Just speechless. Dave your questions are exactly on point and they showed how you passionately took your time and well prepared on them. Dr, Alemayehu's answers are far beyond educational and his way of expressing ideas is very impressive. I'm sure how his students and colleagues feel lucky to have him around them.Thank you so much Dave!
It was amazing interview , great way asking with smart way answering. Doctor has -positive Attitude -Great Aptitude -Great altitude! Quality is your identity! ,long live and good health for you.
Your thorough preparation shines through in every episode, and this one was no exception. The engaging and thoughtful dialogue with Dr alemayew , who is not only a distinguished doctor but also an extraordinary person, made for a truly enlightening and memorable discussion. Kudos to both of you for such a compelling podcast!!!!!
ምነው ምነው ዴቬ በሁለት ክፍል ብቻ የዶ/ር አለማየሁን interview ቋጨሀው ብዙ ክፍሎችን ስንጠብቅ..ማነው እንደኔ ያዘነ 😞
Maybe dr does not have time
he isn’t a fan of Screen-man
እኔም ከፍቶኛል
That's excess for this fool people 😅
Er please add 2 more parts deve with this Kind man
ጋዜጠኛ እንዲህ ተዘጋጅቶ ሲጠይቅ በጣም ደስ ይላል! በርታልን!👏👏 እንደ ዶ/ር አለማየሁ ያሉ ለሃገር የሚጠቅም ሃሳብ ያላቸውን ምሁራን ጋብዝልን
ምን ያድርግ ብለህ ነው የዶክተር እውቀት ይመስጣል እየሰማሁት ወደሌላ አለም ገባሁ በህሊናያ የአበው ትህትና እውቀት ምክር ናፈቀኝ ሳስበቻው አይኔ እባ ያሞላል 😢
ልክ ነህ እኔም እንዳንተ ነው የተሰማኝ
የዶክተርነት ማዕረግ በቦታው የተገኝው በዚህ ሰው ብቻ ነው 👌❤
Owww agelaletse
አንተም እራስህ ትክክለኛ ሰው ስለ ሆነክ ነው🌹🌹🌹 እንደዚህ ትክክለኛ ሰው የፈረጅ ከው ጎበዝ ሰው ነህ 🌹🌹🌹
በትክክል
exactly
ዶክተር ዓለማየሁን አውቃቸዋለሁ ። የዘላለም አክባሪያቸው ነኝ። ጋዜጠኛውን ግን አለማድነቅ ድንቁርና ነው። ሁሉንም መጽሐፎች ማንበብ ብቻ ሳይሆን በጥልቀት ተረድቷቸዋል። ይጠይቃል።አጠያየቁ ለዛ አለው። መልሱን ለአድማጭ ሳይሆን ለራሱ እንደሆነ አድርጎ ያዳምጣል። ለሁሉም ጋዜጠኞች ሥልጠና ብትሰጥ ጥሩ ነበር። አመሰግንሃለሁ❤❤❤
ይህን ቃለመጠይቅ ካደመጥኩ በኃላ መፅሐፍቱን ደግሜ ማንበብ እንዳለብኝ ተረድቻለሁ።
ዳዊት፣
በ እውነቱ እነደዚህ ተዘጋጅቶ እንግዳን መጋበዝ አድማጭንም የተጋበዘውንም እንግዳ ማክበር ነውና በጣም አመሰግንሀለሁ🙏🏾
ዴቭ ስለእውነት በቃላት ድርድራ ባሞካሽህ እምብዛም አይጠቅም, አምላክ የበለጠ ጥብበቡ ይጨምርልህ, ካንተ መገለጥ እኔም ብዙ አተርፋለሁና። እንቶ ፈንቶ ምድሩ እና ሰማዩን ባጥለቀለቀበት በዚ ዘመን እንዲ ያለው ጠብሰቅ ያለ ቁም ነገር ያዘለ ወግ መቋደስ እልም ባለ በርሀ ውስጥ ቀዝቃዛ ውሀን እንደመጎንጨት ነብስን ያረካል, መንፈስን በሀሴት ይሞላል።
በርታልኝ ወንድማለም።
እዉነት ነዉ❤
ጋዜጠኛው የምትጠይቀው ጥያቄ ተገቢና አስተማሪ ነው ዶ/ር አለማየሁ ዋሴን ስላቀረብክልና ይሄንን ሁሉ እውቀት በእርጋታ እንድንቀስም ስላደረከን እናመሰግናለን ቀጥል በርታ🙏👏
"ታሪካችንን መሸከም የሚያቅተን ; በድሆች ሀገር እየኖርን የግል ስኬት የምንመኝ ከንቱ ህዝቦች" wow big respect 🙏 for both of you.
