This song almost made me cry. What's happening in Ethiopia reminds me of what happened in my own country Rwanda 27 years ago. Stay strong brothers and sisters, God is with you all!
@@mutesiarchive true i cried like it's new thing, it's happening every single day. You are beautiful people i hope we will be healed soon and talk about how bad it was.
Your right for same reason when I hear the first time I was like crying, I didn’t even focussed the world he used unit the kelap made, now I know why I feel that way
I could not understand the words, but I feel her pain and what is happening in the sister of my country, Ethiopia, I could not hold back my tears, may peace prevail 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇸🇩🇸🇩🇸🇩🇸🇩🇸🇩
አሜን ሰላም ይስጠን:: የወጣቱን የገበሬው እንደ ቅጠል መርገፍ እግዚአብሔር በቃ ይበልልን::
Amen
አሜን አሜን አሜን
አሜን
I love ጎሳዬ 🥰🥰 ከ ትግራይ ❤💛❤
ሰላም ለሀገሬ አደይ ትግራይ 💊💊💊
ሰላም ኢትዮጲያ ሀገራቹ 🙏🙏
ሰላም ለሁሉም 🙏
Amenn
የዜማው ጥልቀት
- የግጥሙ ብስለት
- የሙዚቃው ቅንብር ውህደት
- የዘፋኙ ጣፋጭ ድምፀት
- የሺዲዮው ውብ ኢትዮጵያዊነት
ሁሉም ነገር ድንቅ ነው!! ❤❤❤🙏maybe one day everything will be ok
Me ml f. F
Good 👍 text
ምርጥ አገላለፅ ዋዉ
ወቅቱን የጠበቀ ምርጥ ክሊፕ። የዘፈኑ መልእክት ከበፊቱ ይልቅ እንደዚህ በቪዲዮ ሲቀርብ ይበልጥ ብዙ ሰው ጋር ይደርሳል። ብዙ ሰው ይማርበታል።
ምርጥ ነባራዊ የሆነ ነገርን እውነታውን በጥበብ ሲገለፅ ብራቮ ጎስሽ
"አፉ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ" 100% ትክክል ይህን ዘፈን ገና ዛሬ ቪዲዮ ክሊፑ በሚበገባ ገለፀው ጐስ አሁን ገና ለፍትህ ጮህ እናመሰግናለን።
Ke 3 amet befit mesmat yetesanew neberk enda nw weyns yane magenazebiyah zeg neber🤣
@@ekrammmd1857 ❤️
በትክክል።
@@ekrammmd1857 i would rather die
@@ekrammmd1857 😂😂😂👍👍
ዘፈን አላዳምጥም ግን ይሄ ዘፈን ልብ ይነካል ያስለቅሳል
Amen 🙏🏽 እግዚአብሔር ኢትዮጵያን በቃሽ ይበላት! ፍቅሩን: መከባበሩን: መቻቻሉንና መተሳሰቡን ያድለን! ይህንን የምታነቡ ብሄረ አማራ...ብሄረ ትግራይ... ብሄረ ኦሮሞና ሌሎችም ኢትዮጵያውያን ሁሉ በእኩል አይኔ አያችኃለው: በእኩል ልቤም እወዳችኃለው! እኛ ስንፋቀር እግዚአብሔር ይቅር ይለናልና አሁንም አልረፈደም ክፋትን: ምቀኝነትንና ዘረኝነትን አስወግደን እርስበርሳችን እንወዳድ🥰 Stay blessed gossaye and May God bless Ethiopia 👆🏽
Thnxs bro for ur nice nd sweet words. "May god bless this country that i love nd live in "
Tnx 🙏🙏💚💛❤
እንባዬ ቅርር ብሎ የሰማሁት ዘፈን.🥺🥺
ፈጣሪ በቃቹ ይበለን
ፍቅር💚 ሰላም💛 ደስታ ♥️
ለመላው አለማችን እመኛለው
🕋💚❤️💪
በጣም ዋጋ የተከፈለበት እጅግ ትልቅ እና ወቅታዊ ስራ መሆኑ ግልፅ ካንጀት ሰርታችሁታል Respect !!
This song almost made me cry. What's happening in Ethiopia reminds me of what happened in my own country Rwanda 27 years ago. Stay strong brothers and sisters, God is with you all!
i have already cried
i did cry, Amen stay blessed!
