🔴መስቀሉን የምናከብርበት ምክንያት||እጅግ ድንቅ ትምህርት||በመምህር ጽጌ ሲሳይ||abagebrekidannewsibket||

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 21 жов 2024

КОМЕНТАРІ • 12

  • @meazakidusan
    @meazakidusan  25 днів тому +5

    ❤ውድ ቤተሰቦቻችን:- ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በሚዲያችን (መዐዛ ቅዱሳን) መምህር ጽጌ በቋሚነት የሚያስተመሩን ስለሆነ ያሏችሁን ጥያቄዎች ሁሉ ኮመንት ላይ በማስቀመጥ መልስ ማግኘት ትችላላችሁ። ቪዲዮውን ላይክና ሸር በማድረግ ለወገኖቻችን በማዳረስ መንፈሳዊ ግዴታችሁን ተወጡ።

  • @mametohem7990
    @mametohem7990 25 днів тому

    አሜን አሜን አሜን እኳን አብሮ አደርሰን🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @meazakidusan
    @meazakidusan  25 днів тому +4

    ❤ውድ ኦርቶዶክሳውያን የእግዚአብሔር ሰላምና ፍቅር ይብዛላችሁ!! ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ እንድትሆኑ አንዲሁም እንደተለመደው አገልግሎቱ ለብዙ ኦርቶዶክሳውያን እንዲደርስ ላይክ አና ሸር በማድረግ እንድትጀምሩ ስንል በአክብሮት እናሳስባለን። ቸሩ አምላክ ቃሉን በልባችን ይፃፍልን።

  • @tesfaneshdejene8981
    @tesfaneshdejene8981 19 днів тому

    ተመስገን ቃለ ህይወት ቃለ በረከት በእድሜ በጤና በጸጋ ያድልልን ይጠብቅልን

  • @DeaconAtnatewos
    @DeaconAtnatewos 13 днів тому

    የህይወት ቃል ያሰማልን

  • @AyehuDamtew-zu3fe
    @AyehuDamtew-zu3fe 25 днів тому

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን መምህር❤❤❤

  • @lealemmeseret749
    @lealemmeseret749 25 днів тому

    ❤❤❤

  • @yeshamabirhan6591
    @yeshamabirhan6591 25 днів тому

    🌻🌼🌻🕆🕆 መስቀል ሀይልነ🕆 መስቀል ፅንነ🕇 መስቀል ቤዛነ 🕆መስቀል መድሀኒተ ነፍስነ 🕇አይሁድ ይክሀዱ 🕆ነአመነ በሀይለ ድህነ መስቀሉ ቃል ህይወት ያሰማልን 🕆እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሠላም አደረሳችሁ።🕆🕇🌻🌼🌻

  • @AmhaGetnet
    @AmhaGetnet 25 днів тому

    መስቀል ክርስቶስን የምናይበት ክርስቶስን የምንመለከትበት መስታውት ነው❤ስቀል አብርሃ በከዋክብት አሠርገወ
    ሰማየ ...የመሃሉ ሀሳብ በተለይ ደንቆኛል ፤ መስቀል እንደ ከዋክብት አበራ ከሁሉ ይልቅ ፀሐይን አሳየ ።

