እጅግ ድንቅ ትምህርት || ርዕሰ ሊቃዉንት አባ ገብረኪዳን || Aba Gebrekidan Girma

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 11 гру 2024

КОМЕНТАРІ • 3

  • @Barthos1
    @Barthos1  4 місяці тому +2

    🌼 ዉድ ኦርቶዶክሳዉያን ላይክና ሼር ማድረግ አይርሱ 🌼

  • @MeazaMichaels
    @MeazaMichaels 4 місяці тому

    በልጄ ተሞገትሁ እንዲህ ነው ቀን ሲጥል
    ቀዩን መስመር ጣሰው የእናቱ ቅምጥል።
    እምጥ ልግባ ስምጥ ልግባ በቁሜ ቅበሩኝ
    ወይ እንዳበደ ስው በገመድ እሰሩኝ።
    ልጆቼን አድርጌ ከዘመድ በላይ
    ትዳር ትዳር እያልሁ ማንንም ሳላይ።
    ተመልከቱኝማ እንዲህ ሆንሁላችሁ
    በእኔ የደረሰ አያድርስባችሁ
    ብርድ ብርድ ይለኛል ሰውነቴ ርዶ
    መብረቅ አቃጠለኝ ከሰማይ ላይ ወርዶ ።
    የፈሩት ይደርሳል የጠሉት ይወርሳል
    ፈተና ሲበዛ ሰው ማንን ይወቅሳል ።
    እንዴት ልሸከመው እንደምን አድርጌ
    የተንዘላዘለን የዘመን ባለጌ።
    ቀስ እያል ሲቆርጥ ሰይጣን ስጋየን
    አንተው ድረስልኝ ቀንስ ስቃየን።
    አውርደኝ እባክህ ጀርባየ ቆሰለ
    ንፍሮ ሆኖብኛል አሁንስ በሰለ።
    ቁስሌም አልደረቀ መቼም ላላገግም
    ውሰደኝ እባክህ ስህተቴን ሳልደግም
    በዚች አለም መኖር ጭራሽ አልፈልግም ።
    አሳርፈኝ ባክህ አንድ ጊዜ አውርደህ
    መከራን ቀምሰሃል አንተም ርደህ ።
    ሁኜብህ ነው እንጂ አልሞት ባይ ተጋዳይ
    ልከስህ አልመጣሁ ልክ እንደ ተበዳይ።
    አይኔ ሊወጣ ነው ዛሬስ ቦታ ለቅቆ
    ሰለቸው ማልቀሱ አያይም አርቆ።
    መኖር አልፈልግም አልዋሽህም ጌታ
    ለንስህ አብቅተህ እስትንፋሴን ግታ
    ምንጊዜም ላልጠቅምህ መቼም ላልበረታ።
    እንባየን እያየህ ምነው ትላለህ ዝም
    አላሳዝንህም ሁልጊዜ ስቆዝም?
    አንተ ብታፅናናኝ አልፈልግም ሌላ
    ፍጥረትህ ነኝና ልጅህን አትጠላ።
    ፅዋዬ ሳትሞላ እንባየን አልጠርግም
    ብቻ ማረኝ እንጅ መኖር አልፈልግም ።
    አልቅሼልሻለሁ ታሪካዊ ለቅሶ
    እኔን እኔን እያልሁ ደረቴ በስብሶ
    እንዴት ቁሜ ልሂድ እንደምን ልጓዘው
    እንደ ሙት አድርገህ ✋ እግሬን ገንዘው።
    ምን አይነት ነው ፍርዱ በቁሙ ለሞተ
    እንዴት ነው ሚፈታ እዕምሮው ለሳተ።
    ባፀናሃት ምድር እንዳልሆን ባይታወር
    ምናል ብትወስዱኝ በጣም ሳልታወር
    አንተን ልሸሸግህ አልችልም መሰወር።
    በአንተ እጅ ስላለ መግደልና ማዳን
    እስትንፋሴን ወስደህ ነፍስያየ ትዳን።

    • @MeazaMichaels
      @MeazaMichaels 4 місяці тому +1

      ወለተ ስላሴ ነኝ እንቆቅልሼ እንዲፈታ በፀሎታችሁ አስቡኝ