@@Wende_Zeedad I was holding myself back honestly. The Imagery in the video is so strong.
@@mutesiarchive true i cried like it's new thing, it's happening every single day.
You are beautiful people i hope we will be healed soon and talk about how bad it was.
Reality 😢
አፈ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን ከዚህ ፈተና!
የ20ክፍለ ዘመን የአኗኗር ጥበብ ህሊናና ልብን ሳይሆን በአፍ በመሆኑ እውነተኝነቱን ምሰክር፣** በአፍ ቅዱሰ ሰው ፣ምግባሩሌላ *
"አፉ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ እንዳንሆን አውጣን እግዚኦ ማረና " ይሰማል በሻሻ ?
የት ሄጄ ነው ግን ይህንን ሙዚቃ ያልሰማሁት ጎስሽ እውነታውን እንደዚህ ግልጽ አድርገህ ስላቀረብክ አከብርሃለው አንድ የህዝብ ነኝ የሚል አርቲስት ከህዝብ ጎን ሆኖ የወገኑን ህመም ሲታመም ማየት እውነት ደስ ይላል ተባረክ ወንድሜ።
"አንቃን"🙏
ሰላም ይስጠን እግዜር ገናና
ከጋረደን ጥቁር ደመና
ጊዜው ይሆን እላለው እኔ
የሚሆነውን ሳስተውል በዓይኔ
ሰላም ይስጠን እግዜር ገናና
ከጋረደን ጥቁር ደመና
ጊዜው ይሆን እላለው እኔ
የሚሆነውን ሳስተውል በዓይኔ
እንዲያው አንዳንዴ ይገርማል
ኧረ እንደው አንዳንዴስ ይደንቃል
እንዴት ተንዶ ፍቅራችን
ማነው ያራራቀን ከእውነት ቃል
በጊዜ አስታከን በዘመን
ራስ መውደድን አስቀድመን
ይቅርታ ራቀ ካፋችን
ዝና እየተቀማ ልባችን
አንቃን
ይብቃችሁ በለን የፍቅር አምላክ ጌታ
አንቃን
ቅድስቷን ምድር ሰላም አውርሳት ደስታ
አንቃን
ከቁጣ አብርደህ ቅን ወዳጅ አርገህ አንቃን
አንቃን
የት ይደረሳል ምን ይወረሳል ይብቃን
አቤቱ አቤቱ
አውጣን ከመዓቱ
ማረን (እግዚኦ)
ማረን ከክፋ አድነን
አቤቱ አቤቱ
አውጣን ከመዓቱ
ማረን ማረን
ከክፋ አድነን
አፋ ቅዱስ ሰው
ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን
ከዚ ፈተና
አፋ ቅዱስ ሰው
ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን
እግዚኦ መሐረነ
ሰላም ይስጠን እግዜር ገናና
ከጋረደን ጥቁር ደመና
ጊዜው ይሆን እላለው እኔ
የሚሆነውን ሳስተውል በዓይኔ
ሰላም ይስጠን እግዜር ገናና
ከጋረደን ጥቁር ደመና
ጊዜው ይሆን እላለው እኔ
የሚሆነውን ሳስተውል በዓይኔ
በሀሜት በወሬ ታጅበን
በግላዊ ምቾት ተከበን
በዚች ጊዜያዊ ከንቱ ዓለም
ዘላለም ቋሚ ግን አንድ የለም
ንብረት ከሰው ልጅ አብልጠን
ክፋት ምቀኝነትን መርጠን
ዘመን አለፈ ስንኖር
የፅድቁን መንገድ የሚያሳይ አጥተን
አንቃን
ይብቃችሁ በለን የፍቅር አምላክ ጌታ
አንቃን
ቅድስቷን ምድር ሰላም አውርሳት ደስታ
አንቃን
ከቁጣ አብርደህ ቅን ወዳጅ አርገህ አንቃን
አንቃን
የት ይደረሳል ምን ይወረሳል ይብቃን
አቤቱ አቤቱ
አውጣን ከመዓቱ
ማረን ማረን (እግዚኦ አንጽአነ)
ከክፋ አድነን
አቤቱ አቤቱ
አውጣን ከመዓቱ
ማረን ማረን
ከክፋ አድነን (እግዚኦ)
አፋ ቅዱስ ሰው
ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን
ከዚ ፈተና (እግዚኦ)
አፋ ቅዱስ ሰው
ምግባሩ ሌላ (ምግባሩ ሌላ)
እንዳንሆን አውጣን
እግዚኦ መሐረነ
አቤቱ አቤቱ
አውጣን ከመዓቱ
ማረን ማረን
ከክፋ አድነን
አቤቱ አቤቱ
አውጣን ከመዓቱ
ማረን ማረን
ከክፋ አድነን
አቤቱ አቤቱ
አውጣን ከመዓቱ
ማረን ማረን
ከክፉ አድነን
This song described 👌 exactly the reality of Ethiopia 🇪🇹 Well done brother 👏 👍
