Розмір відео: 1280 X 720853 X 480640 X 360
Показувати елементи керування програвачем
Автоматичне відтворення
Автоповтор
😂
ትንቢተ ኢሳያስ 9- 6 ላይ አማኑኤል የተባለው ማን ነው ...!? የሙሥሊሙ ጥያቄና የክርስቲያኑ የመልስ እውነታ..! ሙሥሊሙ ፦ ጥያቄ አለኝ ክርስቲያኑ ፦ ጠይቅ ሙሥሊሙ ፦ ትንቢተ ኢሳ 9፥6 ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። ይህ ጥቅስ የሚናገረው ስለ ማን ነው ? ክርስቲያኑ ፦ስለ ኢየሱስ ነዋ ። ሙሥሊሙ ፦ እርግጠኛ ነህ? ክርስቲያኑ ፦ አዎ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ ተብሏል! ሙሥሊሙ ፦ በኢሳያስ ዘመን ኢየሱስ ተወልዶ ነበር? ክርስቲያኑ ፦ አልተወለደም ።ሙሥሊሙ፦ ታዲያ ጥቅሱ ልጅ ተወልዶልናል እያለ እንዴት ለኢየሱስ ነው አልክ? ክርስቲያኑ ፦ ታዲያ ለማን ነው? ሙሥሊሙ ፦ አንተን ልጠይቅህ ። ኢየሱስ በዛን ወቅት ካልተወለደ ለምን ትንቢቱ ላይ ተወለደ የሚለውን ትቶ ይወለዳል አላለም? ይህ ስለ ኢየሱስ አያወራም ።ክርስቲያኑ ፦ እኮ ለኢየሱስ ካልሆነ ለማን ነው? ሙሥሊሙ ፦ በዛን ወቅት ለተወለደው ህጻን ልጅ ። ክርስቲያኑ ፦ ምን መረጃ አለህ? ሙሥሊሙ ፦ መረጃ አለኝ እዛው ትንቢተ ኢሳያስ ላይ 8:3-4 ወደ ነቢይቱም ቀረብሁ፤ እርስዋም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች። እግዚአብሔርም። ሕፃኑ አባቱንና እናቱን መጥራት ሳያውቅ የደማስቆን ሀብትና የሰማርያን ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወስዳልና ስሙን። ምርኮ ፈጠነ፥ ብዝበዛ ቸኰለ ብለህ ጥራው አለኝ። ታዲያ ኢየሱስ አባትም ነበረው?ክርስቲያኑ ፦ የለውም ።ሙሥሊሙ ፦ ታዲያ ትንቢቱ ላይ በዛን ሰአት የተወለደው ህፃን አባት እና እናት እዳለው ይናገራል እኮ ።ክርስቲያኑ ፦ ከኢየሱስ ሌላ ኃያል አምላክ ተብሎ የተጠራ ማን አለ?ሙሥሊሙ ፦ ኢየሱስ ኃያል አምላክ በሚለው ስም መች ተጠራ ? ስሙ ኢየሱስ ነው! ሉቃስ 2 (Luke)21፤ ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ፥ በማኅፀን ሳይረገዝ በመልአኩ እንደ ተባለ፥ ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ።ሙሥሊሙ ፦ አመንክም አላመንክም ለኢየሱስ የተነበየው ይህ ነው ። እርሱም ነቢይ እንጅ አምላክ አይደለም ። ክርስቲያኑ ፦ ነቢይ ነው የሚል የት አለ?ሙሥሊሙ ፦ ዮሐንስ 8፥40 ነገር ግን አሁን ከአምላክ የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤ አብርሃም እንዲህ አላደረገም።ዮሐንስ 8፥26 የላከኝ እውነተኛ ነው እኔም" ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ አላቸው።ዮሐንስ 12፥49 እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ።ዮሐንስ 14፥24 የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም።ነቢይ ማለት ከአምላኩ የሰማውን ወደ ሰዎች የሚያስተላልፍ መልእክተኛ ነው ። ኢየሱስም ይህንን ነው ያደረገው ! ክርስቲያኑ ፦ አመሰግናለሁ ። እውነታው ይቀጥላል …✍ ሳራ ነኝ ሰለምቴዋ
😂
ትንቢተ ኢሳያስ 9- 6 ላይ አማኑኤል የተባለው ማን ነው ...!?