ደግመህ እንድትመጣ እፈልጋለሁ ዶ/ር አለማየሁ 🙏
እዴሜ ልኬን ብሰማው የማልሰለቸው ጥንቅቅ ብቅት ያለ አንደበተ ርዕቱ እውቀቱ ውቅያኖስ በዚች በውስን ገላው ሞልቶ የሚፈስ የኔ ዘመን ሊቅ : እድሜና ጤና አብዝቶ ይስጥህ
ዶክተር አለማየሁ የህይወቴ Game changer ነው ። ፈጣሪ እድሜ እና ጤና ይስጥህ ❤❤❤።
Bro ምን ማለት ነዉ Game changer
@@CheerfulHighway-er2wj Game changer ያልኩበት ምክንያት ህይወቴ በመፅሃፉቹ positively እንዲቀየር ስላረገ ነው ። ለምሳሌ , ስለ ሀገራችን እና ስለ ህዝባችን ያለኝ አመለካከት የተበላሸ ነበር ይህ ንን እንድቀየር እና ቆም ብዬ እንዳስብ አርጎኛል
እውቀት ቆሞ ሲሄድ ማለት ዶክተር አለማየሁ ረጅም ዕድሜና ጤና ያድልልን
አንኳን ደህና መጣህ የፈጣሪ ጥበቃና ምህረት አይለይህ ባለውለታዬ ነህ ሁሌም በልቤ ትልቅ ቦታ አለህ ወደእናት ቤተክርሰቲያኔ ያንተ መጽሀፎች መልሰውኛልና አክብሮቴ የላቀ ነው እረጅም እድሜን ከጤና ጋር ያድለህ።
ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ ለእኔ እጅግ በጣም ታላቅ ሰው ናቸው ...
ቀረፃ ላይ ትንሽ ድምፃቸው የራቀ ነበር...
“By choice” what a powerful word 🥺 Dave pls we need Dr. to see again before the new come pls
ክብር ይስጥልኝ ቁምነገረኛና የሚተረፍባቸው episodeች ናቸው ሁለቱም🙏
ጋዜጠኛ ዳዊት እና ዶ/ር አለማየሁ ስለ ሰማኋዋችሁ ደስ ብሎኛል:: ሰምቼ ለመለወጥ ያብቃኝ ...ክብር ይስጥልኝ። በእውነት!!
የዚህ ቃለመጠይቅ ክፋቱ ማለቁ ብቻ ነው! ዶ/ር ዓለማየሁ(ሲሳይ) በእድሜ በጤና ይጠብቅህ አንብቤ የማልጠግባቸው ሌሎች መፃሓፍቶችን እጠብቃለሁ🙏💚💛❤
ሁሉም ሀበሻ ማየት ያለበት ሾዎ ነው እናመሰግናለን
በመጨረሻ ዶር የተናገረውን ውስጤ ነበር እንዲህ አንብቦ ተዘጋጅቶ የመጣ ምርጥ ጠያቂ እናም ደስ የሚል ቃለ ምልልስ ነበር "እንደነ ሰይፉ መፀሐፍ ፅፈሐል ግን አላነበብኩትም ብለው በድፍረት የሚጠይቁም ስላሉ ለማለት ነው"ዶር ሁሌም አትጠገብም
ተኝቼ እንዳለው አሁን ገባኝ
የ ህይወት ማንቂያ ደወል ብያለሁ ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ
ለእኔ Number one podcast in Ethiopia !
