የአርበኞች ታሪክ/History of Arbegnoch የሀገር ወዳዶች ታሪክ

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 5 лют 2025
  • የሀገር ወዳድ አርበኞች ታሪክ
    ሁለተኛው የኢትዮ ጣልያን ጦርነት ከተጀመረ ከጥቂት ወራት በኋላ በህዳር 29 ቀን 1928 ዓ.ም የኢትዮጵያ የጦር ሚኒስቴር የነበሩት ሙሉጌታ ይገዙ በሰሜን የነበሩትን አለቃዎች የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትን ሊወስዱ የመጡትን ጣልያኖች እንዲመክቱ አዘዙ። የአርበኛ ንቅናቄም በትግራይ ክፍለ ሀገር ከተደረገው ከማይጨው ጦርነት ወዲህ በ1928 ዓ.ም የፀደይ ወቅት ላይ ተነሳ፤ የኢትዮጵያ ግዛት የተበታተነ ሠራዊትም የደፈጣ ውግያ ሥልትን በመጠቀም ወራሪዎቹን ማጥቃት ጀመረ። የተለያዩ አካባቢዎች ነዋሪዎችም የአርበኛዎችን ቡድን ይቀላቀሉ እና ሌሎች ደግሞ በየ ግላቸው በቤታቸው አቅራብያ ጣልያንን ይዋጉ ነበር። አርበኛዎችም አስቀድመው ጣልያኖች ላይ ያደርጉ የነበረው የጦር መሳርያዎችን መውሰድ፣ በመንገድ በሚያልፉ መኪናዎች ላይ ከኮረብታ ላይ ቋጥኞችን ማንከባለል፣ መልዕክተኛዎችን ማገት፣ የስልክ መስመሮችን መቁረጥ፣ የጣልያን አመራር ቢሮዎችን፣ ነዳጅ እና የመሳርያ ማስቀመጫዎችን በእሳት ማቃጠል እንዲሁም ባንዳዎችን መግደል ነበር።
    አመፅ ሲበዛባቸውም ጣልያኖች በትግራይ ተጨማሪ ሠራዊት ማሰማራት ግድ ሆነባቸው። ጣልያኖችም አርበኞችን ሽፍታ እያሉ ፈረጇቸው። በሚያዝያ 26ም በኃይለ ማርያም ማሞ የሚመሩ አርበኞች ለደብረ ብርሃን ቅርብ የሆነ ቦታ ላይ የጣልያን አምድን አጠቁ፤ ወደ 170 የሚጠጉ አስካሪዎችንም ገድለው፤ 4 ጣልያኖችን ማረኩ። በሚያዝያ 27 1928 ዓ.ም አዲስ አበባ በጣልያኖች እጅ ወደቀች፤ ኢትዮጵያውያኑም ለመደራጀት በቅርበት ወደሚገኙ አካባቢዎች አቀኑ፤ አበበ አረጋይ ወደ አንኮበር፣ ባልቻ ሳፎ ወደ ጉራጌ፣ ዘውዱ አስፋው ወደ ሙሎ፣ ብላታ ታከለ ወልደ ሐዋርያት ወደ ሊሙ እንዲሁም የካሣ ወንድማማቾች (አበራ፣ ወንድወሰን እና አስፋወሰን) ደግሞ ወደ ሰላሌ አቀኑ። ኃይለ ማርያምም የአጥቅቶ መሸሽ ሥልትን በአዲስ አበባ ዙርያ አከናወነ። አፄ ኃይለ ሥላሴም በስደት ላይ የነበረውን መንግስታቸውን እና የአርበኞች ተግባራትን ለመደጎም ይገለገሉባቸው የነበሩትን 117 የወርቅ ሣጥኖች ይዘው ከሀገር ሸሹ።
    ንጉሠ ነገሥቱም ከሀገር የወጡት መከላከላቸውን ይቀጥሉ ዘንድ ትዕዛዝ ሰጥተው 10000 ሠራዊት በአበራ ካሣ ትዕዛዝ ስር ትተው ነበር። ሰኔ 14ም ላይ አበራ ካሣ ከሌሎች አርበኞች ጋር በመሆን ከአቡነ ጴጥሮስ ጋር ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን በ40 ኪ.ሜ ርቀት በምትገኘው በደብረ ሊባኖስ ከተማ ስብሰባ አደረጉ። በጣልያኖች ተይዛ የነበረችውን አዲስ አበባም ለመቆጣጠር እቅዶች ወጡ፤ ነገር ግን የትራንስፖርት እጥረት እና የሬድዮ እቃዎች ማጣት የተቀናጀ ጥቃት ለማድረግ እንዳይችሉ አደረጋቸው። በጎሬ የሚገኘው የተገለበጠው መንግስትም ለአርበኞች ወይም ለተቀሩት ወታደሮች ትርጉም ያለው አመራር ይሰጥ ዘንድ አልቻለም፤ ነገር ግን ራሳቸውን በቻሉ ቡድኖች በዋና ከተማዋ ዙርያ አልፎ አልፎ የሚደረጉ መከላከሎች ነበሩ።
