Ewnet ye leben new ye xafeshew ewnet ene eyesusen mamlek eyesus meketel mew enji yaleg haymanot adelem yehen sel serat yasfelegal gen wengel bante senegereh mekebel be lea senegereh mekad adelem wengel ke mesebku metebaber new asfelagi ewnet enem gen ande ke kaleawadi tv meteche bagelegel des yelegal 🇪🇷 neg gen ande ken ke lebe emamelkew ale malet ahunum ke lebe amelkalew ken ke Christian ga hoge le malet new begena anseche ❤❤❤❤❤❤❤❤
የዝማሬው ግጥም እነሆ...
📖መሰንቆዬን በአኻያ ዛፎች ላይ ሰቅዬ
የእንቢልታዬ ቅኝት ዜማው ቀርቶ ከኌላዬ
በአደባባዩ በደርቡ ዜማዬ ባይወጣ
ቢታቀብ አንደበቴ ቃል ከአፌ ሲታጣ
የምስጋናን ቃል የፈለጉብኝ
አመስግን እንጂ ዘምር ቢሉኝ
ልቤ ተነሳ ሊያዜምልህ
ቅኔዬ ነቃ እንዲህ ሊልህ🗣
🌎ቀኜ ትርሳኝ ብረሳህ
ምላሴ ይጣበቅ ባላስብህ
የምወድህ ደስታዬ
ገነቴ ነህ መኖሪያዬ🌅
🌌አንተ አይደለህም ወይ የኪዳን ሃገሬ
ሞት እንዳያገኘኝ ከለላ የሆንኸኝ የሕይወት ድንበሬ
አንተ አይደለህም ወይ ያዘመትኸኝ መሪ
በጸናች እጅ እና በተዘረጋች ክንድ ሆነህ ፊት አውራሪ
አንተ አይደለህም ወይ እንዴት ይዘነጋል
ውለታህ ልቤ ውስጥ ዘለአለም ላይጠፋ በጣትህ ተፅፏል✒️
🌏ቀኜ ትርሳኝ ብረሳህ
ምላሴ ይጣበቅ ባላስብህ
የምወድህ ደስታዬ
ገነቴ ነህ መኖሪያዬ🏞
🌄ክንድህ አይደለም ወይ ትላንቴን የረታ
ዛሬን የሚያኖረኝ የነገ ተስፋዬ የነፍሴ መከታ
እጅህ አይደለም ወይ ያጎረሰኝ ቆርሶ
ያጠጣኝ ስጠማ ከልዑላን ማዕድ በክብር አቋድሶ
እጅህ አይደለም ወይ ያከመኝ ታምሜ
አቅፎ ያባበለኝ እንባዬን ያበሰው ጣትህ ነው ሰላሜ 🌅
🌎ቀኜ ትርሳኝ ብረሳህ
ምላሴ ይጣበቅ ባላስብህ
የምወድህ ደስታዬ
ገነቴ ነህ መኖሪያዬ🏞
🎙አንተ እኮ ነህ ጌታ የዜማዬ ቃና
የቃላቴ ሞገስ የስብከቴ ርዕስ የንግግሬ አርማ
አንተ እኮ ነህ ጌታ የልጅነት ሕልሜ
የጉብዝና ሃሳቤ የምኞቴ አልፋ ርስቴ አለሜ
በአንተ እኮ ነው ጌታ መሻገር መትረፌ
የጭንቄን ማለዳ የእንባዬን ሌሊቶች የቆምኩት አልፌ🌅
🌏ቀኜ ትርሳኝ ብረሳህ
ምላሴ ይጣበቅ ባላስብህ
የምወድህ ደስታዬ
ገነቴ ነህ መኖሪያዬ🌅
🌎ላምጣ በገናዬን መወድሱን ላንሳ
የልሳኔን ጩኸት ሳልገድብ ሳልሳሳ
ታጥቄያለሁ ቅኔ ስምህ ነው ዜማዬ
ለክብርህ እኖራለሁ መዝሙር ነው ስራዬ
ዜማን በልቤ አርገህ ፈጥረኸኛልና
ማምለክ ነው ስራዬ አንተን በምስጋና 🗣
🙏 ኸረ እኔስ አለኝ ምስጋና ለሕይወቴ ጀግና
ኸረ እኔስ አለኝ ምስጋና ለሕይወቴ ጀግና
ቀኜ ትርሳኝ ብረሳህ ምላሴ ይጣበቅ ባላስብህ
የምወድህ ደስታዬ ገነቴ ነህ መኖሪያዬ📖
ግጥም እና ዜማ ዲያቆን ሐዋዝ ተገኝ
Be blessed
I Love Is Vido
betam konjo new ,tebarek.