ዴቭ የማዳመጥ ችሎታው- ጥያቄዎቹ አጠቃላይ ዝግጅቱ በጣም ደስ ይላል።
ዶር አለማየሁ የሚናገረውን የሚኖር ሰው ነው ከዓመታት በፊት የሚሰራበት መስርያ ቤት የሚከፈለው ብር ከፍተኛ በመሆኑ ይሄንን ሁሉ አለፈልግም እንዳለ ሰምቻለሁ።
ዳዊት የጋዜጠኝነት ልዕቀትህ ከዶ/ር ጋር ባደረከው ቃለ መጠይቅ አሳይተህናል 👍 በእውነቱ ከሆነ ሞያቸው የነፍሳቸው ጥሪ የሆኑ ምሁራን ሲዋሀዱ ነብስን እንደሚያለመልሙ አሳይታችሁናል። ሁለታችሁን ፈጣሪ አብዝቶ ባርኮ ለሀገራችን የበለጠ የምታበረክቱ ያርጋችሁ ፤ ብዙ ክብር ለሁለታችሁም 🙏
የጋዜጠኛ ደረጄ ሀይሌ ተተኪ ተገኝቶል ጥሩ አንባቢ ቆንጆ ጠያቂና አንባቢ ዳዊት ተስፋዬ በርታ ለሚጠይቃቸው ጥያቄዎች በደንብ ተዘጋጅቶ ና ተጠንቅቆ የሚጠይቅ ድንቅ ጋዜጠኛ ነው
ለሰው የሚተርፍ የአእምሮ ልህቀት ሊያውም በሳይንስም በእምነትም የተደገፈ ሲሆን እጅጉን ግሩም ነው። ደጃፍ እናመሰግናለን ከደጃችን ስለደረስክ።
ምርጥ እንግዳ ነው የጋበዝከው አለማየሁ ገላጋይን ብታቀርብልን ደስ ይለናል
ከዶክተር አለማየሁ ብዙ ቃለመጠይቆች መካከል በጣም የረካሁበት ነው ... ዴቭ ስለ ቆንጆ እይታዎችህ እና የመጽሐፍ ዳሰሳዎችህ አመሠግናለሁ ... በድጋሚ በሌላ ፕሮግራም እንደምትጋብዘው አምናለሁ ... እናመሠግናለን 🙏🙏🙏
አቤት የአነጋገር ለዛ ለጆሮ የሚጥም መንፈስን በደስታ የማያረሰርስ ድንቅ ጭዉዉት እጅግ በጣም አድናቂዎት ነኝ ዶ/ር አለማየሁ
እንዲሁም አዘጋጁ ሁልጊዜም የምታቀርባቸዉ እንግዶች ምርጦች ናቸዉ በርታ ድንቅ ሰዉ ነህ
I think this kind of podcast can be like public seminars I can’t wait to hear another elite interview
Ethiopian strong
የራሳቸን ታሪክ የ ከበደን ህዝቦች 👌👌👌👌👌
ውድ አንዱ የኢትዮጵያ ስጦታ ነህ ዶክተራችን እንዲሁም ምርጥ አስተዋይ ጋዜጠኛችን
በነፍስ ሓሴት ድምጸት አደመጥኩት ጋባዥም ተጋባዥም እጅግ አመሰግናለሁ ዶ/ር የልቡ እንድናገር ጋባዡ የምሰጠው ትእግስት አለማድነቅ ንፉጉነት ይሆናል።❤❤
በሀገሬ ውስጥ በሚሆኑ፣ በማያቸው፣ በምሰማቸው እንዲሁም በየዕለቱ በማስተውላቸው ነገሮች እጅጉን ተስፋ እቆጥርና ደግሞ የኩራዝ መብራት ያህል ጭላንጭል ተስፋ አያለሁ ልክ እንደዚ።ረጅም ዕድሜ ከሙሉ ጤና ጋር ተመኘው።ያኑርልን።ዴ አመሰገንኩ አንተንም።የድርሻህን እየተወጣህ ነው።የታሪካችን አንድ አካል ነህ።የሚጠቀም ይጠቀማል አንተ ከምታቀርባቸው ሰዎች።በርታ።
ዶ/ር አለማየሁ የአንተ እንኳን ቃለ መጠየቅህ፣ መጽሐፍትህ እንኳን ያስቆጨኛል፣ያስለቅሰኛል። አንተ ትልቅ የኢትዮጵያ ልጅ ነህ! እንደው ሀገራችንን እና ቤተክርስቲያንን ለማዳን እያንዳዳችን ምን ማድረግ ይኖሮብን ይሆን?😢 ጋዜጠኛው ቦታህና፣መክሊትህ ነው ጋዜጠኝነቱ ።ተባረክ
ዶ/ር ረጅም እድሜና ጤናን እመኝልሃለሁ። ለወጣህበት ማህበረሰብም አሁን ካለበት ትልቅ አደጋ ተርፎ የሰው ህይወት ታሪክ ከመጥፋት ፈጣሪ ይጠብቀን። ሃገር ሃሳብና ራዕይ ባላቸው መሪዎች የምትመራበትን ግዛ ፈጣሪ ይስጠን።
ዴቭ በመፅሐፎቹ የምደመምበትን እጅግ የማከብረውን አለማየሁ ዋሴን ለመጀመሪያ ጊዜ ለአንተ ኢንተርቪው ፈቃደኛ ሆኖ በደጃፍ ላይ በእንግድነት ስላስቀመጥከው ክብረት ይስጥልን እያልኩ አለማየሁ ስለሠጠን እጅግ ጣፋጭ ቃለመጠይቅ እሱንም እያመሠገንን ይልመድብህ እላለሁ ፡፡
በመጀመሪያ ለጠያቂው ምስጋናዬ ይድርስህ ፤ ከዛ ቀጥሎ ግን ውይይቱ ፍፁም ማራኪ እና ፈታሽ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ወደ መካከል ላይ ደግሞ ያለማጋነን እንባዬ የአይኔ በር ላይ ደርሶ ነበር ----- የኛ ነገር ልብ ይነካል።
ዶ/ር አለምአየሁ ለአንተም ከፍ ያለ ክብር አለኝ ፤ ያንተን አይነቱን ልሂቅ እድሜ ያርዝምልን ያብዛልንም ብዬ እራሴን ልመርቅ።
በጠቅላላው ምስጋናየ ለጠያቂው ይሁን ።
መሪ ቢሆን ብለህ አልተመኘህም
በጋዜጠኛ ተስፋ በቆረጥንበት ዘመን ብቅ ያለ ድንቅ ጋዜጠኛ። ያነበበ የተረዳ ትዕግስት ያለው አዳማጭ። you the best Dawit Tesfaye. Thank you so much!!!
The best Ethiopian podocast ever i heard,
I salute to Dr Alemayehu for his dedication and discipline.
ጋዜጠኛዉ እዉነት ፈጣሪ ያክብርልን :: ዶ/ር አለማየሁ በጣም የ ተለየ ሰዉ ነዉ ምነዉ ወደ ተግባር እሚለዉጥ ሰዉ እግዜር በሰጠን
ዶክትሬት ከነሙሉ ክብሩ 🎉ለኢትዮጵያ አምስት እንደአንተ ያሉ ሰዎች በቂ ናቸው።
እውንተኛው ዶክተር // ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ // እመጓን ደጋግሜ አንቢዋለሁ ዶክተር ረጅም እድሜ ና ጤና ከነመላ ቤተሰብህ ይስጥህ ኑርልን እውነተኛው ደክተር ዓለማየሁ ዋሴ
የዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴን ለትውልዱ በእጅጉ ጠቃሚና ትምህርት ሰጪ የሆኑ ሀሳቦች የተነሱበትን ቃለመጠይቅ በሁለት ተከታታይ ክፍሎች ስላቀረብክልን ከፍተኛ የሆነ አክብሮቴንና ምስጋናዬን አቀርባለሁ። እስከ ዛሬ እመጓን የት ሆኘ ነው ሳላነበው የቀረሁት በሚል ቁጭት ክፍል አንድን ካደመጥሁ በዃላ አንብቤ ስለነበር ክፍል 2 ትን መሳጭ አድርጎልኛል። ሌሎቹንም አድኜ አነባቸዋለሁ። ❤❤❤
አንተም ብቃትህን ደጋግመህ በዚህ ቃለ ምልልስ ደግሞ ❤❤በጣም ደስ በሚል ሁኔታ ለቦታው ልዬ የሆነ ሰው ስለጋበዝከን እናመሰግናለን ። ቀጣዬን ደግሞ በጉጉት እንጠብቃለን ። በርታ።
ሳዳምጠው ብውል ባድር የማይሰለቸኝ እጅግ ቅን ሰው። እናመሰግናለን ዴቭ። ደጋግመህ ጋብዝልን።
ዴቭ አንዳንድ ጊዜ ሳላስበው እምባየ እየመጣ ነበር የጨረስኩት ። ከ ዶ/ር አለማየሁ ጋር የነበረው ቆይታ ተጨማሪ ክፍሎች በኖሩት ብየ ተመኘሁ🙏❤
ዋው ዶር አለማየሁ ዋሴ የሃገር ሃብት ናቸው እግዚያብሄር ይጠብቅልን ማንም በሚፈነጭባት ሃገር መኖሮን ባዝንም ነገ ሌላ ቀን እንደሆነ ሳስብ ደስ ይለኛል😢
በጣም ደስ የሚል ውይይት ነው፤ ክፍል 1 ላይ እንዳልኩት ዳዊት በጣም ጎበዝ ጠያቂ ነህ በርታ!!!! ዶ/ር አለማየሁን ሌላ ሰፋ ባለ ውይይት እንደምታቀርባቸው እጠብቃለው! በተለይ "ሚተራሊዮን" ስለተባለው መፅሀፍ በደንብ ብትጠይቅልን ደስ ይለኛል ። በርታ!!!!