Your right for same reason when I hear the first time I was like crying, I didn’t even focussed the world he used unit the kelap made, now I know why I feel that way
Wrfg
@@selammulugeta3151 ፣
@@ameame9759 🐆
OMG i cry a lot and it's true with the reality his music,very sad
እውነት ምንልበል ............ምንም አልልም እግዝያብሔር እድሜነ ጤነ ይስጠችሁ።
አለም ፀሃይ ወዳጆን አለማድነቅ አይቻልም ስራዎቿ ያስታውቃሉ : ጎስሽም ምርጥ የመርኬ ልጅ we proud of you
"አፉ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ" 100% ግሩም መልዕክት ጎሳዬ ክብረት ይስጥልን ።
ጎስሽ የሚያክልክ የለም አንደኛዬ ነህ ፈጣሪ ኢትዮጰያን ይጠብቅ💚💛❤️
በትክክል ለኔም እሱጋር የማወዳድረው የለም።
ብዙ ጎበዞች ቢኖሩም ግን ጎስሽ ይለያል
ለኔም የምንግዜም ምርጡ እሱ ነው
Fatrhi salmun yardlne bakachu yebalne
መታሰብያነቱ ወለጋ ላይ,ቤኒሻንጉል ላይ,አማራ ክልል ላይ, ቡራዩ ላይ,ጌዲዮ ላይ,ትግራይ ላይ በግፍ ለተገደሉ ኢትዮጵያውያን ይሁን!!
ሀገራችንን በምህረቱ ይጎብኛት!!
Kkk fota lebash ye egun new yagenew bakh ye tigrayn hizb chefechefe be eg azur techefechefe meches sew yezerawin new yemiyachidew
🙏👍👍👍
Abetu selam lehagerachen bbelom le alem.
እውነት ነው። "አፉ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ"......እህህ ነው ሌላም ምን እንላለን!!
I could not understand the words, but I feel her pain and what is happening in the sister of my country, Ethiopia, I could not hold back my tears, may peace prevail
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇸🇩🇸🇩🇸🇩🇸🇩🇸🇩
ውነትም አፉ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ ትክክለኛ አገላለፅ ነው ግን ፈጣሪ ይቅደማቸው ከነሱ ተንኮል የሱ ቅዱስ ስራ ይቅደም ለወገኖቻችን
በሚገባ የኢትዮጽያዊያንን ነባርያዊ ስሜት የማገልፅ ምርጥ ሙዚቃ🇪🇹❤️🥺
ይህ ዘፈን ለፅንፈኞቹ እና ሰላም ለማይፈልጉት ትክክለኛ መልዕክት ነው።
ጎሳዬ ተስፋዬ እድሜ እና ጤናውን ይስጥህ
Abye ahmed bicha new selam ymyflgew yeh asmesay sint sew ascherse afu kudes new migbaru lela
ጊዜውን የጠበቀ ጀግና መልክት ያለው ሙዚቃ የስልጣን ወንበር ላይ ተጎልታቹ ምስኪኑን ህዝብ ለሚያስጨርሱት ይድረስ 👈ሀገሬ ስላምሽ ናፈቀኝ💚💛❤
ዋው ዋውዋውበጣም የሚገርም ቅኔ ነው
አመሰግናለሁ ጎሳዬ በአሁኑ ሰአት የሀገራችን እውነታ ኢሄ ነው:: አርቲስት እንደዚ ሙያውን ተጠቅሞ የህዝብን ችግር ስቃይ ሲያሳይ በጣም ያኮራል:: ብዙዎቹ አርቲስቶቻችን ለሆዳቸው ያደሩ ፈሪዎች ናቸው::
ሰላም ለሀገሬ 💚💛❤️
ይህንን ሙዚቃ ፖርላማ ውስጥ ከተሰበሰቡ በህዋላ መጀመሪያ ምንም ሳያወሩ ተከፍቶላቸዉ ግጥሙን ፍሬ ሀሳቡን ቢረዱት በመለከቱት - እንዴት መልካም ነበር ።
ግሩም መልዕክት ጎሳዬ ክብረት ይስጥልን ።
betikikl betemesasay beyekiflehageru ketemewoch temarn yemilutu andu landu telat hono yetesalebet akebabi laym bitay enam ethiopiawi batekalay besilku lay linorew yemigeba musica mesel tilk ewnet yeyaze tselotm timhrtm new. abetu maren!.
