ደጃፍ የእኔን ፍላጎት እየተከተለ ቼክ የሚል እየመሰለኝ ነው ክበርልኝ ዳዊትዪ come onnnnn ዶ/ር አለማየሁ come onnnn ትዉልድን እኮ ወደ ማንበብ ወደ ሀገሩ የመለሰ down to earth kind of guy so humble and genious at the same time....በጣም ነዉ የምወደዉ የማከብረዉ ሁሉንም መፀሀፎቹን አንብብያለሁ ቀጥሎ የሚፅፈዉን በጉጉት የምጠብቅ ነኝ❤❤❤❤
You have shown Ethiopian experts and the public what a podcast is. You have demonstrated the efficiency of wisdom explored by sages. Dawit, I have great respect and gratitude for highlighting Thursday's holy day with your discussion.
He's one of the best minds of our time. His narration and storytelling, combined with his intellectual caliber, are limitless. He's one of my favorite intellectual of our time.
Woo absolutely great thank you so much to define my orthodox religion I’m very fascinated when I listen, thanks again my lord Jesus Christ blessed you and your vision 🙏🙏🙏
እመጓ ደስ እያለኝ ቦታው ያለሁ እሲኪመስለኝ ድረስ ተመስጨ ያነበብኩት መፅሐፍ ነው በእሱ ስበብ መንዝ ሞላሌ ሂጀ እመጓን ኡራኤልን ዘብር ገብርኤልን እንዲሁም ብዙ ገዳማትን አየሁ በጣም ደስ የሚል ቦታ ነው መፅሐፍ ላይ ያሉትን እሟሆይን ለማየት ኡራኤል ሂጀ ግን ፍቃዱ ስላልሆነ ሳላያቸው መጠሁ. ብቻ ፈጣሪ አብዝቶ ይባርክህ ፈጣሪ ካለ ጨጭሆ መዳኔአለምን ባየው ደስ ይለኛል ❤
እኔ እራሱ
ፈጣሪ ይቀበልሽ
❤በጣም
የኔም ምኞት ነው እግዚአብሔር ያብቃን
እኔ ደግሞ እመጓን እንዳነበብኩ ወደ እናት ቤተክርሰቲያኔ ወደ ኦርቶዶክስ እንድመለስ አድርጎኛል ከዚ በፊትም አንዴ ተናግሬአለሁ ሁሉንም መጽሀፎች አንብቤአለሁ ብዙ ነገር ተረድቻለሁ ።
@@alemkebede5848 እግዚአብሔር ይመስገን ደስ ይላል :: በቤቱ ያፅናሽ/ህ
ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ በጣም የሚገርሙ መፃህፍቶች አሉህ ሁሉንም መፃህፎች አንብቤአቸዋለሁ ከሁሉም በጣም የምወደው እመጓን በነገራችን ላይ እመጓ ልቦለድ ብቻ አይደለም እራሱን የቻለ የታሪክ መዝገብ ነው በአጋጣሚ ሞላሌ ሄጄ የሞላሌ ከተማ ነዋሪዎች ምናሉኝ መሰላችሁ ዶ/ር እመጓ ባይፅፍት ኖሮ እመጓ ም ሞላሌ አትታወቅም እመጓ ቅዱስ ኡራኤል ለመምጣት ሞላሌን ከተማ ሳይረግጥ አያልፍም በዚህም ከተማዋ እያደገች መጣች አሉኝ እና በጣም የሚገርም መፅሀፍ ነው እናመሰግናለን
ዴቭ ጫጫታ ከሞላበት UA-cam ስላወጣኸን ተባረክ:: እየወጣህበት ያለው ማማ በጣም እየራቀ ሄደ; ብቻ ፈጣሪም ተጨምሮበት እዛው ከፍታ ላይ ይዘኸን እንድትቆይ ምኞቴ ነው :: የዶ/ር እርጋታ ; አገላለጸ wow ትልቅ ክብር ::
