አንተ ብቻ ና || ዘማሪት ህሊና ዳዊት || Gospel Singer Helina Dawit @ARC

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 23 гру 2024

КОМЕНТАРІ • 1,2 тис.

  • @Abiyot_Gurasho
    @Abiyot_Gurasho 7 місяців тому +402

    ይህች ልጅት በዘመኑ ከበዛው ከግርግሩ መሀል አንዴት አምልጣ ይህንን ድንቅ መልአክት አንደተቀበለች ይገርመኛል። Let God multiply this amazing blessing! Amen!!!!

  • @bamatube2745
    @bamatube2745 7 місяців тому +432

    በየደቂቃው እየመጣው የምሰማው እኔ ብቻ ነኝ

  • @TatiDn23
    @TatiDn23 7 місяців тому +562

    ብትሰጠኝ ምንም ነገር
    ሀገር ምድሩ ቢነጋገር
    በዚያ ብዙ አልገኝም
    ከአንተ በልጦ አይሞቀኝም
    በዘመኔ ላትሆን ተራ
    መሀላ አለኝ ከነፍሴ ጋራ
    እኔ አንተኑ ተርቤያለው
    አንተን ደግሞ ጠግቤያለው
    አብርሀም ቤት ይሳቅ ሲመጣ
    መቼ ተተካ ያንተ ቦታ
    እጅ አይበልጥም ከፊት ፈገግታ
    አይቀልም ሰጪ ከስጦታ
    ሙሴ ከነዓንን ባይወርስም
    አለ እንደ እግዚአብሔር ያለ የለም
    ማጉረምረም ማዘን መች ቻለበት
    ማር እና ወተት ሆነህለት ❤❤❤❤

  • @lelabelete7905
    @lelabelete7905 7 місяців тому +289

    ጌታ ሆይ ለኔ ይሄ መንፈስ ያስፈልገኛል 😭😭😭😭😭

  • @haymanotgetachew8294
    @haymanotgetachew8294 7 місяців тому +441

    ብዙ ግዜ ኮሜንት ለመፃፍ ጎበዝ አይደለሁም ለዚኛው መዝሙር ግን ዝም ማለት አልቻልኩም መንፈሳዊ ነገር ሁሉ በእግዝያብሄር ቃል መሰረቱን ሲያረግ ስጋን አልፎ ልብን ይነካል ከሰማሁ ሰዓት ጀምሮ እንባዬ እንደመጣ ነው😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭 እህቴ እግዚያብር ይባርክሽ ፀጋውን ያብዛልሽ !!

    • @chuchuabayalemu5657
      @chuchuabayalemu5657 7 місяців тому +7

      😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊

    • @BirtukanBelete-v5x
      @BirtukanBelete-v5x 7 місяців тому

      😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊

    • @mekebebsemegne1710
      @mekebebsemegne1710 5 місяців тому +3

      እዉነት ነው።

    • @aschalewteshome8332
      @aschalewteshome8332 4 місяці тому +2

      ይሄ ኮሜንት አይደለም በጣም ተመችቶኝ ነው ያነበብኩት መዝሙሩን የሚመጥን አገላለፂ ሁላችንንም ጌታ ይባረከን ይሄንን መዝሙር ቀኑን ሙሉ ነው እየሰማውት ያለው

    • @freweynibulajehad9031
      @freweynibulajehad9031 2 місяці тому

      ❤🎉❤🎉❤🎉❤

  • @ewnetuyohannes4880
    @ewnetuyohannes4880 7 місяців тому +240

    ምን አይነት መረዳት ነው ። ዝማሬዎች ሀሉ ሰው ፣ቁስ፣ ምድር ተኮር በሆኑበት በዚህ ዘመን ፤ ሰማያዊ ፣ መንፈስ ቅዱስ የሚታይበት ፣ ክርስቶስ ተኮር ሲሆን ከዚህ በላይ ምን ደስታ አለ? ክብሩን ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ይወሰድ። አሜን።

    • @birkeboku4248
      @birkeboku4248 7 місяців тому +10

      ጌታ በደሙ ይሸፍንሸ

    • @AbigiyaYidnekachew
      @AbigiyaYidnekachew 7 місяців тому +1

      ❤❤❤❤

    • @kamnal4716
      @kamnal4716 5 місяців тому

      Ewunet nwu siletesexat menfes seciwu yibarek

    • @mesfinlemma5209
      @mesfinlemma5209 4 місяці тому

      እረ እንደው ዝላዩን ትተውት በመረጋጋት ቢያስነልኩን

    • @EtuEyesusgetanew
      @EtuEyesusgetanew 4 місяці тому

      Yene konijo ye zemenu kifat layagegnshi be Eyesus demi teshefegn

  • @betofantaye2388
    @betofantaye2388 7 місяців тому +546

    😭😭😭 የሚያሳስበኝ ይህ መዝሙር ስንቶቻችን ይገባን ይሆን የሚለው ነው!!!

    • @betelehemkebede1136
      @betelehemkebede1136 7 місяців тому +30

      በጣም

    • @NelomaNeloma
      @NelomaNeloma 7 місяців тому +12

      በትክክል

    • @misganawthomas5414
      @misganawthomas5414 7 місяців тому +85

      ከራስ ይጀምራል ፣ ሌላውን እግዚአብሔር ይደርሰዋል!!

