ለእኔ ነው " It’s for me" Lidia Anteneh 2015/2023

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 8 вер 2024
  • ለእኔ ነው
    እንዴት ያለውን ፍቅርህን ነው ያደልኸኝ
    የማይነጥፈውን ሰላምህን ያካፈልኸኝ
    እንዴት ያለውን ምሕረት ነው ያገነንከው
    ለጠፋሁትኝ መስዋዕት ሆነህ የቀረብከው
    እንዴት ያለውን ክብር ነው ያለበስከኝ
    በጸጋህ ብዛት ድነትን ያጎናጸፍከኝ
    እንዴት ያለውን ውስጣዊ ሰላም ደስታ
    አበዛህልኝ ጋረድከኝ 'ካለም ሁካታ
    ያባትህን ፈቃድ ልትፈጽመው ፍጹም ታዘህ
    አቀረብከኝ ዳግም ወደ ራስህ ቤዛ ሆነህ
    አንተ የእኔ አባት እኔም የአንተ ልጅህ ሆኛለው
    ማንም ላይለየን ኪዳናችን በቅዱስ ደምህ ነው
    ጽድቅ አልብሰኸኝ ኩነኔን ከኔ አርቀኸዋል
    'ሚከሰኝ የለም አንዴ ወደህ መርጠኸኛል
    ትማልዳለህ ልታኖረኝ በጽድቅ ህይወት
    ዘመኔን ከብረህ ዘላለሜን በውበት ልታትታይበት
    ለእኔ ለእኔ ነው ይሄንን ሁሉ የሆንከው
    ለእኔ ብለህ ነው ደም ግባትህን ውበት ያጣኸው
    አዎ ለእኔ ነው ክብርህን ትተህ የተዋረድከው
    በሚጠሉህ ፊት ጎልጎታ ላይ የታየኸው
    ኢየሱስን በማወቅ ወደሚገኘው በረከት
    እንዲሁ ገባሁ ጽድቅ ሆነህልኝ በዕምነት
    ስራህ ክብሬ ሆኖ ተሾኩኝ እንደ መልካም ልጅ
    በክብር ስምህ ተጠራሁ ተያዝኩኝ በአንተ እጅ
    በምን ወደድከኝ ስል ለራሴም ይገርመኛል
    ከእኔ አንዳች የለም አውቃለሁ ይሄ ገብቶኛል
    እንደምትወደኝ ለሞት ታዘህ አሳይተኻል
    አቤት እላለሁ ከአእምሮዬ በላይ ሁሉ ሆኖብኛል
    ለእኔ ለእኔ ነው ይሄንን ሁሉ የሆንከው
    ለእኔ ብለህ ነው ደም ግባትን ውበት ያጣኸው
    አዎ ለእኔ ነው ክብርህን ትተህ የተዋረድከው
    በሚጠሉህ ፊት ጎልጎታ ላይ የታየኸው
    1ኛ ዮሐ3:1
    እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥
    ኤፌሶን 2:4-5
    ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥

КОМЕНТАРІ • 147