🤣🤣🤣ምንም ሳይገባቸው ነበረ የ ሚያንጨበጭቡት
@@biniam2301 😂😂😂😂
ከልብኽ፡ስርተኽዋል።
Exactly said 💯
😫😫😫 ሰላም ለኢትዮጵያ ፣ ሰላም ላገሬ ልጆች፣ ሰላምና ጤና ላበሻ ዘር፣ አምላክ ይከተላችሁደ በውነት አምላክ ይብቃችሁ ይበላችሁ🙏🙏🙏❤❤❤🙏🙏🙏❤❤❤❤ እወዳችኋለሁ
ግጥም 100%
ዜማ 100%
ሎኬሽን 100%
ብቻ ሁሉም ያበደ ነው ጎስሽ ❤❤❤🙏⚽️⚽️
ህዝባች የሀዘን ሀዘን ነገር ማየት አይወድም እንጂ ይሄ ክሊፕ እንደቆይታው 1.1M ይቅርና 11M ሲያንሰው ነው❤❤❤
Wow በጣም ልብ የሚነካ ቪዲዮ ነው የሀገራችንን ሁኔታ በ 7 ደቂቃ ጎስሽ እናመሰግናለን ሰላም ለኢትዮጵያ ሰላም ለሀገራችን በቃቹ ይበለን🙏🙏🙏
እባክህ አምላኬ ሠላም ስጠን
ድምፀ መረዋው ጎሲሽ በጣም እናከብርሃለን ትክክለኛ መግለጫ ነው።
አፉ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን ከዚ ፈተና 😭😭😭😭😭አቤቱ አቤቱ ማረን
በጣም ነው ያስለቀሰኝ ፈጣሪ በምህረቱ ይጎብኘን ለገዳዎችም ፍርዱን በቶሎ ይስጣቸው
እኔንም አስለቅሶኛል 😭
ውድ ጎሳየ … ቁጭትህን.. የእውነት መንገብገብህን … የእውነት መቆርቆርህን... የእውነት ማዘንህን... ግልጥልጥ አድርጎ ያሳየ ምርጥ ስራ ነው። ለድምፅ አልባዎቹ ምስኪኖች ድምፅ ስለሆንክ እግዚአብሔር ይስጥህ።
😭😭😭😭😭
😭😭😭🇪🇹🇪🇹ታመናል🇪🇹🇪🇹
ምዕናባዊ ድንበር ህሊና አስምሮ
ያልነበረ ነገር እንዲኖር ቆፍሮ
መጥፋት ከወሰነ መጥፊያ ሰበብ ፈጥሮ
ይህ ድህነት አይደለም በጣሙን ታመናል
ለፈውስ ቸግረን እጅግ ተለክፈናል
ባልነበር ነበር የሰው ልጅ ታመመ
ያልበላውን አክኮ እከክ ተሸለመ
ዋጋ ተከፍሎባት የቆመችን ሀገር
በፆምና ፀሎት የፀናችን መንደር
አንድ ኢትዮጵያ ብለው የተሰውላትን
ሞቷን እንዳያዩ ስንት የሞቱላትን
ሙሉነቷን ረስቶ እልፍ ቦታ ገምሶ
ለታሪክ እንዳይበጅ እንደዚህ ቆራረሶ
እርስ በእርስ መፋጀት እስኪ ምን ይሉታል
ጤናችን ታውኳል ያልነበር ቆፍረን በጠና ታመናል
እብድን በሚያስቀና ልቀን አኛ አብደናል
አንድ ሆነን ኖረን ስንት ምዕት አልፎ
ሰላም ከእኛ አልፎ ለጎረቤት ተርፎ
አንድነት ዘምረን በልዩነት ፋንታ
ልባችን ተሳስሮ በአንድ እየመታ
ዛሬ እንድንጠፋበት ጥላቻን ተመኘ
ዘር ብሔር እያለ ልባችን ተሞኘ
ፈቅደን በአመጣነው ወረርሽኝ ታመስን
ቀና ካልንበት አንገታችንን ደፋን
እውነት የእውነት ታመናል
ድስት ቢገነፍል ያሉት በእኛ ሆኗል
፧
ረሳን? ኢትዮጵያን ብለው አድዋ ሲዘምቱ
ጊወርጊስን ይዘው ምንሊክ ወ ጣይቱ
ካሳ የወደቀው መቅደላ ላይ ወጥቶ
በላይ የሞተላት በገመድ ውስጥ ገብቶ
ሞታቸው ለአንድ ብሔር ከቶ መች ሆነና
ድልን ወገን መርጠው የት አበሰሩና
እኛ ግን..................
