አምደ ዓለም አድዋ - ኤፍሬም ወርቁ - ጦቢያ - S2Ep3_21

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 13 жов 2024
  • አምደ ዓለም አድዋ - ኤፍሬም ወርቁ - ጦቢያ - S2Ep3_21@Arts Tv World

КОМЕНТАРІ • 9

  • @mereitube5941
    @mereitube5941 3 роки тому

    Best of best poem bertalegni wondime fetari yebarkih

  • @Ethiohabtina
    @Ethiohabtina 3 роки тому

    jegna yeJegna lij. nullijn. the best poam. well done bro.

  • @enyewgonderethiopia6873
    @enyewgonderethiopia6873 3 роки тому

    how he is a good poet የኔ ውድ ወንድም በርታልኝ ዘመኖችህ ሁሉ የተባረኩ ይሁኑ

  • @abz8493
    @abz8493 3 роки тому

    👌👌👌
    ከዓመታት በፊት እንዲህ ስል ስንኝ ቋጥሬ ነበር።
    የዚህ ግጥም መነሻም አቶ ተፈሪ አለሙ በአንድ ወቅት "ቋሚ ሰው ተናገር" በሚል ርዕስ ላቀረቡት ግጥም የተሰጠ ምላሽ ነው።
    በወቅቱ በማዳምጥው ግጥምና በምስል ተደገፎ ይቀርብ በነበረው ማስረጃ ከሚገባው በላይ ልቤ ለሰማዕታቱ ክፉኛ ደምቷል። እንደዚህ አይነት ስሜት ውስጥ ስሆን ደግሞ መጫር እወዳለሁ።
    ከአክብሮት ጋር።
    **************
    ምን ቋሚ ሰው አለ
    ★★★★★★★
    ገበየሁ አባቴ፣ አዎን ብለህ ነበር
    ቋሚ ሰው፣ ተናገር
    ጀብዴን፣ ለአለም አብስር
    ክንዴ እንደሰበረ፣ የሞሶሌንን ቅጥር
    በአጭር እንደቀጨ፣ የእብሪተኛን ሚስጥር
    በደስታ እንደሰጠሁ፣ አጥንትና ደሜን ለኢትዮጵያ ክብር።
    ገበየሁ አባቴ፣ በአውነት ነው የምልህ
    እንዳንተ ፍላጎት፣ ልክ እንደ ምኞትህ
    ምንም ቋሚ የለ
    በአባላጌ ጋራ፣ በአድዋ የዋለ
    ጀብድህን ሊደግመው፣ በአፅምህ የማለ
    አደራ ያልከውን፣ ታሪክህን ሚጠብቅ
    መች ቋሚ ተገኝቶ፣ ቃልህን አድምጦ፣ በገድልህ ሚደምቅ
    ግን በተቃራኒው፣ አጥንትና ደምክን በአንድ ላይ ቀይጦ
