Skylight Hotel Beautiful Night Addis Ababa Ethiopia

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 18 вер 2024
  • የማይከናወን ሀሳብን እግዚአብሔር አምላክ በልቦናችን አያኖርም! የዛሬ ስድስት አመት ስፈራ ስችር በልቤ ያለውን በአንደበቴ አጋራሁት። እንሆ ከስድስት አመታት በኋላ ሀሳቡ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ሀሳብ ሆኖ ኖሮ ለሚሊዮኖች ለመጋባትና በውስጣቸው ቤቱን ሰርቶ ለመኖር ጉዞውን አንድ ብሎ ጀምሯል #መቅደስ_የልጆች_ አድማስ
    #ተስፋችን_በልጆቻችን! የሚል መሪ ቃልን አንግበን የነገ ተሰፋ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያዊያን ልጆቻችንን በልዩ ሁኔታ አሳድገን የሀገር ተረካቢዎች ለማድረግ ጉዞአችንን አንድ ብለን ጀምረናል።
    ወዳጆቼ!
    የነገ ሀገር ተረካቢ ኢትዮጵያውያን ልጆች ጉዳይ የማያሳስበው ኢትዮጵያዊ አይኖርም። እኛም እንደ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ከዘርፈ ብዙ ችግራችን ላይ አንዱን መዘን አውጥተን በተባበረ ክንድ መፍትኼ ለመስጠት ነው#መቅደስ_የልጆች_አድማስ ያቋቋምነው። ዋናው አላማችን በዕውቀታቸው የዳበሩ፣ በስነምግባር የታነፁ፣ ማንነታቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁና በአስተሳሰባቸው የዳበሩ የነገ ሀገር ተረካቢ ኢትዮጵያዊ ልጆችን ኮትኩቶ ማሳደግ ነው።
    ላለፉት ረጅም አመታት ማህበረሰቤን በተለያየ መስክ በማገለግልበት ሰዓት ልበ ሩህሩህነቱን፣ ለጋስነቱን፣ ለመልካም ነገር የመተባበር አቅሙን በሚገባ አይቼዋለሁና ይኼንን ፕሮጀክት በኢትዮጵያዊ አንድነታችን ተባብረን ከዳር እንደምናደርሰው ልበ ሙሉ ነኝ። በመልካም ሀሳብ ውስጥ እግዚአብሔር አምላክ ስላለ እንደሚከናወን እርግጠኞች ነን።
    መጋቢት 26 በስካይላይት ሆቴል ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ተገናኝተን በእቅዶቻችን ላይ ተወያይተን፣ ተመራርቀን ማዕከላችንን በይፋ ወደ ሰራ እናስገባለን! ይኼንኑም ስራ የተሳካ ለማድረግ ህዝባቸውን በተሰማሩበት ዘርፍ በማገልገል የራቸውን አስተዋፅኦ እየተወጡ ያሉ ወዳጆችን በካፒታል ሆቴል እንዲገኙ በማድረግ #የእንደራሴነት ሀላፊነትን ሰጥተን ወደ ማህበረሰብ ከአደራ ጋር ልከናቸዋል። ሀላፊነታቸውን በሚገቤ እንደሚወጡ እርግጠኞች ነን።
    በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር የምትገኙ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ በቅርቡ የዚህ ታሪካዊ ፕሮጀክት አካል የምትሆኑበትን የገቢ ማሰባሰቢያ መንገዶች
    ይፋ እናደርጋለን።
    #መቅደስ_የልጆች_አድማስ
    #ተሰፋችን_በልጆቻችን!

КОМЕНТАРІ • 1

  • @ሜና
    @ሜና 5 місяців тому

    ❤❤❤