህ ልብህ ውልቅ ብሏል። ወዳጄ አብዛኛው ጴንጤ እንደ እባብ ብልጥ እንደርግብ የዋህ ነው።እንደዚች አይነት በማር የተለወሰ መርዝ በደምብ ነው ምንለየው።
Sgw qal(incarnated word/God)...qal sga hone
@@TsegayeZenebealsemahutm ljun dnget yanten comment gn ayehut bro Menafk mn aynet bahri endalew abatochachn negrewnal egnam eyayenachu nw…..
Genzeb wedad
Wushetam
Crstos Crstos yemtlu yemtwedut yemtmeslu gn yemtsedbut….
Betkeklm yeHasawiw mesih teketayoch!
ምስል ለምን ትጠቀማለ ልጆቻችን መጣሪ መንፈስ ነው ስንላቸው ስለፎቶ ይጠይቁናል
ስለሱም ማብራሪያ እስጣለሁ ስለሁሉም ፕሮቴስታንታዊ እና ክርስቲያናዊ ምልከታ❤
Because He is catholic. Be careful 🙏
ትምህርቱ የሰንበት ት/ት ቤት ተማሪዎች ት/ት አይደለም። ይልቁን ለአዋቂዎችና የጠለቀ ት/ት መማር ለሚችሉት ስለሆነ ስዕላዊ ገለጻ በጣም ገላጭ ነው!
ኧረ ሌሎች ቪዲዮቼን ተመልከት እኔ ፕሮቴስታንት ነኝ!😂😍😍😍 የምጠቀመው ደሞ የምስራቅ ኦርቶዶክስን ስዕል ነው።
ከማርያም ስጋ ወሰደ አይልም። በስጋ መጣ እንጂ ከስጋ መጣ አይልም።
አዎ ዮሐንስ በስጋ መጣ ብሎ መልስ የሰጠው ከማሪያም ወይም ከሰው ሥጋን አልወሰደም ለሚሉ ለኖስቲካዊያን ነው። 1 ዮሐ 4፥1 ስለኖስቲካዊን ትምህርት ትንሽ አጥንተህ ይህን ክፍል ብታነበው በሚገባ ነገሮችን ወደመረዳት ትመጣለህ። ኢየሱስ የማሪያም የማህፀን ፍሬ ነው።
ከመሠረቱ "መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ" የሚለው ነው መዘዝ ያመጣው። መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ ከሆነ "መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ" የሚሉ በሺህ የሚቆጠሩ የፕሮቴስታንት ክፍልፋዮች የኖሩት ለምንድር ነው? አንዱ "መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ" እያለ አንድ ነገር ይላል፤ ሌላው "መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ" እያለ ሌላ ይላል። እስቲ አታወዛግቡ ወገን።
አይዞህ አናወዛግብህም😂
እሺ 😂
19:02 that a big shame to add " and the son ",, in the first creed, it doesn't add that so don't lead the people into the wrong side😑🙏
@@MirrorMe3 በቀይ ለብቻ ምልክት ያደረኩበት ለዛ ነው።
The Nicene Creed and the Filioque Clause:
The original Nicene Creed, formulated at the First Council of Nicaea in 325 AD, did not include the phrase "and the Son" (Filioque in Latin). The original wording concerning the Holy Spirit stated:
“We believe in the Holy Spirit, the Lord, the giver of life, who proceeds from the Father.”
The Filioque clause ("and the Son") was later added to the Creed in Western Christianity during the Third Council of Toledo (589 AD) and became a point of contention between the Eastern (Orthodox) and Western (Catholic) Churches. The Eastern Churches maintain the original version of the Creed without the Filioque, emphasizing the procession of the Holy Spirit from the Father alone.
It is essential to be accurate when presenting historical or theological matters. Including the Filioque in a context about the Council of Nicaea is historically incorrect and can lead to misunderstanding about the original formulation of the Creed.
Orthodox Tewahedo Church and Miaphysitism:
The Orthodox Tewahedo Churches (e.g., Ethiopian, Eritrean, and Coptic) adhere to Miaphysitism, not Monophysitism.
Miaphysitism: This teaching asserts that Christ’s divine and human natures are united in one composite nature, "without confusion, change, division, or separation."
Monophysitism: Often inaccurately attributed to Miaphysite Churches, it claims that Christ has only one nature, usually divine, with the human nature being absorbed.
Labeling the Orthodox Tewahedo Church as Monophysite is a significant theological error.
My Recommendation
1. For the Nicene Creed: Remove the Filioque from discussions of the Council of Nicaea (325 AD) and clarify that it was a later addition by the Western Church.
2. For the Orthodox Tewahedo Church: Accurately describe its teaching as Miaphysitism to avoid misrepresentation and ensure theological correctness.