ቲያትር የመመልከት ያህል መሳጭ ነው በርታ ዳዊት ዘመናችን የሰጠን ድንቅ ሰው ነህ
የዶክተር ድምፅ ግን ለኔ ብቻ ነው ...ብዙም አይሰማም በተረፈ ግን ቆንጆ ቃለ ምልልስ ነበር
ዶክተር አለማየው እረጅ እድሜ ጤና ይስጥልን መቸም የማይሰለቹ ስጦታ ስለሆኑ ግድ የለም ተልተሎ ይምጡልን ❤ ጋዜጠኛው አመሰግናለው ❤
I am always amazed by Dr.Alemayehu's insight about who we are as Ethiopians now and before. Thank you doc and Dave as well .
ልብን የሚንካ ንግግር በእውነት እውነት ነው ሁላችንም ድሃዎች ነን
ጥንቅቅ ያለ ጠያቂ👌 ጥንቅቅ ያለ መልስ👌
Respect Dave🙏Respect Doc!
What an Interview!!
ዳዊትንም ደ/ር አለማየሁ እጅግ አመሰግናለሁ የሂወት ስንቅ የሚሆን ነገር ስለመገባችሁ፡፡ ዳዊት እንደዚህ ቁምነገር የምናገኝባቸውን ሰዎች ጋብዝልን፡፡
#ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ ከጠበቅዎት በላይ ሁነዉ ስላገኘዎት በጣም ደስ ብሎኛል፤እግዛብሄር የማስተማሪያ ጊዜውን ይባርክ።
ትዝብት፣ቁጭት፣የትውልድ ክፍተት......እየተፈራርቂብኝ በስስት ያየሁት ፕሮግራም❤
Thanks Dave & Doc.
ዶ/ር አለማየሁን አለማድነቅ አይቻልም መፅሐፍቶቹ ቀልብን ይይዛሉ ጥልቅ የሆኑ ሀሳቦችን የያዙ ናቸው አንተም ዴቭ ልዩ የሆኑ ጥያቄወችን እና በደንብ ተዘጋጅተህ እንደመጣህ ያሳያል:: በጣም ግሩም ቃለመጠይቅ ነበር በእውነት ሳምንቱን ሙሉ በጉጉት ስጠብቀው ነበር::
አንተ ደግሞ እንደ አቅራቢ ያነሳሀሃው ሃሳቦች በጣም የሚደነቁ ነበሩ:: በርታ ወንድም ❤❤❤❤
ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ፡ ደጋግመህ ብትመጣም በናፍቆት እንጠብቃለን እንጂ ፈጽሞ አንሰለችም፤ ትውልዱ ካንተ ብዙ የሚማረው ስላለ እባክህ ደግመህ ደጋግመህ ወደ ደጃፍ ናልን፡፡ ለአንተ ብቻ ሳይሆን ለትውልዱ በመደበኛ ስራህ፣ በጽሁፍችህ እና በአስተሳሰብህ /ንግግሮችህ የምትጠቅም ሰው ስለሆንክ ረጅም እድሜ ከጤና ጋር እንመኝልሀለን፡፡ ጋዜጠኛው ምሉዕ የጋዜጠኝነትን ስነምግባር የተላበስክ ስለሆንክ እናመሰግናለን፡፡በፕሮግራምህ እንዲህ ለህብረተሰቡ እና ለሰው ልጅ የሚጠቅሙ በአስተሳሰብ የላቁ፣ ኢትዮጵያዊነት ትርጉሙ የገባቸው እና ትውልድን የሚያስተምሩ ሌሎች እንግዶችንም ደግመህ አቅርብልን በሶሻል ሚዲያ ያለው ወሬ እና ተራ ቧልት ለሚሰለቻቸው እና ለማይወዱ ጠቃሚ ስለሚሆኑ፤ ሁለታችሁንም እግዚአብሔር ይባርካችሁ፡፡
ዋው በእውነት በጣም ደስ የሚል ውይይት ነው ስለ ድህነታችን ስትነግረን ዶር አለማየው ከላይ ያሉት ካልተማረሩ ለውጥ አይመጣም እምትለዋ በጣም ተመችታኛለች ማለት የሚስሊሙን መሪ ዑመር ኢብንኸጣብን አስታወሰኝ መሪ የነበረ 1/3 world ያስተዳድር የነበረ ኸሊፍ ነው እና ታሪኩን እንድታነቡት እጋብዛቹዋለሁ
Dave, this is by far my most favorite episode I have ever watched on your podcast. God bless you Dr. Alemayehu Wase.
