//ረሱል ጃለሌ// አዲስ መድህ በሙአዝ ሀቢብ || New Menzuma Resul jalele

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 6 жов 2024
  • ውድ የዩቱብ ቻናል ቤተሰቦቼ ትምህር ብቻ ሳይሆን ሙሀባንም ትወስዱበት ዘንድ ይህን የነብያችን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለምን መድህ ጋብዣለሁ መልካም ግዜ
    ( ረሱል ጃለሌ ) ኑረል ሀዲ 2
    ግጥም:- ዑስታዝ ሰዒድ
    ዜማ:- ሙዓዝ ሀቢብ
    ።።።።።
    አልሃምዱሊላህ፣ ሹክር ገለታ
    ከላይ ከታቹ፣ ከየት እንዴታ
    ለጠራው ጌታ
    ።።።።።
    አጀብ እዝነቱ፣ ሞልቶ ሚፈሰው
    ሙስጦፋን ሰጦ፣ ያን ትልቁን ሰው
    ከውኑን አደሰው
    ።።።።።
    ባንቱ ነው፣ የበራልን ሌቱ
    ላንቱ ነው፣ ዜማየም ቅኝቱ
    ያላንቱ፣ ማን አለኝ ሌላ (ሻፊዔ ጥላ ከለላ)
    ።።።።።።
    ።።።።።።።።።።።።
    ያን ምቹ ስሙን፣ እስኪ ላድምቀው
    መላ ነው ስሙ፣ መላ ለራቀው
    ያዝ አትልቀቀው
    ።።።።
    ያን የሚያምረውን፣ ጠባይም መልኩ
    ያን የጠፋውን፣ አምሳያው ልኩ
    ትንፋሹ ሚስኩ
    ።።።።።
    ቢከትቡ፣ ቢንጠፈጠፍ ቀለም
    ሲያዜሙም ቢኖሩ ዘላለም
    ማን ችሎት ያንን ጀማላ (ቢለፋም ማዲሁ ሁላ)
    ።።።።።።
    ።።።።።።።።።።።።።
    የከውኑን ሂላል፣ ያለም ረህመቱን
    ያን የሰራውን፣ ልቤ ላይ ቤቱን
    ጥኑ ናፍቆቱን
    ።።።።።
    የመሀባው ጦር፣ ደርሶ ሚወጋው
    ሚያወዛውዘው፣ ሰርክ ሚያፈጋው
    የሸውቅ አደጋው
    ።።።
    እጅግ ነው፣ አፍቅሮ ማይረጋው
    ሲያለቅስ ሌቱን የሚያነጋው
    ዛፍ ድንጋው ግዑዙ ሁላ
    ።።።።።
    ።።።።።።
    ካልወዘወዘህ፣ ሲጠሩ አህመዱ
    ካላስለቀሰህ፣ ሸውቁ መውደዱ
    ታዘበህ ግንዱ
    ።።።።።
    ወዳጅ ነን ብለን፣ የራቅነው ሁሉ
    ምን ይለን ይሆን፣ ቢያየን ግመሉ
    ዛፍ ድንጋ ሁሉ
    ።።።።።
    መከተል፣ ነው እኮ መውደዱ
    ታዲያ እንዴት፣ ይብለጠን ዛፍ ግንዱ
    ለምንድን ቀረን ከኋላ
    ።።።።
    አልሰማህም ወይ፣ ስሙ ሲነሳ
    ህያው መግደሉን፣ ሟች እያስነሳ
    ሰውም እንስሳ
    ።።።።
    ቀላል ነው ባሉት፣ እየከረረ
    ሰከነ በሚል፣ ነዶ እየናረ
    መላው ቸገረ
    ።።።።
    ማን አውቆ ይፍታው፣ ቢለፋም ቢጥር
    ፍቅር ሚስጥሩ፣ ቀረ በሚስጥር
    ማያዩት አጥር
    ።።።።።
    ግመሉ፣ ወፍ አይቀር ሚዳቆ
    አንበሳው፣ ተኩላ እንኳን አውቆ
    ሚናፍቆ ያረሱለሏህ
    ።።።።።።
    ((ሃቢቡሏሂ))
    መውደዱ ሃያል፣ ናፍቆቱ አይቻል
    ስንቱ ዋለለ፣ ሲያቅተው መቻል
    አፍቅሮ ማረፍ፣ ወዳጅ ያስተቻል
    መተኛት ቀርቶ፣ መች ያንጎላቻል
    ።።።።።
    አፊያ ነው ስንል፣ ጤናን ይነጥቃል
    ህመም እንዳንል፣ ማዳንም ያውቃል
    ቀርቧል ያሉ ለት፣ እጅግ ይርቃል
    እዚ ሲያስለቅስ፣ እዚያ ያስቃል
    መሀባ ማዕናው፣ መች ይታወቃል
    ።።።
    ፍቅሩማ፣ ጠብታው ያጠልቃል
