ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ስለ ምስራቅ ወለጋው ግድያ ምን አሉ?| Berhanu Nega of Ezema's take on recent killings in East Wollega

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 29 вер 2024
  • የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ)፤ ከሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ተፈጽሟል ያለውን “የንጹሃን ዜጎችን ጭፍጨፋ” አስመልክቶ ዛሬ ማክሰኞ ህዳር 27፤ 2015 ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ የተገኙት የፓርቲው መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፤ እንደዚህ አይነት ግድያዎችን ከሚፈጸሙባቸው ምክንያቶች አንዱ፤ “እንደ ማህበረሰብ የሚጠብቀን ‘መንግስት የሚባል ተቋም የለም’ ብለን እንድናምን ነው” ብለዋል።
    “ እንዲፈጠር ከሚፈለገው አንዱ ‘መንግስት የለም። በጋራ የሚጠብቅህ የለም። ራስህን የምትጠብቀው፤ በዘርህ፣ በጎጥህ ተሰባስበህ ነው’ የሚለው ነው። በዓለም ታሪክ፤ መንግስትን አፍርሶ፣ ሁሉም በዘር ተደራጅቶ የሚገኝ ሰላም ኑሮ አያውቅም። [ያለው] የእርስ በእርስ ጦርነት (civil war) ነው። ከእርስ በእርስ ጦርነትም፤ የመጨረሻ አስቀያሚ አይነት civil war ነው” ሲሉ የጉዳዩን አሳሳቢነት በአጽንኦት ተናግረዋል።
    የኢዜማው መሪ “በመንግስት እና በሀገር ደረጃ ያላገኘነውን ሰላም፤ በክልል እና በዘር ተሰባስበን እናገኛለን ብሎ ማሰብ የመጨረሻ ጅልነት ነው” ሲሉም ተደምጠዋል። የሰሞኑ ክስተት “አጠቃላይ እየሄድንበት ካለው የብሔር ፖለቲካ ጋር የተያያዘ ነው” ሲሉም አክለዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
    --------------------------------------------------------------------------------
    የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
    ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider...​
    ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
    ትዊተር ፦ / ethiopiainsider

КОМЕНТАРІ • 2

  • @ቀሌ
    @ቀሌ Рік тому +1

    ብሬ አንበሳ 🦁🦁🦁 ሁሌም እውነት ነገር ነው የሚናገርው ግን ሰሚ አካል የለም።መንግስት ጆሮውን ከፍቶ ቢሳማ ኖሮ ይኼ ሁሉ ህዝብ አያልቅም ነበር ።መንግስት በጣም ችለተኝነት አለበት

  • @Thetruthsshallsetyoufree
    @Thetruthsshallsetyoufree Рік тому

    የአንተ ዘር ሆድህ ነው ፍትህ የማይገባህ ገተት ነገ በእግዚአብሔር ፊት ቆመህ እንደምትጠየቅ እርግጠኛ ነን አሁን አንተን የሾመ አራጅ መንግስት እንዳለ ልትነግረን ነው የቆምክ