🔴 እራሴን በዘይት የቀባኸኝ erasen bezeyet yekebahegn
Вставка
- Опубліковано 7 лют 2025
- እራሴን በዘይት የቀባኸኝ
የምከብርባትን ጽዋዬን ሞላኸኝ
ታናሽነቴን አልናቅክም
ተመስገንልኝ ጌታ ዘላለም
እንደትላንቱ ዛሬም ጠራኸኝ
እንደቀደሙ አሁንም ና አልከኝ
ነገን አልፌ እተርካለሁ
በቀኝህ ቆሜ ገና እዘምራለሁ
አዝ……..
በመቅደስህ አመሰገንኩህ
ልጄ ስትለኝ ተመለከትኩህ
አክሊሌን ካንተ እቀዳጃለሁ
ከቅዱሳኑ ጋር እቆማለሁ
አዝ……
ታላቁ ስምህ በልቤ ነግሷል
አንተን ይጠራል ጠላቴም አፍሯል
ሃይል ሆነኸኝ ጋሻ መከታ
የሚያስፈራውን አለፍኩት ጌታ
አዝ……
እግዚአብሄር አንተ እድል ፈንታዬ
ዋልታ ምሶሶ ነህ ለኑሮዬ
ጎዶሎ የለም አንተን ጨብጬ
ፍጹም ወደድኩህ ከሁሉ አብልጩ
አዝ…..
ለእጆቼ ሰልፍን አስተማርከኝ
ለደህንነቴ ቀንድ ሆንከኝ
የጠላትን ቅጥር አፈራርሼ
ለክብርህ ሰገድኩ ፊትህ ደርሼ
ዝማሬ መላዕክትን ያሰማልን !