    ይበርዳል፣ በል ሲለው ይሞቃል
    ያላቃል ሩህን ከገላ
    ።።።።
    ።።።።።
    ።።።።።
    ማዬት ቢሳነው፣ አይኑ ቢጠፋ
    ሶሀባው መጣ፣ ወደ ሙስጦፋ
    ቢያዝን ቢከፋ
    ።።።።።
    ጨለመብኝ ቀን፣ ሃዘን ወረሰኝ
    መሪ እንኳ የለኝ፣ መስጂድ ሚያደርሰኝ
    አቅም አነሰኝ
    ።።።።።
    አንቱ ኖት፣ የዝነቱ መፍለቂያ
    መከራን ችግርን መራቂያ
    መውደቂያ የለኝም ሌላ (ድረሱ አጣሁኝ መላ)
    ።።።።።
    ።።።።።።
    አይዞህ አትዘን፣ አሉት ጀማላ
    ውዱ አድርግና፣ ስገድ ለመውላ
    አሁን ሂድና
    ።።።።
    ከዚያም ለምነው፣ ጌታን ሶመዲ
    አሽረኝ በለው፣ ከያዘኝ ጉዲ
    በሙሐመዲ
    ።።።።።
    ሚያሳምም ሚያድንም አሏህ ነው
    ግን ስሜን ጠርቶ፣ ለለመነው
    ወዲያው ነው ሃጃው ሚሞላ
    (በኔማ እምቢ አይልም መውላ)
    ።።።።።።።
    ።።።።።።።
    ሄዶ ቢፈፅም፣ ያሉትን ዘይኑ
    በርቶለት መጣ፣ የጠፋው አይኑ
    ጠፋ ሃዘኑ
    ።።።።።
    ሁሉን አድራጊው፣ ማሊክ ሙሉካ
    በነቢ ተብሎ፣ እምቢ አይልም ለካ
    በሱ እንመካ
    ።።።።
    ማን ታዬ እስኪ ባዶ ቀርቶ
    ያፈረስ ማነው ነቢን ጠርቶ
    መች ታይቶ ሃጃው ያልሞላ
    ።።።።።።።
    ።።።።።።።።።
    ( ሃቢቡሏሂ)
    ሰይፉ ኻሊዱ፣ የማማ ሜዳ
    አርማ ባንዲራ፣ ጨርቅ አሰናዳ
    ብለው ፃፉበት፣ ያ ሙሐመዳ
    ውጊያው ሲጫጫስ፣ ጦር ሲፈነዳ
    ሁሉም ይል ጀመር፣ ያሙሐመዳ
    ነቢን ሚከተል፣ መንገዱን አውቆ
    በሄዱት ሚሄድ፣ ከራቁት ርቆ
    ቢያሸንፍ እንጂ፣ መች ታዬ ወድቆ
    / ያንቱን ስም፣ ከፍ አርጎ አውለብልቦ
    ኻሊድን፣ ሽንፈት እንዴት ቀርቦ
    ድል በድል ሆኑ ሰይፉሏህ
    ።።።።
    ናፍቆቴዋዬ፣ ዘመድ ወዳጂ
    ላላፊ አግዳሚ፣ ምትከፍቱ ደጂ
    የልቤ ብርሃን፣ ያይኔ ሲራጂ
    ህመሜ አይሽርም፣ ባንቱ ስም እንጂ
    ።።።።።።
    እንኳንስ የጅን፣ ካፍም የሰጡት
    ያመኑት ሲክድ፣ ባኖሩት ሲያጡት
    ሰው አልገኝ ሲል፣ እንዳስቀመጡት
    ሰይዲ አንቱ ኖት፣ ማትለወጡት
    ምትቀርፉት፣ ሃዘኑን ሁላ
    ።።።።
    አያልቅ አያረጅ፣ አይዝል አይላላ
    አዲስ ነው ዳኢም፣ ፊትም በኋላ
    እንዳይረሳም፣ እንዳይሉት ችላ
    ስር ሰዶ ዘልቋል፣ በደም በገላ
    የውዱ መውደድ፣ መሀባውማ
    ለምን አይባል፣ ከልካይ አይሰማ
    ልብ ነው ቦታው፣ ቀዬ ከተማ
    ሌላውን ሳላይ፣ ሌላን ሳልሰማ
    ህይወቴ አድርጌ፣ ግብም አላማ
    ልቤን ከሰጠሁ፣ ቆዬሁ እኔማ
    ።።።።።።
    የኛው ሙሐመድ፣ የኔው ሙሐመድ
    ፅልመት ይገፋል፣ መልኩ ሙሐመድ
    ሃዘን ያጠፋል፣ ሳቁ ሙሐመድ
    ዓይንን ይጠልፋል፣ ዓይኑ ሙሐመድ
    ችግር ያረግፋል፣ ስሙ ሙሐመድ
    ድል ያጎናፅፋል፣ ሱናው ሙሐመድ
    ።።።።
    መሸም ሙሐመድ፣ ነጋም ሙሐመድ
    ዛሬም ሙሐመድ፣ ነገም ሙሐመድ
    አሁን ሙሐመድ፣ ኋላም ሙሐመድ
    ሳርፍም ስቀመጥ ፣ስቆም ስራመድ
    ስሙ ነው ወገን፣ ስሙ ነው ዘመድ
    ።።።