ዳዊት ዛሬ ከባድ እንግዳ ነው ይዘህ የተከሰትክው። በጣም ቆንጆ ቆይታ ነበር እኔን በጣም የገረመኝ ደን ውስጥ ስላሉት ነፍሳት እና አውፋት የገለፀበት ነገር አስገርሞኝ ነው ። እኔ ኒሮዬ አሜሪካ ነው ። የምኖርበት ከተማ በጣም ብዙ ዛፎች ያሉበት ነው ።ከተማው በጣም ይንከባከባቸዋል የተበላሹ ዛፎች ይቆረጣሉ የኔ ጎረቤት የሆነች እቤቱ በግፍ ላይ ያለው ዛፍ ስለታመመ የ ከተማችን ሠራተኞች መተው ቆርጠውት ይሄዳሉ ። ሌላ አምጥትው ይተክላሉ ብላ ስትጠብቅ ቆዩባት ወዲያው ለ ከተማችን ባለስልጣናት ደብዳቤ በ ፃፈች በአስቸካይ አዲስ ዛፍ እንዱተክሉ የሰጠችው ምክንያትሁሌም የሚገርመኝ ነው ። ዛፉ በመቆረጡ አንደኛ በዛፉ ላይ ይኖሩ የነበሩ የተላያዩ አእዋፋት እንስሳት የሚኖርበት ስለነበር አሁን የት እንደደረሰ ስለ ማይታወቅ እና በ አስቸካይ ወዱ ስራቸው እንዲመለሱ ሁለተኛ ዛፉ በመቆረጠ ምክንያት ቤቴ ለ ፀሐይ ስለተጋለጠ ለአየር ማቀዝቀዣ የጥቅምበት የ ኤሌትሪክ ቢሌ ይጨምራል ብላ ምክንያት ፍቅርን በአስቸካይ አዲስ ዛፍ አምጥተው ተከሉላት።
አንዳንድ የተባረኩ ሰዎች ከራሳቸው አልፈው ለሌላው ብርሃን ናቸው ልክ እንደ ዶ/ር ዓለማየሁ🙏🏻
ከተጠያቂው በላይ ጠያቂው አስደምሞኛል:: በዝህ ዘመን የዚህን ያህል በሳል: አዳማጭ እና በዚህ ልክ ተዘጋጅቶ የሚጠይቅ ባለሞያ ማግኘት ከባድ ነው:: ሁለታችሁም ክበሩልኝ::
10ኛው comment አድራጊ ነኝ!!ዳዊት ለዘመናት ተዘጋጅተህ ጨርሰህ ዝም በለህ እኛን ለማስደመም መጥተሀልና እናመሠግንሀለን🙏🙏
እመጓ ለእኔ የሚናፍቀኝ መጽሃፍ ነው እመጓ ቆላ እና እመጓ ደጋ ቅዱስ ኡራኤልን ዘብር ገብርኤልን እንዲሁም ገዳማትን እሟሆይን ሳስብ አብሬ የነበርኩ ያህል ይሰማኛል፣ ዶ/ር ጸጋውን ያብዛልህ
እመጓ ፤ ዝጎራ ፤ መርበብት ከአንድ ትልቅ ክላሲክ ፊልም ያልተናነሰ ስክሪፕት እና የታሪክ ፍሰት ያላቸው መጽሃፍት ናችው፡፡ ይሄ ኮመንቴ ይታይ አይታይ እርግጠኛ አይደለሁም ነገር ግን መጽሃፎቹን ካነበብኩባቸው ጊዜያት ጀምሮ ዘወትር ውስጤን ሲያብሰለስለው ኖሯል ስለዚህ ይሄን ለመናገር ደሞ ከዚ የተሻለ እድል አይኖረኝም፡፡ ስለዚህ እባካችሁ በተቻለ መጠን በ ጥሩ ፕሮዳክሽን የመጸሃፉን ግሬስ በጠበቀ መልኩ ወደ ፊልም ቢቀየሩ ለሃገርም ለትውልድም ትልቅ ሃብት እናስቀምጣለን፡፡ 🥰😍🙏🙏🙏
ተባረኩ
Netflex lay film download eyarek temelket yihe ante kemtasbew belay nw bro😂
@@Xcg1212 እውነት ነው ወንድሜ በጣም ከማስበው በላይ እንደሆነ እረዳለሁ ግን የሚያሳስበኝ ነገር ምን ያህል ሰው መጽሃፍ ያነባል? ምን ያህሉስ አንብቦ ይረዳል? ስለዚህ መንፈሳዊ ይዘቱን እና የቤተክርስቲያናችንን ህግ እና ስርዓት በጠበቀ መልኩ ቢሰራ ለማለት ያክል ነው፡፡ ስለ መልካም ምክርህ አመሰግናለሁ፡፡
ያንትን መፀሀፍ ሶስቱንም መፀሀፍ በትረካ በአቢሲኒያ ሬድዬ በዋሽንግተን ዲስ ስሰማ ከአለማዊ መፀሀፍ ዝባዝንኬ ጋር ተፋታው በጣም የሚገርመው ባብዛኛው ፀሀፊኖች በሀገራችን ሌላው የፃፈውን አንበው ሲሆን የሚፅፉት ያንተ ግን የሚለየው የመስክ ፀሀፊ መሆንነው መሬት ወርደህ ገደሉንም ተራራውንም እያቡዋጠጥክ ጥናት ማረግ ነው እንዲ አይነት ነገር የምታየው በውጭ ፀሀፊዋች ላይ ነው:: እንዲ አይነት መፀሀፎችን ብፅፍ ያንተ መክሊትህ ነው የኔን ህይወት በትልቁ ለውጦታል ስለ አለም ያለኝን አመለካከት እና ስለሀገሬ ፀጋን ተረድቼበታለሁ::
ይህ ሰው ዓለም አየሁ ነው።ለዓለም የሚሆን እውቀት፣የሃይማኖት መረዳት፣ፍቅር፣አክባሪነት፣ያቀደውን መፈፀም የሚችል፣በአንድ ነገር ላይ ማተኮር ከግብ ማድረስ ደግሞ የስነ ጽሑፍ ሰው የሚገርም ስብዕና ሁሉም መልካም ነገር ይገባዋል!