    • @annaalemu7736
      @annaalemu7736 7 місяців тому +15

      እውነት ነው አንዳንዴ ቢገባንም መዝሙሩ ተጀምሮ እስኪያልቅ ብቻ የሚቆይይሆናል

    • @betofantaye2388
      @betofantaye2388 7 місяців тому

      @@annaalemu7736 ይሔ መንፈስ ጓዳችን ድረስ ይከታተለን

  • @Idont7dan
    @Idont7dan 7 місяців тому +310

    ይህን የአምልኮ ዘይቤ እንደ እኔ ነፍቆት የነበረ ማነው? ጉባኤው ዝግ ብሎ በፀሎት መንፈስ መልእክት መስማት የጥንቱ የቤተክርስትያን ምርኮ እየተመለሰ ይመስለኛል፡፡ ጊዜው ይጠብቅ እንጂ ለካ እግዚአብሔር ትውልድ አለው ፡፡

    • @godisgood2672
      @godisgood2672 6 місяців тому +3

      አሜን እግዚአብሔር በዘመን ሁሉ ቅሬታዎች አሉት

    • @yemeserashgebreyes6628
      @yemeserashgebreyes6628 6 місяців тому +1

      Melkitu yigbak eji bebotaw yesu simu mewedesun minew tezenega ere le akakir giza ayinuren kirsitiyanoch 🤦🏾‍♀️ yiker yibelen

    • @GenetmeseleGenet
      @GenetmeseleGenet 5 місяців тому

      ❤❤❤❤❤❤❤​@@godisgood2672

    • @misgegirmaf5896
      @misgegirmaf5896 4 місяці тому

      0😊😊😊😊😊😊😊000😊😊😊😊00!0​@@godisgood2672

  • @selamfikir8454
    @selamfikir8454 7 місяців тому +179

    ልሳንሽን ካጣፈጠው ጌታሽ ጋር ይለቅ ዘመንሽ!!

  • @MarryJo-j7r
    @MarryJo-j7r 3 місяці тому +68

    😢😢😢እኔ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነኝ ለእኔ የዘመርሽ እስኪመስለኝ ነው የምሰማው ኡፍ😢😢ተባረኪ

    • @getachewtadesse6594
      @getachewtadesse6594 2 місяці тому +5

      የኔ እህት፦ ሰላምሽ ይብዛ፥ እንዲህ ዓይነቱ አምልኮ የሚቻለው በቅዱስ እና ሕያው አምላክ መንፈስ ብቻ ነው። ሰው በሥጋ አቅሙ እግዚአብሔርን ማምለክ ፈፅሞ አይችልም። በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ትልቁን አምላክ ማምለክ ደግሞ በጥንታዊቷ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርሰቲያንም የነበረ ለመሆኑ፣ በየትኛውም የዓለም ክፍል የሌሉት የቅዱስ ያሬድ ዝማሬዎች ይገልጡልናል።
      አሁንም ሕያው አምላክ የጥንቱን አምልኮ መልሶልን ሁሉም የሥላሴ አማኞች ( ኦርቶዶክስ፣ ወንጌላውያን ) ተባብለን ሳንለያይ ቅዱሱን ጌታ የምናመልክበትን ጊዜ እንዲያመጣልን በጸሎት መማፀን ይገባናል።

    • @israelalge
      @israelalge Місяць тому +1

      ጌታ ኢየሱስ ክርሰቶስ በጣም ይወድሻል መጽሐፍ ቅዱስ አንብቢ እውነትን ታውቂያለሽ እውነትም ነጻ ያወጣሻል ተባረኪልኝ

    • @tagay-ef3qs
      @tagay-ef3qs 8 днів тому

      እውነቱ ያለቤት ቃሉን ስለዘመረች ነው ወስጥሽን የነካው። የቆምሽበትን ከቃሉ አንፃር እይው።

  • @Peak.570
    @Peak.570 7 місяців тому +144

    ብትወድ በሀይለኛው ንፋስህ
    ብትወድ በነበልባል እሳትህ
    ብትወድ ዝም ባለው ፀጥታህ
    ብተወድ በትንሿ ኮሽታህ
    ብቻ አንተ ና ብቻ አንተ ና

    • @tadalechzewuda4774
      @tadalechzewuda4774 7 місяців тому +4

      ❤❤❤❤

    • @mahletmekete5309
      @mahletmekete5309 3 місяці тому +2

      ብትወድበሃይሌ ንፋስ
      ብትውድ በነበልባልአሳት
      ብትወድ ዝም ባለው ትትታህ
      ብትወድ በትንሻ ጮሽታ 😊🥲😘🥹😇😊😉🙂🛐✝️🇪🇹

  • @meseeretdemeke5824
    @meseeretdemeke5824 7 місяців тому +165

    ምን አይነት መረዳት ነው ጌታ ለዘላለም ይባርክሽ እልፍ ሁኝ እንዳንቺ ያሉ ይብዙልን

  • @Zebiba-k2j
    @Zebiba-k2j 3 місяці тому +13

    😢በጌታ ፊት ስሰማው ይሄን መዝሙር አለማልቀስ አልችልም ምን እንላለን ጌታ ይባረክ❤

  • @ዲቦራየንጉሥልጅነኝ
    @ዲቦራየንጉሥልጅነኝ 7 місяців тому +18

    😭ወይኔ ማነው ክርስቶስ በአካል ቤቱ የገባ በዚህ አምልኮ አጠገቤ እንዳለ ታወቀኝ በልቤ ተንበርክኬ በእግሮቹ ሥር አባ የኔ ውድ እያልኩ ያመለኩበት አምልኮ አቤት ህልውና አቤት የጌታ መገኘት ይታወቀኛል የልብሱን ጨርስ ይዤ አለቅም አትተወኝ አባ አብሬህ ልሁን አትሂድብኝ የቤት መስሶ የቤት ውበት የቤቴ ማረግ የቤት ብርሃን ድምቀት ማእረጌ የቤቴ ውበት ና በቤቴ ክረምት አትሂድብኝ የኔ ድምቀት ውበቴ ሞገሴ እኔኮ ያለ አንተ ባዶ ነኝ አሳ ከውሃ ወጥቶ ሊኖር እንደማይችል እኔንደዛው ነው የኔም ሕይወት ያለአንተ ህልውና አይተነፈስም አያይም አይሰማም አይኖርም አባ እናቴም አባቴም መካሪዬ ወዳጄ የቅርቤ መድረሻዬ መነሻዬ መውጫዬ መግቢያዬ ምርጫዬ ነህ ለዘላለም ከአንተ ወዴትም አልሄድም የድምቀት አለሜ ነህኮ አባ ወዴት ነው ያለህው ጌትዬ ጌታዬ እረ ማን ብዬ ልሰይምህ ምንም አልገደለምko አንተ ቤቴ ገብተህ ያልተቀበልኩት አንድም የለም ከእጅህ ያልስጠህኝ ምንም የለም የኔ አይን መንገዴ ለአንተ ይባል እንጂ ልቤን ውሰድ አባ ልቤን ብቻ ነው ልሰጥህ የምችል ሌላ የሚመጥን አንድም የለም በኔ ዘንድ የማይገባኝን ሕይወት የሰጠሕኝ የምታኖረኝ ተጠንቅቀህ. ወይኔ ዝማሬ አለ በዚህ አምልኮ ክርስቶስ ራሱ ነው በቤቴ ገብቶ የሚንጎዳጎደው ሃሌሉያ የሰላም አለቃ 🙏🏻