КОМЕНТАРІ • 2,8 тис.

  • @SolomonAdamu-e8g
    @SolomonAdamu-e8g 6 місяців тому +170

    ኦርቶዶክስ ነኝ እደዚ ደስ እደሚል አላቅም ነበር አሽረኝ በለዉ❤❤ ሰይድ አቱ ኖት የማትለወጡት ❩😘😘😘😘😘

    • @selmanfaris3552
      @selmanfaris3552 Місяць тому +13

      Allah yehideke

    • @rawdarawda6835
      @rawdarawda6835 Місяць тому

      ❤❤​@@selmanfaris3552

    • @SalmeenAbudhabi
      @SalmeenAbudhabi Місяць тому +7

      አላህቀጥተኛውን መንገድ ይምራሽ 😢😢😢ያርብ እህቴዋ

    • @maya9407
      @maya9407 Місяць тому +4

      Ya rabee allah ketetgnawn mengd yiwfeksh enate

    • @BilalFatu
      @BilalFatu Місяць тому

      @@selmanfaris3552😊😅pretty good day to put out pictures people posted pppppppppppppp

  • @YordanosDagu
    @YordanosDagu Місяць тому +26

    እኔ ኦርቶዶክስ ነኝ ግን ነሺዳ መንዙማ ስሰማ ውስጤ በጣም ደስ ይለኛል ውስጤ ይነካል ❤❤❤

    • @AqrabMoobail12
      @AqrabMoobail12 2 дні тому

      እስልምና ሁሉ ነገርሩ ደስ ይላል❤❤

  • @TseganehKuma
    @TseganehKuma 3 місяці тому +37

    ኦርቶዶክስ ብሆንም በጣም ደስ ይለኛል::❤❤❤ Eid ul Adha Mubarak!

  • @HábìbáÊbŕáhìm-q4y
    @HábìbáÊbŕáhìm-q4y 9 місяців тому +125

    አንቱ የአለም ፀሓይ መቼም ብትወደሱ አትጠገቡም ወላሒ ሸዉቁኽ በረታብን❤❤❤ ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያረሱለላህ
    ሙኣዜ አላህ ይጨምርልህ ከሚስ ሙባረክ ከሸዉቅ ጋር🌼🌼❤

  • @jibichaaynage7914
    @jibichaaynage7914 28 днів тому +2

    Ebakihin muluwun be AFAAN OROMOO siralin❤️❤️❤️

  • @RAHIKABDELA-ls2kf
    @RAHIKABDELA-ls2kf 4 місяці тому +35

    ይሄን ነሺዳ ከሰማው በኃላ ቀጣይ ምትሰራውን ስራ በጣም ከባድ ያደርግብሃል ብዬ አሰብኩ ማለት የፈለኩት በጣም ምርጥ ስራ ነው ለቀጣዩ አላህ ይርዳህ ሙዓዛችን😢

  • @ezuallinone1350
    @ezuallinone1350 4 місяці тому +67

    ኣቶዶክስ ነኝ ሁሉም ነሺዳክ ደስታ ይፈጥራል ❤️😍ማሻአላ

  • @abdulkafeamdino9563
    @abdulkafeamdino9563 6 місяців тому +25

    Mashalah ከዚህ ነሺዳ ሚደብረው ማለቁ ነዉ😍👍🌈👏🌻

  • @seiddessie4606
    @seiddessie4606 9 місяців тому +178

    ሆይ ሆይ መገን የኛ ሙሀመድ ፡አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ አለይህ። ኸይርህ ይብዛ አቦ ሙአዙ 🥰

  • @Mohammed-zero-zero
    @Mohammed-zero-zero 2 місяці тому +3

    muaz habib አንተ የኛ Maher Zain ነህ አላህ ረጅም እድሜ እና በሁለቱም አለም ደስተኛ ህይወት ይስጥህ

  • @Alexis1003-w6d
    @Alexis1003-w6d 6 місяців тому +223

    እኔ አማራ ኦርቶዶክስ ነኝ . ነብዩን ግን የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ወንድሞቼ ነብይ ስለሆኑ በጣም እወዶታለሁ. አከብሮታለሁ. May everlasting peace and blessings be with you and with all your followers.

    • @zekizak-u7z
      @zekizak-u7z 5 місяців тому +4

      Neby ke'Muhammed Sollelohu aleyhi weselem behola yelem.
      Yemecheresha Nebi endehonu qo'aren Negronal❤

    • @TsinatLoic
      @TsinatLoic 5 місяців тому +2

      ❤❤❤❤❤❤❤❤

    • @IbraTaj-f1d
      @IbraTaj-f1d 4 місяці тому +2

      ❤❤❤❤

    • @AbduMehamud
      @AbduMehamud 4 місяці тому +3

      Alah yakbirh wendimachn alah yiwidedih

    • @MohammedSeid-gs8ul
      @MohammedSeid-gs8ul 3 місяці тому +3

      እንዳንተ ያሉትን ወንድሞቻችንን ያብዛልን ተባረክ 💚💛❤💪💪💪💪💪

  • @abdulkafeamdino9563
    @abdulkafeamdino9563 6 місяців тому +50

    አላህ ካዘነላቸው ከማራቸው፤ ኢትኩም ሚነናር ካላቸው፤🤲 ዱአቸውን ከተቀበላቸው፤🤲 ከጀሃነም እሳት ካወጣቸው፤ ለጀነት ፍርዶስ ካላቸው፤👑 ለይለተል ቀድር ከወፈቃቸው፤😢 ረመዳንን ፁመው በመልካም ከተመዘገበላቸው ባሪያዎቹ ያድርገን አሚን 🤲🤲🤲✨ኢድ ሙባርክ✨✨✨