ምርጥ እንግዳ ይዘህልን ስለመጣህ እናመሰግናለን! እመጓ ነብስ ያለዉ መፅሐፍ ነዉ በመፅሃፉ ላይ ያረፉት እያንዳንዱ ፅሁፍ በምክንያት የሰፈረ ነዉ። እመጓ ለመሄድ ሁሌ እናፍቃለሁ። ዶ/ር አለማየሁ ዋሴን በክብር አመሰግነዋለሁ 🙏
በእውነት ዛሬ ደስ አለኝ ሳልጀምረው ኮሜንት ላይ አመስግን አለኝ ውስጤ ዳዋ አመሰግናለሁ ዶ/ር አከብሮታለሁ እጅግ በጣም ደግሞ አመሰግንዎታለሁ እርሶን ማዳመጥ መታደል ነው እንኳን የእርሶ ዘመን ሰው ሆንኩ🙏
ደጃፍ የእኔን ፍላጎት እየተከተለ ቼክ የሚል እየመሰለኝ ነው ክበርልኝ ዳዊትዪ come onnnnn ዶ/ር አለማየሁ come onnnn ትዉልድን እኮ ወደ ማንበብ ወደ ሀገሩ የመለሰ down to earth kind of guy so humble and genious at the same time....በጣም ነዉ የምወደዉ የማከብረዉ ሁሉንም መፀሀፎቹን አንብብያለሁ ቀጥሎ የሚፅፈዉን በጉጉት የምጠብቅ ነኝ❤❤❤❤
ኦ ዮርዲዬ
እመጓ ለማየት በጣም ነው የምጓጓው መጽሐፉን አንብቤ ስጨርስ ወዲያው ነበር የተመኘሁት ፈጣሪ እንዲያሳካልኝ እጸልያለሁ ደራሲ አለማየሁ ዋሴን እጅግ አድርገን እናመሰግናለን ፀጋውን ያብዛልህ 🙏🙏🙏
ግሩም በእውቀት ላይ የተመሠረተ ሐሳብ ነው።ዶ/ር መሬት ላይ ከምቀናባቸው ሰዎች አንዱ ናቸው።ትልቅ ክብር አለኝ በእውነት!የሰው ልጅ መልአካዊ እና እንስሳዊ ጠባይ አለው።ሁለቱ ሲዋሐዱልህ እንደ ዶ/ር ሰው ትሆናለህ!መስተጋብርሕ ከድሐና ከሐብታም ከገጠርና ከከተሜ ብቻ ሳይሆን ከነፍስህና ከስጋህ ጋርም መስተጋብር አለህ!
ዕድሜ ይስጥልን በእውነት
የአንድ ሰዓት በላይ ቃለ-መጠይቅ የ10 ደቂቃን ተቀምጦ የማድመጥ ስሜትን ያክል የፈጠረብኝ ፕሮግራም ነው ። ይህ በተወሰኑ ፕሮግራሞች ወቅት በእኔ ላይ የማስተውለው መመሠጥ ስለሆነ በጣም ደስ ብሎኛል ለዚህ የጠያቂው አጠያየቅ ወሳኝ ስለነበር አመሠግናለሁ የሳምንት ሰው ይበለን።
እኔም እንደዛ ሳላስበው ነው ያለቀብኝ 😢
መፅሐፍ የማንበብ ፍላጎቴን የጨመረልኝ ድንቅ መፅሐፍ እመጓ! ይህን የመሳሰሉ መፅሐፎችህን ስላበረከቱልን ከልብ ማመስገን እፈልጋለሁ! ዳዊት ጎበዝ ጠያቂና አድማጭ ነህ, በአንተ አቀራረብ የእኔንም የማድመጥ አቅም እየጨመርክ ሳይሰለቸን ከአንድ ሰዓት በላይ እንድቆይ ስለምታረግ ችሎታህን ማድነቅ እፈልጋለሁ! ክፍል ሁለትን በጉጉት እጠብቃለሁ!
ዴቫ ልታሳብደን ነው በቃ,,,,,እድሜ ይስጥህ 😊😊😊🙏🙏
ዴቭ የዶ/ር ድምፅ አንሳል እባክህን !! ዶክተር በጣም ነው የማከብርህ እግዚአብሔር አምላክ እድሜ ከጤናጋር ያድልህ ። ዴቭ ግን በየግዜው ላንተ ያለኝ ክብር እና ቦታ እየጨመረ ነው
ፈጣሪ አብዝቶ ይባርክህ!!!
ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ በጣም ነው የምወዶትና የማከብሮት አብዛኛው መፅሀፍቶትን አንብቤያለሁ ፈጣሪ እድሜና ጤና ይስጦት ❤
በሕይወት ዘመኔ በፍጹም የማልረሳው ሰው ቢኖር ታላቁ ሰው ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ ነው እነ እመጓ እነ ዝጓራን የመሳሰሉ ምርጥ እና መሳጭ መፅሐፎችን ፅፈህ ስላቀረብክልን እጅግ በጣም እናመሰግናለን እድሜና ጤና ይስጥልን🙏🙏🙏
የተረጋጋች እና አሰላሳይ ነብስ ያለው ሰው ነው! በድረሰቶቹ እንደሳልኩት ሆኖ ስላገኘውት ደስ ብሎኛል! እድሜና ጤና ይስጥልኝ!❤
እግዚአብሔር ይስጥልን መጽሐፎቹ ሁሉም ቆንጆ ናቸው
ዴቭ ግን በየግዜው ላንተ ያለኝ ክብር እና ቦታ እየጨመረ ነው 💚💛❤
ፈጣሪ አብዝቶ ይባርክህ!!!
ሰላም ተመኘሁላችሁ "ደጃፍ ኘሮግራሙ እያሳሰበኝ መጣ"አገራችን ላይ ካሉት ለሀገችንም ለማህበረሰቡ ጥሩ አርአያ የሚሆኑ ግለሰቦች እንደ አለመታደል ሆኖ ጥቂቶች ናቸው "ይሄ ኘሮግም ከተጀመረበት እለት አንስቶ እኔ ጆሮዬን የምሰጣቸው ግለሰቦች ነው እየቀረቡ ያሉት በዚህም ደስተኛ ነኝ የኔ ስጋት ምናልባት እንቁ የሆኑት ተጋብዘው ካዳመጥናቸው በሀላ የኘሮግራሙን ሚዛን የማይደፍ አቦ በፈጠረህ አታምጣብን ባይሆንም አስቸግረህ ደጋግመህ ጋብዛቸው ይሄ የኔ ሀሳብ ነዉ "ቸር ተመኘሁ ላገሬ (ኢትዮጵያ )
እጅግ በጣም እናመሰግናለን ዶ/ር አለማየሁ ዋሴን እንግዳ አድርገህ ስላቀረብክልን ❤
ዶ/ር የፃፋቸውን መጸሀፍት ልብወለድ ሳይሆኑ የምርምር ውጤት እና እውነታ ናቸው ብዬ አምናለሁ ከቃለ ምልልሱም በጣም የወደድኩት የፕሮፊሰሩ እና የሱ ግነኙነት።
የምታቀርባቸው እንግዶች በጣም አስተማሪ ናቸው እናመሰግናለን።
ዶ/ር አለማየው ዋሴ በጣም የምውድህ የማከብርህ እግዚአብሔር አምላክ እድሜ ከጤናጋር ያድልህ።ሚትራሊዮን ላይ እንዳለው ነቢልናክብረበአል አይነት ሰውን እግዚአብሔር አምላክ ለሀገራችን ያብዛልን አመሰግናለሁ ።ዳዊት ስላቀረብክልን በጣም አመሰግናለሁ
ዳዊት በጣም ነው የማከብርህ የምታቀርባቸው ሰዎች የምጠይቀው አጠያየቅ አሰማምክ ሲናገሩ ተባረክ
እናት ዓለማየሁ ብላ ስም አወጣች ስም ከግብር ጋር ሲስማማ አየን የደኖችን ዓለም በቤተ ክርስቲያን ከኋላው እየተከተልን እንድንዋኝ አደረገን!
እግዚአብሔር ይስጥልን
በጣም የማደንቀው የማከብረው ፀሀፊ ነው እና ከፁሁፎቹ መሃል በጣም ከሳበኝ ኢትዮጲያዊነትን እንዴት እንዳሳየኝ እምነት ማመንን ታማኝነት መልካም ስብዕናን እውነት ለመናገር (((እግዚአብሔር))) ጥበቡን ያብዛልክ ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ ዶ/ር መባል በጣም ነው የሚያንስ👏👏👏
Dejaf is the first useful podcast in ethiopia keep it up and thank you david 🙏😍
ዴቭ የዶ/ር ድምፅ አንሳል እባክህን?
የዶክተር ድምፅ ተፈጥሯዊ ነው!