1ኛ ከወልድ ወጣ የሚለውን በቀይ የለመለየት ሞክሪያለሁ።
2ኛ የኬልቄድን ጉባኤ በኋላ የምዕራቡን አለም ምልከታ ለማስቀመጥ ነው የሞከርጉት ነገር በጣም ሚዛናዊ ገለፃ በተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዙሪያ ለመስጠት ሞክሪያለሁ። ሲመስለኝ ሁለቱም ግን በቂ አይደሉም ግልጽ ማብራሪያ ይጠበቅብኛል።
አንድባህሪ አንድ አካል በተዋህዶ ሁለት ባህሪ አንድ አካል ወይም ሁለት አካል መናፍቃን ትምህርትነው
አሁን ላይ አሌግሳንድሪያ እና ግሪክ የቃላት እንጂ የትምህርት ልዩነት እያሉ ነው። በሲኖዶስ ደረጃ ባይሆንም።
Anathema son of Dioscorus
ስለ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማቴ16 በሚገባ ያብራራል ካቶሊካዊት ሐዋርያዊት ነች
ጴጥሮስ አንድ ቤተእምነትን ወክሎ አይደለም ሥልጣን የተሰጠው የጴጥሮስ ሥልጣን የመላዋ ቤተክርስቲያን ሥልጣን እንጅ በሮም ያለች አጥቢያ ቤተክርስቲያን ሥልጣን አይደለም። ጴጥሮስ በሮም ሰማዕት ይሁን እንጂ በአንፆኪያ ብዙ አገልግሏል በዚያም እጁን ጭኖ የሾማቸው አባቶች አሉ። ከሮም ቤተክርስቲያን ጋር በብዙ ትምህርት እንስማማለን ነገር ግን ስለ ጳጳሳቷ ባላት ምልከታ የተነሳ ብዙ መከፋፈሎችን አስተናጋዳለች።
@gratiaethiopa ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ለሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በአደራ መልክ ሰጠው ጴጥሮስም ለተከታዮቹን አስረከበ ይህም ማለት ከጴጥሮስ ጀምሮ እስከ አሁን ይዘቷን ሳትለቅ ያለች ቤተክርስቲያን ነች እና አሁን ያሉት ጳጳስ 266ኛ ናቸው
This UA-cam page is not Orthodoxy.
አዎ የኦሮቶዶክስ የዩቱብ ቻናል አይደለም የፕሮቴስታንት ነው!
@gratiaethiopa
Protestiantism is denkoro and dedeb all over the world yminorubet gmat new.
ጠቃሚ ቻናል!!!!
ሰብስክራይብ❤
እየሱስ በመንፈስ ቅዱስ መገለጥ ብቸኛ አምላክ ነው (እግዚአብሔር ሰው ሆነ ):: ስላሴ ሚባለው አምላክ የለም :: ስላሴ በጉባኤ የተፈጠረ የሌለ አምላክ ነው ::
ሥላሴ በጉባኤ የተፈጠረ ሌላ አምላክ አይደለም እስኪ አንድ የአንተ አይነት ትምህር የነበረው የቤተክርስቲያን አባት ጥራ። ጆቫዎች አሪዮስ አላቸው አንተ ማነው አባትህ? ማነው ሐዋሪያት ያስተማሩትን ሰምቶ አንተ ያስተማርገውን አይነት ትምህርት ያስተማረ? የጷውሎስ ደቀመዝሙር ጢሞቲዮስ አንተ እንዳስተማርከው አስተማረ? የጴጥሮስ እና የጷውሎስ ተማሪ የነበረው ቄሌምጦስ አንተ እንዳስተማርከው አስተማረ? ወይስ የዮሐንስ ተማሪ የነበሩት አግናጢዮስ እና ፖሊካርፕ አንተ ያስተማርከውን አስተማሩ? ከእነዚህ በሐዋሪያት አፍ ከተማሩ ሐዋሪያትን በአካል ከሚያቁ ሰዎች የተለየ ክርስትና ካለህ አንተ ወደ ሲዖል የሚንደረደር መናፍቅ ነህ!
የምርህን ነዋ 😂
@@gratiaethiopia
እየሱስ ላይ የሚተካከል ሌላ አምላክ አለ የሚል አጋንት ብቻ ነው (ፀረ ክርስቶስ )::
ፀረ ክርስቶስ ወልድ አምላክ አይደለም ሥጋ እና አጥንት ብቻ ነው የሚል ትናንት ማታ ተክሌ አምጦ የወለደ ኑፋቄ ነው! ወልድ ከዘላለም አብ ልጅ ነው! አብ ከዘላለም አባት ነው! አብ አባት የሆልሆነበት ዘመን የለም! ወልድ ልጅ ያልሆነበት ዘመን የለም! ፀረ ክርስቶስ ፀረ ኢየሱስ! ኢየሱስ የመሰረታት የገሀነም ደጆች የማይችሏት ቤተክርስቲያን ጠፍታ ድጋሜ ተክሌ መሰረታት የምትል ተክሌን የምታምን የምታመልክ እና የምትከተል ሰው የሰው ሰራሽ ፍልስፍና አራማጅ መናፍቅ! ወግዝ ከመ አሪዮስ!
