አርጋኖን ዘሠሉስ (የማክሰኞ አርጋኖን)

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 15 гру 2024

КОМЕНТАРІ • 24

  • @ወይኒየኔናት
    @ወይኒየኔናት 3 роки тому

    ሰላማችው ይብዛ አሜን በጣም ደስ ይላል ቃለህይወት ያሰማልን እማምላክ ትባርክልኝ ልመናዋ ፀሎቹዋ ነኛጋር ይሁን እጅግ ደስ ነው ያለው ስለሰማም እግዚአብሔር ይባርክክ ወድሜ አሜን 🙏🙏

  • @geniyearsemalej
    @geniyearsemalej 3 роки тому

    ዋው አንደኛ ነኝ ዛሬ ቃለ ህይወት ያሠማልን በርታ

  • @ፍቅርያሽንፋል-ለ2ወ
    @ፍቅርያሽንፋል-ለ2ወ 3 роки тому

    ሰላም ለዚ ቤት እማምላክ ትባርክክ ወድሜ ቃለህይወት ያሰማልን መንፈስን የሚያድስ የህይወት ፍሬ ነው የመገብከን እግዚአብሔር ያክብርልኝ ጀግና ነክ ጎበዝ 👍❤️እማምላክዬ ባርኪን እኛ ልጆችሽን አሜን 🙏🙏

  • @melataragaw7547
    @melataragaw7547 3 роки тому

    ቃለ ህይወት ያሰማልን

  • @Tube-bg9kh
    @Tube-bg9kh  3 роки тому

    በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
    (አርጋኖን ዘሠሉስ)
    በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባለች የተመረጠች ድንግል ማርያምን ወደዳት አከበራት ከፍ ከፍ
    አደረጋት፡፡
    በሁሉ ላይ አሰለጠናት፡፡ ሁሉን አስገዛላት፡፡ አምላክን በድንግልና የወለደች እርሷም የንጽሕና
    የቅድስና መሠረት ሆነች፡፡
    አቤቱ ሆይ ክብሯን ገናንነቷን በመረዳት አመሰግናት ዘንድ ለልቡናዬ ድምር ዕውቀትን ስጥ፡፡
    አቤቱ ሆይ ላንደበቴ ኃይለ ቃሉን ስጥ የማኅፀኗን መክበር የድንግልንዋን ነገር አወራ ዘንድ፡፡እርሷም ደግሞ እኔን ለማዳን የታመነች ናት፡፡ ለድንቁርናዬም የበጎ ምስራች ወሬ ናት፡፡
    ለእጆቼም የቅድስና አምባር ለእግሮቼም እውነተኛ ጎዳና ላንገቴም ድሪ አሸንክታብ ለራሴም አክሊል
    ዘውድ ላፌም የጣፈጠ እንጀራ ላፍንጫዬም የሽቱ መዓዛ ለመዋረዴም ከፍታ፡፡ ለሕመሜም ጤና ናት፡፡
    ድንግል ሆይ ንጽሕናን እንደ መላእክት የለበስሽ እንደ ነቢያትም መንፈስ ቅዱስን የተመላሽ ሁሉንም
    አቸናፊ በሚሆን በልዑል እግዚአብሔር እጅ የታነፅሽ የመለኮት ማደሪያ ነሽ፡፡
    የአሕዛብ ብርሃን የነገስታት ኃይል የምድር መሠረት የሰማይ ጽናት የአየር ርቀት የባሕር ጥልቀት
    የደመና ግዘፍ የዝናማት መታዘዝ፡፡ የፀሐይና የጨረቃ የከዋክብት ፀዳል አንቺ ነሽ፡፡
    በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ የተመረጥሽ ደንግል እመቤቴ ማርያም ሆይ በሁሉ ተመሰልሽ በሁሉም
    መሰሉሽ አንቺን ግን የሚመስልሽ የለም፡፡
    ሰማይ አይተካከልሽም ምድርም የሆድሽን ስፋት ያህል አትሆንም የማትችለውን ችለሽዋልና፡፡
    የማትሸከመውንም ተሸከምሽ፡፡
    ኪሩቤል የልጅሽ ሠረገሎች ናቸው፡፡ ሱራፌልም ከባህሪ ልጅሽ በታች ወድቀው ይገዛሉ፡፡ ክብር
    ለከፍታሽ ነው፡፡ ገናንነትም ለጌትነትሽ፡፡
    ቅድስት ድንግል ሆይ ጉልበታችን ኃይላችን ሞገሳችን ክብራችን ተድላ ደስታችን አንቺ ነሽ
    ለዘመዶቻችንም መመኪያ ሆንሽ፡፡ የዓለም ሁሉ መድኃኒት ባንቺ ተደረገ፡፡
    የአምላክም ይቅርታ በሰው ልጆች ላይ ባንቺ ጸና የፍጡር ባሕርይ ከፈጣሪ ጋራ ባንች አንድ አካል
    አንድ ባሕርይ አንድ ገዥ ሆነ ይህ ስራ እጅግ ድንቅ ነው፡፡
    ሠሪ ሥራውን መልበስ እጅግ መንክር ነው፡፡ ሠሪውም ሥራውን የለበሰበት ሥርዓት ዕፁብ ነው፡፡
    ፈጣሪ ፍጡሩን መልበስ ይህ ትህትና እጅግ የተደነቀ ነው፡፡
    ድንግል ሆይ አሁንም ወደ ልጅሽ እጮኻለሁ፡፡ እንዲህ ስል ከመላእክት ልዕልና ይልቅ የሰውን
    መዋረድ የወደድህ ሆይ ስለሠራሁት ኃጢአት አትናቀኝ አትንቀፈኝ፡፡
    የሰማያውያን መላእክት አንድነት ይልቅ ምድራውያን ፍጥረታትን ለመሳተፍ የወደድህ ሆይ ነውር
    ነቀፋ ከሌለበት ከመለኮትነትህ ምሥጢር አሳትፈኝ፡፡
    ከኤሳው መልክ ይልቅ የያዕቆብን የፊቱን ደም ግባት የወደድህ ሆይ አቤቱ ስለ ሠራሁት ኃጢአት
    እኔን አታርቅ፡፡ እኔ አንተን ለብቻህ በደልሁ ለራሴም ኃጢአት አብዝቼ ሠራሁ፡፡
    አንተ ንጹሕ አድርገህ ፈጠርከኝ፡፡ እኔ ግን በጠላቴ ምክር በደልሁ አንተ በሃይማኖት በትሩፋት
    አስጌጥከኝ፡፡ እኔ ግን ኃጢአትን በመውደድ ጌጤን ሽልማቴን ተውሁ፡፡
    አቤቱ ሆይ ለመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ እሆን ዘንድ እኔን በምግባር በሃይማኖት ለማነጽ ትጋ፡፡
    መንቀሳቀስ በሌለበት ኃጢአት በመውደቅ የተጎዳሁ እንዳልሆን፡፡
    አቤቱ ሆይ እኔን ይቅር ለማለት ትጋ ይቅርታ ካንተ ዘንድ ነውና፡፡ አቤቱ ሆይ ቁስሌ የሚፈወስበትን
    መድኃኒት አንተ ታውቀዋለህ፡፡ አቤቱ ሆይ ድካሜ የሚበረታበትን ረዳትነት አንተ ታውቀዋለህ፡፡ለዘለዓለሙ አሜን።

