ቅዱስ ስምኦን (ጫማ ሰፊው) - ክፍል 1 / Saint Simon - Part 1

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 14 жов 2024
  • ቅዱስ ስምኦን (ጫማ ሰፊው
    ተአምረ ማርያም ላይ ከተጻፉት እና በትርጓሜ ወንጌልም ላይ በማቴ5÷29 ለሚገኘው ቃል እንደ ታሪካዊ ማስረጃ ከሚቀርቡት ታሪኮች አንዱ የስምዖን ጫማ ሰፊው ታሪክ ነው፡፡
    በ979 ዓም የፋጢማይድ ሥርወ መንግሥት ግብጽን በሚያስተዳድርበት ወቅት በከሊፋ አል ሙኢዝ ሊ ዲን ኢላህ አል ፋጢሚ ዘመን እንዲህ ሆነ፡፡
    ለሥልጣን ሲል ወደ እስልምና የተቀየረ ያዕቆብ ኢቢን ቂሊስ የሚባል አንድ አይሁዳዊ ነበር፡፡ ይህ አይሁዳዊ ምንም እንኳን ለሥልጣን ሲል እስልምናን ቢቀበልም ልቡ ግን ከአይሁድ ጋር ነበር፡፡ ክርስቲያኖችንም በጣም ይጠላ ነበር፡፡ ይህ ጥላቻው የመጣው በከሊፋው ዘንድ በሚወደድ እና እርሱ ይቀናቀነኛል ብሎ በሚያስበው በአንድ ክርስቲያን ምክንያት ነበር፡፡ ይህ ክርስቲያን ቁዝማን ኢቢን ሚና ይባል ነበር፡፡
    ከሊፋ አል ሙኢዝ ደግ፣ ምክንያታዊ እና በሰዎች ነጻነት የሚያምን ዕውቀትንም የሚወድድ መሪ ነበር ይባላል፡፡ ምሁራን ሲከራከሩ መስማት የሚወድድ ሌላው ቀርቶ የእስልምና ምሁራን እስልምናን ከሚቃወሙ ሰዎች ጋር በነጻነት እንዲከራከሩ የሚፈቅድ ሰው ነበረ፡፡
    ይህንን ጠባዩን የሚያውቀው ያዕቆብ ሙሴ የተባለውን የአይሁድ ረቢ ጠርቶ ከፓትርያርኩ ጋር እንዲከራከር እና ፓትርያርኩን እንዲያሳፍረው መከረው፡፡ ሙሴም ጥያቄውን ለከሊፋው አቀረበ፡፡ ከሊፋውም ለፓትርያርኩ መልእክት ላከ፡፡
    በቀጠሮው ቀን በወቅቱ የእስክንድርያ ፓትርያርክ የነበረው አብርሃም ሶርያዊ በሃይማኖት ዕውቀቱ እና ትምህርቱ የታወቀውን ሳዊሮስ ዘእስሙናይን ይዞት መጣ፡፡ ሳዊሮስ ዘእስሙናይ «በከሊፋው ፊት ይሁዲን መናገር መልካም አይደለም» አለው፡፡
    ይህንን ቋንቋ ሙሴ በሌላ ተርጉሞ «አላዋቂ ብለህ ሰደብከኝ» ሲል ተቆጣ፡፡
    ከሊፋ አል ሙኢዝም «መከራከር እንጂ መቆጣት አያስፈልግህም» አለው፡፡
    ያን ጊዜ ሳዊሮስ «አላዋቂ ብዬ የተናገርኩህ እኔ ሳልሆን ያንተው ነቢይ ኢሳይያስ ነው» ብሎ በትንቢተ ኢሳይያስ 1÷3 ላይ ያለውን ጠቀሰ፡፡ ከሊፋው ገረመውና «እንዲህ የሚል የእናንተ ነቢይ አለ?» ሲል ሙሴን ጠየቀው፡፡ ሙሴም «አዎ አለ» አለው፡፡ አባ ሳዊሮስም «እንዲያውም እንስሳት ከአንተ እንደሚሻሉም ገልጧል» አለው፡፡ ይሄን ጊዜ ከሊፋው ሳቀ፡፡ ክርክሩም እንዲቆም አዘዘ፡፡
    ይህ ሁኔታ ያዕቆብን አበሳጨው፡፡ ራሱ ባመጣው ጣጣ በከሊፋው ፊት መዋረዱም ቆጨው፡፡ ስለዚህም ክርስቲያኖቹን የሚያጠቃበት ሌላ መንገድ መፈለግ ጀመረ፡፡ ሙሴንም አንዳች ጥቅስ ከወንጌል እንዲፈልግ ነገረው፡፡
    ሙሴ በመጨረሻ በማቴ 17÷20 ያለውን «የስናፍጭ ቅንጣት ታህል እምነት ቢኖራችሁ ይህንን ተራራ ከዚህ ተነሣ ብትሉት ይሆናል» የሚለውን አገኘ፡፡ ለያዕቆብም ነገረው፡፡ ያዕቆብም ወደ ከሊፋው በማምጣት «በክርስቲያኖች መጽሐፍ ላይ እንዲህ ስለሚል ይህንን ፓትርያርኩ ያሳየን» አለው፡፡ ከሊፋው ተገረመ፡፡ ፓትርያርኩንም ጠርቶ ጠየቀው፡፡ አብርሃም ሶርያዊ ይህ ቃል በእውነት እንዳለ ነገረው፡፡
    ከሊፋውም «በእውነት የክርስቲያኖች ሃይማኖት እውነት ይሁን ውሸት ለመፈተኛ ይህ ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ ይህንን ማድረግ ካቃታቸው ግን ሕዝቡን እያታለሉ ነውና መቀጣት አለባቸው» ብሎ አሰበ፡፡
    ከሊፋ አል ሙኢዝ ለአባ አብርሃም አራት ምርጫ አቀረበለት
    1. የሙካተምን ተራራ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ ማዛወር ወይም
    2. እስልምናን ተቀብሎ ክርስትናን መተው ወይም
    3. ግብጽን ትቶ ወደ ሌላ ሀገር መሄድ ወይንም
    4. በሰይፍ መጥፋት
    ፓትርያርክ አብርሃም ውሳኔውን ለማሳወቅ የሦስት ቀን ጊዜ ጠየቀ፡፡ ከከሊፋው ዘንድ ከወጣ በኋላም ጳጳሳቱን፣ መነኮሳቱን፣ ካህናቱን፣ ዲያቆናቱን እና ምእመናኑን ሰበሰበ፡፡ ያጋጠመውንም ነገር ነግሮ በመላዋ ግብጽ የሦስት ቀን ጾም እና ጸሎት አወጀ፡፡
