ኢትዮጵያዊው ኢትዮጵያዊነቱን || ዘማሪት ትዕግስት ስለሺ || ግጥም ዲያቆን መኩሪያ ጉግሳ || ዜማ ሰማያት

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 26 січ 2024
  • ኢትዮጵያዊው ኢትዮጵያዊነቱን || ዘማሪት ትዕግስት ስለሺ || ግጥም ዲያቆን መኩሪያ ጉግሳ || ዜማ ሰማያት
    ኢትዮጵያዊው ኢትዮጵያዊነቱን
    ነብር ዥንጉርጉርነቱን
    ሊለውጥ አይችልም ...
    እምነቱን አይጥልም : ሀገሩን አይተውም
    ዜማ ከሰማያት ቀድቶ የዘመረ
    በብሉይ በሐዲስ ቀድሶ የከበረ
    ቢፈተን ቢወገር አለለት አምላኩ
    እምነቱን ድንበሩን ደፍራችሁ አትንኩ
    አዝ ...
    የእጸ መስቀሉ ይግማዱን ምድር
    ያባቶቹን ዕርስት መቅደሱን ብትደፍር
    መውጊያውን ነክተሃል ላንተ ይብስብሃል
    ናቡቴ ነው ልጇ ሞቶ ያሸንፍሃል
    አዝ ....
    ታቦት አስቀድሞ ዘምቶ የተዋጋ
    ድንበሩን በጸሎት በኪዳን የዘጋ
    እሳት የለበሰ እምነት ነው ጉልበቱ
    አትችሉትምና ትጥቃችሁን ፍቱ
    አዝ ...
    ብቻውን ሊዋጋ ተነስቶ አያውቅም
    ይጠራል አምላኩን በጉልበት አይቀድምም
    የእምነቱን ጉልበት ከስሙ ጋር አሥሯል
    ቅጥሩ የእሳት ነው ማን ደፍሮ ያልፈዋል ?
    Ethiopian can't change its Ethiopiness
    Nor the leopard its spots
    It won't lose it's faith, forsake it's country

    He who took the melody from heaven and sang
    Taking from the Old and New testament, Praised and glorified.
    Almighty God is there for him even through tribulations and afflictions
    Do not dare and touch the border of his faith.
    Chorus..........
    The land of which the portion of the True cross held
    If you dare to the temple of the inheritance of his fathers
    You've touched the goads and it will be hard for you
    His son is Naboth, who will die and defeat you.
    Chorus......
    He who put the Tabot upfront and fought bravely
    Closed the borders with prayers and worshipped devoutly.
    His power is faith which is clothed with fire
    As you won't triumph, lay down your weapon.
    Chorus......
    He has never stood up alone to fight
    He calls His God first, never leaned on his power.
    He has tied his name with the power of his faith
    The gate is made with fire, who can dare to pass?
    ክራር ዘውዱ ጌታቸው
    መሰንቆ እንዳልካቸው አዱኛ
    ዋሽንት አቡ ገብሬ
    ከበሮ የትምወርቅ ሙላት
    ሐዲስ ሐዋርያ
    የእንግሊዘኛ ትርጉም - ትርሲተ ድንግል
    ስቱዲዮ ያሬድ ተፈራ

КОМЕНТАРІ • 7

  • @Moon-moon21
    @Moon-moon21 5 місяців тому

    ዝማሬ መላዕክት ያሰማልን የአገልግሎት ዘመንሽን ይባርክልሽ

  • @WubalemasratWubalemasrat
    @WubalemasratWubalemasrat 2 місяці тому

    ዝማሬ መላእክት ያሰማልን

  • @sulamtise
    @sulamtise 4 місяці тому

    ዝማሬ መላዕክትን ያሰማልን❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @EliasWolde1234
    @EliasWolde1234 5 місяців тому

    ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን

  • @RomanGenet
    @RomanGenet 2 місяці тому

    አሜን ዝማረ መልአክት ያሠማልን ኢህቴ❤❤❤❤

  • @zemaridagmawiderebe6618
    @zemaridagmawiderebe6618 5 місяців тому

    ቲጂዬ ዝማሬ መላእክት ያሰማልን ፀጋውን ያብዛልሽ ።

  • @user-cf5mq7nc5s
    @user-cf5mq7nc5s 5 місяців тому

    ቲጂ ዝመማሬ መልእክት ያሰማልን