የሙሥሊሙ ጥያቄና የክርስቲያኑ የመልስ እውነታ..!
ሙሥሊሙ ፦ ጥያቄ አለኝ
ክርስቲያኑ ፦ ጠይቅ
ሙሥሊሙ ፦ ትንቢተ ኢሳ 9፥6 ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።
ይህ ጥቅስ የሚናገረው ስለ ማን ነው ?
ክርስቲያኑ ፦ስለ ኢየሱስ ነዋ ።
ሙሥሊሙ ፦ እርግጠኛ ነህ?
ክርስቲያኑ ፦ አዎ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ ተብሏል!
ሙሥሊሙ ፦ በኢሳያስ ዘመን ኢየሱስ ተወልዶ ነበር?
ክርስቲያኑ ፦ አልተወለደም ።
ሙሥሊሙ፦ ታዲያ ጥቅሱ ልጅ ተወልዶልናል እያለ እንዴት ለኢየሱስ ነው አልክ?
ክርስቲያኑ ፦ ታዲያ ለማን ነው?
ሙሥሊሙ ፦ አንተን ልጠይቅህ ። ኢየሱስ በዛን ወቅት ካልተወለደ ለምን ትንቢቱ ላይ ተወለደ የሚለውን ትቶ ይወለዳል አላለም? ይህ ስለ ኢየሱስ አያወራም ።
ክርስቲያኑ ፦ እኮ ለኢየሱስ ካልሆነ ለማን ነው?
ሙሥሊሙ ፦ በዛን ወቅት ለተወለደው ህጻን ልጅ ።
ክርስቲያኑ ፦ ምን መረጃ አለህ?
ሙሥሊሙ ፦ መረጃ አለኝ እዛው ትንቢተ ኢሳያስ ላይ 8:3-4 ወደ ነቢይቱም ቀረብሁ፤ እርስዋም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች። እግዚአብሔርም። ሕፃኑ አባቱንና እናቱን መጥራት ሳያውቅ የደማስቆን ሀብትና የሰማርያን ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወስዳልና ስሙን። ምርኮ ፈጠነ፥ ብዝበዛ ቸኰለ ብለህ ጥራው አለኝ። ታዲያ ኢየሱስ አባትም ነበረው?
ክርስቲያኑ ፦ የለውም ።
ሙሥሊሙ ፦ ታዲያ ትንቢቱ ላይ በዛን ሰአት የተወለደው ህፃን አባት እና እናት እዳለው ይናገራል እኮ ።
ክርስቲያኑ ፦ ከኢየሱስ ሌላ ኃያል አምላክ ተብሎ የተጠራ ማን አለ?
ሙሥሊሙ ፦ ኢየሱስ ኃያል አምላክ በሚለው ስም መች ተጠራ ? ስሙ ኢየሱስ ነው!
ሉቃስ 2 (Luke)
21፤ ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ፥ በማኅፀን ሳይረገዝ በመልአኩ እንደ ተባለ፥ ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ።
ሙሥሊሙ ፦ አመንክም አላመንክም ለኢየሱስ የተነበየው ይህ ነው ። እርሱም ነቢይ እንጅ አምላክ አይደለም ።
ክርስቲያኑ ፦ ነቢይ ነው የሚል የት አለ?
ሙሥሊሙ ፦ ዮሐንስ 8፥40 ነገር ግን አሁን ከአምላክ የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤ አብርሃም እንዲህ አላደረገም።
ዮሐንስ 8፥26 የላከኝ እውነተኛ ነው እኔም" ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ አላቸው።
ዮሐንስ 12፥49 እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ።
ዮሐንስ 14፥24 የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም።
ነቢይ ማለት ከአምላኩ የሰማውን ወደ ሰዎች የሚያስተላልፍ መልእክተኛ ነው ። ኢየሱስም ይህንን ነው ያደረገው !
ክርስቲያኑ ፦ አመሰግናለሁ ።
እውነታው ይቀጥላል …
✍ ሳራ ነኝ ሰለምቴዋ