የአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ቅበላ ፖሊሲን በተመለከተ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፡፡|with amih |

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 20 вер 2024
  • አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተማሪዎች ቅበላ አሰራርን ከ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
    አሰራሩ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ እና ልዩ ብቃት ያላቸው ተማሪዎች ማስተማሪያ ተቋም ያደርገዋል፡፡
    ይህን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተ/ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።
    ***
    ከ2017 ዓ.ም የትመህርት ዘመን ጀምሮ ስለሚተገበረው የተማሪዎች ቅበላ አሰራር ዋና ዋና ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው፣
    👉 አዲሱ የተማሪዎች ቅበላ አሰራር አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሙሉ ራስ-ገዝነት በሚያደርገው የሽግግር ሂደት አንድ አካል ነው
    👉 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ እና ልዩ ብቃት ያላቸው ተማሪዎች ማስተማሪያ ተቋም ያደርገዋል
    👉 አሰራሩ የሚተገበረው በመጪው የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲው አዲስ የቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች ጀምሮ ነው
    👉 ከፍተኛ ብቃት ያላቸው ተማሪዎች የተዘጋጀውን የመወዳደሪያ ነጥብ ፣ የመግቢያ ፈተና እንዲሁም ሌሎች መስፈርቶችን ሲያሟሉ ብቻ ወደ ዩኒቨርሲቲው የሚገቡ ይሆናል
    👉 የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ፍትሐዊ የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋት ፣ ኢትዮጵያ በመጪው ዘመን የምትፈልገውን ብቁ ምሩቃንን ለማፍራት እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ተማሪዎችን ለማዘጋጀት የሚያስችል ነው
    👉 አሰራሩ በመንግስት ወጪ የሚሸፈን የትምህርት ዕድል (ስኮላርሺፕ) እና በግል ወጪን በመሸፈን የተማሪዎችን ስብጥር በጠበቀ መልኩ ማስተናገድ እንዲያስችል ተደርጎ የተቀረጸ ነው
    👉 አዲሱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ቅበላ ስርዓት ለቅድመ ምረቃና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች በፖሊሲው እና በመመሪያው መሰረት የሚተገበር ሆኖ፣
    1. ለሴቶች፣ ለአካል ጉዳተኞች እና ከታዳጊ ክልል ለሚመጡ ተማሪዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ፍትሓዊነቱ ይረጋገጣል፡፡
    2. መንግስት ከፍተኛ ብቃት ያላቸውና ተወዳዳሪ የሆኑ ተማሪዎችን ለሀገር በሚፈለጉ የስልጠና መስኮች ወጪን ጭምር በመሸፈን የሚያስተናግድበት ስርዓት ይኖራል፡፡
    3. በገበያው እጅግ ተፈላጊ በሆኑ የትምህርት መስኮች ጥራት፣ ፍትሐዊነት እና ብዝሀነት ሳይዘነጋ በራሳቸው የትምህርት እና ሌሎች ወጪያቸውን ሸፍነው ለሚማሩ ተማሪዎች እድል ተመቻችቷል፡፡
    በ2014፣ 2015 እና 2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የመልቀቂያ ፈተና ወስደው የማለፊያ ነጥብ ያገኙ ተማሪዎች የሚወጣውን መስፈርት ታሳቢ አድርገው በዩኒቨርሲቲው ፖርታል portal.aau.edu.et መመዝገብ ይችላሉ።
    @addisababauniversityofficial

КОМЕНТАРІ • 9