ኖ አይደለም
@@DagimWorku-dy5px ለሌሎች ሚዲያ የሰጡትን ቃለ መጠይቅ መመልከት ጥሩ ነው።
ዶክተር በጣም ነው የማከብሮት በርስ መፅሐፍ ምክንያት ጣራዉ ክፍት ዎና ዝናብ የማይገባበትን አቡነ አሮን ገዳምን አይቻለሁ አመሰግናለሁ
ዴቭ ቃላት የለኝም ከደረጄ ሀይሌ ቀጥሌ ምርጥ ጠያቂ ትችላለህ 👌👌👌👍
በጣም አመሠግናለሁ ለጋዜጠኛውም ለዶክተር አለማየሁ ዋሴም
በእውነት ይህን ውይይት ከሰማሁ በኋላ በቀጥታ ወደ ፀሎት ነው የሄድኩት እግዚአብሔር እንዲረዳን እኛም እንድናስተውል
ዶክተርን ከማክበር በላይ በጣም እወደዋለሁ እርሱን በማቅረብህ ደጃፍ ሚድያን ጉም ውስጥ ከተኸዋል ዴቭ በርታ አንደኛ ተናፋቂ ሆናለች ሀሙሲት ደጃፍ።
በጣም የሚገርም ፕሮግራም፤ ሁለታችሁንም በጣም አመሰግናለሁ🙏
በእውነት በልቤ ከበረከት በኋላ ቢያቀርበው ብዬ ሳስብ ነበር 👌💙!
እናመሰግናለን!!
ምርጥ ደራሢ ነው። በሌላ መፅሀፍት እንጠብቀዋለን። አቤት ትህትና!!!
ሀገራችን ላይ “ፓድካስት” እያሉ ለሚሞላፈጡ ቲክቶከሮች ትልቅ ትምህርት ነው ዴቭ 🙌💯❤️❤️❤️❤️❤️ እናመሰግናለን ✅
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ውለታ እኮ ብዙ ነው እግዚአብሔር ይመስገን
በጣም አሪፍ ፕሮግራም ነው ቀጥሉበት ዶ/ር አለማየሁ ለሀገር በብዙ የሚጠቅሙ ሰው ናቸው
በጣም ቆንጆ ቆይታ ነው የነበራቹህ።ክፍል ሁለትን በጉጉት እንጠብቃለን።
ዶ/ር አለማየዉ ዋሴ እሸቴ
እጂግ የምወደዉ የማከብረዉ
በጣም ሙህር ፈራ እግዚአቢሄር
ያለዉ ሰዉ ነዉ የቢሄር ጥላቻ የሌለበት ትዉልድን ለማዳን ከልቡ
የሚጥር ሰዉ ነዉ ፈጣሪ እረጂም እድሜ ጤና ይስጥህ በግሌ ብዙነገር ያወኩብህ ሰዉነህ
እጂግ ስለምወዳቸዉ አባት
ስለክቡር ዶ/ር አለማየዉ ስመኝ ባይህ ቺቦ በሚለዉ መፅሀፍህ ላይ
ስለሳቸዉ በመፃፍህ በጣም አመሰግናለዉ🙏🙏🙏
እናመሰግናለን ዶክተር !!! እመጓ ልብወለድ አይደለም " ድንቅና ብርቅ የሆነ አለም በቃኝ የሚያስብል የውድ ቤተ ክርስቲያናችን ውድ ቅርስ የሆነ መፅሀፍ ነው!!! እድሜና ጤና ይስጥልን !!!
ገና ሳልጨርሰው ክፍል 2 ናፈቀኝ.... thank you dawit for inviting this precious mindful guest
የስታተስቲካል ሶፍትዌርዋ ነገር ሰበዝን ሳነብ በጣም የገረመኝና ያሳቀኝ ነገር ነበር ጋዜጠኛው በመጠየቅህ ደስ አመሠግናለሁ
ዶ/ር ሁሌም በቤታችን ተወዳጅ መምህራችን ነው ሁሉንም መጻህፍቶች ማንበብ ችለናል በርታልን ። በማህበረ ቅዱሳን በሚዘጋጅ ሐዊረ ህይወት አቅርበውህ የሚያስተላልፉቸው መልዕክት ሚደንቅ ነው 🙏🙏🙏
ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ ከብዙዎቹ ጥቂቶችን መጸሐፍ አንብባለሁ በጣም መሳጭ አእምሮ የሚያድስ መጽሐፍ ነዉ ያሉክ በጣም ነዉ የምወድህ የማከብርህ እረጅም እድሜ ተመኘሁ ❤🙏❤️
ዶር አለማየሁ ደስስስ እሚሉ ንጥር አዋቂ ናቸው ። ከዶር ተወልዲ ጋ የመስክ ጉዞ አድርጌ አውቃለሁ ። ከብዙ ሰው ጋ ተጉዤ ባውቅም ከሳቸው ጋ የነበረው ጉዞ በህይወቴ እማልረሳው ስንቅ ሆኖኛል ።
ዴቨ እንደሁሌው አርኪ ቆይታ ነው 💚💛❤️