  • @dayemotegegn1031
    @dayemotegegn1031 Місяць тому +4

    ዘመንሽ አይበላ❤❤❤❤❤❤❤የድሮ የአምልኮ ስርዓት❤❤❤❤❤❤ ግርግር የሌለበት ምዕመንን ሁሉ በእንባ ያራጨ አምልኮ❤❤❤❤❤❤ ዝለሉ .. አውለብልቡ ... የሌለበት ጸጥታ የሞላበት ግሩም አምልኮ❤❤❤❤

  • @momydady8357
    @momydady8357 7 місяців тому +65

    አሁን ጊዜው ነው እሱ ብቻ ሊዘመር ሊወራ ሊተረክ !!! ኢየሱስ ጌታ ነው!!!

  • @daniellambebo244
    @daniellambebo244 7 місяців тому +62

    በዘመን መካከል እግዚአብሔር ሰው አለው

  • @NelomaNeloma
    @NelomaNeloma 7 місяців тому +68

    ህሉዬ ይህ መንፈስ፣ ይህ መረዳት፣ይህ ፍለጋ አይወሰድብሽ !
    አንቺ እንደ ቃሉ አሁን ላለችው የምድሬ ቤተክርስቲያን የተሰጠሽ ስጦታ ነሽ ፣ በምሳሌነትሽ ቀጥይ፣ ፀጋው ይብዛልሽ!

  • @Deborah-Sisay.
    @Deborah-Sisay. 7 місяців тому +84

    በዘመኔ ላትሆን ተራ መሀላ አለኝ ከራሴ ጋራ🥹🥹🙌🏼

  • @AsseTaye-m3l
    @AsseTaye-m3l 5 днів тому +1

    ዘመንሽ ይለምልም እንዲህ ስክን ብለሽ የሚገርም ወደ እግዚአብሔር የሚያስጠጋ በእውነት በመንፈስ እንዳመልክ ሆኖልኝ ነው ነብስ አልቀረልኝም እንደሚባለው ከፍ በይ በመንፈስ ፍሬ ያትሰፍርፍሽ ለበረከት ሁኚ ጌታ እሱ ብቻውን ይምራሽ ያሳድግሽ ከዘመኑ ግርግር ይሠውርሽ😍❤

  • @saramaskram2849
    @saramaskram2849 7 місяців тому +45

    ተባረኪ ዘመንሽ ይለምልም ጅማሬሽን ያሳምረው አምላክ ፍጻሜሽን ያሳምርልሽ ዘመነሽ በቤቱ ይልቅ በኢየሱስ ስም

  • @meskerembati768
    @meskerembati768 6 місяців тому +68

    ከጌታ እግር ስር የዋለ ንግግሩ ዝማሬው ያስታውቃል ተባረኪ እህቴ

  • @SA-vh2gv
    @SA-vh2gv 6 місяців тому +19

    በልቤ ውስጥ ለዘላለም
    ያንተ ቦታ ለብቻው ነው
    በቃሚነት በዋናነት
    ፊትህን ነው የምፈልገው
    ለኔ ስኬት ልምላሜ
    ካንተ አንፃር ነው እሚወሰነው
    ሰማዮ እንኳን የሚናፍቀኝ
    አንተ በዛ ስላለህ ነው
    በቤቴ ውስጥ ለዘላለም
    ያንተ ዙፋን ለብቻ ነው
    በቋሚነት በዋናነት
    ሳቅህን ነው እምፈልገው
    በልቤ ውስጥ ለዘላለም
    ያንተ ቦታ ለብቻ ነው
    በቋሚነት በዋናነት
    ፊትህን ነው እምፈልገው
    ለኔ ስኬት ልምላሜ
    ካንተ አንፃር ነው የሚወሰነው
    ሰማዬ እንኳን የሚናፍቀኝ
    ሞልተህ በዛ ስላለህ ነው
    ለኔ ስኬት ልምላሜ
    ካንተ አንፃር ነው የሚወሰነው
    ሰማዮ እንካን የሚያጓጓኝ
    አንተ በዛ ሳለህ ነው
    ስጠኝ ምንም ነገር
    ግን አንተን የሚከተል
    ስጠኝ ውድ ነገር
    ግን አንተን የሚከተል
    ክበር ከጄ ወስደህ
    ግን አንተን አስቀርተህ
    ክበር ከጄ ነጥቀህ
    ግን አንተን አስቀርተህ
    ስጠኝ ምንም ነገር
    ግን አንተ ላይ የሚጨመር

  • @Addis-d3z
    @Addis-d3z 7 місяців тому +64

    እንደ ዳንኪራ ቤት ከዝላይ ከጭፈራ ከዳንስ ከወላይትኛ ጭፈራ በአምልኮ ስም ተዋርደን አፍረንነበር !!! ጌታ ይባርክሽ !! ድሮ እኮ ጴንጤ ይከበር ይታመን ነበር ዘንድሮ አንገት ደፋን

  • @balehtedeset2447
    @balehtedeset2447 7 місяців тому +33

    ⚠️ ወላሂ እንኳን (የመዝሙሩ መልእክት) ኮሜንቶቹ አስለቀሱኝ እግዚአብሔር ይበባርክሽ ይባርካችሁ🔆

  • @hamerenterteiment7077
    @hamerenterteiment7077 7 місяців тому +57

    ሰማዩ ሚናፍቀኝ አንተ እዚያ ስላለህ ነው

  • @tsionyilma5684
    @tsionyilma5684 7 місяців тому +52

    ኢየሱስን ማፍቀር ደስስስስስ ሲል,ለዚህ አለም ጅል ያስመስላል, ሰማይ ሲያየን ደግሞ ዋው ጠቢብ ይለናል❤❤ ኡኡኡኡኡኡኡ ኢየሱሴ እወድሀለው።

