የብሉይ ኪዳን ዳሰሳ | መኀልየ መኀልይ ዘሰለሞን | ፓስተር አስፋው በቀለ

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 20 жов 2024
  • በታሪክ ውስጥ ሁሉ ይህ መጽሐፍ የተለያዩ ስሞች ነበሩት። አንዳንድ ጊዜ «የሰሎሞን መዝሙራት» እየተባለ ይጠራል። ይህ የሚያንጸባርቀው መዝሙሩን የጻፈው ሰሎሞን እንደሆነ ሰዎች ያምኑ እንደነበር ወይም ስለ ሰሎሞን የተጻፈ መጽሐፍ እንደነበር ነው። አይሁድ ይህን መጽሐፍ «ከመዝሙራት ሁሉ የሚበልጥ የሰሎሞን መዝሙር» ብለው ይጠሩታል። ይህ ርእስ የተገኘው ከመኃልየ መኃልይ 1 ቁጥር 1 «ከመዝሙር ሁሉ የሚበልጥ የሰሎሞን መዝሙር» ከሚለው ቃል ነው። በዕብራይስጥ «የመዝሙሮች መዝሙር» ማለት «ከሁሉ የላቀ ታላቅ መዝሙር» ማለት ሲሆን፥ ይህ የሚያሳየው በጥንት ጊዜ መዝሙሩ ምን ያህል ተወዳጅ እንደነበረ ነው። ይህ የዕብራይስጡ ርእስ፣ ጸሐፊው ሰሎሞን መሆኑን ወይም መዝሙሩ ለሰሎሞን የተበረከተ ይሁን ወይም መዝሙሩ የተጻፈው ስለ ሰሎሞን መሆኑን ግልጽ አያደርግም።
    ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ፦
    https: //www.operationezra.com
    • www.operationezra.com ...
    • www.operationezra.com ...
    © Operation Ezra Bible College

КОМЕНТАРІ • 39