አብ - ወልድ -መንፈስ ቅዱስ
ኤፌሶን 7??????🤨
ሰአቱንና ደቂቃውን ልትነግረኝ ትችላለህ ለማረም እንድችል?
Lower your back sound, and it takes me away off the teaching,
እሺ አስተካክላለሁ።
ዮሐ1 በመጀመሪያ ቃል ነበር ቃልም በእ/ግ ዘንድ ነበር;-በመጀመሪያ በተስፋ ቃል ደረጃ ነበር እያለ ነው ሌላው በእ/ግ ዘንድ ነበረ ማለት ህያው ሆኖ ሳይሆን ኢየሱስ ስለ ሙታን ትንሳኤ ሲናገር በሉቃ 20v37 እነ አብርሃም,ይስሐቅ,ያዕቆብ..ምንም ቢሞቱ ለእ/ግ ህያዋን ናቸው ይለናል በሌላ ቦታም በኤር1v5 እ/ግ ኤርሚያስን በሆድ ሳልሰራህ አወቅሁ ለአህዛብም ነብይ አደርጌሀለሁ ይለዋል አየህ በእ/ግ ዘንድ ሁሉ የታወቀ ነው እሱ የሌለን ነገር እንዳለ አድርጐ ነው እሚጠራው ያ ማለት ግን ኤርሚ ሳይወለድ በተጨባጭ አለም ወይ በሰማይ ህያው ሆኖ ነበር ማለት አይደለም,እነ አብርሃምም መሞታቸው ተዘንግቶ አይደለም ነገር ግን በእርግጥ ኤርሜያስ እና አብርሃም እ/ግ እንዳሰበ ቀናቸው ሲደርስ መገለጣቸው ስለማይቀር ነው ..እንግዲህ ቃልም እ/ግ ነበር ሲል ልክ ኤርሚያስ ከመወለዱ በፊት በእ/ግ ሀሳብ ውስጥ ነቡይ እደሚሆን እደሚታወቅ ኢየሱስ ደሞ በኢሳ9v6 ላይ ህፃኑ ሲወለድ ሀያል አምላክ እደሚሆን እና ገዢ እደሚሆን እ/ግ ተናግሯል::በመዝ110v1 በቀኙ እንደሚያስቀምጠው ተናግሯል ስለዚህ በእ/ግ ሀሳብ ለዚህ ክብር ታጭቷል..
ቁ.3 ሁሉ በእርሱ ሆነ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም። በእርሱ ሕይወት ነበረች ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።ብርሃንም በጨለማ ይበራል ጨለማም አላሸነፈውም።ሁሉ በእርሱ ሆነ ሲል ሰማይ ምድሩን ኢየሱስ ፈጠረ ማለት አይደለም ወረድ ብሎ በእርሱ ህይወት ነበረ ህወትም የሰው ብርሃን ብርሃን በጨለማ በራ ጨለማም አላሸነፈውም..ኢየሱስ በእ/ግ ሲቀባ የተሰጠው ተልዕኮ አለ ያም ተልዕኮ በሞቱ ሰማይን ከምድር ማስታረቅ ሲሆን ሌላው ደሞ በሞት ላይ ስልጣን ያለውን ዲያቢሎስ በሞት መሻር ነው ከዚህም በኃላ በትንሳኤ አዲሱ አለም ውስጥ መጀመሪያ ሆኖ መግባት ለእኛም መንገዱን መርቆ ማስከፈት ነው ይህ ሁሉ ኢዲሱ በክርስቶስ የተፈጠረው አለም ይባላል ይህን ነው ሁሉ በእርሱ ሆነ እሚለን ሌላው ኤፌ2v10 እግዚአብሔር ያዘጋጀውን መልካሙን ስራ ለማድረግ በክርስቶስ ተፈጠርን ይላል ይህ ማለት አይን አፍንጫችን በክርስቶስ ተፈጠረ ሳይሆን በእውነት ቃል ውስጣችን ዳግም ተፈጠረ ማለት ነው ስለዚህ እውነት ነው አዲሱ የዓለም ስርዓት እና ዳግም በእውነት ቃል የተፈጠሩት ሰዎች በእሱ ነው የተፈጠሩት::
ቁ.14 ቃልም ስጋ ሆነ;- ያ በተስፋ ቃል ብቻ የነበረው ሙሴ በህግ ነቢያትም ስለ እሱ የመሰከሩለት ወደፊት ከዳዊት ዘር እሚወለድ ሰው የሆነ ንጉስ በተስፋ ቃልነት ብቻ የነበረው ክርስቶስ ሲወለድ የተሰጠው ተስፋ ተጨበጠ ቃል ስጋ ሆነ እ/ግ እደተናገረ አደረገ ማለት እንጂ ቃል እሚባል እ/ግ ወልድ ስጋ ተዋሐደ ማለት አይደለም::
"በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ።ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።"
ዮሐ 1፥1-3
ይህን ክፍል አንተ እንደ ተረጎመገው ልተርጉመው እስኪ 😂 በመጀመሪያ አብርሀም ነበረ። አብርሃምም እግዚአብሔር ነበረ በመጀመሪያ አብርሀም ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ።😂
ይሄ ውሸት ተውጦልህ እያመነከው ነው የኖርከው?