  • @heyabeltube4862
    @heyabeltube4862 7 місяців тому +47

    ስጠኝ ምንም ነገር
    ግን አንተን የሚከተል
    ሀሌሉያ🥰🥰🥰

  • @bezytube1997
    @bezytube1997 7 місяців тому +88

    እህቴ ሂሉ የስንቶቻችንን ልብ እንደነካሽ በመዝሙሮችሽ ብዙ ደቀመዝሙር አፈርተሻል ብቻ እኔ ብቻ አልሆንም እርግጠኛ ነኝ። ዘመንሽ ይባርክ ያንቺስ ጸጋ ይላያል (ልዩ) መገለጥ ነው ያለሽ :: በኛ ትውልድ እግዚአብሔር ሰውን ይጣ ወይ ብዬ እፈራለሁ ግን ለካ ለእግዚአብሄር ሰው አለ። ጸጋሽ፣ አይለይ፣ ዝላቅ፣ ሂጂ፣ ለምልም ❤❤❤❤

  • @ferhiwotsolomon1467
    @ferhiwotsolomon1467 7 місяців тому +112

    ልቤ ወደ ጌታዬ ፈሰሰ ፣፣፣ ተባረኪ የኔ ውድ እህት በሰማሁት ሁሉ ቁጥር ፀልይ ፀልይ ይለኛል እናም እንበረከክና አለቅሳለሁ ፨ብትወድ በሀይለኛዉ ንፈስ ፨ ብትወድ በነጎድጎድ እሳት፨ ብትወድ ፦፦፦፦፦፦ ብቻ አንተ ና ብቻ አንተ ና ፣አንተ ብቻ ና ብቻ ፣ አንተ ብቻ ና ።......።።።በቃ ተባረኪ ምን ልበል

  • @meskeremsimeonoffical7054
    @meskeremsimeonoffical7054 7 місяців тому +30

    እባክህን ጌታ ሆይ በዘመኔ ከባረከኝ አይቀር በዚህ መንፈስ ባርከኝ❤❤❤

  • @MihretFeyisa-jc8gr
    @MihretFeyisa-jc8gr 7 місяців тому +8

    እኔ በቃ አልቻልኩም አልቻልኩም ኢየሱስ ሲባል በእምባ ነው የምዝረከረከው አልቻልኩም ምን አይነት መዝሙር ነው ኢየሱስ ተባረክልኝ ህልዬ በኢየሱስ ስም ተባረኪ ደጋግሜ ነው የምሰማው ጌታ ኢየሱስ ያላቹ ደስ ይበላቹ❤

  • @DechasaAyeru
    @DechasaAyeru 7 місяців тому +59

    እሄን መዝሙር ሰሰማው airport ውስጥ transit አርጌ ሌላኛዉን plane እየጠበኩ ባለሁበት ሰዓት ነዉ የሰማሁት ለፅፈው ባልችልም አሁን ለይ የመጣሁበት አና በዚች ሰዓት ያለሁበት አና ደሞ እየህድኩበት yalewun ሁኔታ የዘምረቺው ነው የመስለኝ እንደዚ ጉልበት ሰቶኝ አቅም ሆኖኝ asinantogn ሚያቅ መዝሙር ያለ Aymeslgnim, መላኮች በሰው መልክ አብርሃም ቤት እንደገቡት እኔ ልብ ወስጥ በመዝምር መልክ የገባ ነዉ የመሰለኝ

  • @yosiefyacob1746
    @yosiefyacob1746 3 місяці тому +1

    ከምድር የሚያስለቅቅ ወደ ሰማይ ከፍ የሚያደርግ ዝማሬ። ድንቅ ዝማሬ!!! ጸጋውን ያብዛልሽ ተባረኪ

  • @GJPhoebe
    @GJPhoebe 7 місяців тому +43

    እንዴት ተባርከሻል
    እህታችን❤
    ለዘላለም በአቋምሽ ፅኚ
    ወደእኛም የተላለፈ ነው

  • @mihiretDenbela
    @mihiretDenbela 7 місяців тому +42

    ስለ ዝማሬው ጌታ እየሱስ ክብሩን ይውሰድ እሱ ብቻ ይታይ❤❤❤

  • @fitsummengistu7706
    @fitsummengistu7706 7 місяців тому +17

    ዛሬም ዘማሪዎች አሉ ለማለት አቅም ሆነሽናል!!!!!!!!! ዘመንሽ ይባርክ ህሉዬ!!!!!!!!!

  • @yidnekachewteka9679
    @yidnekachewteka9679 4 місяці тому +3

    አቤት ኢየሱስ ምን ማለት ይቻላል ከማንባት ውጪ😭😭😭😭

  • @KenianKenyanKenian
    @KenianKenyanKenian 7 місяців тому +4

    ብቻ አንቴ ና
    አንቴ ብቻ ና
    🧎‍♀️🧎‍♀️🧎‍♀️🧎‍♀️

  • @mel20216
    @mel20216 6 місяців тому +13

    ዝማሬዎች ሀሉ ሰው ፣ቁስ፣ ምድር ተኮር በሆኑበት በዚህ ዘመን ፤ ሰማያዊ ፣ መንፈስ ቅዱስ የሚታይበት ፣ ክርስቶስ ተኮር ምን አይነት መረዳት ነው ። ክብሩን ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ይወሰድ። አሜን።