በጣም ደስ ፕሮግራም ነበር ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ በናዝሬት ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤ/ክ አይቻቸዉ ነበር የምሁር ጥግ በእነሱ ነዉ ያየሁት ትህትና እምነት ፅናት እዉቀት ... ከነሱ ምክር አጥብቀዉ የመከሩን መጽሐፍ አንብቡ ሙሉ ሰዉ ትሆናላችሁ ብለዉ ነበር በእዉነት እግዚአብሔር ያክብርልን ይህን የመሰሉ እንቁ ሰዉ ስላቀረብክልን ከልብ እናመስግናለን🙏። እመጓ የሚለዉ መጽሐፍታቸዉ በጣም የምወደዉ መጽሐፍ ነዉ ሳናብ ከእናቴ ተደብቄ ስራ ትቼ ነበር በጣም ትልቅ ትምህርት ነዉ ያገኘሁበት በእዉነት ያንን እመጓ ል ኡራኤል ለሜሄድ ያብቃኝ ፈጣሪዬን ሁሌም ነዉ የምለምነዉ በእዉነት እግዚአብሔር ሁላችሁንም ይባርካችሁ ይጠብቃችሁ❤❤❤
የምወደው የማከብርው የኔ ጠቢብ ዶ/ር አለማየው ዋሴ ❤
ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ በጣም አመሠግናለሁ ለነዚ መፅሀፎችክ ሁሉንም አንብቤአቸዋለሁ እና የእውነተኛ ታሪክ ናቸው ብዬ ተቀብዬዋለሁ በራሴ
መፀሀፎችን በሙሉ ከ10 ግዜ በላይ ደጋግሜ አንቢያለሁ በጣም ነው የማከብር ዶክተር እድሜ ጤና ይስጥህ
ምርጥ ሰዎችን ነው የምታቀርበው 1ኛ ነህ
በእውነቱ ዛሬ ታላቅ ሰው ነው ያቀረብክልን ለምን Subscribe እንዳደረኩ አረጋግጠክልኛል ቀጥልበት👏
ሚገርም መጽሐፍ ነው እራሴን በቦታው እና ስለሀገሬ ኢትዮጵያ ላይ የበለጠ መረጃነው የሰጠኝ እሰከማየው በጣም ጓጉቸለሁኝ😍💚💚💛💛❤❤🙏🙏እግዚአብሔር ያክብርልኝ ዶክተር አለማየሁ ዋሴ😍🙏
እግዚአብሔር ይስጥልን❤❤❤ ይሄን የመሰለ የቃል_ኪዳን ቦታ የተባረከ እንድረግጥ ምክንያት የሆነኝ መፀሀፍ ነው ። እጀግ ክብር አለኝ ለርሰዎ ❤❤❤ ከአንድም 3 ጊዜ ቦታውን እረግጫለው ሁሉ ነገር ሚስጥር ነው ተአምር ነው ።
You have shown Ethiopian experts and the public what a podcast is. You have demonstrated the efficiency of wisdom explored by sages. Dawit, I have great respect and gratitude for highlighting Thursday's holy day with your discussion.
ዶ/ር እናመሰግናለን እመጓ ዝጎራ መርበ ብት ሰበዝ ሜትራሊዮን ሁሉንም አነበብኳቸው ገራሚ ነው!ካንተ ብዙ እንጠብቃለን!
He's one of the best minds of our time. His narration and storytelling, combined with his intellectual caliber, are limitless. He's one of my favorite intellectual of our time.
በጣም ምርጥ ደራሢ ዝና ጩኧት የማይወድ ምርጥ ማንነት ያለው እድሜና ጤናን ይሥጥህ እንወድሃለን ፃፍልን ዴቭ አንተንም እናመሠግናለን ሠው የሆኑ ሠዎችን ሥለምትጋብዝልን
Dr. Alemayew Bahirdar University astemirognal, betam migerim ena influential memihir neber!!!!!!
Nurilin ......
Woo absolutely great thank you so much to define my orthodox religion I’m very fascinated when I listen, thanks again my lord Jesus Christ blessed you and your vision 🙏🙏🙏
The best podcast ever thanks alot
ደግሞ ዓለማችንን ልንቀጭ ነው!