በመጀመሪያ ቃል ነበረ ማለት እንደ ሚልኪያስ አነጋገር
“ አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ ” ማለት ነው።
- ሚክያስ 5፥2
እንደ ኢየሱስ አነጋገር ደግሞ
“ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ ” ማለት ነው።
- ዮሐንስ 8፥58
ደግሞም እንደ ኢየሱስ አነጋገር
“ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥”
- ራእይ 1፥17 ማለት ነው።
እንደ ኢሳያስ ንግግር ደግሞ
"የዘላለም አባት ማለት ነው።"
"እግዚአብሔር ነበረ" ማለት እንደ ቅዱስ ጷውሎስ ንግግር
እግዚአብሔር መተካከል እኩል መሆን ማለት ነው!
“እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥”
- ፊልጵስዩስ 2፥6
አዎ እንደ ቅዱስ ዮሐንስም ትምህር ከእግዚአብሔር ጋር እኩል መሆን ማለት ነው።
“እንግዲህ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ደግሞ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ፦ እግዚአብሔር አባቴ ነው ስላለ፥ ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር።”
- ዮሐንስ 5፥18
"ሁሉ በእርሱ ሆነ" ማለት
ቆላስይስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵-¹⁶ እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው፤ የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤
¹⁷ እርሱም ከሁሉ በፊት ነው ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል።
" ቃል ሥጋ ሆነ" ማለት
“ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥” ማለት ነው
- ፊልጵስዩስ 2፥7
ፍቃድ ያለው ከአምላክ ጋር እኩል የሆነ በእግዚአብሔር መልክ የሚኖር በፈቃደኝነት በትህትና ራሱን ባዶ አድርጎ ሰው ሆነ ማለት ነው።
ቃል ሥጋ ሆነ ማለት
“በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤” ማለት ነው ።
- ቆላስይስ 2፥9
ቃል ሥጋ ሆነ ማለት።
እግዚአብሔር በሥጋ ተገለጠ ማለት ነው!
“እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።”
- 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፥16
ወንድም አልገባኝም ሉቃ 9v20"አንተ ከ እ/ግ የተቀባህ ነህ ይለዋል እንጂ እ/ግ ነህ አይልም..1እ/ግ ነው ያለው:: ኢየሱስ እ/ግ ያከበረው ጌታም ክርስቶስም አድርጐ በ ቀኙ ያስቀመጠው የሰው ልጅ እንጂ እራሱ God ነው ብዬ አላምንም....ብናወራ ጥሩ ይመስለኛል ..
ያው ዮሐ 1፥1 ፊሊ 2፥6 ዕብ 1 ከግምት አስገብተህ አስተሳሰንህን ብታረቀው ጥሩ ነው። ለዚህ ድምዳሜህ ለእነዚህ ጥቅሶች የግድ የራስህን አዕምሯዊ ትንታኔ ሳትሰጥ ክፍሎቹን ቃል በቃል ተቀብለህ እንዲህ ያለ ሥህተት ላይ አትወድቅም። ለትምህርትህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪካዊ እና አመክንዮታዊ መረጃ ከሌለህ ሥለ ግላዊ ትርጉምህ እኔ ልረዳህ አልችልም። ጌታ ከራስህ ያስመልጥህ!