    • @SemiraDari
      @SemiraDari 5 місяців тому +1

      Amiin yaAllah❤❤❤❤❤❤❤

    • @demismuktar
      @demismuktar 25 днів тому

      አሚን

  • @nayeabreham7392
    @nayeabreham7392 3 місяці тому +6

    am christian but i love this neshida .... lovely melody ..seyidi resul jalalaa

  • @TofikFedilu
    @TofikFedilu Місяць тому +6

    የ 21 ክፍለ ዘመኑ ምርጥ ነሽዳ ነው🎉🎉🎉🎉

  • @Ibo88-
    @Ibo88- 6 місяців тому +117

    ይሄ መንዙማ 10 ሚሊየን ገብቶ የሐገራችን የመንዙማን ሪከርድ እንደሚሰብር አልጠራጠርም።ከቀን ወደቀን እየጣፈጠ የሚሄድ🥰🔥

    • @KhB-lz4dg
      @KhB-lz4dg 3 місяці тому +3

      Xzed86esrtesxvht😊😅😮🎉😂❤😮😢🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉eruk🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉

    • @harunjemalcurtain5781
      @harunjemalcurtain5781 26 днів тому

      Yegebale medersewe yeleme eyadere metafate mezuma new

  • @janvs7133
    @janvs7133 2 місяці тому +3

    እንደት ደስ አይልም የረሱል ስም እኮ ነው የደም እንባ እያነባሁ ነው የረሱል ስም ሲነሳ❤❤❤

  • @mdy46
    @mdy46 9 місяців тому +22

    ሶለሏሁአለይህ አለይህ ወሰለም አሏህ ይጠብቅህ ወንድም ወላሂ በጣም ትለይኝባለህ ለኔ

  • @personperson4914
    @personperson4914 9 місяців тому +39

    በደስታዬ በሀዘኔ በህመሜ በጤናዬ የእርሶዎ ስም ጠርቼ ሲመጀን አሏህ ሲለምን ወላሂ አጥቼ አላውቅም ያሀቢቢ ያራሡአሏህ የኛ ነቢዩና ሙሀመዳ ዓሌይሂ ወሠላቱ ወሠላም❤❤❤❤❤

  • @fatema6394
    @fatema6394 9 місяців тому +56

    አይ ሆይ የኛሙሀመድ ረሱል ሶለሏሀ አለይሂ ወሰለም ባረከሏሁ ፊኩም 👍👍👍👏👏👏👏👏

  • @a-h-0707
    @a-h-0707 3 місяці тому +2

    ይሄ መንዙማ ስሰማ የሆነች ምወዳት ልጅ ትዝ ትለኛለች
    ወደ ውጭ ሀገር ስቴድ ይሄ መንዙማ ልክ ገና አንደተለቀቀ እየሰማሁት ነበር ወይ ጊዜ ashkabachua lij 👌👌👌👌
    እና በጣም ነው ምወደው ይሄ መንዙማ
    ዛሬም ሙሀመድ ነገም ሙሀመድ ሰ. ዐ. ወ

  • @MohammedHassen-ns8sx
    @MohammedHassen-ns8sx 5 місяців тому +4

    አለህ ይጣብቅ ሙአዜ በጣም ነው የታመቸኝ አለህ ይጨምርልህ

  • @fe1220
    @fe1220 9 місяців тому +8

    ሙአዜ ወሏሂ ምን እደምትባል አይታወቅም አሏህ ይጨምርልህ ወድሜዋ ልዩ ነህ ሁሌም ሶለሏህ አለይሂ ወሰለም❤❤❤❤😢😢😢😢አሏህ ይጠብቅህ

  • @munirajemal5920
    @munirajemal5920 9 місяців тому +102

    اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِكْ على نَبِيِّنَـــا مُحمَّد ﷺ💚
    ሙዓዝ አላህ ይጠብቅህ 🥰🥰

  • @Mohammed-l2j8b
    @Mohammed-l2j8b 9 місяців тому +182

    ኡስታዝ ሰዒድ አህመድ ሀያታቸውን አሏህ ያቆይልን፤ ብዕራቸው ይባረክ!

  • @ZiyaadaDaawud
    @ZiyaadaDaawud Місяць тому +1

    Maasha allah wandimme akorahan❤❤❤❤wallahi antee baduniyam baa akheram yaa jannat sew neek insha allah Ba wudde nabiy muhammad salallahu aleyihi wasallam barakaa. Allah yiwafiqqih ❤❤❤❤❤❤❤

  • @IbraTaj-f1d
    @IbraTaj-f1d 7 місяців тому +33

    ይህ መንዙማ ልዩ ሲር ያለዉ ነዉ::
    ወሩን ሙሉ ሰማሁት ከቀን ወደቀን ጥፍጥናዉ እየጨመረ የሚሄድ ሆኖ ነዉ ያገኘሁት❤❤
    በርታል ሙዓዛችን
    ሸይኽ ሰዒድ አሏህ ከፍ ያድርጎት❤

  • @Hayat-i1s
    @Hayat-i1s 9 місяців тому +12

    ማሻአሏህ ዛሬምሙሀመድ ነገምሙሀመድ
    ❤ሶለሏሁ አለይሂ ወስለም ❤ ሶለሏሁ አለይሂ ወስለም ❤ ሶለሏሁ አለይሂ ወስለም ❤ ዛሬም ሙሀመድ ነገም ሙሀመድ❤ ፊዳትሁን ነፍሴ የኛ አይነታ ሀቢቡሏሂ 😢 ሁሌም ተወዳጂ የኛ ነብይ ሶለሏሁ አለይሂ ወስለም ❤ባረከሏሁ ፊኩም