    በሰኔ 19 ምሽት ላይም የጥቁር አንበሳ አባላት በነቀምት ሦስት የጣልያን የጦር ጀቶችን አወደሙ እና የአየር ማርሻል ቪንሴንዞ ማግሊዎኮን ጨምሮ 12 የጣልያን መኮንኖችን ገደሉ። ጣልያኖችም በአካባቢው ድጋፍ እንደሚያገኙ ተስፋ በማድረግ በእያንዳንዱ መንደር የሚያናግሩላቸው ሰዎች ይልኩ ነበር። የአዲሷ የጣልያን ምስራቅ አፍሪካ ወኪል አገረ ገዥ የነበረው ሮዶልፎ ግራዚያኒም ምክትሉ የነበረው ማግሊዎኮ ለመገደሉ በቀል ይሆን ዘንድ ነቀምት ከተማ እንድትፈነዳ አዘዘ። በዚህም ከአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ተቃውሞ የገጠማቸው አርበኞች አካባቢውን ለቅቀው ይሄዱ ዘንድ ግድ ሆነባቸው፤ የተቀረው የኢትዮጵያ ሠራዊት መሪ የነበረው ደስታ ዳምጠውም ሠራዊቱን ይዞ ወደ አርበጎና ሄደ። የራስ ደስታ ዳምጠው ሠራዊትም በጣልያን ሠራዊት በተከበበ ጊዜ ወደ ቡታጅራ ሸሸ፤ በየካቲት 12 ቀን በ1929 ዓ.ም በተካሄደው በጎጌቲ ጦርነት ተሸነፉ። በእነዚህ ጦርነቶችም 4000 አርበኞች ተገደሉ፤ ከእነዚህም ውስጥ 1600 የሚሆኑት ራስ ደስታ ዳምጠውን ጨምሮ ተማርከው በጣልያን የሞት ቅጣት ተፈርዶባቸው ተገደሉ።
    ጣልያኖች በመጀመርያዎቹ ሳምንታት በአዲስ አበባ የነበረው ሁኔታ አስቸጋሯቸው ነበር፤ ግንኙነትም ማድረግ የሚችሉት ከኤርትራ ጋር ባለው ረጅም መንገድ ብቻ ነበር፤ ጭካኔ እና ትርምስ በከተማዋ የተስፋፋ ነበር፤ ማርሻል ሮዶልፎ ግራዚያኒም አስቀድሞ 9000 ወታደሮች ብቻ ነበሩት እናም ኢትዮጵያን የሽምጥ ውግያ ተዋጊዎች እንዳያጠቁት ይሰጋ ነበር። ነገር ግን በሐምሌ ወር ላይ 35ሺህ የጣልያን ወታደሮች በተጨመሩ ጊዜ ቁጥጥራቸው ጨመረ። ከዚህ በተጨማሪም ለገዢው ከሮም የመጣ መልዕክት ነበር፤ ሙሶሊኒም ለገዢው ኢትዮጵያውያንን ጭካኔ የተሞላበት አመራር እንዲመራቸው አዘዘው።
    የሸዋ አርበኞችም አዲስ አበባን ለማጥቃት ቆርጠው ነበር፤ በአበራ ካሣ፣ በአቡነ ጴጥሮስ እና በሌሎች አመራሮች መካከል በደብረ ሊባኖስ በተደረገው ስብሰባም ዋና ከተማዋንም በ5 አምድ ተከፍለው ሊያጠቁ ወሰኑ። በሐምሌ 21 ቀን 1928 ጭጋጋማ ጠዋትም ማጥቃታቸውን ጀመሩ፤ ጥቂት ስኬት ቢያገኙም ማጥቃታቸውን ግን ያስተባብሩ ዘንድ አልቻሉም። የአበራ ካሣ ሰዎችም ምንም መቋቋም ሳይገጥማቸው አዲስ አበባ መሐል ድረስ ደረሱ፤ ፍቅረ ማርያም ደግሞ ጎርፍ በሞላው ወንዝ ምክንያት መንገድ ተዘጋበት፤ ከዚህም በኋላ የጣልያን ወታደሮች አስቆሙት። በተመሳሳይ ሰዓትም የአበበ አረጋይ አርበኞች እስከ ግራዚያኒ መኖርያ ድረስ ገፍተው ነበር፤ ነገር ግን በኤርትራ አስካሪዎች ተጠቁ፤ በነበረውም ጎርፍ ምክንያት ሁለቱ የአርበኛ ክፍሎች ጭራሽም ወደ ከተማዋ እንኳን ይገቡ ዘንድ አልቻሉም። በአዲስ አበባም ውግያቸው እስከ ሐምሌ 23 ቀን 1928 ዓ.ም ዘለቀ፤ ምንም እንኳን በኢታሎ ጋሪቦልዲ እና በሰባስቲያኖ ጋሊና የሚመራው የጣልያን ኤርትራ ሠራዊት ማጥቃቶች ቢደርስባቸውም የካሣ ወንድማማቾች አርበኞች በጀግንነት ቦታቸውን ይዘው ቆዩ፤ በመጨረሻ ግን በአየር ኃይል መጠቃት ሲጀምሩ የደፈጣ ተዋጊዎቹ ከተማዪቱን ለቅቀው መሄድ ግድ ሆነባቸው። ከአርበኛ መሪዎች አንዱ የነበሩት አቡነ ጴጥሮስም ተማረኩ፤ ጣልያኖችም አቡነ ጴጥሮስን በአደባባይ ገደሏቸው።