    በሦስተኛው ቀን ማለዳ ቅድስት ድንግል ማርያም ለአባ አብርሃም ሶርያዊ ተገለጠችለት፡፡ «ይህንን ነገር የሚያደርግልህ አንድ ሰው አለ፡፡ ወደ ከተማው ገበያ ስትወጣ አንድ ዓይና የሆነ በገንቦ ውኃ የተሸከመ ሰው ታገኛለህ፡፡ እርሱ ይህንን ተአምር ያደርግልሃል» አለቺው፡፡
    አባ አብርሃም ወዲያው ከመንበረ ጵጵስናው ወጥቶ ወደ ከተማው ገበያ መንገድ ጀመረ፡፡ በመካከሉም አንድ በገንቦ ውኃ የያዘ ሰው አገኘ፡፡ ያም ሰው አንድ ዓይና ነበረ፡፡ ጠራውና ወደ ግቢው አስገባው፡፡ የሆነውንም ነገረው፡፡
    ያ ሰው «እኔ ኃጢአተኛ ነኝ፤ ይህ እንዴት ይቻለኛል» አለው፡፡
    አባ አብርሃምም ያዘዘቺው ድንግል ማርያም መሆንዋን ነገረው፡፡
    ያ ሰው ስምዖን ጫማ ሰፊው ይባላል፡፡ አንዲት ሴት እየደጋገመች መጥታ «ይህንን ዓይንህን እወድደዋለሁ» ብትለው ጫማ በሚደፋበት ጉጠት አውጥቶ የሰጣት እርሱ ነው፡፡
    «አባቴ ሕዝቡን ወደ ተራራው ሰብስብ፡፡ እኔ ከአንተ አጠገብ እሆናለሁ፡፡ በአራቱም አቅጣጫ አንድ መቶ አንድ መቶ ጊዜ ኪርያላይሶን በሉ፡፡ ከዚያም ስገዱ፡፡ ከስግደቱ በኋላ ስታማትብ ተራራው ይነሣል » አለው፡፡
    አባ አብርሃም ወደ ከሊፋው ሄዶ ተራራውን እንደሚያነሡት ነገረው፡፡
    ኅዳር 15 ቀን 975 ዓም ሙስሊሞች፣ ክርስቲያኖች፣ አይሁድ፣ ሌሎችም ተሰበሰቡ፡፡ በአራቱም አቅጣጫ ጸሎተ ዕጣን ተደርሶ ኪርያላይሶን ተባለ፡፡ ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ሰገዱ፡፡ ከስግደት ተነሥተው ጸጥ ሲሉ ኃይለኛ ድምፅ ተሰማና ተራራው ካለበት ተነሣ፤ ፈቀቅም አለ፡፡ እንደገና ሰገዱ፤ አሁንም ተነሥቶ ፈቀቅ አለ፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ ሰገዱ ተነሥቶ ወደ ምሥራቅ ሄደ፡፡ በዚህ ጊዜ ከሊፋው በከፍተኛ ድምፅ ጮኸ፡፡ «በቃ፣ በቃ በዚህ ከቀጠለ ከተማዋ ትፈርሳለች» አለ፡፡ ክርስቲያኖቹ በደስታ አምላካቸውን አመሰገኑ፡፡ ከሳሾቻቸው አፈሩ፡፡ ስምዖን ጫማ ሰፊው ግን ጠፋ፡፡
    አባ አብርሃም በብርቱ አስፈለገው፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ሊያገኘው አልቻለም፡፡ አባ አብርሃም ሶርያዊ ይህንን የድንግል ማርያምን ተአምር ለማስታወስ ከነቢያት ጾም ጋር ተያይዞ እንዲጾም አዘዘ፡፡ በገና ጾም የመጀመርያዎቹ ሦስት ቀናት ይህንን ተአምር ለማስታወስ የምንጾማቸው ናቸው፡፡
    ዛሬ ተራራው ከሦስት ቦታ ተከፍሎ ይታያል፡፡ ከምዕራብም ወደ ምሥራቅ ሸሽቷል፡፡ «ሙከተም» ማለትም «የተቆራረጠ» ማለት ነው ይባላል፡፡ ይህ ተራራ ዛሬ በአሮጌዋ ካይሮ ይገኛል፡፡
    ከዚህ ተአምር በኋላ ከሊፋ አል ሙኢዝ ለቤተ ክርስቲያን ብዙ ነገር አድርጓል፡፡ አያሌ የፈረሱ አብያተ ክርስቲያናት ተጠግነዋል፡፡ አዳዲሶቹም ተሠርተዋል፡፡ ይህ ተአምር የግብጽ ፓትርያርኮች ታሪክ በተሰኘው ጥንታዊ መጽሐፍ እና በሌሎችም መዛግብት ተመዝግቧል:: በተአምረ ማርያም ላይ የምናገኘው ታሪክ ከእነዚህ ጥንታውያን መዛገብት የተገኘ ነው፡፡ በሌላም በኩል ተራራው እና በአሮጌዋ ካይሮ የመዓልቃ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ዙርያ የተደረጉ የአርኬዎሎጂ ቁፋሮዎችም ይህንን መስክረዋል፡፡
    በኋላ ግን ቦታው ሆን ተብሎ የካይሮ የቆሻሻ መጣያ ተደረገ፡፡ ክርስቲያኖቹ ወደ አካባቢው የሚጣለውን ቆሻሻ በመጥረግ ታሪኩ እንዳይጠፋ ታገሉ፡፡ በመጨረሻም ነገር ሁሉ ለበጎ ነውና ቆሻሻዎቹን እንደገና ለአገልግሎት በማዋል /ሪሳይክሊንግ/ መጠቀም ጀመሩ፡፡ ዛሬ ለብዙዎች የሥራ እድል ከፍቶላቸዋል፡፡
    የአል ሙከተም ተራራ ተፈልፍሎ የስምዖን ጫማ ሰፊው ቤተ ክርስቲያን ተሠርቷል፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ መቅደስ ክፍት ነው፡፡ ወንበሩ 25000 ምእመናን ይይዛል፡፡ የስምዖን ዐጽምም በመዓልቃ ቤተ ክርስቲያን በተደረገው ቁፋሮ ተገኝቶ በዚሁ የተራራ ቤተ ክርስቲያን በክብር አርፏል፡፡
    ----------------------------------------
    ዲ.ን ዳንኤል ክብረት