  • @smartadverttube3135
    @smartadverttube3135 9 місяців тому +29

    ወሏሂ ኸሚሴን አስዋብከው❤❤❤❤ በቃ ውብ ኸሚስ እያሳለፍኩኝ ነው
    ማሻ-አላህ ሃቢቢ በርታልኝ

  • @nuruwalle3232
    @nuruwalle3232 2 місяці тому +7

    ወላህ የአላህ እዝነት በአንተ ላይ ይውረድ

  • @zeinunure5172
    @zeinunure5172 Місяць тому +2

    ማሻአላህ ሙአዝ አላህ የትልቁን ሰው(ሰ ዐ ወ) ሙሃባ ይጨምርልን💚

  • @hope2633cu
    @hope2633cu 5 місяців тому +3

    Your sound flow like river water wow😪🙄🥰😍🤩

  • @anusmiz3088
    @anusmiz3088 8 місяців тому +28

    ለጆሮ ምግብ የሆነ መንዙማ ሁሌ እንዳስደመመከኝ አሏህ ይጠብቅህ ሙዓዜ❤

  • @JIRENmedia114
    @JIRENmedia114 5 місяців тому +16

    ሶለሏሁ አለይሂ ወስለም ❤ ሶለሏሁ አለይሂ ወስለም 💚 ሶለሏሁ አለይሂ ወስለም ዛሬም ሙሀመድ ነገም ሙሀመድ ፊዳትሁን ነፍሴ የኛ አይነታ ሀቢቡሏሂ ሁሌም ተወዳጂ የኛ ነብይ ሶለሏሁ አለይሂ ወስለም ባረከሏሁ ፊኩም❤❤❤

  • @AsefaTekilu
    @AsefaTekilu 7 місяців тому +15

    ከልብ ነው የምወድህ በተለይ ይሄ ስራህ በፍቅር እና በመመሰጥ ነው የምሰማው ፈጣሪ ይጨምርልህ ፡፡ ይሄ ነሺዳ ለመስማት ፍቅርና ማስተዋል ብቻ ነው የሚያስፈልገው ፍቅር ብቻ፡፡

  • @hasensaid
    @hasensaid 3 місяці тому +1

    ሙአዝ ሀቢብ ወጣት ሴቶቺንና ወንዶችን ዘፈን ከማዳመጥ ወደሰላዋት ያመጣ ጀግና❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @misbahjemal9295
    @misbahjemal9295 3 місяці тому +114

    ይሄንን ኮሜንት ለምታነቡ በሙሉ
    የአላህ እዝነትና ምህረት አይለያችሁ!🙏

  • @sadiaabduseid8825
    @sadiaabduseid8825 9 місяців тому +22

    ማሻአላህ ተባረክ እረህማን በጣም ልዩዩዩ ነው ሙአዜ ኑርልን ወንድማችን ❤❤❤❤❤

  • @محمدمرسي-ن9ح
    @محمدمرسي-ن9ح 9 місяців тому +10

    ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ከፉ አይካብን ሙአዝ ሀቢብን አሏህ ይጠብቀዉ ለይለን ወነሃር❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉

  • @Al-NamuselHadraTube
    @Al-NamuselHadraTube 7 місяців тому +60

    ከላይ ከታቹ ከየት እንዴታ ለጠራዉ ጌታ። እንዲህ ነው ሙአዜ ሀቅን ማዉጣት። እንደ ሙአዝ ኢብኑ ጀበል (ረ.ዐ) አሏህ ያድርግህ።

  • @HayateHu
    @HayateHu 2 місяці тому +1

    Muslim neg gn menzum Adamche alakm neber ahun gn bezi menzuma tesabku alah ywdedh❤❤❤❤❤

    • @MammadAwwal
      @MammadAwwal 2 місяці тому

      ❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉2❤❤❤❤❤

  • @محمدحكميك
    @محمدحكميك 9 місяців тому +4

    ሳለሏሁ አለይሂ ወሰለም❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤ዉዶች ጠንክሩ የረሱል ወዳጅ መሆን እራሱ ዉበት ነዉ

  • @jemilayasir2837
    @jemilayasir2837 9 місяців тому +85

    The greatest Man in the World is Our beloved Prophet Mohammad S.A.W 💖💖

  • @kedir_yimer
    @kedir_yimer 9 місяців тому +54

    ኡስታዝ ሰዒድ አህመድ ሀያታቸውን አሏህ ያቆይልን፤ ብዕራቸው ይባረክ!
    አንተ ደግሞ በልዩ ድምፅክ ግጥሙንም መድሁኑም አሳመርከው❤ አሏህ ይጠብቅህ

  • @michaelabebaw9518
    @michaelabebaw9518 21 день тому +2

    ሙአዝ ላንተ 💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎ክዘም በላይ የግባውት ❤❤😊❤

  • @Tofiq1213Sadi
    @Tofiq1213Sadi Місяць тому +1

    ሙአዝ፡ከምንምበላይ፡አላህይጠብቅህ፡ግንከአላህ፡በታች፡ለህግማሳወቅህ፡አሪፍ፡ነው፡ማንንም፡እንዳትፈራ

  • @Meryem___473
    @Meryem___473 9 місяців тому +9

    Ya Allah!!! 🥰🥰🥰... kal atahugn eko ! Allah yitebikih ...hayatihin yarzimilin ! Allahumeseli weselim ala nebiyina muhammed .