    ሌላ ደም ሚያስከፍል፣ ቃላቶችን መርጦ
    በረቀቀ ዘዴ፣ አገር ቆርጦ ሽጦ
    ደግሞ በላዩ ላይ፣ ወደብ የሚመርቅ
    ለምን ባይ ጠያቂን፣ ወገን ሚያሸማቀቅ
    በምስጋና ፋንታ፣ ከርቸሌ ሚያማቅቅ
    ገድልህን አጥቁሮ፣ ህገመንግስት ሚያረቅ
    አገር በቁም አስሮ፣ በጎሳና በጎጥ፣ በሴራ ሚራቀቅ
    በስርቆት በአፈናው፣ በአድሎው ሚመፃደቅ
    ከጣና በለስ ትልም፣ ከዕራይ የሚያራርቅ
    እርኩስ መንፈስ በቅሎ፣ የደምህን ወጤት፣ ባንዲራን የሚል ጨርቅ
    እንኳን በክብር ሞትክ፣ ይህንን ጉድ ሳታይ
    የሀገርክን መቸብቸብ፣ የታሪክህን መጉደፍ፣ በአብራክህ ክፋይ።
    ገበየሁ አባቴ፣ ምን ቋሚ ሰው አለ
    እንዳንተ አባላጌ፣ በአድዋ የዋለ
    ገድልህን ሊደግመው፣ በስምህ የማለ
    በሚያሳዝን መልኩ፣ ቴዎድሮስ ዮሃንስ፣ ሚኒሊክ እመየን
    ዘራይና እና አብዲሳ፣ አቢቹ በላይን
    ብዙ ሰማዕታት፣ እንዳንተ እንቁዎችን
    ነፍጠኛ በማለት፣ ሚያጎድፍ ገድላችሁን
    የሀገር መጥፎ ህመም፣ ከፋፋይ ታቅፈን
    ቋሚ ሰው የት ይገኝ፣ ዘካሪ ታሪክን
    ጠባብ ትምክተኛ፣ ፊውዳል ሳይባል፣ ሚያነሳ ስምህን።
    ገበየሁ አባቴ፣ ምን ቋሚ ሰው አለ
    እንዳንተ አባላጌ፣ በማይጨው የዋለ
    ሂድ ንገር ያልከውን፣ ሚመሰክር ገድልህን
    አደራ ያልከውን፣ የጠበቀ ቃልክን
    በእውነት ነው ምልህ
    ዛሬ ላይ አላይም፣ የማለ በስምህ።
    በሚያሳፍር መልኩ፣ ጥላቻን የሚሰብክ
    ለዜጋው ማይራራ፣ ለባህድ ሚብረከረክ
    የጎጥ ዛር አጓርቶ፣ ግዑዝ ወንበር ሚያመልክ
    በብሄር ከበሮ፣ በክልል ጥሩንባ
    ናላችንን ሚያዞር፣ በነጋ በጠባ
    አፅምህን ወሮታል፣ ከፋሽሽት ሚስጥሮ
    በጊዚያዊ ስልጣን፣ በባህድ ዶላር ሰክሮ
    ወገን በቃኝ እሰኪል፣ አንገት ደፍቶ ኑሮ
    በክብር እስኪቀብርህ፣ ቋሚ ዘራፍ እስኪል፣ በዋይተህ ተማሮ።
    ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
    መታሰቢያነቱ: በህይወት ላሉ እንዲሁም ለአርበኛ ገበየሁ ጎራው፣ ለዮፍታሔ ንጉሤ እና ለሌሎችም አፅማቸው በታሪክ ጉዶች ከተቀበረበት ተቆፍሮ ወጥቶ ለአመታት በአልባሌ ሁኔታ ለተንከራተተ የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ሰማዕታት።