  • @winoman4051
    @winoman4051 5 місяців тому +6

    በጉባኤው ውስጥ በሆንኩኝ ብዬ ተመኘሁ ፣ ጥፍት ብዬ ልንሳፈፍ ፣ በመንፈስ ልወሰድ ተመኘሁ🙏🙏🙏 ፀጋው ይብዛልሽ🙏🙏🙏

  • @henoksolomon0254
    @henoksolomon0254 2 місяці тому +2

    ዝማሬ ሳይሆን መልእክት ነው ። ተርጓሚ በራሱ ያስፈልገዋል ተባረኪ

  • @AsratWolde-u3i
    @AsratWolde-u3i 3 місяці тому +3

    እችን ዘማርት ዛረ ቀን12. 1. 2017.እሁድ ጥዋትና ማታ በዝ ቸርች ስትዘምር /ስታስመልክ/ አይችያታለው ከዝ በፍት ስሟንም አላቃትም፥ ስትዘምርም አይችያት አላቅም፤ ግን ምና አይነት ድንቅ መንፈስ ነው ያላት? የህን የምያምር ድምጽና እስትንፋስ የሰጠሽን አምላክሽን በእንደዝ አይነት መንፈስ በማመለክሽ በጣም የታደልሽ ነሽ፤ አሁንም ፀጋውን ያብዛልሽ፤ ብርክ በይ፤ ብዝዎችን ወደ እግዚአብሔር መንፈስ የምጋብዝ፥ ብዞዎችን ከዓለም ከጥፋት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የሚሳብ የምያመጣ፥ ብዙ የደከሙትን የምያበረታታ፥ ብዞዎችን በብዙ መከራና ችግር ውስጥ ያሉትን የምያፀናና፤ መዝሙሮችን በእግዚአብሔር መንፈስ ሆኖ ሰለ ምዘምሩ ዘማርዎች በኢትዮጵያ ስላሉ ስለ እነሱ እግዚአብሔር ይመስገን በእውነት።

  • @TeferaMekurya
    @TeferaMekurya 6 місяців тому +13

    በጌታ ምን አይነት መንፈስ ነው ዛሬ እድሉን አግኝቼ በጳውሎስ አለማቀፍ ቤተ ክርስቲያን ተጋብዛ በዚህ አምልኮ አስመልካናለች ለብዙ ሰዓት እንባዬን መቆጣጠር አልቻኩም የእውነት ጌታ አብዝቶ ይባርክሽ

  • @abenezerdawit3323
    @abenezerdawit3323 7 місяців тому +31

    ጌታ ሆይ በዚህ ህልውና ውስጥ አኑረኝ አባ😭😭😭 ምን መታደል ነው እህቴ ዘመንሽ ይለምልም ❤🙏🙏

    • @IChangedMyName_123
      @IChangedMyName_123 7 місяців тому +2

      Amen Amen 🙏 Tebareki bebezu yene konjoo ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

    • @tigesttigestt797
      @tigesttigestt797 7 місяців тому +1

      በባዶነት ስሜት ዉሰጥ ሆኜ በተስፋ እና በአምቦ ተሞላዉ 😢😢😢

  • @TgDiana-dh5rk
    @TgDiana-dh5rk 6 місяців тому +10

    እንዲሁ አይንሽን ጨፍነሽ ወደሠማይ ብቻ እንድንገናኝ ብቻ የመድረክ ሾ የሚያሣዩ ጨፍሪዎች በበዙበት በዚጊዜ ጌታን ስላንቺ አመሠግነዋለው ያለቅሬታ ትውልደን የማይተው ስሙ ይባረክ እንዲሁ እየዘመርሽ ሳትደባለቂ ዘመንሽ ይጠቅል እሕቴ ከፊቱ ደስታን ያጥግብሽ ለየት ባሉ ዝማሬና ዜማ ይባርክሽ

  • @hqqseybahiru4341
    @hqqseybahiru4341 13 днів тому +2

    አምላክ አብዝቶ ይባርክሽ አህቴ 4:18 አቤት ልቤ አንዴት አንደተደሰተች 🙏🙏🙏

  • @Absalat700
    @Absalat700 7 місяців тому +10

    ብትውድ በሀይለኛው ንፈስ
    ብትወድ በመበልባል እሳት
    ብትወድ ዝም በላው ፀጥታ
    ብትወድ በትንሷ ኳሽታ
    ብቻ አንተ ና ውዴ😢

  • @mesfintechan4307
    @mesfintechan4307 2 місяці тому +1

    ሁሌ የምሰማው ዝማሬ። በሰማውት ቁጥር ደግሞ የምኮነንበት!!!!!!! ምን አይነት ድምፅ ፣ምን አይነት ፀጋ ? አለውቅም ብቻ እህቴ እግዚአብሔር የለመንሽውን ሁሉ ይስጥሽ።አያሳፍርሽ።

  • @BaryBa
    @BaryBa 7 місяців тому +5

    እኔ አሁን ብዚህ ስዓት ይህን መዝሙር መንፈስ ቅዱስ እንድያስርደኝ ነው😢😢😢

  • @samuelestifanos2840
    @samuelestifanos2840 6 місяців тому +2

    በዘመናችን የሚወጡ አንዳንድ መዝሙሮች እንደ እኔ አስተያየት ስሜትን ከመንካት የዘለለ ብዙም መንፈስን ሲያረሰርሱ አይስተዋልም ጌታ ይመስገንና እንደእዚች እህት ያሉ የዘመናችን ዘማሪዎች መዝሙር መንፈሳዊና ከመንፈስ አንደሚፈልቅ የሚያሳዩ ቅሬታዎች ሆነዋል።ጌታ እንደእነዚህ ያሉቱን ያብዛልን ከማለት ውጪ ምንም ማለት ሚጠበቅብኝ አይመስለኝም !

  • @lovetube262
    @lovetube262 6 місяців тому +5

    ለካስ ብዙ ተርበንና ተጠምተን ነበር ጌታ ኢየሱስ ሆይ ያማረውን ዜማ እና ቅኔ ይፍሰስልህ እህቴ ህሊና በብዙ ተባረኪ የፀጋው ባለቤት የተመሰገነ ይሁን አሜን ።