  • @BezabishGurmessa
    @BezabishGurmessa 5 місяців тому +5

    I'm protestant I love this neshida,🥰🥰🥰

  • @hamdiabdinur
    @hamdiabdinur 9 місяців тому +7

    Masha allah muaz Habib bexam des yelal Allah yechemrelh

  • @maliksani9396
    @maliksani9396 Місяць тому +1

    ❤❤❤❤❤❤ ፊደካ አቢ ዋ ኡም የራሱል አላህ (ሶላላሁ አለይሂ ዋሳልም)

  • @mustefajemal6811
    @mustefajemal6811 7 місяців тому +4

    Yehan nashed masmat makome akatgi😘 salu Aliha nabye ASW😍 😍😍😍😍😍 muaz

  • @merlu1997
    @merlu1997 9 місяців тому +22

    ወላሂ በቀን 10ጊዜ እየሰማው ልጠግበው አልቻልኩም የ ሀቢቡን መውደድ በወዳጁ ❤❤❤❤❤ሙአዝ አላህ ይጠብቅህ🤲

    • @Sebr-e1w
      @Sebr-e1w 9 місяців тому

      ረሱልን ሰላሏሁ አለይሂ ወሰለም መውደድ በተግባር ነው በጭፈራ ሳይሆን

    • @KutibaMohammed
      @KutibaMohammed 29 днів тому

      😢😢😍😘😭

  • @jemilalalemda7398
    @jemilalalemda7398 9 місяців тому +6

    ቃል የለኝም አሏህ ይጠብቅህ ❤❤❤❤❤❤

  • @Seadyia
    @Seadyia 9 місяців тому +32

    ፍቅሩማ ጠብታው ይጠልቃል
    ይበርዳል በል ሲለው ይሞቃል
    ያላቃል ሩህን ከገላ
    ሰይድ ረሱል ጃለላ
    ዓለይሂ ሶላቱ ወሰላም❤

  • @Hubbimu
    @Hubbimu 6 місяців тому +8

    Ahuns Gra Gebagn Wellahi Bademtew Bademtew Mechem Ayselech😢😢❤❤❤❤

  • @saaladdiinidiris9916
    @saaladdiinidiris9916 6 місяців тому +2

    I'm Oromo I love it so much Thank you #Muaz_Habib for present this beautiful menzuma To us ❤🙏

  • @BurhanMama-s3j
    @BurhanMama-s3j 9 місяців тому +7

    MashAllah arif sira nwa bertelan Allah yitebak

    • @HasanMohammed-s7m
      @HasanMohammed-s7m 7 днів тому

      😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤😂😂😂😂❤❤😂❤❤😂😂😂😂😂

  • @welidnurhussien3341
    @welidnurhussien3341 9 місяців тому +14

    ሙዓዜ የኔ ወንድም 🥰🥰🥰 ጀዛከላህ ኼር ሀቢቢ
    اللَّهُمَّ صَلَّ وَسَلَّم وَبَارِكَ عَلَيْهِ وَعَلَى آلِهِ

  • @abobakir87
    @abobakir87 6 місяців тому +7

    ሰላላሁ አለይሂ ዎሰልም😢💔

  • @MohammedSaed-be4vp.
    @MohammedSaed-be4vp. 2 місяці тому +5

    اللهم صلى وسلم وبارك على سيدنا محمد صلى الله عليه وسلم ♥️💚🫶🫶🕌

  • @ኑራኑሪ
    @ኑራኑሪ 9 місяців тому +16

    ባረካላህ ፍኩም🌺❤❤❤

  • @SuLingard-nr7go
    @SuLingard-nr7go 9 місяців тому +54

    ደጋግሜ እየሰማሁት ነው ምንም አይሰለችም ወላሂ ምርጥ ስራ ነው ጣፋጭ ነሺዳ

    • @mohammadsied-ux7ew
      @mohammadsied-ux7ew 9 місяців тому +1

      አወ ምርጥ ስራ ነው😂😂😂 አላህ ይህድክ በድን መቀለድ😢😢

    • @SuLingard-nr7go
      @SuLingard-nr7go 9 місяців тому

      @@mohammadsied-ux7ew 😭😭

    • @reima8186
      @reima8186 9 місяців тому

      ​@@mohammadsied-ux7ew😏🤮

    • @Mehomed
      @Mehomed 6 місяців тому

      ቲቲአረ ዝም​@@mohammadsied-ux7ew

    • @melkamuyahi1845
      @melkamuyahi1845 6 місяців тому

      የኛን እረሡል ሡ ወ ማወደስ ነው በዲን መቀለድ ያልከው አንተን ሂዳያ አሏህ ይስጥህ​@@mohammadsied-ux7ew

  • @mirhantube
    @mirhantube 4 місяці тому +6

    ሙዓዜ ምርጡ ❤

  • @lov3888
    @lov3888 6 місяців тому +101

    ክርስትያን ነኝ ግን ስሰማዉ ደስ ይለኛል

    • @abdulkafeamdino9563
      @abdulkafeamdino9563 6 місяців тому +1

      አላህ ካዘነላቸው ከማራቸው፤ ኢትኩም ሚነናር ካላቸው፤🤲 ዱአቸውን ከተቀበላቸው፤🤲 ከጀሃነም እሳት ካወጣቸው፤ ለጀነት ፍርዶስ ካላቸው፤👑 ለይለተል ቀድር ከወፈቃቸው፤😢 ረመዳንን ፁመው በመልካም ከተመዘገበላቸው ባሪያዎቹ ያድርገን አሚን 🤲🤲🤲✨ኢድ ሙባርክ✨✨✨