  • @elmestoagya6253
    @elmestoagya6253 25 днів тому +1

    .......................መስቀል......................... #
    መስቀልን ያለ ክርስቶስ ፤ ክርስቶስን ያለ መስቀል የምተሰብክ ቤ/ክርስቲያን የለችንም። ኑራንም አታውቅም። ያለ መስቀል የተገለጠ ክርስቶስ፣ ያለ ክርስቶስ የሚገለጥ መስቀልም የለንም። ያለ ክርስቶስ የምናከብረው መስቀል፤ ያለ መስቀልም ያከበርነው ክርስቶስ የለንም ።
    በዐለ ክርስቶስ የተለየው በዓለ መስቀል ፤ በዓለ መስቀል የተለየው በዓለ ክርስቶስ የለንም ። ክርስቶስ የማይከብርበት መስቀል ፤ መስቀል ያልከበረበት ክርስቶስ የለንም። በክርስቶስ ደም ያልተቀደሰ መስቀል ፤ መስቀልን ያልቀደሰ ክርስቶስ የለንም ።...ክርስቶስን የማይገልጥ መስቀል ፤ ክርስቶስ የማይገለጥበት መስቀል የለንም ፤ ኑሮንም አያውቅም ።
    መስቀል " የቤ/ ክርስቲያን መሠረት ነው። መስቀል የባሕር ጸጥታዋ? የመርከቦች ወደባቸው ነው።(መሰረተ ቤ/ክርስቲያን ዛኀኑ ለባሕር ወመርሶ ለአሕማር ድጓ # መስቀልን የምታከብር እና በመስቀል የምትከብር እምነት እንጅ መስቀልን የምታመልክ እምነት የለችንም። ደግሞ ኑራንም አታውቅም ፤ ወንጌል መስቀላዊት ሕግ ናት ። ወንጌል ጥንቷ መስቀል ነው፤ ፍጻሜዋም መስቀል ነው።
    ደግሞ ቅዱስ መጽሐፍ
    መስቀል ሲል ብዙ ምስጢረ መስቀል አለው። መስቀል የሚታይ መልክና የማይታይ መልክ አለው። መስቀል ተዳሳሽና ኢተዳሳሽ ፤ ረቂቅና ግዙፍ መስቀል አለ ።እኛ መስቀል ስንል ከእን፥ ከወርቅ ፥ ከብር ፣ ከነሐስ ፣ከእንጨት የተሠራውን መስቀል ብቻ ማለታችን አይደለም። ይህ መስቀል የማይታየውን መስቀል የሚያሳይ መስቀል ነው።
    ክርስቶስ የሚታየውን መስቀል የተሸከመው ከቀራንዮ እስከ ሊቶስጥራ ፤ ከሥድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት (እስከ ሠርክ )ነው። ነገር ግን ሠለሳ ሦስትዓመት ሙሉ የተሸከመው መስቀል ከባድ ነው። ኧረ እንዲያውም 5500 ዘመን ሙሉ መስቀል ላይ ነው። ማለቴ ስቅለተ ሕሊናውን ነው። (ተሰቅለ በእንቲአነ...) ለጌታ እኮ በጠባብ ማኀጸን በአጭር ቁመት መወሰን መስቀል ነው።
    ለጌታ በከብት በረት መወለድ ፣ በአህያና በላም እስትንፋስ መሟሟቅ መስቀል ነው። የሦስት ዐመት ከመንፈቅ ስደት ይህም መስቀል ነው። የኦሪት ጌታ ለሕገ ኦሪት መገዛቱ፤ የእብራይስጥ ጌታ ፊደል ሊማር መግባቱ፤
    የአሌፍ ትርጓሜዋ የአሌፍን ትርጒም መጠየቁ፤ ሊቀ አበው በውስተ ሊቃነ አበው የተሰኘ ወደ አበው መሄዱ ኧረ ምኑ!!! ብቻ ምን ልበላችሁ?! የቆሮንቶሱ ረኀብ መስቀል ነው። ዐርባ መዓልት ዐርባ ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ። ማቴ 3፥1 ይህ ረቂቅ መስቀል ነው ። በመስቀል ላይ ኹኖ ተጠማሁ አለ? ዋ !!
    የሕይወትን ውሃ ሲሆን፤ እንደምን ውሃ ይጥማው !? የሕይወትንስ ሲሆን ፣ እንጀራን እንደምን ይራበው? ምን እንላለን? ምንስ እንናገራለን? እና? ወንድሜና እኀቴ እጸ መስቀሉ የተሰቀለውንና በተሰቀለው ላይ የተፈጸመውን መስቀል የምናይበት መስቀላችን ነው።
    መስቀል ማዕድ ነው። ወሠራዕከ ማዕደ በቅድሜየ..በፊቴ ማዕድን ሠራህ መዝ 22፥ ማዕድ ታውቃላችሁ? ማዕድ እኮ ክቡርነው እንደ ዛሬው ስሐንና ባቲ ሳይመጣ። ሰዎች ማዕድን ተሰብስበው ይመገቡት ነበር። ማዕዱ ሲያበቃ ተመራርቀው ማዕዱን አክብረው ስመው ያነሱት ነበር።
    ማዕድ ክቡር ነው። ደግሞ መስቀል የሕይወት እንጀራ የቀረበበት ማዕድ፤ የሕይወት መጠጥ የቀረበበት ጽዋችን ነው።ጥበበኛው" ጥበብ ቤቷን ሠራች ሠባት ምሰሶንም አቆመች ፍሪዳ ጣላች ወይንንም ጠመቀች ማዕድንም አዘጋጀች ምሳ 9፥ 2 ስለዚህ መስቀል ማዕድ ነው።
    አንተ ወንድሜ ሥጋዊ ማዕድ እንዲህ ክብር ካለው ሰማያዊ ማዕድማ ምን ያህል ክብር ይኖረው? መስቀል ማዕድ ነው። መስቀል መሠዊያ ነው...፤ መስቀል.. ኀይላችን ነው። መስቀል ቤዛችን ነው። ምናልባት መስቀል ኀይላችን ነው በማለቴ የተቆጣ ይኖር ይሆን? ይህማ እንዳይሆን ቅ/ጳውሎስ እኮ የመስቀሉስ ነገር በማያምኑት ዘንድ ሞኝነት ነው" እንዳለን። ለዳንበት ለኛ ደግሞ የእግዚአብሔር ኀይል ነው "አለን ።1 ቆሮ 2 ስለዚህ መስቀል መድኀኒታችን ፤ መስቀል ቤዛችን" ስንል ልክ ነን።
    ቅ"ጳውሎስ ለዳንበት ለኛ ብሎ የዳንበት እንደሆነ ከነገረን ። መድኀኒታችን " እንለዋለን።
    ጳውሎስ ኀይላችን "ካለውም ኀይልነ " እንለዋለን።
    መስቀል ኀይልነ፤
    መስቀል ጽንዕነ
    መስቀል ቤዛነ
    መስቀል መድኀኒተ ነፍስነ፤
    አይሁድ ክህዱ ንህነሰ አመነ
    ወእለ አመነ በኀይለ መስቀሉ ድኀነ "
    እያላችሁ መስክሩለት ........... ... ።..
    ለ ደ ረ ሳ ች ሁ 🤔
    እ ን ኳ ን አ ደ ረ ሳ ች ሁ !!!

  • @MelkamuTadesse-e1v
    @MelkamuTadesse-e1v 25 днів тому +1

    በዓለ መስቀል የመከራና የደስታ ምሥጢር ነው። መስቀል ሲታሰብ ክርስቶስ ይታሰባል፤ መስቀል ሲታሰብ መከራ ክርስቶስ ይታሰባል፤እንኳን ሉብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ።