1-2 ዓመት ላሉ ልጆች የምግብ አማራጭ እሮብ | 1- 2 years toddlers meal plan Wednesday

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 7 лют 2025
  • እሮብ
    1-2 ዓመት ላሉ ልጆች የምግብ አማራጭ
    ቁርስ
    ግብዓቶች
    ስኳር ድንች
    አፕል
    አሰራር
    ስኳር ድንቹን እንቀቅለዋለን፡፡ ከትፈን ከ አፕል ጋር ማቅረብ
    ምሳ ሩዝ በአትክልት
    ግብዓቶች
    ሩዝ፣ ካሮት ፣ ጎመን ፣ ቦለቄ ፣ ነጭ ሽንኩርት ፣ ከሙን ፣ ዘይት ፣ ጨው
    አሰራር
    1. ቦለቄ ለቅመን አጥበን ዘፍዝፈን እናሳድራለን፡፡
    2. ቦለቄውን ውሃውን እናጠለዋለን ፣ እንቀቅለዋለን፡፡ መጥበሻ ላይ ዘይት ካጋልን በኋላ ከሙን (በጣም ትንሽ ) ጨምረን አመስ አመስ እናደርገዋለን ፡፡ ቦለቄውን ጨምረን ትንሽ እንቆላዋለን፡፡
    3. ነጭ ሽንኩርት በዘይት እናቁላላለን፡፡
    4. ካሮት እና ጎመን ጨምረን እናበስላለን፡፡
    5. ውሃ ከከለስነው በኋላ እስከሚፈላ እንጠብቃለን
    6. ሩዝ ጨምረን እናበስለዋለን ሩዙ ከበሰለ በኋላ አውጥተን ትንሽ ቀዝቀዝ ካለ በኋላ ቦለቄውን እንደባልቀዋለን፡፡
    እራት የምስር ሾርባ
    ግብዓቶች
    ምስር ፣ ነጭ ሽንኩርት፣ እርድ ፣ ዘይት ፣ ውሃ ፣ ጨው
    አሰራር
    1. ነጭ ሽንኩርት በዘይት እናቁላላለን፡፡
    2. ምስሩን ጨምረን አብረን እናቁላላዋለን፤ ድስታችን መያዝ ሲጀምር ውሃ እንከልሰዋለን፡፡
    3. ምስሩን በደንብ እስኪበስል እንጠብቃለን፡፡

КОМЕНТАРІ • 3