ይህ ብቸኛ የሆነ አምላክ ለቀደሙ የ እምነት አባቶቻችን ክርስቶስን በተመለከተ በግልፅ የነገራቸው ነገር አለ ወይም የሰጣቸው ተስፋ አለ እሱም ከ አብርሀም እና ከዳዎት ዘር እሚወለድ እና የእስራኤላዊያን ሁለ ተስፋ እና በረከት እደሚሆን..ዘዳ 18v18 ከወንድሞቻቸው መካከል እንደ ሙሴ ያለ ሰው እንደሚያስነሳ..በኢሳ 11v 1 ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፥ ከሥሩም ቍጥቋጥ ያፈራል።የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ፥ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።
እግዚአብሔርን በመፍራት ደስታውን ያያል። ይህ እንደሙሴ ያለው ሰው ሲመጣ እ/ግ መንፈሱን በሙላት እንደሚሰጠው እና ያ የተሰጠው መንፈስ በዋናነት እ/ግ እንዲፈራ እደሚያደርገው እና ደስታውም ፈጣሪውን በመፍራት እንደሆነ ያሳየናል::ሌላው በ .......
ኢሳ 42v1-7 እነሆ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ..........
5 ሰማያትን የፈጠረ የዘረጋቸውም፥ ምድርንና በውስጥዋ ያለውን ያጸና፥ በእርስዋ ላይ ለሚኖሩ ሕዝብ እስትንፋስን፥ ለሚሄዱባትም መንፈስን የሚሰጥ አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።እኔ እግዚአብሔር በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፥ እጅህንም እይዛለሁ እጠብቅህማለሁ፥ የዕውሩንም ዓይን ትከፍት ዘንድ የተጋዘውንም ከግዞት ቤት በጨለማም የተቀመጡትን ከወህኒ ቤት ታወጣ ዘንድ ለሕዝብ ቃል ኪዳን ለአሕዛብም ብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ።እግዲህ እዚም ለይ እደሚናገረው መንፈሱን እሚሰጠው እራሱ እ/ግ እደሆነ,የራሱ ባሪያ እደሆነ,እጁ መያዝ እዳለበት እና ደጋፊውም እደሚሆን ይናገራል.. ይህ ሁሉ እሚያስፈልገው ሰው በመሆኑ ነው..ሌላው ቁ.5 ላይ የሰማይ የምድር ፈጣሪ ብቸኛው እ/ግ ክርስቶስን በ ፅድቅ እደሚጠራው በተስፋ ይናገራል..ስለዚህ bro ከ እ/ግ ውጭ ፈጣሪ የለም ኢየሱስ እ/ግ ጌታ እና ክርስቶስ ያደረገው እና አክብሮ በቀኙ ያሰቀመጠው ሰው ነው::
ከእግዚአብሔር ውጪ ፈጣሪ አለ ብሎ የሚያስተምር የክርስትና ትምህርት የለም! ይህ አንዱ መለኮት ለአባቶች የሰጠው ኪዳን ነው። እንደሰጠውም ኪዳን መሰረት የድንግል ማሪያምን እውነተኛ ልጅ ሙሉ ሰው የሆነውን እውነተኛ ሰው የሆነው ኢየሱስ አክብሮታል ደግፎታል በቀኙ ይዞታል። ነገር የድንግል ማሪያም ልጅ ሊሆን የወደደው እና ከእርሷ ስጋን የተካፈለው ለዘላለም የመለኩት ቃል የሆነ ሙሉ የመለኮት ባሕሪ ያለው እውነተኛ መለኮት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ነው። ስለዚህ አንተ በጠቀስካቸው ክፍሎች እንደተፃፈው እውነተኛ ሰው የሆነውን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የተሞላውን ፤ ችላ ባልካቸው ክፍሎች ደሞ የተፃፈውን እውነተኛ አምላክ ለዘላለም ከአብ ጋር የነበረ የተፈጠረ ሳይሆን የተወለደውን ክርስቶስ ጌታ አዳኝ የሆነውን እንሰብካለን።