Tbarkkk
6:09
ክንድህ አይደለም ወይ ትላንቴን የረታ
ዛሬን የሚያኖረኝ የነገ ተስፋዬ የነፍሴ መከታ
እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ ሐዊዬ
Bexam new ymiwedachu Feni anchim yetebaraksh nesh!
አንተ እኮ ነህ ጌታ የዜማዬ ቃና
የቃላቴ ሞገስ የስብከቴ እርስ የንግግሬ አርማ
አንተ እኮ ነህ ጌታ የልጅነት ህልሜ
የጉብዝና ሀሳቤ የምኞቴ አልፋ ርስት አለሜ
ባንተ እኮ ነው ጌታ መሻገር መትረፌ
የጭንቀት ማለዳ የእንባዬን ለሊቶች የቆምኩት አልፌ
ቀኜ ትርሳኝ ብረሳህ
ምላሴ ይጣበቅ ባላስብህ
የምወድህ ደስታዬ
ገነቴ ነህ መኖሪያዬ ❤ተባረክ ዘርህ ይለምልም
እንደዚህ ውስጥን የሚኮረኩር መዝሙር እድዘምርልን ለረዳህ መድሀኒአለም ክብር ምስጋና ይድረሰው ❤❤
የደረቀን መንፈስ የሚያረሰርስ፣ የተጠማን የሚያረካ፣ የደነዘዘን ልብ የሚያነቃ፣ የማይታዘዝን ልብ የሚለውጥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት ድንቅ ዝማሬ!! ሃዊና ተባረክ ወንድሜ ከዚህ በላይ ጌታ መንፈስ ቅዱስ ያግዝህ! ከማንነትህ አልፎ ይስራ!
Hawiye zemenh ይባረክ
አሜን አሜን ናቲዬ ወንድሜ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ። በጣም አመሰግናለሁ እግዚአብሔር በአንተ በኩል በብዙ ረድቶኛልና ስላንተ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ። ፀጋ ይብዛልህ ናቲዬ
@@ZEMARIHAWAZTEGEGNE Amen Hawina
እልልል 🙏✍️✍️❤️
፩) መሰንቆዬን በአሃያ ዛፎች ላይ ሰቅዬ
የእንቢልታዬ ቅኝት ዜማው ቀርቶ ከኋላዬ
በአደባባዩ በደርቡ ዜማዬ ባይወጣ
ቢታቀብ አንደበቴ ቃል ከአፌ ሲታጣ
የምስጋናን ቃል የፈለጉብኝ
አመስግን እንጂ ዘምር ቢሉኝ
ልቤ ተነሳ ሊያዜምልህ
ቅኔዬ ነቃ እንዲህ ሊልህ
አዝማች
ቀኜ ትርሳኝ ብረሳህ
ምላሴ ይጣበቅ ባላስብህ
የምወድህ ደስታዬ
ገነቴ ነህ መኖሪያዬ
፪) አንተ አይደለህም ወይ የኪዳን ሀገሬ
ሞት እንዳያገኘኝ ከለላ የሆንኸኝ የሕይወት ድንበሬ
አንተ አይደለህም ወይ ያዘመትኸኝ መሪ
በጸናች እጅ እና በተዘረጋች ክንድ ሆነህ ፊት አውራሪ
አንተ አይደለህም ወይ እንዴት ይዘነጋል
ውለታህ ልቤ ውስጥ ዘለአለም ላይጠፋ በጣትህ ተፅፏል
አዝማች
፫) ክንድህ አይደለም ወይ ትናንቴን የረታ
ዛሬን የሚያኖረኝ የነገ ተስፋዬ የነፍሴ መከታ
እጅህ አይደለም ወይ ያጎረሰኝ ቆርሶ
ያጠጣኝ ስጠማ ከልዑላን ማዕድ በክብር አቋድሶ
እጅህ አይደለም ወይ ያከመኝ ታምሜ
አቅፎ ያባበለኝ እንባዬን ያበሰው ጣትህ ነው ሰላሜ