ጠያቂው በጣም አደነኩት በጣም ጎበዝ ነክ ዶክተር የዘወትር አድናቂክ ነኝ
የ ዶር አለማየሁ መጽሐፎች ድንቅ ሚስጥራት ያዘሉ ናቸው። ምስጋና ለጋዜጠኛው እና ለዶር።
አለማየሁ ገላጋይን ጠይቅልኝ በእናትህ🙏🙏🙏
እንዳልገቡኝ እንኩአን ያልገባኝን ዕይታዎች ሰላሳያቸሁኝ እግዚአብሔር ያክበራችሁ.
አለማየሁ ዋሴ ዶክተር መፅሐፍ እንዳነብ የረዳኝ ሰው ሺህ አመት በጤና ኑርልኝ አንድ ቀን ባገኝህ ደስ ይለኛል።
Just speechless. Dave your questions are exactly on point and they showed how you passionately took your time and well prepared on them. Dr, Alemayehu's answers are far beyond educational and his way of expressing ideas is very impressive. I'm sure how his students and colleagues feel lucky to have him around them.Thank you so much Dave!
It was amazing interview , great way asking with smart way answering.
Doctor has -positive Attitude
-Great Aptitude
-Great altitude!
Quality is your identity! ,long live and good health for you.
ዋው እጅ ባፍ ያስጭናል ሚገርም የጋዜጠኝነት ብቃት❤ ዶ/ር የሚለው ስም ትክክለኛ ቦታውን ያገኘበት ሰው ዶ/ር አለማየሁ ጥልቅ እውቀት ድንቅ እይታ እዳንተ አይነቱን ለሀገር የሚጠቅም ምሁር ያብዛልን ኢተርቪው እራሱ ሌላ መፀሀፍ ነው ያነበብኩትን መልሼ ማንበብ አለብኝ ለካ አንባቢም በእውቀቱ ልክ ነው እሚገባው❤❤
የዛኔ እመጓን ሳነብ ለቀናት በመጽሃፉ ላይ ስለተነሱት ጉዳዮች እያሰብኩ ተክዣለሁ። ዛሬም ከብዙ አመት በኋላ ትንሽ በበሰል አእምሮ ነገሮችን እንዳመዛዝን እና እንድተክዝ አድርጎኛል። አለማየሁ እግዚአብሄር የስራ ዘመንህን ይባርክልህ። የተመኘከውን እኛም ለማየት ለመፈጸምም ያብቃን። ወንድማችን ዳዊት ድንቅ ቃለ መጠይቅ ነበር በርታልን። ደጃፍ ብቸኛ የምከታተለው ፓድካስት ነው።
በእውነቱ comment ማንበብ ራሱ ሌላ ሶስተኛው ክፍል ነው፡፡ ሁሉም ልክ ነው ፡፡ ጋዜጠኝነትን እንድናከብረው መሪያችን ይህ ጠያቂ ነው ብዬ አስባለሁ ፡፡ ለነገሩ የደራሲው goal ማስፈፀም ከቻለ ...እንዲህ ነው እንጂ ለሙያ መሰጠት አውቀውት ወደውት ማሳወቅ ማስወደድ በጣም ጎበዝ በርታልን ደግሞም አለንልህ ፡፡ ስለ ዶ/ር አለማየሁ ብዙ ተብሏል ለዛ የኔ ምንዛሪ ፅሁፍ ለእርሳቸው አትመጥንም ብቻ እሳቸውን በአንድ ቃል ለመግለፅ ያህል "አዋቂ" ናቸው ፡፡ እንደው ትንሽ ቅር ያለኝ ነገር ቢኖር የሰበዝን ደራሲ አግኝቶ ስለ ሰበዝ የመጨረሻው ታሪክና ስለታሪክ ነጋሪው እንዲሁም ስለታሪኩ አለማንሳት ከባድ ነገር ይመስለኛል ፡፡ትንሽ ስለ እርሷ ብታነሳ እና እሳቸውም ትንሽ ሀሳብ ቢያንሸራሽሩ መልካም ነበር ብዬ አስባለሁ ፡፡ በተረፈ ግን አሪፍ ነው ፅድት ያለ interview ነው፡፡ የሠማነውን ለመልካም ፍሬ ያብቃልን፡፡ አ ሜ ን ፡፡
