ፈላስፋ እና ባለቅኔው ሰለሞን ዴሬሳ (Solomon Deressa: The philosopher and poet)

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 21 сер 2024
  • “…ህይዎቴን በሙሉ እስከ ዛሬ ድረስ የኖርኩት የመሸበት አድራለሁ ብዬ ነው ስሞትም የመሸበት እቀበራለሁ ነፍሴ ወደ ሄደቺበት ትሂድ እኔ ለሷና ለነገ ግዴታ የለብኝም። ያለብኝ ግዴታ ዛሬ ካንተ ጋር በሃቀኝነት መኖር ነው።”
    (ሰለሞን ዴሬሳ)
    ሰለሞን ትውልዱ ወለጋ ነው፣ በ1930 ዓ.ም. ጊምቢ ውስጥ ጩታ በተባለች መንደር። ወላጅ አባቱ አቶ ዳንኪ ሊንጊ ሲሆኑ ወላጅ እናቱ ወ/ሮ የሺመቤት ዴሬሳ ይባላሉ። መጠሪያ ስሙን የወረሰው ከእናቱ አባት ከአያቱ ከብላታ ዴሬሳ አመንቴ ነው። ሰለሞን በትውልድ መንደሩ ብዙም ለመቆየት አልታደለም፣ ገና የአራት አመት ታዳጊ ልጅ ሳለ ወደ አዲስ አበባ መጣ። ሰለሞን በልጅነቱ ቀለም የመቀበል አቅሙ ደካማ ነው የሚባል ዓይነት ልጅ ነበር። በአዲስ አበባ ያልሄደበት ትምህርት ቤት አልነበረም። ተፈሪ መኮንን፣ዊንጌት፣መድሃኒዓለም የመሳሰሉ ትምህርት ቤቶችን አዳርሷል። ምን በትምህርቱ ደካማ ነው ቢባልም ሰለሞንን ገና በ16 ዓመት እድሜው የቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ኮሌጅን ከመቀላቀል ያቆመው ግን አልነበረም። በነገራችን ላይ ወንድሙ ይልማ ዴሬሳ በንጉሡ ዘመን የፋይናንስ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመሆን በላቀ ደረጃ አገራቸውን አገልግለዋል።
    ሰለሞን በዩኒቪርሲቲ ቆይታው የስነ-ፁሑፍና ፍልስፍና ትምህርቱን ቢጀምርም ትምህርቱን ሳያጠናቅቅ በኢትዮጰያ ሬድዮ የእንግሊዘኛ ዜና አንባቢ ሆኖ ለ 3ወራት እንዳገለገለ የነፃ ትምህት እድል አግኝቶ ወደ ፈረንሳይ አቀና።ምናልባትም የወደፊት ሂዎቱና አስተሳሰቡ ላይ ጉልህ ተፅዕኖ ካሳደሩበት መካከል ይህ የፈረንሣይ ኑሮው አንዱ ነው። ቱሉዝ በተባለች በደቡብ ፈረንሳይ በምትገኝ ከተማ ይማር የነበረው ሰለሞን ብዙን ጊዜ አውሮፓና ፓሪስን በመጎብኘት ያሳልፍ ነበር። ሰለሞን ፈረንሳይ ሳለ የዘመኑን ታላላቅ አሳቢያን (thinkers) ፣ ገጣሚያን፣የጃዝ ሙዚቀኞች እና ሰዓሊያን የማግኘትና አብሮ የመወያየት እድልም አግኝቶ ነበር። ይህም በኋላ ላይ ሰለሞን ይዞት ለመጣው የጥበብና የፍልስፍና ዘይቤ የራሱን አስተዋጽዖ ያበረከተ አጋጣሚ ነበር። ፓሪስ ሳለ ሰለሞን ካገኛቸው ሰዎች መካከል ጀምስ ቦልደዊንና ቸሰተር ሃይምስ ተጠቃሽ ናቸው።
    ሰለሞን ፓሪስን የለቀቀው ለወዳጁ እስክንድር ቦጎሲያን ሚዜ ለመሆን ወደ አሜሪካን ባቀናበት አጋጣሚ ነበር። ለሚዜነት ወደ አሜሪካን አገር ያቀናው ሰለሞን ዳግም ወደ ፓሪስ ባይመለስም በፓሪስ ሳለ በፈረንሳይኛ ቋንቋ የጻፋቸው ግጥሞቹ ግን የህትመት ብርሃንን ለማየት ታድለዋል።
    በአሜሪካ ቆይታው በቅድሚያ ወደ ካሊፎርኒያ በማቅናት ከጌታሁን አምባቸው ጋር በጋራ በመሆን በቴፕ እየቀረፁ አማረኛ ማስተማር ጀመሩ። ይህ በንዲህ እንዳለ እሱን ጨምሮ 11 ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት “ኢትየጵያን ዲክሽነሪ” ላይ አሻራዉን አሳርፏል። ምን ይሄ ብቻ ከሉካንዳ ጀምሮ እስከ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባሉት ቦታዎች ሰርቷል።እዚያ እያለ ለኢትዮዮጵያ ሬድዮ ለወጣው ክፍት የስራ ቦታ ተወዳድሮ በማለፉ ወደ ሀገሩ ተመልሶ በድጋሚ ኢትዮጵያ ሬድዮ ተቀጥሯል። እንዲሁም የኢትዮጲያ ሬድዮንና ቴለቪዥን ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆኖም አገልግሏል።
    ሰለሞን ዘርፈ ብዙ የእውቀት ሰው ነው። ደራሲ ነው፣ገጣሚ ነው፣ፈላስፋ ነው፣ ሃያሲ ነው፣መምህር ነው ወዘተ። “ልጅነት” የተሰኘውን አነጋጋሪ የግጥም መድብል እስኪያወጣ ድረስ ሰለሞን በጋዜጠኝነቱ ነበር ይብልጥ የሚታወቀው። ይህ ስሙን የተከለበት መድብሉ ብዙ የወዛገበና ትችት የዘነበበት ቢሆንም ባልታሰበ መንገድ ለደራሲው የገጣሚነት ማረጋገጫ ቡራኬዎች ነበሩ።