  • @ትእዛዙሙሉጌታ
    @ትእዛዙሙሉጌታ 3 роки тому

    Kale hywt yasmaln amen

  • @jonejone6465
    @jonejone6465 3 роки тому

    አሜን

  • @amenamen4274
    @amenamen4274 3 роки тому

    Kale heyewt yasmalen

  • @hamanotzetewhado1641
    @hamanotzetewhado1641 3 роки тому

    Amen amen

  • @hamlemalabate6056
    @hamlemalabate6056 3 роки тому

    Kalehyewt yasmalen

  • @zekiyohans2401
    @zekiyohans2401 3 роки тому

    kale hyewt yasemaln

  • @hamanotzetewhado1641
    @hamanotzetewhado1641 3 роки тому

    Amen

  • @memiwelo5380
    @memiwelo5380 3 роки тому

    Kale hyewt yademakn

  • @melkamkebde8394
    @melkamkebde8394 3 роки тому

    Kalhyewtn yasemaln

  • @lemlemabera345
    @lemlemabera345 3 роки тому

    አሜን

  • @ethiopiahagre7337
    @ethiopiahagre7337 3 роки тому

    Kale heyewt yasmalen

  • @hirutgebyehu331
    @hirutgebyehu331 3 роки тому

    Kale hyewt yasemaln

  • @almazengdaw3547
    @almazengdaw3547 3 роки тому

    kale hyewt yasemaln

  • @tamruworku2094
    @tamruworku2094 3 роки тому

    Amen

  • @mesertworku9946
    @mesertworku9946 3 роки тому

    kale hyeywt yasemaln

  • @tgtg7713
    @tgtg7713 3 роки тому

    Amen

  • @memyself3205
    @memyself3205 3 роки тому

    Amen

  • @eneerase2852
    @eneerase2852 3 роки тому

    Amen

  • @hawazalmu727
    @hawazalmu727 3 роки тому

    Amen