በእውነት ምንም አይሰለችም ባላለቀ እያልኩ ያዳመጥኩት ፕሮግራም ነው።በድጋሚ እንደምትጋብዝልን ተስፋ እናደርጋለን። ቁጭት ይጭራል....በተረፈ ለአቅራቢውም ለቀራቢውም ክብርን ያድልልን
እንደዚህ ህይወት የሚሆን ነገር ሲወራ እንዴት ደስ ይላል
እግዚአብሔር ይስጥልን
ዶ/ር አለማየሁ አገራችን ከዚህ ወስብስብ ወጥታ የምስባትን ኢትዮጵያ ያሳይህ፦
በጣም ግሩም ጋዜጠኛ የሀገራችንን የድህነት እና የጦርነት ችግር መንስኤ እና መፍትሄ በሚሰንዳችው መፃህፍት የጠቆመውን ደራሲ ስለሀሳቦቹ እንዲያብራራ በመጋበዝህ አስኳሉን እንድናገኘው አርገኸናል ።ምስጋናዬ ይድረስህ።🎉
እግዚአብሔር ጨምሮ ጨምሮ ጥበቡን ይግለፅልህ ይህን ስል ግን ልቤ አንተን እምገልፅበት ሌላ ቃል ስላጣው ነው።
እዉነት እኔ ማንበብ የጀመርኩት ማንበብ የወደድኩት በዚህ ጥበበኛ ሰዉ ምክንያት ነዉ እግዚአብሔር እረጅም እድሜና ጤና ይስጥህ ከዚህ በላይ ሞገስ እና የሰዉ መዉደድ ይስጥህ እዉቀትማ ከዚህ በላይ ምናለ
Your thorough preparation shines through in every episode, and this one was no exception. The engaging and thoughtful dialogue with Dr alemayew , who is not only a distinguished doctor but also an extraordinary person, made for a truly enlightening and memorable discussion. Kudos to both of you for such a compelling podcast!!!!!
ጋዜጠኛ ዳዊት ተስፋዬ በጣም እናመሰግንሃለን።
አንተ መጽሐፍቱን በጥልቀት በመመርመርህ ለእኛም የሚገባንን መልዕክት እንድናገኝ ምክንያት ሆነሃል። በርታ !!!
እግዚአብሔር ልቡናህን ያብራልህ!!!
ቀልብን የሚያነቃ ብዙ እዳሰላስል የሚያደርግ አገላለፅ እና ሀሳብ የሁለቻቹንም ውይይት እጅግ በጣም አከብራቸዋለሁ
በእውነት ጥያቄና ጠያቅ እንድሁም ተጠያቅ ባማረ መልኩ ገጠመ እግዝአብሔር ረጅም እድም ከጤና ጋር ይስጥል!!!!
እኔ መፃሐፎቹን ሰነብ የተመኛሁት ይህን ድንቅ ሰው ማግኛት ነው።
ካንተ ብዙ ተምሬአለሁ ዶ/ር፣ ረጅም እድሜ ከጤና ጋር እመኝልሃለሁ። አንድ መድረክ ላይ ራስህን ለማግኘት የፈጀብህን ዓመት ስትናገር ሰምቼህ ነበር፣ ጉዞው ከባድ ቢሆንም ራሱን ያገኘ ሰው ደግሞ እንዲህ ከራሱ አልፎ ለሃገር በረከት የሚሆን ከሆነ የዚች ሃገር ጥያቄ መልስ ያለው ራሳችን ጋር ነው ማለት ነው። እንዳንተ ያሉትን ያብዛልን ..........እናከብርሃለን አርያችን ነህ
የሚገርም ፕሮግራም ነው ዴቭ፤ በርታ 👍👏 ዝም ብለው ከሚያዝጉን ጋዜጠኞች አንዱ ስላልሆንክ እግዚአብሔር ይመስገን ። አለማየሁ ዋሴ ዶ/ር ሁሌም በንግግሮችህ ስለምታስተምረን እናመሰግናለን ክበርልኝ ወንድሜ🙏
Dr Alemayhu Wase thank you very much for your deep analysis of the selfish scholars,politicians and riches who are abusing motherland Ethiopia .