ቆፍረን ቆፍረን ወረርሽኝ ገዝተናል
ዶሮ ጭራ ጭራ በእኛ ላይ ደርሷል
አብደን ለይቶልን ጨርቃችንን ጥለናል
መድሀኒቱን ይዘን ከታቢ አጥተናል
ፀበሉ እያለ አጥማቂው ጠፍቶናል
ታ
መ
ና
ል
የቃል ኪዳን ምድርን አጅግ በድለናል
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ይህን የሚናገር ሰው ነበር የጠፍው የምርጦች ምርጥ ሙዚቃ ነው
አረ አላህዬ በቃቹ በለን የመጣብንን በላ አንሳልን እርስ በእርስ ምንዋደድ ምንተሳሰብ አድርገን ልብ ስጠን አሚን።
ቃላት የለኝም ምነው እኔም እንዳንተ ብሆንኩና ብሶቴን ባሰማህ ብዬ ተመኘሁ በጣም ሐርፍ እና ያለዉን ሀቅ የሚያሳይ ሙዚቃ ነው ወንድሜ
አፉ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ 😢😢😢
አቤቱ ጌታ ሆይ እምዪን በቃሽ በላት🤲🏾
ያአላህ ማረን በቃ በለን
ከልብ የተሰራ ከልብ የተዘፈነ ያመቱ ምርጥ ሙዚቃ ክበርንልን 🙏🥰
ከድምፅ ከግጥም የተዋጠለት ሰራ ነው በጣም ነው የማከብርህ
ለመጀመሪያ ግዜ በሙዚቃ አለቀስኩ
ልብ ሰባሪ ነው
እስቲ ማነው እንደ እኔ የልጅነት ደግነቱ ደጋግ ጎረቤቶችን እያሰብ ያአን ደግ ግዜ እየናፈቀ በፍቅር እያለቀሰ ያየው ? አሜን ማረን 🙏🏾😭🇪🇹እናመሰግናለን ጎስሽ ምርጥ ስራ ነው
አምላክህ እግዚአብሔርን የጠራህበት መንገድ አንጀት ይበላል። አንተ ሰው አንድ ቀን መንፈሳዊ መዝሙሮችን ስትዘምር እሰማለሁ። ተባረክልኝ! ለበረከት ሁንልኝ!
