የእግዚአብሔር ልጅ በብሉይ ኪዳን | The Angel of The Lord | ያህዌ የእግዚአብሔር መልአክ Melos Teshome

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 26 лис 2023
  • የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን በተለምዶ ኦንሊጂሰስ በመባል የሚታወቀው ቤተእምነት በጣም አደገኛ እና መፅሀፍቅዱስን የሚፃረር የሀሰት እምነት ነው:: ኢየሱስ ኢየሱስ ይላሉ ግን የመፅሀፍ ቅዱሱን ኢየሱስ ፈፅሞ አይቀበሉም:: በወንጌል የሚያምኑ ይመስላሉ ግን የአዲስኪዳንን ወንጌል ፈፅሞ ወደጎን በማለት የራሳቸውን ሰው ሰራሽ ዶክትሪን እና ሀይማኖታዊ ህግጋቶቻቸውን ከመፅሀፍ ቅዱስ በላይ የሚያምኑ ወገኖች ናቸው:: ምእመኖቻቸውም መፅሀፍ ቅዱስን እያነበቡ ስለ አምላካቸው ከማወቅ ይልቅ ድርጅቱ እና የድርጅቱ አስተማሪዎች የሚሉትን ብቻ እንዲቀበሉ ይገደዳሉ:: ኢየሱስን መፅሀፍ ቅዱስ እንደሚለው በቅጡ ሳያምኑ እና ሳይቀበሉ የውሀ ጥምቀት የዘላለም ህይወት ያስገኛል ብለውም ያምናሉ::
    በአጭሩ መፅሀፍ ቅዱስን ያለአግባብ በአውዱ እና በስርአቱ ካለማንበብ እና ካለመረዳት የተነሳ የተፈጠረ ድርጅት "CULT” ነው:: ከዚህም የተነሳ የኢየሱስ ማንነት ላይ እጅግ በጣም ስተዋል!
    ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የወልድ እና የመንፈስቅዱስን መለኮታዊነትን የሚክድ ቤተእምነት ነው:: አንዱ እግዚአብሔር ወይም አንዱ መለኮት በአብ ፣ በወልድ እና በመንፈስቅዱስ ተገልጦ እንደሚኖር አያምኑም::
    በኦንሊጂሰስ አስተምሮ በስጋ የተገለጠው ቅዱስ የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ሳይሆን እግዚአብሔር አብ ነው:: ኦንሊጂሰሶች የወልድን ዘላለማዊነትም ይክዳሉ:: የእግዚአብሔር ልጅ ለነሱ ከድንግል ማርያም የተወለደ የስጋ ሰውነት ብቻ ነው:: ስጋውንም ሰማያዊ ወይንም መለኮታዊ ከሰማይ የመጣ ስጋ ነው እንጂ የዳዊትን ዘር በስጋ ተካፈለ ብለው አያምኑም:: (ሮሜ 1:3, ሮሜ 9:5, ዕብ 2:14, ራእይ 22:16)
    ልጁ ከዘላለም ጀምሮ የነበረ የምድር እና የሰማይ ፈጣሪ መሆኑን ይክዳሉ (ዩሀ 1:3, ዕብ 1:2, ዕብ 1:10, ቆላስያስ 1:16) የእግዚአብሔር ልጅ በስጋ ከመምጣቱ በፊት ከአባቱ ጋር ይኖር የነበረ መሆኑንም አያምኑም (ዮሀ 1:1, ዮሀ 6:38, ዮሀ 16:28, ዮሀ 17:5)
    ኦንሊጂሰሶች እባካችሁ ለእግዚአብሔር ቃል ለመፅሀፍ ቅዱስ ስልጣን ሰጥታችሁ ለህሊናችሁ ታማኝ በመሆን ቃሉን ካነበባችሁት ሳታውቁት የወደዳችሁት የመፅሀፍ ቅዱሱ ኢየሱስ በሙላት ይገለጥላቹሀል:: የኢየሱስ ማንነት ላይ መሳሳት ከዘላለም ህይወት መጉደልን ያስከትላል:: 1ኛ ዮሀ 5:12 ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። እባካቸሁ ከቃሉ ጋር እግዚአብሔር እየተማፀናችሁ ጊዜ አሳ ልፉ:: እግዚአብሔር እውነቱን ይግለጥላችሁ ወዳጆቼ!

КОМЕНТАРІ • 1