ጥሩ ..እግዚአብሔር ለአባቶቻችን የሰጠው ቃል ኪዳን ምን ነበር? እግዚአብሔር ከአዳም ውድቀት ጀምሮ እስከ መጨረሻዎቹ ነቢያት ድረስ ይህን የተስፋ/የኪዳን ቃል ግልፅ በሆነ ቃል እየነገራቸው ነው የመጣው..ተስፋው ከመፈፀሙ በፊት በነበረው መፅሀፍ ላይ በየትኛውም ክፍል ውስጥ 1ኛ እግዚአብሔር አብን መስተካከል እሚችል አግዚአብሔር ወልድ የተባለ አካል አባቶቻችን(የእምነት) ሰምተውም አይተውም አያውቁም..2ኛ ብቸኛው መለኮት እና ፈጣሪ የሆነው እ/ግ አብ ስለተስፋው በተናገረባቸው ቦታዎች ውስጥ ሰው የሆነ ከአብርሃም ከዳዊት ዘር ይመጣል አለ እንጂ አብሮት ያለ ወልድ መለኮት በስጋ ይዋሐዳል የሚል ተስፋ አባቶቻችን አልሰሙም coz ብቸኛው ፈጣሪ እደዛ ብሎ ስላልነገራቸው ..ስለዚህ ለአብርሃም በዘፍ 12,15,17 በሰጠው ተስፋ ከ አብርሃም ወገብ በሚወጣው የምድር ወገኖች እደሚባረኩ እንጂ መለኮት በዘርህ ይመጣል እሚል የለም,ዘፍ 49v10 ላይ ያዕቆብ የአብርሃም የልጅ ልጅ ልጆቹን ሲመርቅ ገዢ የሆነው ከ ልጁ ይሁዳ ነገድ ይመጣል የሚል ተስፋ ከ እ/ግ ሰማ እንጂ መለኮት በስጋ የሚል ነገር አያቅም,የ እ/ግ ባሪያ ሙሴ በ ዘዳ 18v18 የሰማው ተስፋ እንደራሱ ያለ ሰው እንጂ መለኮት በስጋ የሚል አልነበረም..ነብዮ በለአም በ ዘኍልቁ 24v19 ከያዕቆብ ገዢ ይወጣል ይለናል አሁንም መለኮት በስጋ የሚል ነገር የለም....እሺ ዳዊትን እንየው እስኪ በ2ሳሙ 7v12 ዕድሜህም በተፈጸመ ጊዜ ከአባቶችህም ጋር ባንቀላፋህ ጊዜ፥ ከወገብህ የሚወጣውን ዘርህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ፥ መንግሥቱንም አጸናለሁ። እርሱ ለስሜ ቤት ይሠራል፤ የመንግሥቱንም ዙፋን ለዘላለም አጸናለሁ። እንግዲህ እዚም ላይ ብቸኛው ፈጣሪ እ/ግ አብ ስለ ሰለሞን እና ክርስቶስ ተስፋ ሲሰጥ የዳዊት ወገብ ፍሬ እንጂ መለኮት በስጋ እሚል የለም..መዝ 132v11 እግዚአብሔር ለዳዊት በእውነት ማለ አይጸጸትምም፥ እንዲህ ብሎ:- ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ። እዚህም ላይ መለኮት በስጋ የለም..ኢሳ 11v1,ኢሳ 7v14,ኢሳ 9v6,ኢሳ 42,ኢሳ 61, ኤር 23v5,..እንግዲህ ተስፋው ሰው እንጂ መለኮት እንዳልሆነ በማያሻማ ቃል መለኮት የሆነው እግዚአብሔር ተናግሯል.. 0k አሁን ደሞ ብቸኛው መለኮት ሰለ ራሱ ምን አለ ሆሴ 11v9 እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁም ok ወደፊት ሰው ሆነህ በሰጋ አትዋሐደም ተብሎ ቢጠየቅ the answer is no! Coz ሚል 3v6 እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም..እንዴት እናምናለን ተብሎ ቢጠየቅ the answer is እመን! how? ዘኍ 23v19 ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን?!!! ስለዚህ bro ብቸኛ እና እውነተኛ አምላክ አብ ብቻ ነው ኢየሱስ እ/ግ ያከበረው በቀኙ ያስቀመጠው ሰው እንጂ መለኮት አይደለም!!
“ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።”
- ኢሳይያስ 7፥14
ከእርሷ የሚወለደው የእግዚአብሔር አካላዊ መገቸት ነው።
“ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።”
- ኢሳይያስ 9፥6
ከእርሷ የሚወለደው የዘላለም አባት (ለዘላለም የነበረ ዘላለምን ያስገኘ) ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን ብቸኛው ኃያል አምላክ ነው። ይህ ስም የእስርኤል አምላክ የእግዚአብሔር ስም ብቻ ነው! ሌላ ሊጋራው አይችልም!
