ፈላስፋ - ዓለማየሁ ገላጋይ (ደራሲ እና ሀያሲ) ሐዋዝ ሀሳብ Hawaz Hasab

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 5 лют 2025
  • በአተያይ ብቃቱ ወጣ ይላል፡፡ አስተሳሰቡም ጥልቅ ነው፡፡ ታዋቂው ፀሐፊ እና ሀያሲ ዓለማየሁ ገላጋይ አዲስ አበባ ውስጥ በ 1960 ዓ.ም አራት ኪሎ አካባቢ ተወለደ፡፡ በዳግማዊ ምኒሊክ ትምህርት ቤት የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርቱን ተምሯል፡፡ በአዲስ አበባ ስኩል ኦፍ ጆርናሊዝም ተምሮ ሊመረቅ ችሏል፡፡ ደራሲ እና ሀያሲ ዓለማየሁ ገላጋይ በተለያዩ የሀገራችን ጋዜጦች ላይ በሚያቀርባቸው ጭብጠ ብዙ መጣጥፎቹና እና ሂሶቹም ይታወቃል፡፡
    በተጨማሪም "አጥቢያ" ፣ "ቅበላ" ፣ "በፍቅር ስም" ፣ "የስብሃት ገብረ እግዚአብሔር ሕይወት እና ክህሎት" ፣ "ኢህአዴግን እከሳለሁ" ፣ "የፍልስፍና አፅናፎት" ፣ "መልክአ ስብሐት" ፣ "ኩርቢት" ፣ "የብርሃን ፈለጎች" ፣ "ወሪሳ" ፣ "ታለ በእውነት ስም" ፣ "ሐሰተኛው በእምነት ስም" ፣ "ቤባንያ" እና "የተጠላው እንዳልተጠላ" የተሰኙና ሌሎች በርካታ መፅሐፍቶችን አሳትሞ ለአንባቢያን አብቅቷል። አለማየሁ ገላጋይ በአንድ ወቅት የ ሐዋዝ ሀሳብ መድረካችን የክብር እንግዳ ሆኖ ያካፈለውን ሀሳብ ታደምጡ ዘንድ ጋብዘናል፡፡ ነገር ግን ከወዲሁ አስቀድመን ስለቪዲዮው የምስል ጥራት ከፍተኛ ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ እንዳትታዘቡን አደራ! ትኩረታችሁን ሁሉ የቪዲዮው ድምፅና ሀሳቦቹ ላይ ብቻ አድርጋችሁ ስሙት፡፡ እናመሰግናለን!
    "ሐዋዝ" የግዕዝ ቃል ሲሆን ፤ ትርጓሜውም "የሚያምር" ፣ "ደስ የሚል" ፣ "መልካም" እና "ቆንጆ" የሚል ነው፡፡ ይህንን ውብ ኢትዮጵያዊ ቃል የ "ዩቲዩብ ቻናላችን" መጠሪያ ስም አድርገን የተጠቀምንበት ዋና ምክንያት ፤ በዩቲዩብ ቻናላችን ላይ የሚለቀቁ ሀሳቦች ሁሉ ፤ ከመዝናኛነት በዘለለ … ደስ የሚሉ ፣ የሚያምሩ ፣ እንዲሁም የሰው ልጆችን አዕምሮ ፤ በበጎ ሊያንፁ የሚችሉ ፤ ቅንና ጠቃሚ ጭብጦች የሚተላለፉበት ዩቲዩብ ቻናል እንደሚሆን ፍፁም በመተማመን ነው፡፡

КОМЕНТАРІ • 2

  • @amsalgebreegziabher5584
    @amsalgebreegziabher5584 7 місяців тому +1

    ምርጥ ንግግር ነበር ደራሲ አሌክስ እያዝናና አስተምሮኛል🙏❤🙏❤🙏❤አመሰግናለሁ🙏❤🙏❤👏👏👏👏

  • @yohannesmamo-c5k
    @yohannesmamo-c5k 7 місяців тому +1

    Isn't it so hard to have some thing new to talk when needed 🤔, ደራሲ አሌክስ always impresses me.
    Much love, and thank🙏