አዝማች
፬) አንተ እኮ ነህ ጌታ የዜማዬ ቃና
የቃላቴ ሞገስ የስብከቴ ርዕስ የንግግሬ አርማ
አንተ እኮ ነህ ጌታ የልጅነት ሕልሜ
የጉብዝና ሃሳቤ የምኞቴ አልፋ ርስቴ አለሜ
በአንተ እኮ ነው ጌታ መሻገር መትረፌ
የጭንቄን ማለዳ የእንባዬን ሌሊቶች የቆምኩት አልፌ
አዝማች
፭) ላምጣ በገናዬን መወድሱን ላንሳ
የልሳኔን ጩኸት ሳልገድብ ሳልሳሳ
ታጥቄያለሁ ቅኔ ስምህ ነው ዜማዬ
ለክብርህ እኖራለሁ መዝሙር ነው ስራዬ
ዜማን በልቤ አርገህ ፈጥረኸኛልና
ማምለክ ነው ሥራዬ አንተን በምስጋና
(ኸረ እኔስ አለኝ ምስጋና ለሕይወቴ ጀግና
ኸረ እኔስ አለኝ ምስጋና ለሕይወቴ ጀግና)፬
አዝማች
እንዲህ አይነት ቅኔ ሁሌም ይናፍቀኛል❤❤❤
ወዳጄ ተባርከሀል ። ደጋግመህ ባርከን አንተም በእንደነዚህ አይነት ሰማያዊ ዜማ 🎸🎻🎸🎻❤❤❤❤
ታማኝ ወንድሜ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ ። እጅግ አመሰግናለሁ ። ፀጋ ይብዛልህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም
@@ZEMARIHAWAZTEGEGNE አሜን 🙏🙏🙏
የምወድህ ደስታዬ ገነቴ ነህ መኖሪያዬ ኢየሱሴ 😰😰🙏ምንጭ ይብዛልህ ድንቅ ዝማሬ ነው
ጌታን የመረጥክ ለእሱ እምቢ ያልክ እውነትን ይዘህ የተነሳህ የወንጌል አርበኛ አብዝቶ አብዝቶ ይባርክህ ሀይማኖት እውነት አይደለም እውነት ህይወት መንገድ ኢየሱስ ብቻ ነው ዝማሬ ለየሱስ ስግደት ለኢየሱስ ጉልበት ሁሉ ለእሱ ይንበረከካል ብዙዎች ይህን እውነት ገፍተው በሰዎች ተወደዋል አንት ተምሳሌት ነህ ለወንጌሉ የጠራህ ስለአንተ ኢየሱስ ይመስገን አሁንም ብዛ ውረስ በስሙ ስልጣን የጨለማ ብርሀን ሁን ኢየሱስን የደበቀብን ሀይማኖት ለእኛ ምን ያደርግልናል ኢየሱስን ከ ሌላ እማልክት እኩል አናማልክም ኢየሱስ ብቻ አዳኛችን ነው ኢየሱስን ብቻ ብቻ እንሰብከዋለን
Ewnet ye leben new ye xafeshew ewnet ene eyesusen mamlek eyesus meketel mew enji yaleg haymanot adelem yehen sel serat yasfelegal gen wengel bante senegereh mekebel be lea senegereh mekad adelem wengel ke mesebku metebaber new asfelagi ewnet enem gen ande ke kaleawadi tv meteche bagelegel des yelegal 🇪🇷 neg gen ande ken ke lebe emamelkew ale malet ahunum ke lebe amelkalew ken ke Christian ga hoge le malet new begena anseche ❤❤❤❤❤❤❤❤