    ★★★★★★★★★
    ዛሬ ደግሞ እንዲህ ስንኝ ቋጨሁ።
    **************************
    ትውልድ ይታየኛል
    ★************
    ወጣት፣ ይታየኛል
    ቄሮ፣ ይታየኛል
    ፋኖ ይታየኛል
    ኮበሌ፣ ይታየኛል
    ዘርማ አለሁ፣ ይለኛል።
    በአንድ ለአምስት ሴራ፣ ሲመሽ የባተተ
    ለትህነግ ያልሸሸ፣ አልሞ ያልሳተ
    ጉግሰኛ ለመሆን፣ ነጭ ፈረስ የሻተ
    ትውልድ ይታየኛል፣ የተዛባ ታሪክ፣ የተተረከለት
    ለቅድመ አያቶቹ፣ አድዋ ለቀሩት
    በቁጨት የሚበግን፣ እውነቱን ደርሶበት
    አዎ! በሃሳብ ይነጉዳል
    በሲቃ፣ ይዋጣል
    ለሰሜን ዕዝ ጀግና፣ ለማይካድራ ንፁሃን፣ ከልቡ ይቆጫል
    ደማቸውን ሊያብስ፣ ገድላቸውን ሊደግም፣ ቃል ኪዳን ይገባል።
    አዎ! ቄሮ ይታየኛል
    ፋኖ ይታየኛል
    ኮበሌ ይታየኛል
    ዘርማ ይጠራኛል
    ነብሮ አለሁ ይለኛል።
    ማንነቱ የገባው፣ ወጣት ትኩስ ሃይል
    ጥቁር ሰውን ሚያዜም፣ አንዲት ኢትዮጵያ የሚል
    ከጠበኩት በላይ፣ ትዉልድ ይታየኛል
    ፍቅር ያሸንፋል፣ ኢትዮጵያ ቤቴ ሚል
    ብረት ሳያነሳ፣ ሴራ እያከሸፈ የተቀዳጀ ድል
    ጥበት ተጠይፎ፣ ዜግነትን ሚሰብክ
    ለእኩይ ለጉግማንጉግ፣ የማይበረከክ
    በኢትዮጵያዊነቱ ፀንቶ፣ አይዞህ ወንድሜ ሚል
    ልክ እንደ አንደበቱ፣ አነጣጥሮ ሚጥል
    የአሎሌን መርዝ ነቅሎ፣ በርግብ የታጀበ ዘንባባ ሚተክል
    ጎጠኝነት ይወደም፣ አንድ ኢትዮጵያ የሚል።
    ***-************----******
    ክብር ለኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ቅድመ አያቶቻችን፣ ፍትህ በጥቂት ጉግማንጉጎች እኩይ ደባና ሴራ በግፍ ለተሰዉ ዕንቁ የሐገር መከላከያ ሰራዊት ሰማዕታት፣ ከቅያቸው ለሚፈናቀሉ ለሚታገቱ ከትምህርት ገበታቸው ለሚጉላሉ በግፍ ለሚገደሉ በባዶ ስድስት ማሰቃያ እስርቤቶችና ጭቃኔ በተሞላበት ሁኔታ ለተገደሉና ያላግባብ በእስር ለሚሰቃዩ ኢትዮጵያዊያን ወገኖች።
    አንድ ኢትዮጵያ፣ አንድ ሕዝብ!!!
    ዔልፋዖስ ኒቐሥ

