መን-ደፈራ mendefera 🇪🇷🇪🇷🇪🇷

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 15 гру 2024
  • #መን--ደፈራ
    የጉዞ ማስታወሻ
    መንደፈራ በኤርትራ የደቡብ ክልል ዋና ከተማ ስትሆን፡ ከባህር ጠለል በላይ 1972 ሜተር ከፍታ፡ ከኣስመራ በስተደቡብ 54 ኪ.ሜ.ርቀት ላይ የምትገኝ፡ በልምላሜዋ የምትታወቅ የገበያ ማእከል ከተማ ናት።🤔🤔🤔
    #መንደፈራዎች
    የቀደምት ኣባቶቻቸዉን ትላልቅ ወንድም እህቶቻቸዉን ምክር የሚሰሙ፡ እርስ በርሳቸዉ ፍቅርና ዉህደት ያላቸዉ ። የኣዜንዳ፡ የኣስላምያ፡ የገዛ ከኒሻ፡ የባድረ፡ #የሳንጆርጆና የመሳሰሉ ት/ቤት ዉጤቶች መሆናቸውን በአይኔ አረጋግጫለሁ ።💪💪💪💪
    #ሳንጆርጆ
    በመንደፈራ ልዩ ኣሻራ ታሪክ ያላት፡ #የእነደጃዝማቾች #ሓረጎትኣባይ፡ #ወልዱመሓሪ፡#ተፈሪወልደሚካኤል፡ #ስብሃቱዮሃንስ፡ #የእነኣዝማችበርሀገብረኪዳን፡ #ግራዝማችኣስመሮምወልደገርግስ፡ #ጀነራልሃይሌባይከዳኝ፡ #ኣብርሃደቦጭና
    የመሳሰሉትን ያፈራች ኣንጋፋ፡ የባህል ማንነት ቅርስ ትምህርት ቤት ናት ሳንጆርጅ ።
    ሳንጆርጆ የማሕበራዊ ክብርና እሴት ዉጤት። የጥበብ ሞራል፡ ግብረገብና ዕዉቀት ምንጭ ቅርስ መሆኑን በቆየውበት ትንሽ ቀናት ከተወለዱባት ልጆቿ አረጋግጫለሁ። 🙆🙆🙆🌹🌹
    መንደፈራ የእነ ቪቶሮ ቦሲ፡ ወዲ ኣዉኣሎም፡ ወዲ ከሊፋ መንደር።
    #ነዋሪዎችዋ
    በምሽት በጎዳና የሚዋደዱ ጓደኛሞች፡ የሚፋቀሩ ጥንዶች፡ የሚግባቡ ኣብሮ ኣደጎች፡ በጋራ ሆነዉ በገዛ ማንዳ፡ በሆስፒዳሌ፡ በእንዳ ቤንዚና፡ ጎቦ ቲቦ፡ በካቴድራል፡ መስጊድ ጃምዕ፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ኣካባቢ እየተዘዋወሩ ሲንቀሳቀሱ ለመንደፈራ ልዩ ድምቀት ይሰጣሉ።
    በተለይ እኔ በቆየሁበት ቀናቶች መብራት ከመኖሩ ያለመኖሩ ግዜ ይበልጣል የመብራት በየግዜ መጥፋቱ የበለጠ ውበት አለው ለሚፋቅ ጥንዶች😂😂😂።
    #መንደፈራዎች
    በተለይም ወጣቶችዋ #መንዱፈይ ብለዉ ነዉ በፍቅር የሚጠሯት።
    ካሻቸዉ በጨርሒ በመረብ፡ በሰምሃር በመርከብ፡ በእምባባ በኣስመራ፡ በደንደን በኣወትና ሌሎች ሆቴሎች ተሰይመዉ፡ ኣልያም በክዶሕምባሻ፡ በካፌ ቤቶች እንዲሁም በጠላቤቶች ገብተዉ ጨዋነት በተላበሰ ሁኔታ መዝናናቱን ያዉቁበታል። ፍቅር 100% ጠብ 0% ነዉ ኣይታሰብም።
    ጠላቸዉ ዋዉ!! ኣቤት መጣፈጡ፡ መንፈስን ማደሱ፡ እንዳ ኲዌት፡ እንዳ ሳዳም፡ እንዳ ስላስ፡ እንዳ ሃና፡ እንዳ ጓል ዓረዛ፡ እንዳ ኣደይ ሓረጉ . . . ወዘተ የተጠመቁትን የቀመሰ የምን ዉስኪ የምን ቢራ፡ የምን ኮኛክ የምን ቮድካ ኤድያ! የሚያሰኝ ነዉ። ከፈለጉ ሄዶ መቅመስ ነው!👌👌👌👌
    ከጠላዉ ጋራ ሙዚቃዉ ይደመጣል፡ ወጉም ኣብሮ ይወርዳል። ታሪክ ይደረደራል. በተለይም ደግሞ ጠና ያሉት ይበልጥ ጆሮ ይስባሉ። ይበልጥ ይደመጣሉ። መንደፈራ ማለት ስያሜዋን ይገልጻሉ።
    መንደፈራ ከሁለት #መን እና #ደፈራ ከሚል ቃል የተገነባና "ማን ደፈራት" የሚል ትርጓሜ እንዳለዉ ያስታዉሳሉ።
    መንደፈራ በጥንት ዘመን እጅግ በጣም በጫካ የተከበበችና የዱር ኣራዊቶች መኖሪያ እንድነበረች፡ በወቅቱ ጫካዋን ደፍሮ ገብቶ መንጥሮና ለሰዉ መኖሪያ ምቹ እንድትሆን ስላደራጓት በሁኔታዉ የተገረሙ ሰዎች " #ቦታዉን #ማንደፈረዉ" ለማለት የተጠቀሙበትና የጀግንነት ታሪክ ያላት መሆንዋን በጨዋታ እያዋዙ ለወጣቱ ታሪክ ያስተምራሉ።
    እርግጥም እዉነት ነዉ። መንደፈራዎች ድፈረታቸዉ ጥግ ድረስ ነዉ። እጅግ በጣም ደፋሮች ናቸዉ። ይሁንና ድፍረታቸዉን ካለቦታዉ ላይ ኣያዉሉትም። ሰዉ ኣክባሪዎችና
    መንደፈራ በቆየውበት ጥቂት ቀናቶች የሚያስደስት ግዜ አጣጥሜ ዓዲ መንጎቴ፣ዓዲ ቆዶ፣ዓዲ ኣዳ የሚባሉ የገጠር ለምለም ስፍራዎችን ተመልክቻለሁ።
    በተለይ ስነስረዓታቸው ለእንግዳ ያላቸው አቀባበል ፍቅር እንድትናፍቃቸው እያደረገኝ ጉዞዬን ወደ አስመራ ሽኮር አድርጊያለሁ 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏�
    👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
    • መንደፈራ በአንጎላ

КОМЕНТАРІ •