yes❤❤
ይህን መዝሙር ስሰማ ያሉብኝን ችግሮች እረስቼ እረፍት ይሰማኛል ዝማሬ መላእክት ያሰማልን እግዚአብሔር ይመስገን 🙏🙏🙏
ተመልሰ ኮ ወደ ኦርቶደክስ⛪⛪⛪⛪👈❤❤
ተመልሶአል ወደ ቀጥተኛዋ መንገድ
⛪
ፀጋውን ያብዛልህ ተወዳጅ ድንቅ ዝማሬ ነው ❤
"የምወድህ ደስታዬ
ገነቴ ነህ መኖሪያዬ!!
ኢየሱስ
ደግሜ የምልህ ካለኝ ጌታ ትጋትህ ይጠብቅልህ ፥ በጣም ደስ የሚል ስራ ጌታ ሚታይበት ጌታ ሚከብርበት ስራ ይሁን
አሜን ኣሜን
ዝማሬዎችህ እኮ ኢየሱስ አብሮኝ እያለ እንድናፍቀው ይበልጥ ውድድድድ እንዳደረገው ያደርጉኛል ይብዛልህ ከፍ በል ወንድሜ
ጌታ ኢየሱስ አብዝቶ ይባርክ ጸጋውን ያብዛልክ ዘመን እሚሻገር ዝማሬ ነው።❤❤👏
ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን ፀጋዉን ያብዛልህ
የኔ ወንድም ጌታ ኢየሱስ ዘመንህን ይባረከው የተለየህለት ጌታ ያክብርህ
አሜን ፫ዝማሬ መላእክት ያሠማልን 😢😢😢እረ እንዴት ይረሳል 😢😢😢😢
Amen amen ewunet new yalesu minm nenign be buzu tebarek
ሃዊዬ ከተረተረት ያመለጥክ የወንጌል ጀግና ነህ ለአንተ የተገለጠልህ ጌታ ለሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ይገለጥልን ዘመንህ ይባረክ ሁሌም የምትቀኝለት የአብ የድንግል ማሪያም ልጅ ጌታ እየሱስ ፀጋውን ያብዛልህ የመንግስቱ ወራሽ ያድርግልን አሜን
Andun telo lelawn mawdes ayhonbhm🤔
ወንድም አትሳሳት በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሆነን ጌታን የምናስቀድም ወራሾች የሆንን ስሙ ሲጠራ የምንንበረከክ በኢየሱስ በተከፈለልን ዋጋ የምንኖር ነገር ግን የእናንተን የአምልኮ መንገድ የማይመቸን በስርአተ ቅዳሴ የምንረሰርስ በከበሮ በመሰንቆ ዝማሬ ማመስገን የምንፈልግ ጌታ የወደዳቸውን የመረጣቸውን ሐዋርያት ድንግል ማርያም ሰማእታት የምናከብር የምንወድ ብዙዎች አለን ቀሲስ አሸናፊን ማየት በቂ ነው።።ጌታ ተገለጠልን ብለው ህዝቡን ምድራዊ ያደረጉም እንደ አሸን በዝተዋል እኮ።።ጌታ ለእነሱም ይድረስላቸው።።
ተመለሰ ላንተም እግዚአብሔር ያስብህ🙏
የዚህ ኮመንት ባለቤት ዛሬ ላይ ምን ይሰማው ይሆን 😂😂😂😂😂😂
😂😂😂😂እውነት ብለሻል 😂@@meaziwendemumeaziwendemu7012
እውነት ነው በምንም ሁኔታ ውስጥ ብናልፍ ውለታው አይረሳም። ያለፍነውን ሁሉ ያለፍነው በሱ ነው።የሚመጣውንም በሱ እናልፋለን ። እግዚአብሔር ይመስገንልን።ተባረክልን ቤቢሾ