КОМЕНТАРІ • 291

  • @እኔሰየድንግልነኝወለተማረ

    ተመሰገን አምላኬ የቅዱሰ ሰሞኦን ታሪክ እንዳይ ሰለረዳህኝ ተመሰገን።።ጌታዬ።።

  • @senayit7198
    @senayit7198 6 років тому +58

    የአባቶቻችን እረዴት በረከታቸው ይደርብን አሜን፫

  • @sara-nd8mw
    @sara-nd8mw 3 роки тому +107

    ተመስገን አምላኬ በባእድ ሀገር ሆኘ ይህን የመሰሉ ቁዱሳን አባቶ ታሪክ እንድሰማ ስለፈቀድክልኝ ተመስገን የቅዱሳኑ በረከት ይገርብን

    • @yohamnanmanki7592
      @yohamnanmanki7592 Рік тому +1

      አሜን በረከታቸው ይደርብን 🥺🙏♥️♥️✝️

    • @Israel9563
      @Israel9563 Рік тому

      Amen amen amen 🤲🤲🤲

    • @werkitazarra4338
      @werkitazarra4338 Рік тому

      አሜንአሜንአሜን፣በረከታቸው፣ይድረሰን

    • @EtifalemYifiru
      @EtifalemYifiru Рік тому

      አሜን አምን አሜን

    • @mmekdesttadese
      @mmekdesttadese 5 місяців тому

      አሜንበረክታችዉ ይድረብንአሜንአሜን🤲🤲🤲

  • @kibrealemye8319
    @kibrealemye8319 6 років тому +46

    በእውነት ልኡል እግዚያብሄር እረዥም እድሜና ጤናን ይስጥልን ብዙ ጥራችሁ መንፈሳዊ ህይወትን ለምታስተምሩን ወድም እህቶቸ ፀጋውን ያብዛላችሁ እናም ይህንን የተመረጠና የተባረከ ትምህርትን እባካችሁ ሌላም የቅዱሳን ፌልም ልቀቁልን