    በ1929 ዓ.ም በግራዚያኒ እና በአሌሳንድሮ ሌሶና የሚመራው የጣልያን አገዛዝ የኢትዮጵያን መከላከል ለመስበር እና የጣልያን የበላይነትን ለመጫን ጭካኔ የተሞላበት ዘመቻ ከፈተ። ምን አይነት ሥልት መጠቀም እንደነበረባቸው ግን ስምምነት አልነበራቸውም፤ በዚህም ሌሶና እንደ ሙስታርድ ጋዝ ህዝብ ላይ መልቀቅ ያለ መጥፎ ውሳኔ ወሰነ።
    ጣልያኖችም በጥቅምት ወር 1929 ዓ.ም ከእጀሬ በቅርበት በምትገኝ ቦታ እንደ ፍቅረ ማርያም ያሉ የተቃውሞ መሪዎችን አጠፉ። በአዋሽ ሸለቆ እና በደቡብ ሸዋም እነ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ተገደሉ።
    በታህሳስም እንደ ኢምሩ ኃይለ ሥላሴ እና ወንድወሰን ካሣ እንዲሁም እንደ ካሣ ወንድማማቾች ያሉ አርበኛዎች ተማርከው በሞት ተቀጡ።
    በየካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም አብርሃም ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶም የተባሉ ጣልያን ላይ ያመጹ ኤርትራውያን በአዲስ አበባ ማርሻል ግራዚያኒን ሊገድሉ ሞከሩ። ጣልያኖችም በምላሹ ህዝቡን መፍጀት እና ማሰቃየት ጀመሩ።
    በሦስት ቀናት ውስጥ ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያንን ገደሉ፤ ቤቶችን አቃጠሉ፤ ንጹሐንንም ገደሉ። የሞተውም ህዝብ ከ1400 እስከ 30 ሺህ ይደርስ ነበር።
    የግድያ ሙከራውንም እንደ ሰበብ በመጠቀም በጥቃቱ ዕለት የተገደሉትን 62ቱን ጨምሮ ብዙ የኢትዮጵያ ምሁራንን ገደሉ።
    በግንቦት ወር በ1929 ዓ.ም አርበኞችን አግዛችኋል በሚል ጣልያኖች በደብረ ሊባኖስ የነበሩ 449 መነኩሴዎችን፣ ዲያቆኖችን እና ምዕመናንን ገደሉ።
    የጣልያኖች ጭካኔ በበዛ ቁጥርም የአርበኛዎች ንቅናቄ እየጨመረ ሄደ።
    በ1929 ዓ.ም የበጋ ወቅትም ላይ ኃይሉ ከበደ በላስታ የነበረውን አመጽ መራ፤ የዚህም ምክንያቱ ጣልያኖች በክርስትያኖች ላይ ጭፍጨፋ ማድረጓ ነበር። ይህ አመጽም በመላው ኢትዮጵያ ተስፋፋ፤ የደፈጣ ተዋጊዎችም በጣልያኖች ላይ ቅዱስ ጦርነት አወጁ።
    እንደ በላይ ዘለቀ እና ኃይሉ ከበደ ያሉ የደፈጣ ተዋጊ መሪዎችም በጣልያን ጦር እና በግንኙነት መስመሮች ላይ ስኬታማ ማጥቃቶች በማከናወን ጣልያኖች ከተለያዩ ቦታዎች ሸሽተው እንዲሄዱ ለማድረግ ቻሉ።
    በመስከረም ወር 1930 ዓ.ም ማርሻል ግራዚያኒ የአየር ጥቃት በመከወን እና የሙስታርድ ጋዝ በመልቀቅ አመጹን ሊያፍን ሞከረ። በመስከረም 24ም ኃይሉ ከበደን ማርከው ገደሉት።
    በላስታ የነበረውን አመጽ ሊያፍኑ ቢችሉም በጎጃም፣ በበጌምድር እና በሰሜን ግን የደፈጣ ውግያ ተስፋፋ፤ እንደ በላይ ዘለቀ እና መንገሻ ጀምበሬ ባሉ የኢትዮጵያ የአርበኛ መሪዎች አማካኝነትም ብዙ ድል መገኘት ጀምረ። በህዳር ወር በ1930 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጦር ጣልያኖችን ለማስወጣት ሀገር አቀፍ አመጽ አወጀ።
    ማጣቀሻ(Reference)
    en.wikipedia.o...

КОМЕНТАРІ •