(Cover) የምስጋና መዝሙሮች - ቃልኪዳን ጥላሁን | ዳንኤል አምደሚካኤል | መሰረተ ክርስቶስ መዘምራን

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 24 січ 2025
  • Amharic Praise Songs - Kalkidan Tilahun | Daniel Amdemichael | Meserete Kristos Choir
    እኔ አፌን አልከፍትም ለአለም ክብር
    እዘምራለሁኝ ለእግዚአብሔር
    እቀኝለታለሁ በአዲስ በአዲስ ዜማ
    የምስጋናዬ ድምፅ በአርያም ይሰማ
    ምስጋናን ትወዳለህና
    አምላኬ አመሰግናለሁ (2)
    ክብርን ትወዳለህና
    አምላኬ እኔ አከብርሀለሁ (2)
    አምልኮ ትወዳለህና
    አምላኬ እኔ አመልክሀለሁ (2)
    በታላቅ ግርማ በዙፋኑ ላለው
    የምስጋናን ዘውድ በራሱ ለጫነው
    እዘምራለሁ
    በአለም ታላቅ ገናና ሞገስ ያለህ
    ከቶ ማን ይቆማል በድፍረት አጠገብህ
    እኛ ግን እናይሀለን
    በውበትህ በዝቶልን ምህረትህ
    ምስጋና አይጓደልብህ
    የተገባህ ስለሆነ የተገባህ
    ምስጋና አይጓደልብህ
    ገዝተኸናል ጌታ በዘለአለም ፍቅርህ
    ከወደድከው
    ምስጋናዬን ጌታ ከተቀበልከው
    እሰዋለሁ
    ዛሬም ነገም ጌታዬ አልሰለችም
    ምስጋናን ትወዳለህና
    አምላኬ አመሰግናለሁ (2)
    ክብርን ትወዳለህና
    አምላኬ እኔ አከብርሀለሁ (2)
    አምልኮ ትወዳለህና
    አምላኬ እኔ አመልክሀለሁ (2)
    ምስጋና አይጓደልብህ
    የተገባህ ስለሆነ የተገባህ
    ምስጋና አይጓደልብህ
    ገዝተኸናል ጌታ በዘለአለም ፍቅርህ

КОМЕНТАРІ •