የድልዬ ተባረኪልኝ አመሰግናለሁ በጣም። እግዚአብሔር ይባርክሽ እህቴ በነገር ሁሉ መባረክ ይሁንልሽ።
ጌታ አብዝቶ ይባርክህ ሐዋዝዬ የምር ወደ ቀድሞ ቤትህ መተህ እንድታለመልመን የዘውትር ፀሎታችን ነው
ቅድም በችኮላ ሰምቼዉ አለፍኲት
አሁን ቀስ ብዬ ግጥሙን ስሰማዉ እንዴት ድንቅ ነዉ ተባረክ😭😭😭
ቀኜ ትርሳኝ ብረሳህ
አንተ እኮ በረከታችን ነህ ሀዊ
ወደፊት ነው ፀጋ ይብዛልህ
አምላክ እንደዚ የምትዘምርበትን
ፈጣሪ ጨምሮ ጨምሮ ይሰጥህ
መዝሙሮችክ ሁሌም ቢሆን
የሰልክ ጥሬዎቼ ናቸው
ቀኜ ትርሳኝም ይቀጥላል
፨ቀኝ ትርሳኝ ብረሳህ ምለሴ ይጣበቅ ባላስብህ፨እንኳን ደስ አለን ለአዲሱ ዝሜሬ ጌታ ከፍ ይበል
ቀኜ ትርሳኝ ብረሳህ
ምላሴ ይጣበቅ ባላስብህ
ፀጋ ይብዛልህ ወንድሜ ልፋትህንና ትጋትህን እግዚአብሔር ያስብልህ በሒወትህ አሁንም እርሱን ማክበር ይሁንልህ
በጣም የሚገርም ዝማሬ ተስፋን የሚያድስ ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር የሚጨምር ዘመንህ ይለምልም። እውነት በጣም በብዙ ተባረክ
እንዴት ነፍስን የሚያረሰርስ መዝሙር ነው🙏🙏🙏🙏፡፡ ተባረክ ጌታ አምላክ ከዚህ በላይ ፀጋ ያብዛልህ🙏🙏
በኢየሱስ ስም ዘመንህ ይባረክ ፀጋው ይብዛልህ ተባረክ
አ አምላኬ ስምህ ለዘላለም ከፍ ይበል። ይህን ጥዑም መዝሙር እንድትሠራ የረዳህ ጌታ ስሙ ይክበር።
ወንድሜ ሀዋዝ የጌታ ጸጋ ይብዛልህ፤ ተባረክ።
Hawazeye, siwodih eko, yene tihut wondim, tebarek
Tebarek hawazye tsegaw yibzalik lene new meliekitu 😇🙏😇 semche mwtgeb alchalkum❤❤❤❤❤❤❤❤❤
ምን እንደምል አላውቅም😭😭የምር ሲከፋኝ እና ሲጨንቀኝ ዝማሬዎችህ እጅጉን ያፅናኑኛል ብቻ ብርክ በልልኝ
Ere mn aynete mezemir nw suse asiyzachewene tolu lekeku tebaeku enwedachewalen gitan tebaeku
Zamari Hawish Tsega yabezalek Geta Eyesus bichawun Yadinal Yitadagal Amen Hallelujah
በአንተ ስለአለው የጌታ ፀጋ ክብር ይሁንለት ለእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ።
wooooww, ሀዊዬ፣ I have no words. እውነትም ዜማን /ቅኔን በልብህ አድርጎ የፈጠረህ፣ አባት እና አምላክ ይባረክ። አሁንም ይጨምርልህ ወንድሜ፣ ሌላ ምንም አልልም።
የምወድህ ደስታዬ፣ገነቴ ነህ መኖሪያዬ
ስለአንተ ኢየሱስ ይባረክ ተባርክ ወንድሜ
ባንተ ስላኖረው ቅኔ እግዚአብሔር ይባረክ! እርሱ ሊልቅ ይገባዋል - ያንስበታል!