  • @MmMm-ls9iy
    @MmMm-ls9iy 8 місяців тому +4

    የአባቶቻችን እረዴት በረከታቸው ይደርብን አሜን፫🙏💙🌿

  • @Ggg-vs1iy
    @Ggg-vs1iy 4 місяці тому +2

    አሜን የቅዱስ ስምኦን ረደት በረከት ምልጃና ፀሎት አይለየን አሜን💚💐💚💛💛💛❤❤❤❤⛪👏🙏🙏👏⛪

  • @ፍቅሬእናቴህይወቴስማእቷአ

    ስላም ላንተ ይሁን ወንድሜ እባክህን ሌሎች ፊልሞችን ልቀቅልን ይህንን በሌላ ተለቆ ነበር ብዙ ያላናያቸው መንፍሳዊ ፊልሞች አሉ ለምሳሌ የአባ ሚናስ ፣ የአባኖፍር ፣ አባ ፍልቶኦስ ፣ ቅዱስ መርሚና ብዙዎች አሉ እባክህን ልቀቅልን እግዚአብሔር ይስጥልኝ

    • @yekidusantarik
      @yekidusantarik  6 років тому +17

      ሰላም እህቴ አንች እንዳልሽው የማላደርገው አውቄ
      ነው እናንተ በዚህ ተነሳስታችሁ እራሳችህ እየገዛችሁ መንፈሳዊ ፊልሞችን አንድታዩ ነው፡፡ እኔ ሁሉንም የማስገባ ከሆነ መንፈሳዊ
      ፊልሞችን የሚያዘጋጁ ሰወች ይከስራሉ፡፡ እኔ የምለቃቸው በውጪ ላሉትና መግዛት ለማይችሉት በማሰብ ነው፡፡

    • @kedesthoylemgnilen6824
      @kedesthoylemgnilen6824 5 років тому +3

      eko wendime legna megzat lemanichilew likejilina hager west yalut yegezalu egna gin anchilim

    • @ሰውሆይለህሊናህኑር
      @ሰውሆይለህሊናህኑር 5 років тому +2

      @@yekidusantarik ሰላም ወንድማችን የቅዱሳንን ፊልም ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ ማለቴ መንፈሳዊ መዝሙር ቤት ውስጥ
      በስደት ስለሆንን ስለማላውቅ ነው

    • @yekidusantarik
      @yekidusantarik  5 років тому +4

      @@kedesthoylemgnilen6824 እሽ የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ፤ የነሱንም ስራ እንዳለበላሽ በማሰብ ነው ቶሎ ቶሎ የማለቀው፡፡

    • @yekidusantarik
      @yekidusantarik  5 років тому

      @@ሰውሆይለህሊናህኑር አዎ መንፈሳዊ መዝሙር ቤቶች ውስጥ ማግኘት ይቻላል፡፡

  • @ባዓታነገሯወደማታየሚኒሊክ

    የ#ቅዱሱ አባት የስምኦን በረከት እረዴቱ ይደርብን ይድረሰን በዚህ መነፈሳዊ የፊልም ትረካና ትርጉም የተሳተፋችሁ ሁሉየ ህይወትን ቃልያሠማልን
    አሜን አሜን አሜን🇨🇬🇨🇬🇨🇬

  • @ኦርቶዶክስናትዉቤቴ
    @ኦርቶዶክስናትዉቤቴ 3 роки тому +3

    የኣቦታችን በረከት እና ረዲኤት ይደርብን ኣሜን፫

  • @Tewab
    @Tewab 6 років тому +19

    አሜን አሜን አሜን
    የፃድቃን የቅዱሳን ረድኤት በረከት ይደርብን
    ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
    🙏🙏🙏

  • @redidani5893
    @redidani5893 Рік тому +3

    እንዴት ደስ እንዳለኝ በስመአብ ብዙ ብዙ ስራልን እሽ እእእ ንጉስ ሰለሞን አዳምና ሄዋን የልጅነት ትውስታዎቼ ናቸው 😔😔😔😔

  • @roziawoke1301
    @roziawoke1301 2 місяці тому

    አምላኬ አመሰግናለሁ ምን አይነት ድንቅ ነው ቀናተኛው ስምኦን ❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @melkamaddis9582
    @melkamaddis9582 6 років тому +7