ዴቫችን ዕድሜና ጤና ይስጥክ ዶ/ር ረጅም ዕድሜ እና ለሀገርክ ለህዝብክ ያሰብከው የሚሳካበት ዘመን ይሁንልክ ።
አቤት መማር እንደዚህ ነው ዶ/ር አለማየሁ እይታህ አለማድነቅ አይቻልም ግሩም ድንቅ እይታና ትንታኔ ነው ❤❤❤❤❤❤
ሁሌም የማይሰለቸኝ ብሰማው ብሰማው እድሜ እና ጤና ይስጥ
እድሜ ይስጥልን ፀጋውን ያብዛልን ያቆይልን የምትመኛትን ሃገር ያሳይልን Dr. እናመሰግናለን 😊
ወንድም ዓለም የዛ ስው ይበለን እድሜ ጤና ይስጥልኝ አቅራቢውም እናመሰግናለን
ብዙ ቁም ነገሮችን ያዘለ የሚገርም ቃለ መጠይቅ ነው። ለኹለቱንም ክፍል ርእስ ይሰጠው ቢባል "መስታወት" የሚለው ቃል የሚገልጸው ይመስለኛል። በተለይ እኔ የሕይወት ዘመን ስንቅ የሚኾኑ ብዙ እይታዎችን አግኝቼበታለኁ። በአጠቃላይ ጋዜጠኛ ዳዊት በጥያቄዎችህ ፤ ዶ/ር አለማየሁ በምላሾችህ ውስጥ ብዙ እንድንማር ስላደረጋችኁን እግዚአብሔር ያክብርልን!
Yemiyaweraw Hulu des yemil endiaynet interview aycha alekem seriously balalake beya new mayew yeneberew Dr egeziabher yetebkelen
መፅሀፍቶቹን አንብቤ በዋዛ ትቻቸዉ አመታት አልፈዋል፡፡ ዴቫ ጥያቄችህን ስታነሳ ብዙ ነገር አስታወሰኝ ወድጀዋለሁ ወንድሜ ፡፡ መቼ እንደምመለስባቸዉ ባላቅም ሁሌም የራሴን ጥረት አድርጌ ለመረዳት እንደምሞክር አስብ ነበር ፡፡
this videos are like alarm bro thank you so much !!!
አቅራቢው ደስ ትላለክ እምታነሳቸው ነጥቦች እሚገርሙ ናቸው ባላለቀ እያልኩ ነበር እሰማ የነበረው እኔም መጽሀፉን ሳነብ አግኝቸ ብጠይቀዉ እያልኩ መረባቸውን ነጥቦች አንስተክልኛል ላመሰግንክ እወዳለሁ አመስግናለሁ በርታ ድጋሜ እንደምታቀርብልን ተስፋ አደርጋለሁ. ዶ/ር ላንተ ቃላት የለኝም እወድሃለሁ ልክ እንዳን አይነት አሳቢዎችን ያብዛልን እግዚአብሔር ካለክ ላይ ጨምሮ ይባርክህ እግዚአብሔር ይስጥልን🙏
በነካ እጅህ ስለሜትራልዮንም ጠይቅልን ተጠያቂው እግዚአብሔር እድሜ ከጤና ያድልልን ዶክተር🙏
እኔ ለራሴ ዮኒቨርሲቲ የመግዛት ያክል የሚደንቅ ትምህርትና experience አግኝቼበታለሁ። በጣም አመሰግናችኋለሁ።
የእውቀት መለኪያውን ጥግ የደረሱ ሰዎች ጥብበን እንደሸማ ተላብሠው ሲናገሩ ማዳመጥ በራሱ መታደል ነው። እግዚአብሔር እድሜና ጤናውን ያድላችሁ ለሁለታችሁም።
ይገርማል እጅግ አስደሳች አስተማሪ ቃለ መጠይቅ ነው እውነተኛዋ ኢትዮጵያ ስትገለጥ እንናንተን ትመስላለች
ዶ/ር ቃለህይወት ያሰማልን ነው የምልህ አንተ ያነሳሀቸው ህሳቦች በሙሉ በህይወታችን ብንተገብር በፈጣሪ ዘንድ ትልቅ ዋጋ ያስገኘናል::
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ የዶ/ ር አስተሳስብ
እና ምልክታ አብሮት እንዲኖር ልንፀልይ ይገባል:: ስም ባልጠቅስም ትናንት እንደሱ የአገሬው ህዝብ ኑሮ ሲያሳስበው የነበረው ሊህቅ እና ፀሀፊ ዛሬ ላይ ምን እያለ እንዳለ በዘመናችን አይተናልና
እኛም መስማት ብቻ ሳይሆን እየሰማን በትንሽ በትንሹ ለመተግብር ዛሬ አንድ እንበል ጋዜጠኛው በጣም ጏብዝ ነህ በርታልን
Endayalkibign betam yaschenekegn interview.
ዳዊት በሌላ ሀሳብ ዙሪያ ድጋሚ ጠይቅልን🤲🤲🤲🤲🤲
እሚገርም እይታ ነው ፈጣሪ ማስተዋልን እና ልቦናን ይስጠን እስቲ ።