  • @AbdiyeB
    @AbdiyeB 6 місяців тому +5

    Mash Allah this is beautiful manzuma😮😮😮

  • @حبيبييارسولاللهصلاللهعليهو-ك5م

    የኔ ነቢ 😢 ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም. ❤አጂብብብ የሆነ ስራ ነው ሙአዙ

  • @MesafintFissha
    @MesafintFissha 6 місяців тому +519

    ኦርቶዶክስ ነኝ ግን ነሺዳዎችህ ነብሴን ያድሳሉ ማሽ አላህ

  • @Tofikseyid-nv8ws
    @Tofikseyid-nv8ws 9 місяців тому +9

    ሙዓዜዋ ኡፈይ ትለያለክ ወንድሜ ❤❤❤🎉🎉🎉🎉 ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ❤❤🎉🎉🎉
    መውደጃ የለኝም ሌላ
    ድረሱ አጣሁኝ መላ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም❤❤🎉🎉🎉

  • @MaheDarik
    @MaheDarik 2 місяці тому +1

    የሚገርም ድምፅ ግጥም ዜማ ❤

  • @YenusssJbrilll
    @YenusssJbrilll Місяць тому +1

    mashalalah allah afiyahn mulu yadrigew hajahan ymulalh .ayzoh ketilibet wendima yenus jbril ke ke debretabor university

  • @xbhf9217
    @xbhf9217 9 місяців тому +11

    ሶለሏህ ዓለይሂ ወሰለም ሶለሏህ ዓለይሂ ወሰለም ሶለሏህ ዓለይሂ ወሰለም❤❤

  • @timajidris6272
    @timajidris6272 9 місяців тому +40

    Assalatu Wassalamu Alayka Ya Habibi Ya Rasool Allaah ﷺ❤️
    May Allaah bless Ustath Seid Ahmed , Muaz Habib and all of you ❤️

  • @EfrataAmare-ou6si
    @EfrataAmare-ou6si 3 місяці тому +32

    ለምንድነው ግን ደስ ምትሉኝ❤

  • @MuleykTemam
    @MuleykTemam 2 місяці тому +2

    Ar allahin firuu mitbarataatut sawoch bazii ayinatimaa zafan xabiquu yarb hulachininim astakaakilan😢😢😢

  • @NejatJemil
    @NejatJemil 28 днів тому +1

    ማሻአላህ አላህ ይጨምርልክ

  • @NesruMuhidin-cp8dm
    @NesruMuhidin-cp8dm 9 місяців тому +7

    Wlhi ahhhhhhhhhhh muazeeee wlhi ya liben nw yegaletskilign endi endasdesatkegn alah yesdesitik ❤❤❤❤❤❤❤

  • @OsamaAbdu-lv9ix
    @OsamaAbdu-lv9ix 9 місяців тому +20

    اللهم صل و سلم على سيدنا ومولانا محمد💚💚💚

  • @Muhaba-Hairu-Teyime
    @Muhaba-Hairu-Teyime 9 місяців тому +24

    የነቢን መድህ የሚወድ ማዲሆችን ሊያከብር ይገባል

  • @riyadshow
    @riyadshow 8 днів тому

    Nashiida kana dhagefadhe quufe hin beeku❤❤❤❤❤❤

  • @anu.man.
    @anu.man. 6 місяців тому +7

    ይሄንን መንዙማ ስምቼው ልጠግበው አልቻልኩም ሙአዝ አላህ እድሜህን ያርዝምልን ❤❤

  • @ZeinebMuhamed-u9q
    @ZeinebMuhamed-u9q 9 місяців тому +8

    ሶለሏሁ ዓለይህ ወሰለም❤❤❤❤

    • @user-ሚጣ
      @user-ሚጣ 9 місяців тому +1

      ❤❤❤❤❤❤❤❤ወደድኩሽ

  • @hassenmohammed1375
    @hassenmohammed1375 9 місяців тому +8

    ወላሂ ቃላት የለኝም ደጋግሜ ብሰማው አልጠግብ አልኩኝ ሙአዜ አላህ ይጠብቅህ ዱአዬ ነው ❤❤❤

  • @ኑርየቁርአንማዕከል
    @ኑርየቁርአንማዕከል 5 місяців тому +41

    እስኪ ሙአዝን የምትወዱት👍👍👍

    • @AbduMehamud
      @AbduMehamud 4 місяці тому +1

      Le alah biye ewedewalew antenm

  • @HusniMustefa-h3i
    @HusniMustefa-h3i Місяць тому +1

    Beset forever❤❤❤

  • @kadijaa8750
    @kadijaa8750 4 місяці тому +1

    S a w🥰🥰masha Allah ታበረክ አላህ መሸማ መሀመድ ነገም መሀመድ አሁንም መሐመድ ❤❤❤❤❤❤ ሁለም መሀመድ ሀቢብ የአለም ጀግኖች ጀግና s a w❤❤❤❤❤