    በ1960ዎቹ በብዛት በመጽሄቶች ላይ ይጽፋቸው የነበሩት ጽህፎቹ በጥልቅ ፍልስፍናዎቹ የተቃኙ ነበሩ። ሰለሞን በአገረ አሜሪካ ፍልስፍናን በማጥናት ዲግሪውን የተቀበለ ሲሆን በ University of Minnesota በመምህርነት አገልግሏል። እራሱን በኢትዮጵያዊ ማንነቱ የሚገልጸው ሰለሞን ስለ ብሄር ማንነት ጉዳይ፣ በተለይም ሰለኦሮሞነቱ ለሚነሳለት ጥያቄ የሚሰጣት መልስ “What do I know as to who passed my grandma for me to claim that I am an Oromo” የምትል ነበረች።
    ፈላስፋው ሰለሞን
    -----
    ልጅነት፣ዘበት እልፊቱ ወለሎታትና የናይጄሪያው ጸሃፊ ወሌ ሾዬንካ ስብስብ ስራዎችን ጨምሮ 3 መጽሀፍትን ለአንባቢያን ያበረከተው ሰለሞን ደሬሳ “ኪነጥበብ ለኪነጥበብነቱ” ወይም “art for the sake of art” በሚለው ፍልስፍናው ነው የሚታወቀው። በአንድ ወቅት ከያሬድ ጥበቡ ጋር ባደረገው ቆይታ እግዛብሔር የሚውደውን እንደሚቀጣ እንዲሁም አብዛህኛው ኢትዮጵያዊ ሰለሚየምንበትና ፈጣሪ ስለሚዎደን ይቀጣናል ስለሚሉት እምነት ሲጠይቀው ሰለሞን የሰጠው መልስ እንዲህ በማለት ነበር።
    “እንደኔ አስተሳሰብ ስለተዎደድን ነው የምንረገጠው የሚለው በተለይ ከአይሁዶች የዎረስነው ብሉይ ኪዳንባንቀበል፤ ከወደድከኝ የኔ ወንድም አትርገጠኝ፣ ጌታዬ ከዎደድከኝ አትርገጠኝ፣ ከረገጥከኝ ካጉላላሀኝ አልወድህም ብዬ እኔ ለራሴ ቆርጫለሁ።”
    ስለግጥም ያለውን አመለካከትም እንዲህ ነበር የገለጸው ሰለሞን…
    ”በአጭሩ ለኔ እንደሚመስለኝ በስድ ንባብ የተፃፈ እንዲገባህ፣ በግጥም የተፃፈው እንዲሰማህ ነው።ገባህ አልገባህ ሁለተኛ ነገረ ይመስለኛል።ግጥምን የማነበው እንዲገባኝ ሳይሆን እንድመሠጥበት ነው”
    ብዙዎች ሰለሞንን ሱሪያሊስት ገጣሚ ነው ይሉታል። በህይወቱ ዘመን መጨረሻም ሰለሞን ባልተለመደ መንገድ ሲሞት ሬሳው በእሳት እንዲቃጠል ነበር የተናዘዘው። ይህም ወጣ ያለ አመለካከት እና ፍልስፍና ለማራመዱ አንድ ማሳያ ነው።
    የሰለሞን መጨረሻ
    -----
    ፈላስፋ እና ስደተኛው ገጣሚ ሰለሞን ዴሬሳ በአሜሪካ ግዛት ሚኔሶታ ከተማ ሂዎቱን እየመራ ሳለ ባደረበት ፅኑ ህመም ሳቢያ ለ7 ወራት ሲታከም ቆይቶ ጥቅምት 23,2010 በ80 አመቱ ላይመለስ አሸልቧል። የአልጋ ቁራኛ እስከሆነበት ድረስ በሚኔሶታ ዩኒቨርሲቲ የሀይማኖት ንፅፅር መምህር የነበረው ጋሽ ሰለሞን የአንድ ሴት ልጅ አባት ሲሆን 3መፀሐፍትን ለአንባቢያን አበርክቷል። ስረዓተ ቀብሩም በኑዛዜው መሰረት በሚኔሶታ ከተማ በሚገኘው የባህር ዳርቻ ልጁ ፣ባለቤቱ እንዲሁም ወዳጆቹ በተገኙበት በግባዓተ ዕሳት ተፈፅሟል።
    ለተጨማሪ ፅሁፎች የሰዋስው መተግበሪያዎችን ያውርዱ ወይም ድረ ገፃችንን ይጎብኙ!
    sewasew.page.l...
    #ሰለሞን #ደሬሳ #ታሪክ #ኢትዮጵያ #ሰዋስው #Solomon #Deressa #History #Ethiopia #Sewasew

КОМЕНТАРІ • 3

  • @tarik3153
    @tarik3153 Рік тому +2

    Weshetam yenatu abatem endihum abatum semachew temesasay nw. Kebur yelma dheresa agotu enji wendemu adelum. Yehenen rasu selomon beandebetu tenagrual.

  • @briefbeats8738
    @briefbeats8738 Рік тому

    What is the name of the background music

  • @fikreselssiegonfa1104
    @fikreselssiegonfa1104 Місяць тому

    ዘጋቢ ጋዜጠኛ ሰለሞን ዴሬሳ በአእናቱ አባት ተጠራ እንጂ ይልማ ዴሬሳ ወንድም አይደለም