ዳዊቴ እናመሰግናለን
እግዚአብሔር አምላክ ይመስገን እመጓ ቦታውን ተሳልሜ እማሆይንም አግኝቼ አውርቻቸው ነበር በእውነቱ እድለኛ እንደሆንኩ ይሰማኛል እግዚአብሔር ይመስገን
ዶ/ር በቅርብ እርቀት ሁኜ አውቀዋለሁ መቼም ወደር የማይገኝለት የዘመናችን ፍጡር ነው ።የስጋንና የነፍስን ነገር አጣምሮ የያዘ ሰው ነው ዴቭ እመነኝ ብዙ አትርፈህበታል
ሚገርም ሰው ነው አለማየሁ ዝጎራ♥♥
ይገርማል አጋጣሚ ስገባ ዶ/ር አለማየው ዋሴን ሳየው በደስታ ልቤ መታ ለቤቱም አዲስ ነኝ
እንደ አጋጣሚ ሆኖ እመጓ፣ዝጎራ፣ሰበዝ፣መርበብት፣ሜትራሊዮን ችቦ አንብቢያቸዋለሁ እናም ሚገራርሙ መፅሐፎችን አበርክቶልናል እናከብረዋለን እንወደዋለን እጁ ይባረክ ጠያቂውም ክበርልን የኔን ጥያቄ በሙሉ ነው የጠየክልኝ ቀጣይ ምን መፅሐፍ እንደሚያበረክትልን ብጠይቀው ቆንጆ ነው በተረፈ ክፍል 2 እንጠብቃለን
ዶ/ር እነዚህን የመሰሉ መጽሀፎች ስለአበረከትክልን እናመሰግናለን።
እኔ በፍጹም የዶ/ር መጽሀፍት ልብ ወለድ ናቸው ብዬ አላምንም ለምን በቤተክርስቲያን መዛግብት , መፃህፍት እንዲሁም ታሪክ ተሰንደው የተቀመጡ በመሆኑ ነው
The only podcast I have watched in youtube...keep it up!
በስመአብ! ሐሙስ የቀን ቅዱስ ማለት ይሄኔ ነው:: 🤩
ምርጥ አሠላሳይ በምርጥ ጠያቂ:: 🙏🏽🤩
መምህሬ እንኳን በሰላም መጣህ ::
የ ዶ/ር መፅሀፎች በሙሉ ልባለድ በፋፁም አይደሉም ❤it is based on true story
አሁን የሚያወሩት እራሱ ዶክተር አለማየሁ ሌላ መፅሀፍ ነው ለእርሶ ያለኝ ክብር እንዲቀጥል እና እንዲጨምር ነው ያረኩልኝ አመሰግናለሁ ዶ/ር
ዋው እመጓ እጅግ ተወዳጅ መጽሀፍ ነው የማይጠገብ ማቆም አልቻልኩም ነበር እናመሰግናለን ዶክተር
ሰውን የምለካበት እግዚአብሔርን የማይበት❤ እናመሰግናለን
ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ ከምላቸው ጥቂት ጉንቱ ሙሁሮች አንዱ ዶክተር አለማየሁ ዋሴ መሆኑሳስብ እድሜ ይስጥልን ያብዛልን ፡፡
እግዚአብሔር ይስጥልን በጣም ጥሩ ጥያቄና መልስ ነው:: መፀሕፏችን ሁለቱን ዝጎራና እመጏን አንብቤዋለሁ:: እንደኔ አስተያየት ልብ ወለድ ነው አልልም:: ሐይማኖት ብዙ ጊዜ እምነት ነው እንጂ ማረጋገጫ ማቅረብ አይደለም:: ፀሐፊውም ለዚህ ይሆናል የተውት ብየ ደምድሜአለሁ:: ግን እግዚአብሔር ቢፈቅድልኚ አገሬ ገብቸ ሰላም ቢሆንቧታውን ሔጀ ማየት በጣም ነው የምመኘው:: እንደዚህ አይነት ፁህፎች ማንበብ ሒወትን ያድሳል: በጣም ደስ ይላል:: ኢትዬጵያ ሚስጥር ነች ይባላል ይህ ትክክል ነው:: በሰሜኑም በደቡብም በምስራቅም በምእራብም በመሐልም ተፆፎ ያላለቁ ብዙ ታሪኳች አሉ:: የሚቀጥለውን መፀሐፍ ለማየት ቸኩያለሁ:: ስለሚስጥር ያሉት ትክክል ነው ይህ የምእራብ አገር ስልጣኔ ብለው ሐጢያትን ብቻ የሰውን ማውራትና ያንን ሰው ለመጣል የሚጠቀሙበት መሳርያ ነው😭😭😭😭ለኞ ባህላችን ነበር የሚጠቅመን ግን ተበላሸን!!! እግዚአብሔር ይቅር ብሎ ልባችንን ይመልስልን🙏
Enamesegnalen Doctor Kettu Besrawot
ጋዜጠኛው 👏👏👏👏👏 ልብ አርስ ጋዜጠኛ እውነት ዳ/ር እድሜና ጤና ፈጣሪ አምላክ ይስጥልን
Dave በምዕራፍ ፪ የእንግዳ ምርጫዋችህ የምር ድንቅ ናቸው በዛ ላይ የእንግዳ ምርጫህ እያዋዛህ ስለሆነ መልክ ሰቶታል። dave እናመሰግናለን ⭐️⭐️⭐️
የኔም ጥያቄ ነበር እመጓን አንብቤ ስጨርስ "ልብወለድ ወይስ የማይታመን እውነተኛ ታሪክ"
ዶክተር እጅግ በጣም ነው ማከብሮት! ልዑል እግዚአብሔር ጨምሮ ጨምሮ እድሜና ጤና ይስጥልን🙏 አዲስ መፅሐፎት ናፍቆናል!