    አሜን የቅዱሳን አባቶቻችን በረከት ይደርብን

  • @Meme-gq9iu
    @Meme-gq9iu 2 місяці тому

    የአባቶቻችን እረዴት በረከተቸዉ ይደርብን አሜን❤❤❤

  • @enatmesfin
    @enatmesfin 4 роки тому +18

    በረከታቸው ይደርብን ይሄንን መንፈሳዊ ፊልም ላይ የተሳተፋችት ሁሉ እግዚአብሔር በማይጠፋው በሰማያዊው ቀለም ስማችሁን ይጻፍ አመሰግናለሁ ቃለ ሕይወት ያሰማልን እግዚአብሔር ለሁለተኛ ጊዜ ነው ያየሁት

    • @classicphone5908
      @classicphone5908 3 роки тому

      አሜን ፫ አባቶቻችን በረከት አይለየን

  • @ክርስቶስፍቅርነዉየድንግል

    ቃለ ህይወት ያሰማልን የአባታችን የቅዱስ ስምኦን በርከት በህዝብ ክርስቲያን ላይ ይደርብን አሜን አሜን አሜን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር አሜን ❤💛💚

  • @እየሩሳሌምየማርያምልጅእየ

    አሜን አሜን አሜን ቃለህይወትን ያሰማልን የቅዱሳኖቹ በርከታቸው ይደርብን

  • @FasicaMesele
    @FasicaMesele Рік тому +1

    ያባታችን ስምዖን በረከታቸውና ጸ ሎታቸው ከእኛ ጋር ይሁን። ❤❤❤❤

  • @LetiHaylu
    @LetiHaylu Місяць тому +1

    YE SIMON REDET AND BEREKET AYELYEN AMEN ❤❤❤

  • @rahelmamo4970
    @rahelmamo4970 Рік тому +1

    የቅዱስ ስምኦን ረድኤት በረከቱ ይደርብን ቦታውንም ረግጬ ስለተባረኩ እግዚአብሔር ይመስገን በእውነት❤❤❤

  • @enesyemaryamnegnyemaryam2770
    @enesyemaryamnegnyemaryam2770 6 років тому +5

    አሜን ቃለሁወት ያሰማልን የቅዱሳን በረከታቸዉ ይደርብን ቃለሂወት ያሰማልን

  • @mxmmxm8889
    @mxmmxm8889 5 років тому +4

    አሜን አሜን አሜን ይህነን ቅድሰ ቃል ልመሰተ ሰልፍቅድከለኘ ከብረ አነ መሰገን ለተ ይሁን ይአባታችን ብረከተ ይድረብን

  • @getenetgirma2435
    @getenetgirma2435 5 років тому +3

    ቃለሒወትን ያሰማልን የቅዱሳን በረከት ይደርብን አሜን

  • @እኔሰየድንግልነኝወለተማረ

    አሜን ቃለሂይውትን ያሰማልን ቸረነትህንና ምህረት እረድኤትህ ቅዱሰ ሰሞኦን ይድረብን ለኛ አሜን

  • @fatmaman2519
    @fatmaman2519 6 місяців тому

    አሜን አሜን አሜን የአባታችን ስምኦን እረዴት ና በረከቱ አይለየን🙏🙏🙏

  • @ቲጅየድንግልማርያምልጅ

    የቅዱስ ሰምኦን ምልጃውና ፆለቱ በረከቱ ከኛጋ ይሁን አሜን ፫ ለዚች ስአት እና ደቂቃ ስላደረስከን ልዑል እግዚያብሔር የተመሰገነ ይሁን አሜን ፫

  • @GcGc-h2j
    @GcGc-h2j 6 місяців тому

    አሜን አሜን አሜን የአባታቸ በርከታቸዉ እርደታችዉ ይደርብን ይህንን ቃል እድነሰማ ሰለፈቀደልን እግዚአብሄር ይመሰገን

  • @talatalaco9976
    @talatalaco9976 4 роки тому

    አሜን አሜን አሜን
    የቅዱሳኑን በረከት ያሳድርብን
    ተመስገን ይህንን የቅዱሳኑን በረከት እንዳይ ሰለፈቀድክልኝ አምላኬ እጅ አመሰግናለሁ ተመስገን

  • @shoma8844
    @shoma8844 6 років тому +5

    አሜን አሜን አሜን ቃለህይወትን ያሰማልን እግዚአብሔር አምላክ ከቅዱሳን ረድኤት በረከት ያሳትፈን አሜን፫

  • @mangestu4336
    @mangestu4336 5 років тому +2

    በእዉነቱ እግዚአብሔር አምላክ የተመሰገነ ይሁን የቅዱስ አባታችን ስምኦን በረከትና ረድኤት አለየን ይህንን እንድናይ የፈቀደልን ፈጣሪ ይመስገን አሜን

  • @hannasalam672
    @hannasalam672 Рік тому

    ሁሉ በእግዚአብሔር ይቻላል ተመስገን አማኑኤል የድንግል ማርያም ልጅ 🙏የአባቶችእረዴት በርከታቸው ፅናታቸው ተጋድሎዓቸው ይደርብን አሜን አሜን አሜን