,ሙዚቃውን ልክ እንደአዲስ ደጋግሜ ባየው አልጠግብ አልኩ ጎስሽ ተባረክ የሀገሪቱን ሁኔታ ቅልብጭ አድርገህ አሳይተህበታል
የወሎ እውነተኛ ታረክ ነው አላህ ሰላሙን ያውርዲልን ያርብ😭😭😭😭😭
😢😢
አቦ የኛ ጀግና ስሙ በልልኝ ለነዛ ዘረኞችና ቂመኞች በሙሉ
ሰላሙን ለሀገራችን ያውርድልን በተከፋይ አክቲቨስትና ስላጣን በሰከሩ ፖለቲከኞች ከመነዳት እግዛብሄር ይጠብቀን 🙏🏽
አሜንንንንን ማረን አውጣን ከዚህ መዓት
ጎሳዬ ትለያለህ ወቅቱን ያሳየህን እንዳልከው እግዚሀብሄር ለኢትዮጵያ ሰላሙን ያምጣልን
በተለያየ ሚዲአውች ዘፍኞችን በጣም እየወቀስኩ ነበር የሀገር ዋልታ የአማራ ህዝብ ይህሁሉመከራን እያለፈባለበት አንድእኳን ዘፍኝ ጉሳዬ እናመሰግናለን ታሪኩባባ ብታካትት ለኛፈልምም ዘፈን የተደጋገፎናቸው
የዚህ ሙዚቃን በአውዲኦ ልብ አላልኩትም ነበር። ለካ ይሄን ያህል መልክት ይዞ ውሏል። ተባረክ ትችላለህ ከማለት ውጭ አቅም የሌለኝ ስለሆነ ብቻ ተባረክ ሆነ መልሴ ጎስሽ❤🙏🙏
ዳሬክተር ካሜራማን ተዋንያን የተዋጣ ስራ። የተዋጣ ግጥም ፐ❤❤❤❤🙏
አሁን ላለንበት ሁኔታ የሚሆን ምርጥ 📽️video
ጎሳዬ ዛሬ ገና ቆንጆ clip ሰራህ በጣም ጎበዝ ድምፃዊ ነህ clip (video )ላይ ግን ምንም አያምረኝም ነበር አክትህ ለማንኛዉም ዛሬ ደስ ብሎኛል አመሰግናለሁ ጎስሽ
አቤቱ ይቅር በለን :: እግዚአብሔር ምህረቱን ይላክልን
Ere zima gn endit newu yemtal betam semchowu altegbm aleni 😘😘😘👍👍👍
ለወቅቱ የሚሆን የሚመጥን ስራ ነው ዘፈኑ በቪዲዮ ድጋሚ መሰራቱ ይበልጥ እንድንወደው አድርጎናል ምርጥ እይታ፣ ምርጥ ምስል ባጠቃላይ ምርጥ ስራ ነው ጎስሽ እግዚአብሔር አገራችን ሰላም እንዲያደርጋት የሁላችንም ምኞት ነው
ሰላም ይስጠን!!
Abet gers hoy. Ere direslin. Eee hizbih aleke. 😭😭😭😭😭🙏🏼
Wow This song is for all Ethiopians, the message teaches us well ,God bless Ethiopia and its people.💚💛❤️
አፉ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ:: የኢትዮጵያ መሪ ነን ባዮች እውነታ:: እግዚአብሔር ይቅር ይበላቸው::
Musicውን ብሰማው አልጠግበውም ነበር😘ይባስ ክሊፑን ሳይ ደግሞ😢ሀገሬ አሁን ያለችበት ይህ ነው😭😭ጎሲዬ respect🙏
fetari selam yesten 🙏🙏🙏
አሜን
ፍቅር💚 ሰላም 💛ደስታ ❤ ለሃገራችን💚💛❤💚💛❤
በጣም ገራሚ ስራ ነው ሙዚቃ ብቻ ሳይሆን true documentary ነው🙏🙏🙏
ጎሳየ ተስፋየ ክበርልን እናመሰግናለን ከ ሰሜን ወሎ ህዝብ እዉነት ያለንበትን ሁኔታ ነዉ ፍንትዉ አድርገህ የገለፅክልን 🙏
ኣሜን ሰላም የውርደልኩም ብሓፈሻ ንኩልና ጎስ ሓወይ🇪🇷🤍🇪🇹
Tebarekkkk Abo. Des yemil Sera new Goseshhhhhhhh
ሰላም ለሁሉ 🕌💒🕌💒🕌💒
በጣም ያሳዝናል ኦ ኣምላኬ ማረን
🙌🙌🤲🏻🤲🏻🤲🏻🇪🇷🇪🇹🌺♥️🌺♥️
ነዘረኝ ትችላለህ ሠላምሽ ይመለስ ጦቢያየ
የእውነት እንባዪን መቆጣጠር አቃተኝ😭😭...ፈጣሪ ሁላችንም ያስበን 🙏🙏
