Ethiopia

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 26 жов 2024

КОМЕНТАРІ • 17

  • @fitsumfitse1389
    @fitsumfitse1389 2 роки тому +2

    thank you girum aterarek new

  • @ambaw1004
    @ambaw1004 2 роки тому +9

    " ከ አድር ባይ ብዕር ባዶ ወረቀት ብዙ ይናገራል "
    በዓሉ ግርማ ዕዉነት ይችላል ሥንል በምክንያት ነው። ይህንን ደራሲዉ የተሰኘዉን መጽሀፈ ወ ትረካ ፤ እዱሉ ገጥሞአቸዉ ካደመጡት ለ ጓድ :- ኮ/ሌ መንግሥቱ ኃ/ ማርያም መልዕክት አለኝ፤
    ጎበዝ እባክዎትን ይህንን ድንቅ ደራሢ በዓሉ ግርማ
    በዕርሥዎ በሚዘዉሩበት የደርግ ዘመን ወቅት ፤ የፖለቲካ ድራማ የሰራችሁበትን እና እምጥ ወይም ሥምጥ ታስገቡት የማናዉቀዉን ድራሹን ያጠፋችሁብንን የ ደራሲ በዓሉ ግርማ የመጨረሻዎቹን ገጾች ከህይወት ከመለይትዎ በፊት እንዲነግሩን ( እንዲናዘዙልን ) እናም በክብር እንድንቀብረዉ ? ሥል በትህትና እገልጻለሁ፤ ባይነግሩን ግን ጸሐፉቱ ከዚ ቀደም እንደከተበዉ
    " የህሊና ደውል " ሆኖ ይዉጋዎት ብዬ ለማለት እደፍራለሁ፤ አንትሽ እና ሙሉ በዚ ሥራ ላይ የተሳተፋችሁ ተራኪያኖች እጄን በአፌ አስጭናችሁ በምኔ ላጨብጭብ ፤
    ክ በ ሩ ል ኝ

    • @ethioemmatube
      @ethioemmatube  2 роки тому +1

      አምብሽዬ ያው ባለህ ተሰጥኦ ትረካውን በማቀናበር ለዚህ ጀግና ደራሲ ክብርህን ገለፅክለት እኮ።አንተ ባታግዘን ይጎልብን ነበር።እንጂ በአሉ ግርማማ በእንባቢዎቹ ልብ ውስጥ ዘላለማዊ ሀውልት አለው

    • @ambaw1004
      @ambaw1004 2 роки тому

      @@ethioemmatube አንትሽዬ ልክክ ያለ ልክ ነዉ ያልከዉ፤ በዓሉ ግርማ በሁላችንም ዉሥጥ ሀዉልቱን ሰርቶ ያለፈ ሰው ነዉ፤ እናንተም ሥለተረካችሁት በአድማጮች ሥም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ፤ ክፍል - 4 ላይ ሢራክ ምን ይገጥመዉ ይሆን ሆዴን ቆረጠኝ ?

    • @keludifamilyshow
      @keludifamilyshow 2 роки тому +1

      @@ambaw1004 አምብዬ የለም የለም አንተም ላይ መንፈሡ አለ😂👍

    • @danieltsega5225
      @danieltsega5225 Рік тому

      አምባው .....bro...በአሉን ደርግ አልገደለውም፥ማን እንደሚገድለው ኦሮማይ ላይ በግልጽ አስቀምጦታል፥ደጋግመህ በደንብ አንብበው።
      ይሄን የቤት ሥራ ሰጥቼሀለሁ
      ከይቅርታና ከምሥጋና ጋር

    • @ambaw1004
      @ambaw1004 Рік тому

      @@danieltsega5225 መልካም ዳንኤል ኦሮማይን አምብቤዋለሁ ። በማስተዋል ደግሜ ማየት ይኖርብኛል ማለት ነዉ ። ለጥቆማዉ በጣም ነዉ የማመሰግነዉ ።