  • @tigistashuma6088
    @tigistashuma6088 8 місяців тому

    እግዚያብሔር፣ይመስገን፣አሜን፣አሜን፣አሜን፣የፃድቃን፣የሰማይታት፣በረከታቸው፣ረዴት፣ይድርብን፣ቃለሂወት፣ያሰማልንተስፍ፣መንግስተ፣ሰማያትን፣ያዋርስልን፣የአገልግሎት፣ዘመናችሁን፣ይባርክልን፣በእድሜ፣በጤናው፣ያኑርልን

  • @fikrtbahru6525
    @fikrtbahru6525 Рік тому +1

    የአባታችን በረከት አይለየን

  • @SenayFshaye-l4y
    @SenayFshaye-l4y 5 місяців тому

    አግዚኣቢሄር ይመስገን ኣሜን ኣሜን ኣሜን🙏✝️⛪️

  • @zinashteshome2764
    @zinashteshome2764 4 роки тому +1

    Egezibehre Yemesgani Amen Amen Amen Amen Amen Amen 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

  • @high1166
    @high1166 6 років тому +3

    አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን የቅዱሳኖች በረከታቸው ይደርብን የአባታችንን እግዚ አብሄር ይፈቀድልንና የአብርሃምን ታሪክ ማወቅ እንፈልጋለን ልቀቁልን

  • @ሁለተሀዋሪያትየድንግልልጅ

    አሜን አሜን አሜን ቃል ህይወት ያሰማልን

  • @almazderebe2023
    @almazderebe2023 Рік тому

    መባረክ እኮነው እግዚያቤርን ቃል ባናተላይ ተመስሎ እድንማር ያደረገን ክብር ይግባው

  • @gfccucu4334
    @gfccucu4334 3 роки тому

    አሜን አሜን አሜን የቅዱስሳን በረከታቸው ፉቅራቸው ይደርብን
    አቤቱ የሰራዊት ጌታ ሆይ ስለ ወዳጆችህ ብለህ ንፁህ ልብ ፉጠርልኝ ንፁህ ፉቅር ስጠኝ

  • @tizitabehrnu9709
    @tizitabehrnu9709 Рік тому

    እግዚአብሔር ይመስገን 🙏
    የአባቶቻችን በረከቶች ይደርብን

  • @ምልኣትየማርያምልጅነኝ

    ተመስገን አምላኬ የዚህ ቅዱስ ስምኦን አባት በረከቱ ይደርብን

  • @እግዚአብሄርእረኛየነውልቤ

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሠማልን የቅዱሳን በረከታቸው ይድርብን

  • @እሴተማርያምየድንግልልጅ

    ቅዱስ አባታችን በረከትወት ይድረሰን አሜን

  • @hadasberhe4812
    @hadasberhe4812 5 років тому +2

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን በረከታቸው ይደርብን

  • @asmertasmert783
    @asmertasmert783 3 роки тому

    ኣሜን ኣሜን ኣሜን ቃለ ህይወት የስመዐልና ናይ ቅዱስ ኣቦና ሳሞኦን ረድኤቶምን ፀጋ በረኸቶምን ኣይፈለየና ኣሜን

  • @አምላከቅዱስጊወርጊስአባቴ

    የአባታችን በረከት ረደኤት ትደርብን በፆለታቸውም ይማሩን አሜን፫✝️

  • @ፊዮሪየእናቷ
    @ፊዮሪየእናቷ 3 роки тому

    ቃለ ሂወትን ያሰማልን የእናታችን ንፅህት ድንግል ማርያም ልጅ ጌታችን መዳኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ስሙ ከአፃናፍ እስከ አፅናፍ የተመሰገነ ይሁን የቅዱሳን በረከት አይለየን

  • @brhanie6823
    @brhanie6823 3 роки тому

    ቃለ ህይወት ያሰማልን የቅዱሳን በረከት እረድኤት አይለየን አሜን፫

  • @ሳምራዊትየማርያምልጅ-ቸ4ፈ

    አሜን አሜን አሜን
    የቅዱሳን እረደኤት በረከታቸው ይደርብን

  • @buzekonjo
    @buzekonjo 6 років тому +1

    Amen amen amen kale hiwot yesamelen yeqidusanoch barekatina ridet kahulan gera idernl Amennnnnn

  • @የማርያምኔኝየማርያምልጅ

    አሜን አሜን አሜን የቅዱሳን በረከታቸዉ ይደርብን 🙏🙏🙏

  • @hcggxgv7146
    @hcggxgv7146 3 роки тому

    የኣባቶታችን በረከት ኣይለየን

  • @AbcDe-ii9dz
    @AbcDe-ii9dz Місяць тому

    ተመስገን ገታየይ ስለኩሉ ነገር ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @ፋኑየእናቷልጅ
    @ፋኑየእናቷልጅ 6 років тому +3

