የስልጤ ታሪክ/History of Silte የስልጢ አዜርነት ወለኔ ገደባኖ ታሪክ

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 5 лют 2025
  • የስልጤ ማኅበረሰብ ታሪክ
    የስልጤ ማኅበረሰብ ከሀረር እንደተነሳና የሀድያ ሱልጣኔት ትውልድ እንደሆነ ይናገራል። የስልጤ አገር ለመጀመርያ ጊዜ በፅሁፍ የተጠቀሰው በ14ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ስልጤጌ ተብሎ ነበር። በቃል በተላለፈ ታሪክ መሰረት የስልጤ ቅድመ አያቶች የሀረር ነዋሪዎች የነበሩት ካቢር ሐሚድ እና አው ባርክሀድሌ ነበሩ።
    ወራቤም ለመጀመርያ ጊዜ የተጠቀሰው ከ440 ዓመታት በፊት በ1583/1584 ዓ.ም በአፄ ሠርጸ ድንግል ዘመነ መንግሥት የኦሮሞ ሰዎች ወራቤን እና ፋንፋራን በጦር ሲከብቡ ነበር።
    የስልጤ ወደ አሁኑ አካባቢው አመጣጥ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደሚጀምር ይታመናል። ይህም ኢማም አህመድ ኢብን ኢብራሂም አል ጋዚ (ወይንም አህመድ ግራኝ) በክርስቲያን አቢሲኒያ ላይ ከፍተኛ ወታደራዊ ዘመቻ ሲያካሂድ ነበር። በስልጤ በቃል በተላለፈ ታሪክ መሰረትም በሀረር የተወለዱ አንድ ሀጅ አልዬ የተባሉ የሐይማኖት መሪ አንድ ኡምናን የተባለ ቦታ ላይ እንዲሰፍሩ እስኪነገራቸው ድረስ ዘመቻውን ተከትለው መጥተው ነበር። በዛም በሰፈሩበት አካባቢም አንዲት ሴት አገቡ፤ ከእርሷም የተወለደላቸው የመጨረሻ ልጅ ገን-ስልጢ ተባለ፤ እርሱም የስልጢ ማኅበረሰብ መነሻ እንደሆነ ይታመናል። ሀጂ አልዬ በአባታቸው ሀረሪ በእናታቸው የአረብ ዝርያ እንዳላቸው የሚነገር ሲሆን በስፍራው ሲደርሱ በመጀመሪያ መቀመጫቸውን ያደረጉት አልቾ ወሬሮ ላይ እንደነበር በታሪክ ይነገራል፡፡ ስልጢ በቀደመ ትርጉሙ (ማለትም እንደ ጋን ስልጢ ዘሮች) በአሁኑ ጊዜ ካሉት የስልጤ ክፍሎች አንዱን ብቻ ይይዛል። ተመሳሳይ ቋንቋ የሚጋሩ ይህንን አተራረክ የሚከተሉ ሌሎች የሙስሊም ክፍሎች ግን አሉ። እነሱም አዜርነት በርበር፣ ማልጋ፣ አሊቾ ወሬሮ እና ወለኔ ገደባኖ ናቸው፤ እና እነዚህ አምስት ክፍሎች (ስልጢን ጨምሮ) “ኢስላም” ተብለው ይጠሩ ነበር። ይህ ቃል በአገር ውስጥ ቋንቋ በቀላሉ “ሙስሊም” ማለት ነው፣ ነገር ግን በተለይም እነሱ የሚጋሩትን ቋንቋን “ኢስላምኛን” (ወይም “ስልጥኛን”) የሚናገሩ ሰዎች እንደ ማለት ነው። በዚያን ወቅት የነበረው የስልጤ ሕዝብ ወደ አሁኑ ስፍራ ከመድረሱ በፊት ገደብ ዝዋይ /ላቂ ደንበል/፣ ሲዳማ፣ ከቡልቡላ አጠገብ ባለው አሊቶ ዳገት በሚባሉ አካባቢዎች ቆይታ እንዳደረገ የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በወቅቱ ለሕዝቡ እንቅስቃሴ እንደ ምክንያት የሚገለፀው በግራኝ አህመድ የተነሣ ጥሩ የመኖሪያ አካባቢ ለመፈለግ እንደሆነ ይነገራል፡፡
    በሁሴን መሐመድ ገለፃ መሰረት ኢስላም የሚለው በአመራር ሥርዓት ውስጥ አምስቱንም በመወከሉ ምክንያት እንደ አንድ መታሰብ አለባቸው ነገር ግን ስልጤ የሚለው ቃል አምስቱንም እንዴት ወደ መወከል እንደመጣ አይታወቅም። ነገር ግን ለስልጢ ማለትም ለገን ስልጢ ዘሮች የተሻለ ቦታ እንደተሰጠና በአካባቢው እንደ ቅዱስ በሚታዩት ሐጅ አሊዬ ከመሞታቸው በፊት ተአምራትን እንደሰሩ ያምናሉ። ገን-ስልጢ በጦርነት መሬት ያገኝ ዘንድ የአባቱ የሐጅ አሊዬ ጦር ከምርቃት ጋር ተሰጠው።
    በ16ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከተከወነው ከኦሮሞ መስፋፋት በፊት ስልጤ ከወለኔ እና ከሀረሪ ህዝቦች ጋር በአንድ ወቅት የሀርላ ህዝቦች ቅጥያ እንደነበረ ይታመናል።
    በ17ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሀድያ ሱልጣኔት ገራድ ሲዴ መሐመድ ነበር። ሲዴ መሐመድ ስልጢ የተባለው ጎሳ መስራቾች የልጅ ልጅ እና የሀላባ ብሔረሰብ መስራች እንደሆነ ይታሰባል። ገራድ ሲዴ መሐመድም በሀድያ ጦርነት ከቀዳማዊ አፄ ሱስንዮስ ሠራዊት ጋር ገጥሞ አሸነፈ። ይህም ለቀጣዮቹ 300 ዓመታት በአቢሲንያ አገዛዝ ውስጥ እንዳይጠቀለሉ አደረጋቸው።