  • @MekidesMekides-bo8lv
    @MekidesMekides-bo8lv 3 місяці тому +1

    እባክ ጌታ ሆይ የ አለም ምኞት አስወግደ መንፈስ ቅዱስ ስጠኝ🙏😭😭😭

  • @MamaFikir-j1r
    @MamaFikir-j1r 7 місяців тому +10

    ምንም ልል አልችልም እግዚአብሔር ብቻ ከአለም፣ከሰይጣንና ከስጋ ከዚ መንፈስ ሊያሶጡሽ ካሰቡ ነገሮች ሁሉ እግዚአብሔር ይጠብቅሽ።

  • @MussieLakew-k4s
    @MussieLakew-k4s Місяць тому +1

    ተባረኪ አረሰረስሽን Powerful ❤

  • @ErmiasBelay-bu8jl
    @ErmiasBelay-bu8jl 6 місяців тому +8

    ህሊና ስሟ ትፅእኖ አሳድሮባት
    ምድራዊ ነገር ከቶ አይሆንላት
    ጌታ ብርክርክ ያርግሽ

  • @yyy-dx5lu
    @yyy-dx5lu 3 місяці тому +1

    ተባረኪ ዘመንሽ ይባረክ ከግርግር መንፈስ የሌለበት ያወጣሽ በመንፈስ ዘምረሽ ከመንፈስቅዱስ ጋር የምታገናኝ ተባረኪ ጌታ ሰጩ ይባረክ አሜን። እንዲህ ከአባታችን ከአምላካችን ጋር የሚያገናኝ መንፈስን የሚያረሰርስ መዝሙር ነበር የጠፋው በዘመኑ አባቴ ሰው አጥቶ አያቅም። አባቴ ተባረክ

  • @Jesus20247
    @Jesus20247 7 місяців тому +6

    ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ
    ምን ይሻለኛል ፣ ኢየሱስ ፣ ኢየሱስ
    እኔ እንጀ በእንባ የሰማሁት መዝሙር ዱሮ በተባለበት ዘመን ጌታ ሰው አለው አለው
    ምን አለ በጉባኤው በኖርኩ !!❤❤❤❤❤❤❤
    🤔😂❤

  • @asnakeasres
    @asnakeasres 7 місяців тому +6

    ህሉ እባክሽ ከዚህ በላይ እንጂ ወደ ታች መዉረድ አይሁንብሽ ዘመንሸ በከፋታ ይለቅ ምናምንቴዎች ጋር አትገኝ ተባረኪ

  • @tesfubekeletube2024
    @tesfubekeletube2024 7 місяців тому +4

    ጌታ ሆይ መንፈስህን አብዛልን በእውነት ። የምድር ሀብት ንብረት ሁሉ ያልፋል ። አንተን መናፈቅ አንተን ማለት ማለት ይሁንልን ።
    ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ና ወደ ቤቴ ግባ ! ቀድሰኝ ለውጠኝ 😭😭😭 ያለ አንተ ድጋፍ እኔ እኮ ምንም ነኝ ። ስለዚህ ናና አበርተኝ !!

  • @Singermajanofficial
    @Singermajanofficial 7 місяців тому +11

    መንፈስ ቅዱስ ባይኖረን ግን ምን ይውጠን ነበር🤦
    በቃ አልቻልኩም ለመሳቅም ለማልቀስም አቃተኝ☺☺☺
    ብቻ ዝም ብሎ በፊቱ መፍሰስ እንዴት ደስ ይላል መሰላችሁ ኡኡኡኡፊፊፊፊ🙏🙏🙏

  • @haimanotbelete
    @haimanotbelete 7 місяців тому +7

    እግዚአብሔር ይመስገን ወደ ፀባዖት ወስዶ የምያስደምም ሰማያዊ ዝማሬ ድንቅ ድንቅ እጅግ እጅግ እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል
    እህታችን ህሊና ዳዊት ጌታ አብዝቶ ይባርክሽ ቅባት የዝማሬ ቅባት 📖💕🙏

  • @DanMesfin-d8x
    @DanMesfin-d8x 2 місяці тому +2

    እውነት ወደ ህልውናው ተመለስን? በጉባኤ የናፈቀኝ መረጋጋት ሆነ እኮ! እግዚአብሔር የሚገኘው ብዙ ጊዜ በተረጋጋ እውነት ውስጥ ነው። ነፍሴ ረሰረሰች ኡፍፍፍፍ ብሩክ ሁኚልኝ! ❤❤❤

  • @abigiyaworku5923
    @abigiyaworku5923 7 місяців тому +13

    በቋሚነት በዋናነት የምፈልገው ፊትህን ነው።😭😭😭😭😭😭😭🙌🙌

  • @kidistg.mariam3542
    @kidistg.mariam3542 5 місяців тому +3

    ከፍ ያለ የመረዳት ባለጠግነት የበዛልሽ አንቺ እህታችን ስጦታችን ዘመንሽ በዘመርሽለት ጌታ ፀጋ ይለምልም❤❤❤❤ እወድሻለው

  • @MimiNegash-t6n
    @MimiNegash-t6n 7 місяців тому +14

    አብርሃም ቤት ይስሐቅ ሲመጣ መቼ ተተካ ያንተ ቦታ አባ ያንተን ቦታ ሊተካ የሚችል በሰማይ ሆነ በምድር ከቶ አይገኘም ስምህ ብሩክ ይሁን ❤️❤️❤️🙏🙏

  • @melat_4christ538
    @melat_4christ538 6 місяців тому +7

    ለኔ ስኬት የሚወሰነው ከአንተ አንፃር ነው
    ክበር ከእጄ ወስደህ ብቻ አንተን ህልውናህን ጠረንህን አስቀርተህ
    ስጠኝ ውድ ነገር ግን አንተን አስቀርተህ
    በዘመኔ ላትሆን ተራ መሀላ አለኝ ከነብሴ ጋራ
    ከእጅህ አይበልጥም የፊትህ ፈገግታ ❤❤❤

  • @SA-vh2gv
    @SA-vh2gv 5 місяців тому +3

    በልቤ ውስጥ ለዘላለን
    ያንተ ቦታ ለብቻ ነው
    በቋሚነት በዋናነት
    ፊትህን ነው የምፈልገው
    ለኔ ስኬት ልምላሜ ካንተ አንፃር ነው የሚወሰነው ሰማዮ እንኳን እሚናፍቀኝ
    አንተ በዛ ስላለህ ነው
    በቤቴ ውስጥ ለዘላለም ያንተ ቦታ ለብቻ ነው በቋሚነት በዋናነት ሳቅህን ነው የምፈልገው በልቤ ውስጥ ለዘላለም ያንተ ቦታ ለብቻ ነው በቋሚነት በዋናነት ፊትህን ነው እፈልገው ለኔ ስኬት ልምላሜ ካንተ ሀሳብ ነው እሚወሰነው ሰማይ እንኳን እሚናፍቀኝ ሞልተህ በዛ ስላለህ ነው