    የኣባታችን ረድኤት በረከቱን ያሳድርብን።አሜን

  • @SfddSrsd
    @SfddSrsd Рік тому

    የአባታችንረዴትበረከትይደርብንአሜን
    ልኡልእግዚያብሔርየተመሠገነይሁን
    እንዳይስለፈቀደልኝ

  • @asterastu1364
    @asterastu1364 4 роки тому

    አሜን አሜን አሜን ቃለህይወት ያሠማልን አግ ዚያ ብሔ የቅዲሳን በረከታቸዉ ይደርብንየ የሰሞን አባታችን በረከቱ ይደርብን አሜን

  • @sarahmohammed8130
    @sarahmohammed8130 2 роки тому

    የቅድሳን አባቶቻችን ርድኤት በረከታቸውን ይደርብን አሜን፫

  • @tigstwelo9351
    @tigstwelo9351 Рік тому

    አሜንአሜንአሜን❤❤❤❤❤❤

  • @ሔኤሜን
    @ሔኤሜን Рік тому

    አሜን የቅዱሳን አባቶቻችን በረከት ቡራኪ ትድረሰን

  • @samiraamira9609
    @samiraamira9609 5 років тому +1

    አሜን አሜን አሜን የአባቶቻቺ መላጋ ፃሎት አየልስይን

  • @ዳሩሰላም
    @ዳሩሰላም 3 роки тому

    በረከታቸውን ፆሎታቸውን የቅዱስ ስምኦን ከኛ ጋ ይሁን ቃለ ህይወት ያስማልን

  • @Tigestmulu-sz7zl
    @Tigestmulu-sz7zl Місяць тому

    ተመስገን አምላኬ የቅዱሳነን ታሪክ እንድስማ ስለረዳህኝ ተመስገን ጌታዬ።።።።።

  • @sliymamed7265
    @sliymamed7265 6 років тому +2

    አሜን አሜን።አሜን
    የቅዱሳኑ ርእድት ብርክታችው ይድርብን

  • @እርጅኝድንግልማርያም
    @እርጅኝድንግልማርያም 6 років тому +3

    ቃለህይዎትን ያሰማልን በረከታቸው ይደርብን

  • @ሜሮንትግራወይቲ
    @ሜሮንትግራወይቲ 6 років тому +3

    ቃለ ህይወት ያሰማልን በረከት ቅዱስ ስምኦን ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን
    ክፍል ሁለት በደስትል እንጠብቃለን

  • @tijimasresha8342
    @tijimasresha8342 3 роки тому +1

    እግዚአብሔር ተመስገን የአባቶቻችን እረደዬት በረከት ይደርብን 🙏🙏🙏

  • @yordanosambebir8411
    @yordanosambebir8411 5 років тому +6

    በጣም እናመስግናለን እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛላችሁ

  • @fgryfgry3882
    @fgryfgry3882 3 роки тому

    አሜን አሜን አሜን ያባቶቻችን በረከት ይደርብን አምላኬ ሆይ ልቦናችነን ክፈትልን ካገራችን ገብተን ለንስሀ አብቃን አሜን

  • @zebenayabebe8569
    @zebenayabebe8569 3 роки тому

    አቤት መታደል አባቴ ሰመኦን በረከትህ ትጎብኘኝ 🙏🙏🙏🙏🙏🙏😭😭😭😭😭

  • @meaziyoutube7899
    @meaziyoutube7899 5 років тому +1

    ያባታችን በረከታቸው ይደርብን ፁሉት ልመናቸው አይለየን

  • @እግዚአቤሄርመልካምነው

    ተመስጌን አምላኬ ይህን እዳይ የረዳሀኝ ተመስጌን ተመስጌን ተመስጌን 🙏🙏🙏

  • @ah7053
    @ah7053 4 роки тому

    አሜን አሜን አሜን አሜን
    በርከታችው አይለያን
    በእውነቱ ይህን የቅዱስ ታሪክ ለሰማችሁት ቃለ ህይወት ያሰማልን እንድሰመ ስለርደህን እግዚአብሔር ይማሰገን

  • @asnew8192
    @asnew8192 2 роки тому

    ቃለ ህይወት ያሰማል ያስተላለፋችሁልን እህት ወድሞቼ ጸጋውን ያብዛላችሁ እኛ በውበታችን ተመክተን እራስ ወዳድ ነን ግን ቅዱስ ስሞኦን አይናቸውን በወስፌ አወጡት የቅዱስ ስሞኦን በረከታቸው ይደርብን አሜን፫

