ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካአል

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 9 лют 2025
  • welcome to" መክሊት ዘተዋሕዶ " UA-cam channel This channel is the official channel of Meklit the Tewahido" መክሊት ዘተዋሕዶ " you will find ancient Ethiopian church history, preachings ,and other videos.
    #መክሊት_ዘተዋሕዶ #ሊቀ_መላዕክት_ቅዱስ_ሚካኤል#meklit_the_tewahido
    ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል
    ኀዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ኅዳር 12 ቀን ነው፡፡ እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል፡፡(ይህን ሁለተኛውን ሹመት ያገኘው በሚያዚያ 2 እንደሆነ አክሲማሮስ በሚባለው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ አናገኛለን፡፡)
    የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ ግን አይደለም ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም ጭምር ነው ፡፡ ይህም እንደሆነ እንድንረዳ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባለውን እስራኤል ዘሥጋን ሲራዳና ሲጠብቅ እንደነበረ ተጽፎልን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ በኢያሪኮ ምድረ በዳ እንደተገለጠለት “… ዐይኑን አንሥቶ ተመለከተ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ የያዘ ሰው በፊቱ ቆመ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? አለው፡፡ እርሱም “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ” (ኢያ.5፡13) ይለናል፡፡
    ቅዱስ ዮሐንስ ስለ ቅዱስ ሚካኤል እንዲህ አለ "በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱም ዘንዶውን ተዋጉት፥ ዘንዶውም አልቻላቸውም፥ ከዚያም በኋላ በሰማይ ቦታ አልተገኘለትም። ራእ 12፤7 ነቢዩ ዳንኤልም እንዲህ አለ "በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል" ዳን ፲፪፥፩። በዚህም የመልአኩ ስልጣን በህዝቡ ላይ በሐዲስ ኪዳንም ፀንቶ እንደሚኖር ነቢዩ ዳንኤል አስቀድሞ ነግሮናል፡፡
    የመክሊት ዘተዋሕዶ ቤተሰብ ይሁኑ
    ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።

КОМЕНТАРІ • 14

  • @ሰለሁሉምነገርእግዚአ-ደ5ዐ

    አሜን እንኳን አብሮ አደረሰን 🙏🙏🙏

  • @honeylee4728
    @honeylee4728 3 роки тому +1

    አሜን አሜን አሜን ቅዱስ ሚካኤል በረከቱ አይለየን 🙏

  • @lidiyarak3151
    @lidiyarak3151 3 роки тому +1

    Amen amen amen 🙏🙏

  • @haregashimales5118
    @haregashimales5118 3 роки тому +1

    Amen kale hiwote yasmalena

  • @tigest3176
    @tigest3176 Рік тому +1

    Amene kale hiwete yasemalne

  • @yalewbelay5351
    @yalewbelay5351 3 роки тому +1

    አሜን አሜን አሜን እንኳን አብሮ አደርስን ቃለ ሄወት ያስማልን

  • @እግዚአብሔርፍቅርነው-ወ3ሸ

    አሜን አሜን አሜን እንኳን አብሮ አደረሰን" ቃለ ህይወት ያሰማልን" የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት አይለየን

  • @truwrket4049
    @truwrket4049 3 роки тому +1

    አሜን አሜን አሜን እንኳን አብሮ አደረስን ቃለህወትያስማልን

  • @sarabarca2704
    @sarabarca2704 3 роки тому +1

    የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት አይለየን 🙏❤️🙏

  • @sarabarca2704
    @sarabarca2704 3 роки тому +1

    አሜን አሜን ❤️

  • @sorik449
    @sorik449 3 роки тому +2

    ጌታ ይባርክህ ወንድም ዳኒ

  • @ሀሙ
    @ሀሙ 2 роки тому

    አሜን አሜን አሜን 💚💛❤️🙏🙏🙏

  • @haregashimales5118
    @haregashimales5118 3 роки тому +1

    Amen

  • @addamhand7991
    @addamhand7991 2 роки тому +1

    አሜን !