Abeba Ina Nib | አበባ እና ንብ - New Ethiopian Music 2019 (Official Video)

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 30 жов 2024
  • #janoband #abebainanib#ethiopianmusic Jano Band - Abeba Ina Nib | አበባ እና ንብ - New Ethiopian Music 2019 (Official Video)
    አንቺ ቆንጆ ውብ አበባ በይ ቀስሜሽ ልግባ
    አንተ ቆንጆ አማላይ እረፍ እኔው ላይ
    ውቧ ፍቅሬ ውዷ ፍቅሬ ልምጣልሽ በርሬ
    ሎጋው ንቤ ሸጋው ንቤ ሁንልኝ በቅርቤ
    ቀስሜሽ መግባቴ ማሬን ካጣፈጠው
    አበባዬ እያልኩ ስምሽን ላቆላምጠው
    ተራራ አሻግሬ ማዶ ባላይሽ (2)
    ምሴን አገኛለሁ አርፌ ላይሽ
    አሀሀሀሀሀ... አዬዬዬዬዬ...(2)
    በኛ መገናኘት ይሠራል እንጎቻው
    እንጀራን አይፈጥር ማንም ለየብቻው
    ፍቅራችን ለሌላው ወለላን ያዝንብ (2)
    ለሠው ኗሪ ናቸው አበባ እና ንብ
    አዝማች..........
    ሠዎች ሲዋደዱ ተሳክቶ ምርጫቸው
    አንቺ ነሽ አበባ ፍቅር መግለጫቸው
    ተምሮ ሲመረቅ ተድሮም ሲያገባ (2)
    ሰው እንኳን ደስ አለህ ይባላል በአበባ
    አሀሀሀሀሀ... አዬዬዬዬዬ(2)
    በአበባው ገላዬ ስማርክህ አንተን
    ስንቱን እንጠቅማለን እኛ ተገናኝተን
    በል ናልኝ ወደ እኔ ካኖርከኝ ለሌላው
    ሁሉም ጣፋጭ ይብላ ይድረሰው ወለላው
    አዝማች..........
    ጣዝማን ሰርቼ ባንቺው ውብ ሽታ
    መድሐኒት ላርገው ለሠው በሽታ
    ክብር ነሽና ባለ ማረግ
    ያኮራል አንቺን በእጅ ማድረግ
    ሌላው አንስቶ ቢሠጠኝ ለሠው
    ከአንድ ሌት በላይ አልተነፍሰው
    ያንተ ስራ ነው ላገር ያኖረኝ
    ቅመሜን ወስዶ ማር ያስጋገረኝ
    አሀሀሀሀሀ... አዬዬዬዬዬ...

КОМЕНТАРІ • 1,2 тис.