  • @mesitawtikorma8468
    @mesitawtikorma8468 3 роки тому

    አሜን አሜን አሜን የአባታችን እረዴት በረከታቸወ ይደረብን አሜን፫

  • @abeethiopiaethiopia5800
    @abeethiopiaethiopia5800 2 роки тому

    የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን
    በርከታቸው ይደርብን

  • @እመቤቴአቺንያመነማንአፈረ

    የቅዱስ አባታች ስምኦን ረደት በረከት ይደርብን አሜን
    ክፍል 2 በተስፋ እጠብቃለሁ

    • @yekidusantarik
      @yekidusantarik  4 роки тому

      ክፍል 2 ua-cam.com/video/FK3iZzctKBo/v-deo.html

  • @BfhgdGriyyr
    @BfhgdGriyyr Рік тому

    እግዚአብሔር ይመስገን❤❤❤🤲🤲🤲🤲🤲

  • @vanishathvanishath2441
    @vanishathvanishath2441 3 роки тому

    የአባታችን በረከት እረደኤት ይደርብን አሜን፫

  • @zebaasrat9290
    @zebaasrat9290 6 років тому +2

    አሜን አሜን አሜን
    ያባቶቻችን በርከት ይደርብን
    ቃለህወት የስማልን
    P2

  • @ኮኮብየጌታባርያ
    @ኮኮብየጌታባርያ 3 роки тому

    የአባታችን ስምኦን በረከቱ ይደርብን

  • @fekertemariamgetachew5081
    @fekertemariamgetachew5081 Рік тому

    ቅዱሰ አባታችን በረከቱ በኞ ላይ ይደር

  • @selambeyene2781
    @selambeyene2781 5 років тому +1

    አባቶቻችን በረከታችሁ አለይን አሜን
    ቃለ ህይወት ያሰማልን

  • @Bgxbbvst-rc5yx
    @Bgxbbvst-rc5yx 6 місяців тому

    የቅዱስ ስምኦን እረድኤት በረከቱ ይደርብን😢❤❤

  • @BetySisay-h3w
    @BetySisay-h3w Рік тому

    የአባቶቻችን እረዴት በረከት ይደርብን አሜን።🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

  • @akezaberhe6216
    @akezaberhe6216 Рік тому

    _ብሓቂ ቃለ ህይወት የስመዐልና ናይ ቅዱስ ስምኦን ረዳኤቱ በረከቱ ምስ ኹላትና ህዝብ ክርስትያን ይኹን አሜን_

  • @የድግልልጅነኝበስደትያለሁ

    አሜን፫ የቅዱሳኑ በረከት ይደርብን

  • @SenaitKassa-k3p
    @SenaitKassa-k3p 8 місяців тому

    አሜን አሜን አሜን ቃል ሄውት ያስማልን አሜንአሜንአሜንቃልሄውትያስማልን

  • @HeluSweet-v6b
    @HeluSweet-v6b 7 місяців тому

    Amen yesu rdiet bereket yderbn aemen

  • @jddjdhh5938
    @jddjdhh5938 3 роки тому

    በረከታችን ይደርብን ይሄንን መንፈሳዊ ፍልም ላይ የተሳተፋችሁ ሁሉ እግዚኣብሄር የማይጠፋው በሰማያውን ቀለም ስማችሁን ይፃፉ እነማሰግናሁን ቃለ ሕይወት ያስማልን እግዝኣብሄር ኣሜን ( ፫)።

  • @zerena-6573
    @zerena-6573 10 місяців тому

    አባቴ በረከታቸዉ ይ ደርብን

  • @adanuetio1511
    @adanuetio1511 4 роки тому

    አሜን አሜን አሜን የቅዱስ ሰምኦን ረድኤት በረከታቸው ከሁላችንም ጋር ይሁን

  • @mikimolat7801
    @mikimolat7801 6 років тому +1

    አሜን አሜን አሜን በረከታቸው ይደርብን አሜን አሜን አሜን

  • @tmretmre3793
    @tmretmre3793 3 роки тому +1

    የ ቅዱሳኖች ረድአት ቤረከታቼወ ይድሬን

  • @meratngaatuumeratngaatuu6365
    @meratngaatuumeratngaatuu6365 3 роки тому +1

    Amen amen amen amen amen amen amen amen amen amen amen amen amen amen amen Amen amen amen amen amen amen amen amen amrn amenn🙏🙏🙏🙏⛪️⛪️⛪️

  • @ጩጬዋነኝእናቴንናፋቂ

    ኣሜን አሜን ኣሜን ቃለ ህይወት ያስማልን የኣባቶቻችን በረከትና ረዲአት ይደርብልን 🙏🙏🙏

  • @እግዚአብሔርእረኛየነ-ገ5መ

    የአባቶቻችን በረከት እረድኤት ይደረብን አሜን አሜን አሜን

  • @هيامالعيسائي-ب9ه
    @هيامالعيسائي-ب9ه 4 роки тому

    ተመሰገን ኤሄ ላሳየን በረከት የቅዱስ ስምኦን በረከት ከሁላችን ዩሁን

  • @eyeruskonjoabebe228
    @eyeruskonjoabebe228 4 роки тому

    የቅዱስ ስሞኦን እረድኤት በረከት ይደርብን አሜን

  • @beti5276
    @beti5276 6 років тому +2

    ቃለ ህይወት ያሰማን በረከታቹሁ ይደረብን

  • @tsedaytseday9415
    @tsedaytseday9415 4 роки тому

    አሜን አሜን አሜን የቅዱሳን አባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን🙏