በድንቅ የተዋሃደ ስራ ነው። ሁላችሁንም ጌታ ይባርካችሁ ።
ስንቴ ሰማው ጌታ ሆይ ተባረክ ውንድምዮ ተባርከ ቅር🎉🎉🎉🎉🎉🎉
mezmur endezi guaguche tebeke alawekem betam des yelal,,,geta abzeto yebarkeh!!!
እናንተን ያስነሳልንን እግዚአብሔር አባቴን አመስግናለሁ
አሁን ስራ እየስራሁ በኤርሮን ስማሁ ቁጭ ብየ ልስማህ ቸኩያለሁ ጸጋው ይብዛልህ አዋዝየ ወንድሜ ስጦታችን ነህ ።
Ewnetegna ye zelalem hiwot sinq ... sile hulum neger yedingil lij eyesus kiristos simu yikber.....
Wendme Hawaze Egziabher Abate chemero chemro yebarkeh Edmena tena yesteh Betam Arif Mezmur newe
Hawaz wendemachen segaw yebezalh tebarekuleg!
Zimare Malaikt yasamalin tsagawun yabzalik Tabarakilin Wandimmachin 🙏🙏🙏❤❤❤⛪⛪⛪
የኔ መልካም ሐዋዝየ የርዳ እግዚአብሔር የተመስገነ ይሁን ክብር ሁሉ ለእየሱሰ ክርስቶስ ብቻ ይሁን ተባርክልኝ የእየሱሰ ጀግና ደሞ ስወድኮ 😍😍😍😍
ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን ! እኛ የምደረ በዳ ተጓዦች ነን ፥ በዚህ የምድረ በዳ ታዲያ ጠላት የጺዖንን( ለእግዚአብሔር በቻ የሆነውን ምስጋና አምልኮ ፥ ኑሮ ....ወዘተ) ከእኛ ይፈልጋል እኛ ግን የጺዖንን (ለክርስቶስ ) የሆነውን ነገር ማስነካት የለብንም ፥ ቤተሰቦቼ በልዩ ልዩ ፈተና እና ችግር ላላችሁ በጌታ በኢየሱስ ስም መጽናናትና መጠግ ይሁንላችሁ !
በኢየሱስም ክብሩ እሱ ይወሰድ
ቀኜህ ትርሳኝ በርሳህ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️🙏🙏🙏
እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልህ ድንቅ ስራ ነው በርታልን
ነፍስን የሚያርስ ዝማሬ ነው ጌታ እየሱስ ይባርክህ ዝማሬዎችህ ሁሌም ህይወትን ያድሳሉ እየሱስን ያስናፍቃሉ ምኖርለትን ህይወት ዞር ብዬ እንድመለክት ያደርጉኛል ተባረክ ጌታ ፀጋውን ያብዛልህ
ጌታ ዘመንህን ይባርክ ! የተወደድክ ወንድሜ ድንቅ ጥበብ ተችሮሃል ያበረታህ አቅም የሆነህ ጌታ ይክበር ❤
even if I am not from you guys, something touched my heart when I am listening this gospel song! I can not stop listening it! much grace brother!