“ለብዙ ሺህ ምሕረት ታደርጋለህ፥ የአባቶችንም በደል ከእነርሱ በኋላ በልጆቻቸው ብብት ትመልሳለህ፤ ስምህ ታላቅና ኃያል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።”
- ኤርምያስ 32፥18
“የያዕቆብም ቅሬታ ወደ ኃያል አምላክ ይመለሳሉ።”
- ኢሳይያስ 10፥21
ደግሞም በኤርሚያስ መጽሐፍ እግዚአብሔር ተብሎ የሚጠራ መሲህ እልክላችኋለሁ ብሎ እግዚአብሔር ቃል ገብቷል።
"እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቍጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እርሱም እንደ ንጉሥ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል።
በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፥ የሚጠራበትም ስም፦ እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው።" ኤር 23፥5-6
ለሚልኪያስ ደግሞ ከዛለለም ጀምሮ የሚኖር ወይም የነበረ በአንቺ እንደመሲህ ይመጣል በማለት መሲሁን ኢሳያስ የዘላለም አባት ነው እንዳለው ሁሉ ሚልኪያስ ደግሞ ከዘላለም የነበረ ይለዋል።
“አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።”
- ሚክያስ 5፥2
ደዊት ደግሞ በመንፈስ ሆኖ ከእርሱ ወገብ ሊወለድ ያለውን ጌታዬ ብሎ ጠርታል። ይህም ብቻ ሳይሆን መላዕክት ከመኖራቸው በፊት የነበረ መሆኑን መስክሯል።
"እግዚአብሔር ጌታዬን፦ ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው።እግዚአብሔር የኃይልን በትር ከጽዮን ይልክልሃል፤ በጠላቶችህም መካከል ግዛ።ከአንተ ጋር ቀድሞ በኃይልህ ቀን፥ በቅዱሳን ብርሃን፥ ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከሆድ ወለድሁህ።እንደ መልከ ጼዴቅ ሥርዓት አንተ ለዘላለም ካህን ነህ ብሎ፥ እግዚአብሔር ማለ አይጸጸትም።እግዚአብሔር በቀኝህ ነገሥታትን በቍጣው ቀን ይቀጠቅጣቸዋል።" መዝ 110
“እርሱም፦ እንኪያስ ዳዊት፦ ጌታ ጌታዬን፦ ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል?”
- ማቴዎስ 22፥43-44
አዎ ዳዊት የገዛ ልጁን ጌታ ብሎ ጠርቶታል እና ልጁ ሆኖ ሳለ እንዴት ጌታዬ ብሎ ይጠራዋል?
“ወደ ሰማይ የወጣ የወረደስ ማን ነው? ነፋስንስ በእጁ የጨበጠ ማን ነው? ውኃንስ በልብሱ የቋጠረ ማን ነው? የምድርን ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን ነው? ይህን ታውቅ እንደ ሆንህ፥ ስሙ ማን የልጁስ ስም ማን ነው?”
- ምሳሌ 30፥4
ሰሎም የእግዚአብሔር ልጅ ያለው ማንን ይሆን?
“በአምላካቸው በእግዚአብሔር አበረታቸዋለሁ፥ በስሙም ይመካሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።”
- ዘካርያስ 10፥12
እግዚአብሔር በእግዚአብሔር አበርትቶናል!
“ሰውም እንደሌለ አየ፥ ወደ እርሱ የሚማልድ እንደሌለ ተረዳ ተደነቀም፤ ስለዚህ የገዛ ክንዱ መድኃኒት አመጣለት፥ ጽድቁም አገዘው።”
- ኢሳይያስ 59፥16
መሲሁ የገዛ የእግዚአብሔር ክንድ እንጂ በአጋጣሚ በሰዎች መካከል የተገኘ ሰው አይደለም።
አካል የሆነ አዲስ ኪዳን ተገልጧል በጥላው ውስጥ መሲሁ እግዚአብሔር ራሱ መሆኑን በዚህ መልክ በግልጥ ተመልክተናል። እርሱ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ዘላለማዊና ዘላለምን ያስገኘ የዘላለም አምላክ ነው። እርሱ ብቸኛው ኃያል አምላክ ነው። እርሱ አማኑኤል የእግዚአብሔር አካላዊ መገኘት ነው።
ሚደንቅ አቀራረብ
beteley ኬልኬዶን gubae lay yakerebikew mizanawi yehone tintane new mikniyatum kelkedon gubae politics atalacgew enji ye Oriental orthodox and be kelkedon gubae yemiyamnu sile christ identity sigeltu temesasay new
ኦርቶዶክስ ግራጫ ነጣ ያለ ጥቁር ነው ስትል
protestant ና ሌሎች ኬልቄዶንን ውሳኔ ሚቀበሉት ደሞ የለም ግራጫ ጠቆር ያለ ነጭ ነው ይላሉ
ተመመሳሳይ አስተምሮ ግን የተለያየ አገላለፅ
በፖለቲካ ምክንያት ግን ርስ በርስ ተወጋገዙ church ውስጥ politics ሲገባ እንዲ ነው ነገር ሚበላሸው
አሁንም ድረስ ተወያይተው የተበላሸውን ለማቅናት ፍቃደኛ አይደሉም። እሱ ነው የሚያሳዝነው። በሁለቱም ወገን አጥባቂነት አለ።
አሁንም ድረስ ተወያይተው የተበላሸውን ለማቅናት ፍቃደኛ አይደሉም። እሱ ነው የሚያሳዝነው። በሁለቱም ወገን አጥባቂነት አለ።
@@gratiaethiopia ጌታ ማስተዋል ይስጠን 🙏
@@emanuelwoubshet7 አሜን!