ጎስሽ በጣም ቆንጆ ዘፈን ድምፅህ ናፍቆኝ ነበር
እግዚአብሔር ያክብርህ ከፍም ያድርግህ። ድሮም እወድሃለሁ አሁንም እወድሃለሁ መቼም እወድሃለሁ ገናም እወድሃለሁ እስከዓለም ፍፃሜ እወድሃለሁ። ፈጣሪ ይባርክህ። ከፊትህ ይቅደም።
ጅግና ነህ
የወለጋን ታሪክ በአንድ ላይ አሰቀመጥህው ዘፈኑን ስሰማ እነዛ የታረዱት ወገኖቸ ናችው የታዩኝ እናመሰግናል ለማንም የማታጎበድድ ብርቱው ወንድማችን ጎሳየ🙏✔️
እናንተ ትግሬዎችን በ ሂወት ያቃጠላችሁስ
@@biniam2301 እኔ ጥርት ያልሁ አማራ ነኝ ከገዳይ ጋላ ወያኔ ትግሬ ይሻለኛል
@@ቴወድሮስበዛብህ If you want my honesty እኛ ትግሬዎች ደግሞ 10000% ከናንተ ምርጥ ኦሮሞዎች ይሻሉናል
@@biniam2301 ትግሬ አይደለህም ተባኖበሀል ጋላው😃
ጎስሽ ምንም ቃል የለኝም ወቅቱንና ጊዜውን የሚገልፅ ስራ 👏👏👏👏👏
አሜን እግዚአብሔር ሰላሙን ያምጣልን ለሀገራችን ሰላም ለንፁሃን
እውነት ነው እግዚአብሔር እሱ በቃችሁ ይበለን ከበደን እውነት ከበደን ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም
ጎስዬ የኔ አንደኛ በፊትም ይህ ዘፈን ውስጤን ይነካው ነበር አውን ደሞ ይበልጥ ያለንበትን ውኔታ ስለ ሚገልፅ በ እንባ ነው የጨረስኩት (ሰላም ይስጠን እግዜር ገናና ከጋረደን ጥቁር ደመና እግዚኦ ማረን ይቅር በለን )
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤ጎሳዬ ቃል የለኝም ግን በጣምምምም ምርጥ ስራ ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤ሰምቼ የማልጠግበው ❤❤❤
ሰላም ለሀገራችን ለኢትዮጵያ 💚💛❤️
Ewnte nwe Gosaye Tesfay Ethiopiawe nwe mengest yemetale yehedale hezbun yalkedawe Gosaye nwe demetsken selasemakeln kelbachin enamsgenalen
💔💔💔🥀🥀🥀እዋይጉ እንታይ ኾን" በዲልና አንታ ፈጣሪ ዓለም??በደልና ይቅረ በለልና 🙏🏽🙏🏽🙏🏽🇪🇷🥲
👍🙏
fetari ytebkih ,ybarkihm ewnet nw 1 enihun
ይብቃቹ በለን ፈጣሪዬ እምባችን ደረቀ እኮ ፈጣሪ አምላኬ ፈተናችን በዛ የመሃን ምጥ ሆነብን የሀገራችን ነገር።
ከምንም ከማንም በላይ ሠላም የህይወት አኗኗርን አሰመሰካሪ ሰለዚህ ሠላም ፣ ሠላም ለሁሉም 🙏🙏🙏🙏🙏
የምር ወንድማችን ፈጣሪ እድሜ ይስጥክ ተባረክ😔😔😔😔
እግዚአብሔር ይባርክህ ወንድሜ
ዘፈኑን መጀመርያም እወደው ነበር አሁን ደሞ ይበልጥ ወደድኩት ፈጣሪ ሀገራችንን ሰላም ያርጋት🙏🙏🙏
በጣም የምኖድህ የምናከብርህ የኛ ጀግና ጎሳዬ ተስፋዬ ዝቅ ስንል ዝቅ ብለህልናልና ከፍ በልልን ስናዝን አዝነሀልና ደስታን ይስጥልን ያለዉን ነገር እንዲህ ግልጽ አድርገህ አሳይተኸናል
እሪፍ ወቅቱን የጠበቀ ምርጥ ሙዝቃ ነው ጎሳዬ ሰላም ለሀገራችን💚💛❤
"አፉ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ....." የሀገሬ ጠላቶች እንዲህ አይነቶቹ ናቸው!
አንቃን ይብቃችሁ በለን የፍቅር አምላክ ጌታ
አንቃን ቅድስቷን ምድር ሰላም አውርሳት ደስታ
አሜን 🙏