ዓቢይ ዜማ ተሰምዓ በሰማይ ዲበ መንበሩ እንዘ የዓርግ ወልድ/፪/ ኲሎሙ መላዕክት ትንሣኤሁ ዘመሩ መላዕክት ሱራፌል ወኪሩቤል/፪/
Вставка
- Опубліковано 1 січ 2025
- ዕርገተ ክርስቶስ
ስለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት ቅዱስ ዳዊት «አምላክ በዕልልታ እግዚአብሔር በመለከት ድምጽ ዐረገ ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ» በማለት በትንቢት መነጽርነት ተመልክቶ በመንፈስ ዘምሯል። ይህም ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ከሙታን ተለይቶ በተነሳ በአርባኛው ቀን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ቢታንያ ይዟቸው ሄዷል።ሉቃ 24፡50 ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት ለደቀ መዛሙርቱ በተለያየ ቦታ ተገልጾ ታይቷቸዋል። ትምሕርትም አስተምሯቸዋል። «ኢየሱስ የመረጣቸውን ሐዋርያትን በመንፈስ ቅዱስ ካዘዛቸው በኋላ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ ያደርገውና ያስተምረው ዘንድ ዐርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግስት ነገር እየነገራቸው በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ህያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው»ሐዋ 1:3። በነዚህ ቀናት ውስጥ ጌታችን ሥርዓትን አስተምሯቸዋል። ቤተ ክርስቲያንም ይህንን ትምሕርት ኪዳን ብላ ትጠራዋለች። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ ለሐዋርያት የነገራቸው መጽሐፈ ኪዳን ይባላል ፡፡