የመተሐራ የጎርፍ ተጠቂዎች እሮሮ | Methara flood victims cry for help

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 16 вер 2024
  • የመተሐራ ስኳር ፋብሪካን ተንተርሳ የተቆረቆረችውን አዲስ ከተማ ቀበሌ የአዋሽ ወንዝ ክፉኛ ጎድቷታል። በቀበሌዋ የሚገኙ በርካታ ቤቶች በሃይለኛው ጎርፍ እንዳልነበር ሆነዋል። ብዙ ቤቶች ፈራርሰዋል። አጥሮች ተደርምሰዋል። በየቤቱ ያሉ ንብረቶች የውሃ ሲሳይ ሆነዋል።
    ማክሰኞ ነሐሴ 26፤ 2012 ለሊት አካባቢውን ባጥለቀለቀው ጎርፍ ምክንያት፤ በሺህዎች የሚቆጠሩ የቀበሌዋ ነዋሪዎች ከቀዬአቸው ተፈናቅለው በዙሪያ ገባው ባሉ ትምህርት ቤቶች እና በየሰው መኖሪያ ቤት ተጠልለው ይገኛሉ። ነዋሪዎቹ የዕለት ተዕለት አፋጣኝ እርዳታ እንደሚሹ በስፍራው ለተገኘው የ"ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ዘጋቢ ተናግረዋል።
    ጎርፉ ሐሙስ ነሐሴ 28፤ 2012 የአንድ መካከለኛ ሰው ወገብ ድረስ የሚደርስ ከፍታ ነበረው። ተጨማሪ ጎርፍ ይመጣል የሚል ስጋት ያላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች፤ ከውሃ የተረፉ ንብረቶቻቸውን ለማዳን ሲረባረቡ ታይተዋል። በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ብዙዎቹ ተመሳሳይ ጥያቄ ያነሳሉ፦ “መንግስት ከወዴት አለ?” የሚል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
    የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎቻችን ለመከታተል፦
    ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider...
    ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
    ትዊተር ፦ / ethiopiainsider

КОМЕНТАРІ • 4

  • @yosephyohannes4035
    @yosephyohannes4035 4 роки тому +2

    እባካቹሁ ያቅማችንን እናድርግላቸው ...?

  • @etubayeh924
    @etubayeh924 4 роки тому

    fetari bekachu yebelen enji zenderoma egzooo yamale betam

  • @Allmma-ko3pw
    @Allmma-ko3pw 4 місяці тому

    😢😢😢😢😢

  • @اولاديمنعيونياحبكممنقلبي

    አረ የመንግስት ያለህ !!!!!
    ህዝብህ እንዲህ እያለቀሰና፡እየሞተ ስለፖለቲካ ምን ይሉታል?
    አረ አላህ ሆይ ባቃ በለን የዘንድሮው የውሀ ጉዳት በሁሉም ሀገር ነው። ያረብ በምህረትህ አኑረን።