ሰባልዮስስ
የሱ ትመህርት ኑፋቄ ነው በሁሉም ኑፋቄዎች ዙሪያ ትምህርት ለማወጋጀት እንሞክራለን።
አሁንም በሮማ እና በሌክሳንደሪያ አሁን ለመሳሌ አቀረአረበህ በሮማ ጫማ ላይ ሆነህ ነው ያቀረብከው. ሌላው ደግሞ በዓለ ሆኖ ሲያቀርብ አንደሁ ነው. መከፋፈል መከፋፈል ነው. ሁለቱም የሚሉትን በተረዳ አንድ ነው.
ሙሉ ቪዲዮውን አይተሃል ወንድሜ?
ወቀሳ 1:-- በቅዱስ ዲዬስቆሮስ ትዕዛዝ ፍሌቪያን ተደበደበ ላልከው definitive ማስረጃ የለም። ወደ ግዞት ሲወሰድ በንጉሠ ነገሥት ቴዎዶስዮስ 2ተኛ ወታደሮች ተደብድቦ ሞተ ብለን እናምናለን። ፀረ-ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ግሪኮቹና ካቶሊኮቹ ደግሞ፥ ግማሹ በባርሱማ ትዕዛዝ በተከታዬቹ ተደብድቦ ሞተ ይላሉ፥ ሌሎቹ ደግሞ በቅዱስ ዲዬስቆሮስ ትዕዛዝ ተደብድቦ ሞተ ይላሉ።
አዎ እሱን ልክ ነህ ያሉት ጽሁፎች ሁሉ የግሪክ እና የሮም ናቸው። ችግሩ ከተዋህዶ ወገን ያገኘሁት አንድ ጽሁፍ ቅዱስ ፍላቢያኖስ በጉባኤው አልተገኘም የሚል ስለሆነ ጉባኤ ላይ የተገኘን ሰው እንዳልተገኘ መቁጠሩ ምናልባት ተዋህዶውች ሊናገሩት ያልፈለጉት ነገር ይኖር እንደው እንድል አድርጎኛል። እኔ የተዋህዶ አማኝ አይደለሁም ነገር ግን በትክክል የተፈጠረውን ነገር ማወቅ እና ሚዛናዊ ድምዳሜ ላይ መድረስ ስለነበረብኝ ብዙ ጹፎችን ለመመለከት ሞክሪያለሁ ግን ሁለቱም ጉባኤያት የሁለተኛ ኤፌሶን እና የኬልቄዶን ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት እና የአባቶቻችን የሥልጣን ሽኩቻ የተስተዋለበት ነው። ዛሬ የቃላት ብቻ እንጂ የትምህርት ልዩት የለንም ሊሉ ያው በሲኖዶስ ደረጃ ባይሆንም ያነ በዛ ደረጃ መቋሰል በጣም ያሳዝናል።
@@gratiaethiopia Where do you live homie? I assume you reside in the US, as I do - I like your attitude. I just encountered limitations on UA-cam and am being forced to restrict the length of my comments - sorry for repeated short responses. Study more on this topic - I've conducted extensive research on it, drawing upon over 20 scholarly sources. Through the grace of God, I've successfully defended the Miaphysite Christology of the EOTC against several Diaphysite apologists in recent debates. You do know St. Cyril is a Miaphysite. I encourage you to explore the provided links below, where you'll discover an eight-part defense of OO Christology by the Lion's Den brothers, which extensively references the early church fathers. ua-cam.com/video/VlSqTTsGneQ/v-deo.html
@@gratiaethiopia Additionally, please peruse the links below, where you'll encounter Agen of the Apostolic Orthodoxy offering a splendid elucidation of the Oriental Orthodox Christology. ua-cam.com/video/SH5Y2nUYR5c/v-deo.html
Also refers to Sam Shmoun's contents on various theological topics, including: the Divinity of Christ, responses to Muslim arguments, the role of early Church Fathers, the concept of intercessory prayer by saint etc.... ua-cam.com/video/P9JHSQibXC0/v-deo.html
አዎ ቅዱስ ቄርሎስ በግልጽ ተናግሯል የአንድ ባሕሪ ትምህርትን ግሪኮቹ እና ሮማዊያኑ ለዚህ ያላቸውን ምላሽም ማወቅ እፈልጋለሁ ቪዲዮቹንም እመለከታለሁ። ማንበብ ስለሚቀለኝ (ማጣቀሻ ስለሚኖረው) መጽሐፍ ብጠቁመኝም ደስ ይለኛል።
@@gratiaethiopia If you reside in the D.C., MD, VA area, I highly recommend a visit to the Manuscript Division of the Library of Congress, renowned for its extensive collection of rare books. Additionally, the Semitics/ICOR Library in Washington D.C. is known for its exceptional resources.
አንድባህሪ አንድ አካል በተዋህዶ ሁለት ባህሪ አንድ አካል ወይም ሁለት አካል መናፍቃን ትምህርትነው
according to ?????