ተባረክ ወንድሜ
ሀዋዝየ እግዚአብሔር ይባርክህ ዝማሬ መላአክትን ያሰማልን
እግዚአብሔር ይመስገን ማልቀስ ሆኗል ስራይ ተባረክ♥ የኔ ኢየሱስ፡
የጌታ ኢየሱስ ጸጋ ይብዛልህ ሃዋዝዬ! እኛንም ደጋግመህ ባርከን በዝማሬዎችህ
Geta eyesus yibarkeh tsegawen yabzaleh hawaz wendeme!
ዘዋዝ ጌታ ይባርክ ድንቅ ዝማሬ ነው
ምን ልበል በእውነት.!!እድሜና ጤና ይስጥህ የአባቴ ልጅ.!!!!!
ዘመንህ በቤቱ ይለቅ ቃላት ያጥረኛል ለመናገር አንተን የባረከ አምላክ ስሙ ይባረክ ጌታ እየሱስ
Wow what a mezmur
Geta ahunm tsegawun yabzaleh wendeme
ድንቅ ዝማሬ ተባረክ ❤️🙏
Zmare melaekt yasemaln enamesegnalen wedme hawaz betam new emnwedh degmo wede tewahdo btmeles betam des yl neber ahunm tsegawn yabzalh
ኸረ ምን ልበል ቃላት አጠረኝ እኮ 🥺🥺
ብቻ ተባረክ ፀጋው ይብዛልህ በቃ 🙏
Woooooooooooooow betam dinik mazimur naw Egziabher enkuan eradah💓💓
ዝማሬ መለአክ ያሠማልን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🥰🥰🥰
አንተ እኮ ነህ ጌታ የዜማዬ ቃና
የቃላቴ ሞገስ የስብከቴ ርዕስ የንግግሬ አርማ
አንተ እኮ ነህ ጌታ የልጅነት ሕልሜ
የጉብዝና ሃሳቤ የምኞቴ አልፋ ርስቴ አለሜ
በአንተ እኮ ነው ጌታ መሻገር መትረፌ
የጭንቄን ማለዳ የእንባዬን ሌሊቶች የቆምኩት አልፌ
ቀኜ ትርሳኝ ብረሳህ
ምላሴ ይጣበቅ ባላስብህ
የምወድህ ደስታዬ
ገነቴ ነህ መኖሪያዬ
Amen for you!
ጌታ ኢየሱስ አብዝቶ ይባርክህ ገና ከዚህ በላቀ ሁኔታ ክርስቶስ ባንተ ውስጥ ይታያል !!! ሀሌሉያ ።
ይገርማል! አጽናኙ ጌታ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ተመስገን!
ጌታ ሰሙ ይባረክ !!! ፀጋ ይብዛል !!! ተባረክ!!!
Amen Amen Tebarek Fetari ybarkh
Zemenih yilemlim,Tsegaw Yibzalih,Tebarek...
ሒዊዬ የተለየህለት ጌታ ያክብርህ ክብር ከሱዘንድ ነው
አግዚአብሔር ይባርክ በመዝሙርህ ባረከን ቃለህይወት ያሰማልን ብሰማው ብሰማው አልጠግብ አልኩኝ አቤቱ ገ
ጌታዬ፡፡፡፡፡፡፡፡
ሐዋዝ ተባርከሀል ፀጋ ይብዛልህ በርታልን ሁሌ አሰንደተባረኩ ነው መዝማሬህ
ዋውው ሐዋዝዬዬ በጣም የምገረም ሰራ ነው የሰረኮ በእውነት የጌታ ኢየሱስ መንፈስ የአገልግሎትህን ፍቅር ዕለት ዕለት ይጨምራል በብዙ ተባረክ ፀጋውን ያብዛልህ የኛ ጀግና እንወዳለን ❤❤ ሁሌም ኑረልን
ፀጋ ይብዛልህ የተባረክ ወንድሜ ዘመንህ በጌታ ይለምልም❤️❤️❤️
ወንድሜ ሐዋዝ ጸጋ በዝቶልሀል ከጌታ የተሰጣችሁን አደራ አትጣሉ በናንተ ብዙዎችን ጌታ እያስመለጠ ነዉና ወደ ኋለ እየተመለከታችሁ ወንድሞችን አታድክሙ ተባረክልኝ
የኔ ብርቱ ወንድሜ ጌታ ስላተ አመሰግነዋለሁ 😍😍😍
እግዚአብሔር በብዙ ይባርክህ ፤መልዕክትን ሞልቶ ቅኔን ያፍስስልህ!!!
