ፈረስ መልዓክ ነው፤ የቅድስና እና የነፃነት ምልክት!!
Вставка
- Опубліковано 10 лют 2025
- ፈረስ መልዓክ ነው፤ የቅድስና እና የነፃነት ምልክት ነው !!
የአገው ህዝብ የፈረስኞች ማህበር
ደገኛው ተራራ እና አቀበቱን ፣ ሜዳ እና ሸለቆውን በፈረሱ ይወጣዋል። ደገኛ እና ፈረሰኛ ኢ_ተነጣጣይ ናቸው። ፈረስ አንድም የቅድስና እና የነፃነት ምልክት ነው። ሌላም ስፓርት ነው። ፈረሰኛው ጊዮርጊስ ከአድዋ ተረክ ጋር ትስስሩ ብዙ ነው።
ነገስታት የፈረሳቸው ስም የባህሪ መገለጫቸው ነው። "የጠቅል አሽከር !" ተብሎ ይፎከራል። በሀይለስላሴ ለማለት ነው። በዝብዝ (አፄ ዮሃንስ)፣ ዳኘው (አፄ ምኒሊክ)፣ ታጠቅ (አፄ ቴዎድሮስ) ወዘተ የፈረስ ስማቸው ነው። ፈረሶች መጫኛም፣ማረሻም፣ የጦር ጀትም ሆነው አገልግለዋል። አባ ጠና ንጉስ ተክለሀይማኖት ከጎጃም እስከ ከፋ የሚሰግርበት ፈረሱ ነበር። አባ ሻንቆ ንጉስ ሚካኤል ከደሴ እስከ አሰብ ሀገር የሚቃኝበት ተሽከርካሪው ነው። በላይ ዘለቀ ከ50 ሺ ጦር በላይ ተንቀሳቅሶ ማሰባሰብ የቻለው በፈረስ ነው።
የትናንቷ ኮሶበር የዛሬዋ እንጅባራ የፈረሰኛ ማህበሯን በድምቀት እያከበረች ነው
ደጋው የጎጃም ክፍል ከጮቄ እስከ ብር አዳማ፣ ከግሽ ዓባይ እስከ እንጅባራ ፈረስ መጓጓዣውም፣ ማረሻውም፣ መጫኛውም፣ ከፈረስ ጭራ ማጌጫ መስሪያውም ነው። የአገው ፈረሰኞች በ1888 ዓም በመንገሻ አቲከም፣ በ1928 ዓም በመንገሻ ጀምበሬ ተመርተው ነፃነትን በደም ግብር ገዝተዋል። ቀዳማዊ ሀይለስላሴ በብሉናይል የሱዳን ግዛት በመተከል መሃል በአገው ምድር በኦሜድላ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። በወቅቱ እነ መንገሻ ጀምበሬ በጦር ጀት ወይም በመኪና ሳይሆን በፈረስ እየተዘዋወሩ ወራሪን እንደ አረም ነቃቅለው አካባቢያቸውን ነፃ ቀጠና ፈጥረዋል። የጃንሆይ መንገድ የሆኑት ቻግኒ፣ እንጅባራ(ኮሶበር)፣ ፍኖተሰላም ወዘተ ስያሜያቸው ከነፃነት ጋር የተያዘዘ ነው። በዚህ ነፃነት ውስጥ ፈረስ ባለውለታ ነው።
ውለታ አክባሪ የሆነው የአገው ህዝብ ፈረስን መሰባሰቢያው አድርጎ ለአዘነ ማስተዛዘኛ፣ ለተደሰተ ማጀቢያ፣ የክብረበዓላት ማድመቂያ፣ የሰላም እና የልማት መምከርያ ማህበር አድርጎ በርካታ ዓመታትን ተሻግሯል።
"የበሬን ምስጋና ወሰደው ፈረሱ
ከሗላው ተነስቶ ከፊት በመድረሱ" እያለ አርሶአደሩ በደቦው (ወንፈል)፣ በበራዮ(በውቂያው) ለፈረስ አክብሮቱን ይገልፃል።
ፈረሰኞቹ አዲናስ እያሉ ዘንገና ዳር ላይ ተሰይመዋል። የደጋው አየር ከዘንገና ውሃ እየቀዳ የባንጃን፣ የአንከሻን ፣የሺኩዳድን፣የዚገምን ምድር ያለመልመዋል። ከለመለመው ሜዳ ላይ ፈረሶች ይሰግራሉ። በፈረስ ጭራቸው አዲናስ እያሉ እንግዳ ይቀበላሉ።
እንኳን አደረሳችሁ፤ አደረሰን !! - Розваги
❤❤❤❤
አርበኝነታችን ለሰላማችን
🏇🏇🏇🏇🏇
🏇🏇🏇🏇
🛸🛸
አገውና ፈረስ
“ግንዱን፦ አንተ አባቴ ነህ፤ ድንጋዩንም፦ አንተ ወለድኸኝ ይላሉ ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡኝ፥ በመከራቸው ጊዜ ግን፦ ተነሥተህ አድነን ይላሉ።”
- ኤርምያስ 2፥27 zare degmo feres melak new alachu? Geta meheret yargelachu
ፈረስማ ከአንበሳ ይልቅ የኢትዮጵያ እንጂ አንበሳስ በልጦት ባላረመ