  • @ከድራቲዩብ
    @ከድራቲዩብ Рік тому

    👍

  • @ከድራቲዩብ
    @ከድራቲዩብ Рік тому

    💚💛❤❤💋

  • @muleftamule3661
    @muleftamule3661 11 місяців тому

    § ✓Best ever ✓§

  • @keludifamilyshow
    @keludifamilyshow 2 роки тому +4

    አጃይብ ነው!!!!አማርኛ ቋንቋ አፍ መፍቻዬ መሆኑን እስክጠራጠር ድረስ የቃላት አመራረጥና አሠካክ አስደማሚ አይገልፀውም። ስም ከመቃብር በላይ ይኖራል ሲባል ተረት አለመሆኑን ተረዳሁ።በዓሉ ግርማ ሁሌም በልባችን ትኖራለህ። ግርምት ላይ የጣለኝ የአብዮቱ ዘመን ጋብቻ በእርጥብ ጫት ፊትለፊት ነው የሚጠየቀው ወይስ የደራሲው ሙድ ነው😂የዘመኑ የድርቅ ስሜት ውስጤን ተሠማኝ ስንት ወገን ረገፈ አንተነህ ወንድሜ የእትዬ አልታዬን የስራ ልምድ እና የሚቀላውጡትን ቡና ስትዘረዝረው ፅጌ በየደቂቃው የምታጠጣና የምታበላው አድባሩን ስትገልፀው አንዷ የቡናው ተካፋይ አርገኸኛል። የእእስክንድር ሰውሰራሽ ጥርስና ካፊያው ደርሶኛል😁ጥበብ አንዳንዴ ለታገለላት ለወደቀላት አትሆንም ስለዚህም ይመስለኛል አንዳንዴ በእሱ አባባል የኪነት ጀግና ጥልቅ አዋቂ ሁሌም ከእርካታ የሚርቀው ህይወት ይህቺ ናት አታገጣጥምም ድስት ግጣሙን አያጣም ፤ማለት አባባል ነው።እንጂ እውነት ቢሆን ኖሮ ይህ ደራሲ የአጥንቱ ፍላጭ ልትሆን የሚገባት ሄዋን ፅጌ ሳትሆን ፀሀይዋን በኪሴ ይዤላት በመጣሁ ብሎ የተመኘላት ሰብለ ነበረች።ልቤ መሬት ሳይወርድ አለሁ ክብርና ምስጋና በያላችሁበት ይድረሳችሁ።🙏

    • @ethioemmatube
      @ethioemmatube  2 роки тому +3

      ጥሩ ጆሮ ካለው ሰው የሚወጣ ሀሳብ ጉልበት ይሰጣል።በአሉን በዚህ መጠን ስለገለፅሽው ክብረት ይስጥልን

    • @ambaw1004
      @ambaw1004 2 роки тому +1

      ከሉዲዬ ልክክ ያለ ልክ ብለሻል ! በዓሉ ግርማ ብዕሩ ዕውነትን ለመግለፅ በትግል ላይ እንደነበረች ፤ ስሜቱን ሰው ከማንም በላይ ክቡር መሆኑን እንደገለጸች ፤ ምኞቱ በብዕሩ ለወገኖቹ ደስታን መቸር መሆኑን ፤የድርሰት ፍቅሩ የልክፍት ያህል ከድርስት እንደተቃራኘ መኖሩን ደፋርና
      አዋቂ ታላቅ የሥነጽሁፍ ሰዉ እንደነበረ በፁሁፎቹ ከእውነትና ክድርሰት ሊለየው የሚችል ሞት ብቻ እንደነበር ይህንንም ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን በብዕር ውጤቶቹ ቁልጭ አድርጎ ያሳየን ታዋቂዉ ደራሲ ዛሬ በህይወት ቢኖር ብዙ ስራዎችን ሊያካፍለን ይችል የነበረ ሲሆን የበርካታ ሰማዕታት አሟሟት ሚስጥር ሲገለጽ? የንጉሡ አዕም ከኮ/መንግስቱ ኃ/ማርያም ቢሮ ስር ተቆፍሮ ሲወጣ የ60ዋቹ የንጉሱ ባለስልጣኖች አፅም ከአዲሰ አበባ ከርቸሌ በፍለጋ ሲለቀም የእነ አቡነ ቴዎፋሊዎስ አፅም ክልዑል አስራተ ካሳ መኖሪያ ግቢ ውስጥ በቁፋሮ ሲገኝ በዓሉ ግርማ የት ገባ ?
      በመጭረሻ ለበርካታ ደራሲ በዓሉ ግርማን ለበርካታ ዓመታት መለስ ያላገኙትን ቤተሰቦቹን በተለይም ባሌቤቱንና ልጆቹን ለአንድ ደቂቃ በህሊና ጸሎት እንድናስባቸው እንጠይቃለን ፤

    • @keludifamilyshow
      @keludifamilyshow 2 роки тому +2

      @@ambaw1004 አምቤ ወንድሜ ምን እንደምል አላውቅም ስንቱን ተነጠቅን ስንቱ የህይወቱን አንድ አካል እስትንፋሡን በክብር እንኳን ሳይቀብር እንደዋዛ ከሞተበላይ ከቆመ በታች ሆኖ የህይወትን እጅግ መራራ ፅዋ ተጎነጨ ቃላት የለኝም ኢትዮጵያ ሀገራችን ድጋሚ ልትወልደው የማትችለውን በአምስት ሺ ዘመን ታሪኳ እንኳን ያልወለደችውን ስንቱን አጣችእኛም አጣን ቤት ይቁጠረው ። ነፍሳቸውንም በአፀደ ገነት ያኑርልን💔

    • @ambaw1004
      @ambaw1004 2 роки тому +1

      @@keludifamilyshow አሜን ከሉዲዬ ፤ ሁሉም እንደየሥራዉ በሰማይ ቤት ይጠየቅበታል የእጃቸዉን ያገኙታል ፤

  • @fasikafiseha7958
    @fasikafiseha7958 2 місяці тому

    የበዓሉ ድርሰት ግን ለኔ ብቻ ነው የሚለይብኝ??

    • @ethioemmatube
      @ethioemmatube  2 місяці тому

      ኧረ ለሁላችን ነው።ዘመንን ከዘመን አስታርቆ በሁሉም ትውልድ የተወደደ እኮ ነው በአሉ ግርማ
      Thankyou