  • @jesusloveyou5996
    @jesusloveyou5996 7 місяців тому +16

    እብድ በ በዛበት ዘመን ሃኒቾ ነበረች መፅናኛዬ እግዚአብሔር አንቺን ደግሞ ሸሽጎ አወጣሽ በክርስቶስ ደም ተሸፈኚ አደራሽን እነ እንቶኔ መድረክ ላይ እንዳትገኚ በጌታ ይሁንብሽ ❤❤❤

    • @meriwameskele1304
      @meriwameskele1304 7 місяців тому

      Mindnew intone....yetesetenin kemamesgen....ilik... negative neger mecommet.....ere bro simekir gilts adrgeh... yekirstos akal memyanist way...tebarek❤

  • @jesusislord1536
    @jesusislord1536 7 місяців тому +11

    ኦ ጌታ ሆይ አንተ ብቻ ና! አንተ ብቻ ና !
    ኦ መንፈስ ቅዱስ ተባረክ ሰምቼ አልጠግባትም የተባረከች በዚህ ዘመን ጌታ አንችን ስላስነሳ ጌታ ይባረክ የተባርክሽ ዘመንሽ ይለምልም አንተ ማለት አንተ ማለት ማረፊያዬ ነህ ሁሉ ነገሬ ነህ እየሱስ ብቻ አንተ ና አንተ ብቻ ና ❤

  • @danielbelsti
    @danielbelsti 5 місяців тому +1

    ኢየሱስ ጌታ ነው።
    ለኔ ስኬት ልምላሜ
    በእግርህ ስር ከርሜ
    በኑሮዬ አስቅድሜ
    ሰማዩን ናፍቄ
    ከሐጢያት ርቄ
    ፊትህን ፈልጌ
    በጽድቅ ስኖር ነው
    የኔ ስኬት ሚወሰነው።
    ኢየሱስን ተርቤያለሁ
    መቼ ይሆን የምጠግብህ

  • @PastorAshenafi
    @PastorAshenafi 7 місяців тому +4

    ክብር ለጌታ ይሁን የእግዚአብሔር ፊት የሚፈልግ ትውልድ ለካ አንተ አለህ

  • @MengistuDan
    @MengistuDan 4 місяці тому +1

    ኢየሱስ ከስጦታዎች ሁሉ ይበልጣል

  • @mesfinmarka1131
    @mesfinmarka1131 7 місяців тому +14

    ምን ዓይነት መንፈስ ነው ኦ ጌታ ሆይ ልጅህን በሷ ላይ ስላከበርክ ተመስገን

  • @birukwakeyo4563
    @birukwakeyo4563 Місяць тому +1

    እኔን የሚገርመኝ እግዚያብሔር በየዘመኑ በየወሩ በየቀኑ በየሰአቱ የደበቃቸዉ የሱን ብቻ አጀንዳ አጀንዳቸዉ አድርገዉ እንዲያወሩለት ቃሉ ብቻ እንዲዘምሩለት የተመረጡ ምርጦኝ ለእርሱ ለክብሩ መግለጫ ለእኔ ደግሞ መፅናኛ መበርቻ አረ ሰንቱ-- እ/ር ዘመንሽን እስከመጨረሻ ይባርክ ይብዛ ይጨመርልሽ

  • @EnkwanemAgegenhegn
    @EnkwanemAgegenhegn 11 днів тому +1

    አብርሀም ቤት ይሳቅ ሲመጣ
    መቼ ተተካ ያንተ ቦታ
    እጅ አይበልጥም ከፊት ፈገግታ
    አይቀልም ሰጪ ከስጦታ
    ብትወድ በሀይለኛው ንፋስህ
    ብትወድ በነበልባል እሳትህ
    ብትወድ ዝም ባለው ፀጥታህ
    ብተወድ በትንሿ ኮሽታህ
    ብቻ አንተ ና ብቻ አንተ ና

  • @EyuSolomon
    @EyuSolomon 7 місяців тому +6

    ጌታ በዘመናት መካከል ትውልድ አለው ስሙ ይባረክ ፀጋው ይብዛልሽ የእውነት ህይወቴ የተነካችበት ነው ዛሬ ስሰማው ፈውስ ሆኖልኛል

  • @mekdesmekuria4207
    @mekdesmekuria4207 2 місяці тому +2

    በጣም ድንቅ መዝሙር እግዚአብሔር ዘመንሽን ይባርክልሽ።

  • @mintwabkebede8233
    @mintwabkebede8233 7 місяців тому +6

    ስጠኝ ምንም ነገር ግን አንተን የሚከተል

  • @MelesMessa
    @MelesMessa 3 місяці тому +2

    ዘመንሽ ይባረ! ከፀሎት ሕይወት መቼም አትራቂ፡፡ ከዚህ በላይ እጅግ በጣም ጨምሪ፡፡ ለሰው ውጤት ሰጥቸ አላውቅም ለአንቺ ግን ... ::

  • @bemnismart9289
    @bemnismart9289 6 місяців тому +7

    ምን አይነት ቅኔ ነው እንዴት ውብ መዝሙር ነው ተባርኬበታለው ጌታ ዘመንሽን ይባርክ ዘመንሽ በጌታ ቤት ይለቅ❤❤

  • @ExcitedBoardGames-kw3ir
    @ExcitedBoardGames-kw3ir 2 місяці тому

    ኢየሱስ የኔ ወዳጅ የኔ ስኬት አተና አተ ብቻ ነክ እንካ ሁለ መናዬን ልኑር ካተ ጋራ በዝማሬ ውስጥ ባለዉ መንፈስ ባርከኝ ሁሉ ቀርቶ አተ ብቻ ና ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ

  • @ethiopianqueen5854
    @ethiopianqueen5854 7 місяців тому +6

    ደስታ ስታጠግበኝ ከፊትህ ጋ 🎤🎤 ህሉዬ ተባረኪ ብሰማው ብሰማው አልጠግብ አለኩ ሚገርም ዝማሬ ❤️❤️

  • @Maye4433
    @Maye4433 Місяць тому

    አሜን ብሰጥ ባይሰጥ ጉዳዩ ከስጦታው ገር ሰይሆን ከራሱ ከሰጭው ጋር ነው ቋም ርስታችን ነው እሱ ሁሉም ያልፋል

  • @selamalemu3523
    @selamalemu3523 7 місяців тому +4

    ኢየሱስ አንተ ብቻ 😭😭😭

  • @HailuWolde-j6e
    @HailuWolde-j6e Місяць тому

    ዘማሪ ህሊና ዳዊት ለመዝሙር የተሰጣች የእግዚአብሔር አገልገይ ነች

  • @hanaayele-s9g
    @hanaayele-s9g 6 місяців тому +4

    አረረረ ሃሌሉያ ሃሌሉያ 🙏🙏🙏🙏
    ተባረክ እየሱስ🙏 አረ ብርክ በይ 🙏🙏🙏🥰

  • @tsiontsion3938
    @tsiontsion3938 6 місяців тому +2

    ጌታ ብቻ ሙሉ እንደሚያደርግ እኔ ምስክር ነኝ....
    ጌታን ባል; ልጆች ሁሉን ጠየኩት ሁሉን ሰጠኝ ዛሬም ግን ጌታ የወደደኝንና የሚያስብልኝን ያህል ማናቸውም አይሆኑም የጌታ ፍቅር ሁሌም ትኩስ ነው ።
    የጌታ ፍቅር በምድረ በዳ ሙሉ ያረጋል;
    ጌታን ይበልጥ አሁን አፈቀርኩት ይስሀቅ ቢመጣ ነፍስ ሙሉ አትሆንም ለካ ነብሴ አንተን ነው የናፈቀችህ አልኩት
    " ኢየሱስ የኔ ስስት" ሁሌም ወድሀለሁ ያንተ አብሮነት ከኔ ጋር ባይኖር ድሮ ገና ነብሴን ከመኖር አቋርጫት ነበር
    ❤️ ህይወት የቀጠለው ባንተ ነው በምድርም በሰማይም።
    ይቀጥላል❤❤

  • @TessemaAyalew
    @TessemaAyalew 5 місяців тому +5

    የኔ ልጅ ነፍሴ ስለአንቺ ጌታን ታከብረዋለች ለምልሚ አሁንም ክውስጥሽ የማይቋረጥ ምንጭ ይፍለቅ

    • @tt55-m2i
      @tt55-m2i Місяць тому

      Amen min ayinet memereq nw??? Amen..lezelam Amen

  • @mululemma7409
    @mululemma7409 7 місяців тому +16

    መንፈስ ቅዱስ ያዘመረሽ ከነፍስ ውስጥ የወጣ ዝማሬ እግዚአብሔር ይባርክ

  • @Wongelyashenfal
    @Wongelyashenfal 7 місяців тому +12

    የተባረክሽ እህታችን እልፍ ሁኚ ❤

  • @LideyaTadep
    @LideyaTadep 6 місяців тому +1

    ምን አይነት ክብር ❤❤❤❤❤❤❤ ነው ❤❤እረ ሁሁ ሁሁሁ 😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢

  • @AdanechAlana
    @AdanechAlana 6 місяців тому +4

    Yewunten new hilena behewute buzu muzumere semicheyalewu yaniche mezemure new kemengede yemelesegn salaqi bineba Temolicheyalew 😢😢😢😢😢😢geta yibarekish 🙌🏿🙌🏿🙌🏿

  • @MameYegeta-z7z
    @MameYegeta-z7z 2 місяці тому

    የጌታ መንፈስ የሚታይበት ታላቅ መልክት! እህቴ ዘመንሽ ይለመልም ! ደዊትም በገና ሲደረድር እርኩሰ መንፈስ ከሳኦል ይርቅ ነበር !

  • @tnsaesefiwtnsu-js5js
    @tnsaesefiwtnsu-js5js 6 місяців тому +3

    በዘመን እጥፍጣፊ ላይ እደቆምን የጋረደን ደስታውን ሳይሆን ተድላችንን እድንከተል ያደረገን ከኢትዮጲያ ቤተክርስቲያን ላይ እሱ ይግፈፈው😢😢😢😢😢

  • @user-wr7vs6wg3jbl
    @user-wr7vs6wg3jbl 5 місяців тому

    ለእኔ ስኬት ልምላሜ ከአንተ አንጻር ነው ሚወሰነው ❤❤❤ሰማይ እንኳን ምናፋቀኝ አንተ በዛ ሰላለህ ነው ሀ

  • @mikymanabiy7629
    @mikymanabiy7629 7 місяців тому +5

    ከታረደው ነገርግን ህያው ከሆነው በግ ዙፋን ስር የሚፈስና ወደ እግዚአብሔር የሚያስጠጋ ሰማይን የሚያስናፍቅና ሁሉን የሚያስንቅ ዝማሬ ሂሉ ተባረኪ ተባረኪ ከሀና በመቀጠል አንቺ አገኝ

  • @ዲቦራየንጉሥልጅነኝ
    @ዲቦራየንጉሥልጅነኝ 7 місяців тому +1

    ዘመንሽ በዚሁ ህልውና ርእስ ሳትቀይሪ ስፍራ ሳትለውጪ በእግሩ ሥር ሆነሽ በህልውና ማምለክ ይሁንልሽ 😭አንቺን አይቼ ክርስቶስን አየው አምልኮ ከዚህ ይዘት ሳይወጣ ሲሆን ብቻ ነው ክርስቶስ የሚታይበት ጠረኑ ሽታው በቤታች የሚገባው በአካል አጠገባችን እያየነው የምናመልከው ሃሌሉያ ተባርከሻል ቀናውብሽ ህሊናዬ አቤት መገለጥ አባት ሆይ ና ወደቤቴ ግባ ና ጌታ ሆይ ና ታስፈልግኛለህ

  • @mistrecheru6461
    @mistrecheru6461 7 місяців тому +3

    ኢየሱስ ጌታ ነዉ።

  • @BetiKef
    @BetiKef 7 місяців тому +2

    ብቻ አንተ ና ኢየሱስ❤❤❤❤❤