🔴የአገልግሎት ክፍያ ከ5 አመት ላነሰ አገልግሎትም ይከፈላል

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 15 жов 2024
  • #laborlaw
    #severancepay
    #tax
    #dollar
    #forex
    #nbe
    የስንብት ክፍያ የሚገባው ሠራተኛ
    የሙከራ ጊዜውን የጨረሰ እና የጡረታ አበል ለመቀበል ብቁ ካልሆነ
    1) ድርጅቱ በመክሰሩ ወይም በሌላ ምክንያት ለዘለቄታው በመዘጋቱ የሥራ ውሉ ሲቋረጥ፤
    2) በሕግ ከተደነገገው ምክንያት ውጭ በአሠሪው አነሳሽነት የሥራ ውሉ ሲቋረጥ፤
    3) በአንቀጽ 29 መሰረት ሠራተኛው ከሥራ ሲቀነስ፣
    4) በአሠሪ ወይም በሥራ መሪ ወሲባዊ ጥቃት ወይም ትንኮሳ የተፈፀመበት እንደሆነ ወይም ድርጊቱ በሌላ ሠራተኛ እንደተፈፀመ ሪፖርት ተደርጎለት አሠሪው ተገቢውን እርምጃ ባለመውሰዱ ሠራተኛው የሥራ ውሉን ያቋረጠ እንደሆነ፤
    5) አሠሪው በሠራተኛው ላይ ሰብአዊ ክብሩንና ሞራሉን የሚነካ ወይም በወንጀል ሕጉ መሠረት የሚያስቀጣ አድራጎት በመፈጸሙ የተነሣ ሠራተኛው የሥራ ውሉን ያቋረጠ እንደሆነ፤
    6) አሠሪው ለሠራተኛው ደኅንነት ወይም ጤንነት የሚያሰጋ አደጋ እንዳይደርስ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት እርምጃ ባለመውሰዱ የተነሳ ሠራተኛው የስራ ውሉን ሲያቆርጥ፤
    7) ሙሉ ወይም ዘላቂ የአካል ጉዳት በመድረሱ ሠራተኛው ሥራ ለመሥራት አለመቻሉ በሕክምና ተረጋግጦ የሥራ ውሉ ሲቋረጥ፤
    8) ቢያንስ አምስት ዓመት በአሠሪው ዘንድ የሥራ አገልግሎት ኖሮት በህመም ወይም በሞት የሥራ ውሉ ሲቋረጥ ወይም በሥራው ላይ የሚያስቆይ ከሥልጠና ጋር የተያያዘ ለአሠሪው የውል ግዴታ ሳይኖርበት ሥራውን በገዛ ፈቃዱ ሲለቅ፤
    9) በኤችአይቪ/በኤድስ ህመም ምክንያት በራሱ አነሳሽነት የሥራ ውሉን ያቋረጠ እንደሆነ፤

КОМЕНТАРІ • 4

  • @ggezahegngosse664
    @ggezahegngosse664 5 днів тому

    የስራ መሪ ማለት ማንኛዉም ኃላፊ ማለት ነዉ ወይም በአዋጅ የተገለጸዉን ኃላፊነት መሰረት ሥልጣን ያለዉ ነዉደ

    • @BekoTube-BM
      @BekoTube-BM  5 днів тому

      በአዋጁ የተገለፁትን ስራዎች የማድረግ ስልጣን ያለው ነው

  • @yegezukebede
    @yegezukebede 5 днів тому

    አንድ ሰራተኛ ከ10 ዓመት በታች አገልግሎ ጡረታ ቢወጣ ጡረታ ይከፈለዋል? 14:52

    • @BekoTube-BM
      @BekoTube-BM  4 дні тому

      ከ10 አመት በታች ያገለገለ ሰራተኛ እድሜው ለጡረታ በመድረሱ ወይም በህመም ምክንያት ማንኛውንም ደመወዝ ሊያስገኝ የሚችል ስራ መስራት እንደማይችል በህክምና ቦርድ ከተረጋገጠ የአንድ ጊዜ የዳረጎት ክፍያ ይሰጠዋል:: የዘለቄታጡረታ አበል መብት ግን አይኖረውም