    ከ19ነኛው መቶ ክፍለ ዘመን መዝግያ በፊት በስልጤና በዙርያቸው ባሉት በ7 ቤት ጉራጌ፣ በክስታኔ ጉራጌ እና በአርሲ ኦሮሞ ዘንድ መሬት እና የውኃ ምንጮችን ለመቆጣጠር ጦርነቶች በተደጋጋሚ ይካሄድ ነበር።
    በ19ነኛው መቶ ክፍለ ዘመንም በምኒልክ ጦር ከመወረራቸው በፊት የጋን ስልጢ ሥርወ መንግስት የመጨረሻው ገራድ ሴዲሶ ካልቦ ይባል ነበር።
    ዳግማዊ ምኒልክ ወደ ደቡብ ያደረጉት ዘመቻ በስልጤና በዙርያቸው ያለውን ህዝብ ታሪካዊ አኗኗር የለወጠ ነበር። የስልጤ ምድር በንጉሠ ነገሥቱ አስተዳደር ውስጥ የገባችው እ.ኤ.አ በ1888 የቀቤና፣ የ7ቤት ጉራጌ እና የስልጤ ጦር ከምኒልክ የጦር መሪዎች መካከል አንዱ በነበረው በራስ ጎበና ዳጬ ጦር በተሸነፈ ጊዜ ነበር።
    ከእነዚህ ጊዜያት በኋላም የስልጤ ማኅበረሰብ ለንግድ ወደተለያዩ አካባቢዎች መጓዝ ጀመረ።
    በ1930ዎቹም ከሲዳማ የቡና ገበያዎች ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ በሚሄደው የንግድ መስመር ላይ ስልጤ ሚናውን ይጫወት ነበር።
    በጣልያን ይዞታ ጊዜ አውራ ጎዳናዎች እስኪሰሩ ጊዜ ድረስም የሲዳማ ቡና ወደ አዲስ አበባ የሚደርሰው በበቅሎዎች ጀርባ ላይ ተጭኖ ከወራት ጉዞ በኋላ ነበር። በዚህ ሂደትም ቡናውን በሚያመርቱት በሲዳማ ገበሬዎች እና ቡናውን ከገበሬዎች ተረክበው በሚሸጡት በስልጤ ነጋዴዎች መካከል ግልፅ የሆነ ከስራ ክፍፍል ተፈጠረ።
    እ.ኤ.አ በ1935 ዓ.ም የሥነ ብሔር አጥኚ የሆኑ ጀርመናውያን ወራቤን ጎብኝተው ነበር። በጠፍጣፋ ኮረብታም ላይ ትልቅ ከተማ አገኙ፤ በምስራቅ በኩልም ትንሽ ሐይቅ እና ሜዳዎች አሉ፤ ምናልባትም በዛ በዝናብ ወቅት ውኃ ይጠራቀማል፤ ከዚህ በተጨማሪም በቅርበት የሚገኙ የተጌጡ ሐውልቶች በዚያ ነበሩ፤ እነርሱም በ1920ዎቹ በፔሬ አዛይስ ተገልጸዋል፤ ነገር ግን ኋላ ላይ ወደ አካባቢው የመጣው የጀርመን አሳሽ ቡድን ለጥናት በጣም አስፈላጊ ከሆኑት ሐውልቶች ውስጥ ሁለቱን አጥቷል። የአካባቢው ሰዎች እንደሚያስቡትም ከሆነ እነዚህ ሐውልቶች ወደ አዲስ አበባ ተወስደዋል፤ ነገር ግን በዚያ ሊገኙ አልቻሉም።
    በአንድ ወቅት ስልጤ እንደ 7 ቤት እና ሶዶ ክስታኔ ካሉ ህዝቦች ጋር የጉራጌ ማንነትን ይጋራ እንደነበረ ማስረጃ አለ። እ.ኤ.አ በ1955 የአፄ ኃይለ ሥላሴን የብር ኢዮቤልዩ ለማክበር በአዲስ አበባ በተዘጋጀው የዓለም አቀፍ ኤክስፖዚሽን የጉራጌ ኤግዚቢሽን አንዱ ክፍል ነበር። ይህ ኤግዚቢሽንም ስልጤን ጨምሮ ከተለያዩ የጉራጌ ሰዎች በተውጣጡ ሽማግሌዎች እና የተማሩ ወጣቶች የተዘጋጀ ነበር። ባህሩ ዘውዴ እንደገለጹት ከሆነም በዘመኑ ጉራጌ በኢትዮጵያ የችርቻሮ ንግድን ተቆጣጥረው የነበሩትን የየመን አረብ ነጋዴዎችን ተፎካክሮ ገበያውን የተቆጣጠረበት ጊዜ ነበር።
    በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ ኢህአዴግ በአዲስ አበባ ሥልጣን ከያዘ በኋላም እ.ኤ.አ በ1992 የስልጤ አዜርነት ወለኔ ገደባኖ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ተመሰረተ። ኋላም ላይ ስሙን ቀይሮ የስልጤ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ፖርቲ መስርቶ ለማዕከላዊ መንግስት ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ በማቅረብ ከጉራጌ ዞን ተለይቶ የራሱ ዞን ተሰጠው።
    ማጣቀሻዎች(References)
    1. repository.kul...
    2. en.wikipedia.o...
    3. en.wikipedia.o...
    4. en.wikipedia.o...
    5. am.wikipedia.o...

КОМЕНТАРІ • 50