  • @fekat_tube
    @fekat_tube 3 роки тому +1

    መልኬ ብቻ ብዬ ራሴን ከምቆልል ያለኝን አቅም ልጠቀም እስኪ ሰብስክራይብ በማድረግ ልግስናችሁን ግለፁልኝ 🙏🏾💚💛❤

  • @abz8493
    @abz8493 3 роки тому

    👌👌👌
    "ወጥመድን ለወፎች በከንቱ የሚያጠምዱ
    እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉ
    ከጎዳናቸውም እግርህን ፈቀቅ አድርግ ደም ለማፍስፈሰስ ይፈጥናሉና" ታላቁ መፅሃፍ
    ★★★★★★
    " ነፃ አውጭዎቻችሁ እኛ ነን እያሉ ነፃነቱን ከሚነፍጉት ሞራለ ቢሶች፣ ነፃነቱን በተስፋ የሚጠብቅ ዜጋ ከቁራ መልክተኞችም ከራሱም በፍፁም ነፃ አይወጣም"። ከእኔ
    ምክንያቱም ወደዚች ምድር ሲመጣ በቅድመ አያቶቹ የተከሰከሰ አጥንትና የፈሰሰ ክቡር ደም ነፃነቱ ከትውልድ ትውልድ ሲወራረድ እንደመጣ ሊዘክሩለትና ሊያስተምሩት በማይሹ የጋራ ታሪክ የለንም ባዮች የባህድ የሚስጢር ኪስ የእናት ጡት ነካሾች በለጋ አዕምሮው ያልበር ማንነትና ጥላቻ በተስፋየ የኮኽን ብዕር በረቀቀና በተቀነባበረ መልኩ ሲግቱት ነፃ ሆኖ የመፈጠሩ ስብዕና በዕቡ ጉግማንጉጎች እኩይ አስተምሮ እንደማይታደለው አስረግጦ ባለመናገሩ ነው።
    ይኸንንም አይቶ እንዳላየ የሚያይ፣ እስኪያልፍ ያለፋል እያለ፣ የሚተክዝን ዜጋ፣ ትግስትና አርቆ አስተዋይነቱን፣ እንደ ፍርሃት በመቁጠር፣ ጥበት፣ የበታችነት ስሜትና ስብዕና የተጠናዎታቸው ፣ ራዕያቸው ከሃገር ልዑዓላዊነት፣ ከወገን ደህንነትና፣ በሳላም ውሎ ማደር ይልቅ፣ በጎጥ ዙሪያ፣ የልዮነት ሹርባ እየጎነጎኑ፣ ድርና ማግ ሆኖ ሚኖር ህዝብን፣ በማይቆም የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ መክተት፣ የኢትዮጵያና ህዝቦቿን ሰላምና ብልፅግና ማይሹ ባህዳንን፣ እኩይ ተልዕኮ ማስፈፀም፣ ባፈናቀሉት ወገን ስም፣ ምፅዋት መሰበሰብና፣ የህገወጥ መሳሪያ ደላላ ሆኖ፣ የስልጣን ዘመንን ማራዘምና፣ ቀፈትን መሙላት ነው።
    ለዚህም ተልዕኳቸው ደግም፣ ለምን እንዴት ስለምን፣ ወዴት ለማን ብለው የማይጠይቁ፣ ሩጠው ያልጠገቡ፣ የነገ ሃገር ተረካቢዎችን ህይወት፣ እስቀማስቀጠፍ እኩይ ሴራ ያሴራሉ። "
    **
    ፍቅር እስክንገዛ
    ★-★----★
    እንደ ዕንቁ እያየቸኝ፣ በእናትነት አይኗ ተመስጣ ሀገሬ
    እንደ ልብህ ቦርቅ፣ እንዳሻህ ኑርባት በቅድስቷ ምድሬ
    ብላ ስትመክረኝ፣ ከጎና አስቀምጣ፣ ፍቅር እየመገበች በእጆቿ ለፀጉሬ
    መች ህልሜ እውን ቢሆን፣ ብመረቅ ተምሬ
    በክልል ሸንሽኖን፣ የአንችው እኩይ ፍሬ
    ብየ መልስ እንዳልሰጥ፣ ለእምየ ለፍቅሬ
    በደሌን ስሰማ፣ ልቧ እንዳይሰበር፣ ሃዘኗ እንዳይበዛ