ትናንት በብዙ ምህረትና ፍቅሩ የተረዳን በሱ ዛሬን የደረስን እኛ ረስተነው ይሆን?
ባሳደገን ላይ አድገን የሰጠን ነገር ከብሮብን ዓለምና ምኞቱ ላጠመደን
ወይም ደግሞ የጠላትን ድምፅ ሰምተን ትናንት የረዳን ከስንት ክፉ ነገር ያስመለጠን ዛሬ ትቶናል ብለን ተስፋ ቆርጠንም ላለን ትልቅ የመንፈስ ቅዱስ መልዕክት ነው ።
ራሴን እንዳይ አድርጎኛል😢😢
ተባረክ ወንድሜ ፀጋው ይብዛልህ
Betam new des yemilew!! geta kezihem belay abzeto yebarkeh
"እኔስ አለኝ ምስጋና ለሕይወቴ ጀግና! "ተባረክ ሀዊዬ ስላበዛልህ ፀጋ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።ይጨምርልህ ያትረፍርፍህ ወንድሜ!
የረዳክ ጌታ ይባረክ
ተባረክ ሃዊ ጌታ ፀጋውን ያብዛልህ የሚባርክ ፡የሚያስተምር መዝሙር ነው
Bante eko nw geta meshager meterefe yechenken maleda yenbayen lelitoch yekomekut alefe 🙏🙏🙏tebarek wendeme
Tebark wendeme Geta eyesus tsegahun yebzale hulem endzmrk legeta nur God Bless You more 🙏🙏🙏
Aunm yibzalh yihe menfes
አብዝቶ ይባርክህ !!
Tabarek tsegaw yibzaleh😍😍
ለእውነት የጨከንክ ብድራትህ ከላይ ነው ተባረክ ወንድሜ!!!
GETA EGZIABHER AHUNM AHUNM ABIZTO TSEGAWN YABZALH!!!!!!!!!!! Tebarkebetalehu, wendme.
Hawii በመዝሙሮችህ ከአምላኬ ጋር እነጋገራለሁ።መዝሙሮችህ በርግጥም የእርሱ ድምፅ ናቸዉ።ተባረክ
Betam yemwedeha wendeme tebarekelegni🔥🔥🔥🔥🔥❤💛💚💙
ጌታ አብዝቶ ይባርክህ በጣም ነው ምወዲህ
ሃዊ የረዳህ ጌታ ስሙ ይባረክ።
Amennnn geta ኢየሱስ ybark bebzu bante መዝሙሮ ተጽናንቻለው በብዙ
ድንቅ ዝማሬ ነው አብ አባት ዘመንህ አገልግሎትህን ይባርክ ለበረከት ሁን ሄዊዬ🙏🙏🙌🙌❤
እግዚአብሔር አብዝቶ ይባረክ ሐዋዝዬ❤🙏
Geta eyesus abzito yibarki wandime hawaz🙏🙏🙏🙏
አሜን፣አሜን፣አሜን፣ዝማሬ፣መላህክትን፣ያሰማልን፣ተስፍ፣መንግስትክን፣ያዋርስልን፣የአገልግሎት፣ዘመንክን፣ይባርክልን፣በእድሜው፣በጤናው፣ያኑርልን፣ተዋህዶ፣ሐይማኖታችን፣ለዘላለም፣ትኑርልን፣አሜን
ተዋህዶ ሀይማኖታችን????