እመጓ ገብቶኝ ያነበብኩት መፀሐፍ ነው, ዶክተር አለማየሁ ድንቅ ፀሐፊ ነው 👏👏👏👏👏👏🙏🙏🙏🙏 እጅግ አክባሪው ነኝ አድሜ ሰቶህ የበለጠ እንድትጽፍ አመኝልሀለሁ 🙏🙏
በጣም ደስ ብሎኛል አመሰግናለሁ ግን እባክህን ዋው ዋው አትበል ማንያዘዋል ትመስለኛለህ እና የውሽት ነው የሚመስለኝ እና በጣም ያስጠላኛል
እንደማንያዘዋል አስቀያሚ ፕሮግራም እንዳይሆን ዋው ዋው የምትላትን አቁም
በርታልን።
Egzer yakibirilin 🙏🏼 Dave antenm Dotor'nm
ዶ/ር ዓለማየሁ የከጻፋቸው መጻሕፍት ውስጥ የብዙ ቦታዎችንታሪክና ምስጢራትን እኔ የማውቃቸው አሉኝ ልብወለድ እንዳልሆኑ ምስክር ነኝ!!
በጣም ለኢትዮጵያ ዝብ ጠቃሚ ነው ኡስታዝ በድሩ ሁሴን
ዘይገርም በእውነቱ ዘይደንቅ በየእለቱ ኑርልን ዶክተራችን
በጣም ደስ የሚል ቆንጆ ውይይት ነው፣ ዳዊት በጠም ጥሩ ጠያቂ ነህ በደንብ ተዘጋጅተህ እንደምጠይቅ ያስታውቃል ፣ ያው የዶ/ር አለማየሁ ሊቅነት የታወቀ ነው!!!
እጅግ በጣም የመከብራው የምወዳው ዶክተር ነው።እግዚአብሔር ይጣብቃው
ቃለ ምልልሱን ዘግይቸ ሰማሁት ጠያቂውን በጣም አመሠግናለሁ የዚህ አይነት ጋዜጠኞች ብዙ አይደሉም በርታ!!! ስለ ዶ/አለማየሁ ዋሴ ሁሉን አቀፍ ብቃት በመፃህፍቱም በሚዲያዎችም ስለምከታተል ለዚህ ትውልድ አርአያ መሆኑን አረጋግጣለሁ
ዋው ደጃፍን በመውደዴ አትርፌለሁ
ዶ.ር አለማየሁ ግሩም ሰው🙏
እመጓ መጽሐፍ ን አንብቤ ከሶስት ወንድሞቼ ጋር ቦታው ድረስ ሄጄ ነበር በእውነት ያየሁት ነገር ትክክል ነው መፅሐፍላይ ያነበብኩትን በታ ሁሉ ሄጅ አይቻለው. በህይወቴ በጣም ትልቅ ስንቅ ነው የሆነኛ ወደመንፈሳዊ ህይወት ብቶኛል: ሁላችሁም ብትጠቀሙበት መልከምነው. በዚህ አጋጣሚ ግን ለመሄድ የተፈቀደላቹ. (. ዘብር ገብርኤል ን ፣ አርባራ መድሐኒያለምን ፣ የመሣሠሉ ብዙ ድን ቅ ቦታዎች አሉ እረ ም ያለ ግዜ ይዛቹ ሄዱ አትቸኩሉ ብዙታምራትን እና በረከትን ታገኛላቹ እግዚያብሄር ይፈቀድላቹ ኣሜን።
በጣም ጎበዝ ጠያቂ እና ጋዘጠኛ ነህ። በርታ ይሄን የመሰለ ፕሮግራም ስላሳየህን እግዚአብሔር ይስጥ።
ጋሽ አለማየሁ ዋሴ እሸቱ እግዚአብሔር እድሜ ከጤና ነው እምመኝልህ 🙏🤌🏼🥰
ከዛሬ ስድስት አመት በፊት የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ በነበርኩበት ጊዜ ነበር ከ ዶክተር አለማየሁ ዋሴ እሸቴ የመጀመርያው መጽሃፍ ጋር የተዋወኩት። ያን ጊዜ እመጓን ሳነበው የተሰማኝ ስሜት ለአፍታም ቢሆን የምረሳው አይደለም። በወቅቱ የተሰማኝን ምርጥ ስሜት በቃላት ለመግልጽ ይቸግረኛል። እነሆ ከስድስት አመት በፊት እመጓን ሳነበው የተሰማኝን ስሜት አሁን ላይ በ ደጃፍ podocast በዚኛው episode ድጋሜ አግኝቼዋለው። ዴቭዬ በጣም ነው የማመሰግነው በርታልኝ። ለዶክትር ያለኝ አክብሮትና አድናቆት ልዩ ነው። በርቱልኝ። please release the next part right now. I can't wait.❤❤❤