    ከወንድም ተፋልሜ፣ ክብሯን እያስጠበኩ፣ ለአብራክ ቅጥረኛ፣ ለሴራው ልገዛ
    እሱ ጎጥ አቅሮት፣ እኔም በፀሎቴ፣ ፍቅር እስክንገዛ።
    በየአቅጣጫው ለሚፈናቀሉ፣ በየትምህርት ተቋሙ ለሚሞቱ፣ የብሄር ፖለቲካው ሰለባዎችና ለኢትዮ ኤርትራ ተጎጅዎች።
    **
    👌 👌 👌 👌
    ከአያት የተላከ ስንኝ
    ****************
    በብሔር ብሔረሰቡ ስም፣ ላም አለኝ በሰማይ ቀፋዮች
    ነፃ ባልወጣ ነፃ አውጭ፣ ማንነትሽ የተገፈፈች
    ደም በተጠሙ ጎጠኞች፣ በእነ እኩይ ታሪክ ፈታዮች
    ዜግነት ያጣህ ወዳጀ፣ የሆንክ አጅ ተወርች
    መፅናኛ ጉልበት ይሁንህ፣ ተቀበል ከአያት ስንኞች
    ★★★★★★★★★
    የሀገር ትርጉም ሚስጥሩን፣ ገና ጠልቀህ ሳታውቀው
    ኢትዮጰያዊ ነኝ አትበለኝ፣ አፍህን በእኔ ስም አታሟሸው
    በሰማዕታት ደም አጥንት፣ በተገኘው ነፃነት
    አትደንፋበት አታቅራራ፣ አንተ ከምኑም የለህበት
    የነፃነት ተምሳሌ ነኝ፣ ቅኝ ተገዝቸ አላውቅም
    ብለህ አትፎክር በጉራ፣ በፍፁም ነፃ አይደለህም
    ፋሽስት ወራሪን አርበድብደው፣ ነፃ ቢያቆዩ ኢትዮጵያን
    ምን ተረፋቸው ሰማዕታት፣ ቅድመ አያት ምዕምናን
    በስማቸው ተመጳድቀህ፣ በገድላቸው ተኩራርተህ
    መቸ ታሪክ ስትደግም፣ ባንዲራህን ስጠብቅ ታየህ።
    እናም ልጀ ወዳጀ ሆይ፣
    በአንድ ወቅት ቅኝ ገዥዎች ቢወሩኝም፣
    የነፃነት ውጤት ነኝ፣ ባርነትን አላውቅም
    ብለህ አትደንፋ በጉራ፣ በፍፁም ነፃ አልወጣህም
    እስኪ ቆም ብለህ አስተውል፣ ጠያቂ ይሁን አይዕምሮ
    ትውልድ ለዘመናዊ ባርነት፣ በነፃ አውጭ ነኝ ባይ፣ በደላላ ተሸጋግሮ
    ወገን ክብር ተነፍጎት፣ ከቆሻሻ ጋር ተወርውሮ
    በሰበብ በአሰባቡ፣ ዜጋ ባዶ ስድስት ተጠፍሮ
    ጤንነትህ ተቃውሶ፣ ጠኔ አንጀትህ ተቀብሮ
    ማንነትህ ተገፎ፣ ስብዕናህ በረንዳ አድሮ
    ልሳንህ በአፈሙዝ፣ በአንድ ላምስት ተቸንክሮ
    የህግ ያለህም ስትል፣ ስታሰማ እሮሮ
    ለህይወትህ ዋስትና፣ ትውልድ ጎጥህ ተቆጥሮ
    ከአንተ በዕውቀት ሚያንሰው፣ በዘመድ አዝማድ ተቀጥሮ
    የመጨረሻ እጣ ፈንታህ፣ ስደት እና እንጉርጉሮ
    ያውም የዘንድሮውስ ባርነት፣ በራስህ የአብራክህ ክፋይ
    ቀየ ጎሳህን ተገን አርጎ፣ ከእድር ከቀየህ ፈንቃይ
    የእናት ጡት ነካሽ ሆኖ፣ አንዲት ሀገርህን ከፋፋይ።
    እናም ልጀ ወዳጀ ሆይ፣
    በፍጱም፣ ቀኝ ተገዝቸ አላውቅም
    የነፃነት ውጤት ነኝ፣ በባርነት አላለፍኩም
    ብለህ አትደንፋ በጉራ፣ በፍፀጱም ነፃ አይደለህም
    በእከከኝ ልከክልህ፣ ጊዚያዊ ጥቅም ተተብትበህ
    እውነታው ውስጥህ ታምቆ፣ ውሸት ከሆነ አንደበትህ
    ውስጥህ በፍርሀት ሲርድ፣ ከንፈር መምጠጥ ከሆነ ምርጫህ
    ዜጋ በግፍ ሲገደል፣ ያለ ሐጢያቱ ሲማቅቅ