  • @abdulhakimmohammed7492
    @abdulhakimmohammed7492 7 місяців тому +4

    አላህ ይባርክህ❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉😊😊❤❤🎉🎉🎉

  • @ilme_time
    @ilme_time 9 місяців тому +9

    ኡስታዝ ሰኢድ አህመድ ብዕራቸዉን አላህ ይባርክላቸዉ ሙአዜ አንተ ደግሞ ድምፅህ እንደ ቢላል ድምፅ ተወዳጅ ያድርግልህ🥰🥰🥰🥰🥰🥰

  • @Geechkoo
    @Geechkoo 9 місяців тому +18

    ምንኛ ያማረ ስራ ነው❤❤❤
    ጥበብ ኢስላምን ሲኻድም ጥበብ ራሱ ያምርበታል ። በነቢ ሲሆን ደግሞ ይብሳል ألهم صلي وسلم عليه

  • @NasirMechal
    @NasirMechal 27 днів тому

    ፊትም ተመርቀሃል ነብዩ ሰ.ዓ.ወ በአንተ አንደበት ይዘክሩ አላህ ይጠብቅህ ❤❤❤❤❤

  • @ليديكاتم
    @ليديكاتم Місяць тому +1

    ቃላት የለኝም ኮ ሙአዜ ❤❤❤

  • @EthmLek
    @EthmLek 9 місяців тому +5

    አላህ ያቆያቹ ማዲሆቻችን ...አሚን❤❤❤❤❤❤❤

  • @asmamawahmed
    @asmamawahmed 9 місяців тому +45

    መገን ነብየ
    ሸጋ ስራ ነው
    ወንድሜ በርታ

    • @najaatkadir4895
      @najaatkadir4895 9 місяців тому +1

      ከአንተ አይጠበቅም ወንድሜ

    • @mahud-nine
      @mahud-nine 9 місяців тому +5

      ጥሩ ስራ ነው ሙአዝ
      ያ ሙሃመዳ😍😍

    • @MehamddawedSenbet
      @MehamddawedSenbet 9 місяців тому +3

      ማሻአላህ

  • @anufriki5030
    @anufriki5030 9 місяців тому +21

    ድንቅ ግጥም በሚጣፍጥ ዜማ ተሟሽቶ በውብ ድምፅ ጥርት ባለ ስቱዲዮ የተሰራ ድንቅ ስራ ነው ሙዓዜ በቃ ቃላት የለኝም👌👌👌👌👌

    • @zeniqune9480
      @zeniqune9480 9 місяців тому

      ወላሂ እውነት ነው ❤❤🎉🎉🎉

    • @murthe-wise535
      @murthe-wise535 9 місяців тому

      መንዙማው ምርጥ ነበር ግጥሙ ግን የተመታ ነው። "በአንቱ(በነብዩ ሰዐወ) እንመካ" የሚለው ነው ምርጥ ግጥም? መመካት በአላህ ብቻ ነው! ይህኮ ግልፅ ያለ ሽርክ ነው

    • @diyanadiya4905
      @diyanadiya4905 9 місяців тому +2

      ​@@murthe-wise535በነቢያችን ይሁንብህ ብለን ስንለምነው እምቢ በማይለን ጌታ ላይ እንመካ ነው ያለው

  • @JibrelAbdulhab
    @JibrelAbdulhab Місяць тому +1

    Alahu akbr

  • @mohammedAhmed-xv1jv
    @mohammedAhmed-xv1jv 6 місяців тому +2

    اللَّهُــمَّ ᷂صَلِّ ᷂وَسَـــلِّمْ ᷂وَبَارِك ᷂على ᷂نَبِيِّنَـــا ᷂مُحمَّدﷺ💚

  • @HIAHjs-i9i
    @HIAHjs-i9i 9 місяців тому +6

    የመዳም ቤት ተፀዳ ወላሂ እንዴት እደወደድኩት አላህ ይጣብቅሀ😍 የኔ ነቢ ረሱል ሰ አ ወ❤❤❤

  • @nurhusensherif1931
    @nurhusensherif1931 9 місяців тому +10

    ይነዝራል ሀቢቢ❤

  • @MameHabib-qz7gu
    @MameHabib-qz7gu 9 місяців тому +5

    የዚህ ዘመን ምርጥ የሀበሻ ስጦታ ነህ።❤❤❤

  • @medinaabdulkadir29
    @medinaabdulkadir29 22 дні тому

    ሙአዝ ለ ወጣቶች ጥሩ roll model ነህ ። አላህ ይጨምርልህ ማሻአላህ❤❤❤

  • @SumeyaAhemed
    @SumeyaAhemed Місяць тому

    ❤❤❤❤❤❤❤❤ اللهم صل وسلم على نبينا محمد صلى على وسلم وبارك عليه ❤❤❤❤❤❤

  • @DaniDanisa-cm8qu
    @DaniDanisa-cm8qu 4 місяці тому +2

    በአላህ ስም እምላለሁ እንደ አይነት ሙነሺድ አይቼ አላውቅም አላህ ይጨምርልሕ❤❤❤❤❤❤❤❤❤