    እንዴት ስለምን ብለህ፣ ያንተን የሱን መብት ሳጠይቅ
    ታዲያ በምን ሂሳብ ነው፣ እኔ ነፃ ነኝ ምትለኝ
    በሙሰኛ ዳኛ አቃቢ፣ ያለ በደሌ ወንጅለህኝ
    በውሸት አስመስክረህ፣ በቁመናየ ቀብረህኝ በፅናቴ ክፋት ቋጥረህ፣ ከእርምጃየ ገተህኝ
    መስጊድ ደብር ተደግፈህ፣
    ቁራን ዳዊት አነብንበህ፣
    ፍትህን ከልክለህኝ
    ታዲያ በምን ሂሳብ ነው፣ ነፃ ሰው ነኝ ምትለኝ።
    እናም እውነት እውነት እልሀለሁ፣ ልጀ ወዳጀ ሆይ
    ያውም የባሪያ ባሪያ፣ በምድር ብቻ ሳይሆን በሰማይ
    ግዑዝ አካልህ ከርሱን እንጅ፣ ስዕብናውን የማያይ
    ወገንህ ግፍ በዝቶበት፣ እራሱን በእሳት ሲያቃጥል
    የተቀደሰ ንፁህ ህይወት፣ ሲጣል በዱር በገደል
    ውሃ በአንድ ኮዳ የጠጣ፣ የሐገር መከታ ሰራዊት፣ በባልጀራው ሲገደል
    የነፃ ሰው ተምሳሌት ሆነህ፣
    ከጠገበው ጋር ጮቤ ሳትረግጥ፣ ጊዜ ላነሰው ሳትነጠፍ
    ከስርቆቱ ከግድያው፣ በይሉኝታ ሳትለጠፍ
    የተከፋን ልብ ሳታደማ፣ የለመለመን ሳታነጠፍ
    እውነትን እሬት ሳትቀባ፣ ውሸትን ሸልመህ ሳታቅፍ
    ለምን ማለት ስትጀምር
    ለዜጎች ነፃነት ክብር፣
    ያላድሎ ስትከራከር
    ለሀገር ለወገን ዕልውና፣ በፅዕኑ ስትፉለም
    ጎጠኝነትን አሽቀንጥረህ፣ ስለ አንድ ኢትዮጵያ ስታልም
    ብሄር ቀለም የግል ጥቅም፣ ከምናብህ ሲፀዳ
    እውነትን ምርኩዝ አርገህ፣ ስትወጣ ከጔዳ
    ሙሉ ሰው የምትባል፣ ቃልኪዳኑን የማይከዳ
    እሄኔ ነው በተዘዋዋሪም ሆነ በቀጥታ፣ ቅኝ ተገዝቸ አላውቅም
    ብለህ መመፃደቅ ያለብህ፣ በስብዕናህ ስትኮራ፣ ውስጥህን ሲሰማው ሰላም
    ጥላህን ሳትፈራ፣ ሳትኖር በቅዠት አለም
    የተቦተለከልህን ሳይሆን፣ የራስህን ራዕይ ስታልም
    እሄኔ ነው በተዘዋዋሪም ሆነ በቀጥታ፣ ቅኝ ተገዝቸ አላውቅም
    የነፃነት ውጤት ነኝ፣ በባርነት አላለፍኩም
    ብለህ መመፃደቅ ያለብህ፣ ውስጥህን ሲሰማው ሰላም።
    ********************
    ክብር ለቅድመ አያቶቻችንና መከላከያ ሰራዊታችን፣ ፍትህ በጥቂት ጉግማንጉጎች እኩይ ደባና ሴራ በግፍ ለተሰዉ ዕንቁ የሐገር መከላከያ ሰራዊት ሰማዕታት፣ ከቅያቸው ለሚፈናቀሉ ለሚታገቱ ከትምህርት ገበታቸው ለሚጉላሉ በግፍ ለሚገደሉ በባዶ ስድስት ማሰቃያ እስርቤቶችና ጭቃኔ በተሞላበት ሁኔታ ለተገደሉና በእስር ለሚሰቃዩ ኢትዮጵያዊያን ወገኖች።
    ★★
    አንድ ኢትዮጵያ፣ አንድ ሕዝብ!!!

    ዔልፋዖስ ኒቐሥ

  • @haymibelete8247
    @haymibelete8247 3 роки тому

    አቦ ብዕርህ አዪንጠፍ

  • @firduharon1179
    @firduharon1179 2 роки тому

    ephye berta jegna neh