ክልላዊ የተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ በሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ በይፋ ተጀምሯል
Вставка
- Опубліковано 30 січ 2025
- ክልላዊ የተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ በሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ በይፋ ተጀምሯል
ወልድያ፣ ጥር 15/2017 ዓ.ም (ግብርና ቢሮ)
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ
"የተቀናጀ ማህበረሰብ ተፋሰስ ልማት ለዘላቂ ምርታማነት ዕድገት" በሚል መሪ ሀሳብ በሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ ስጋው ማረጃ ተፋሰስ የ2017 ዓ.ም የተቀናጀ የማህበረሰብ ተፋሰስ ልማት ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ተካሂዷል።
በተፋሰስ ልማት ማስጀመርያ መርሃ-ግብሩ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ፣ የግብርና እና አካባቢ ጥበቃ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ከፍያለው ሙላቴ፣ የክልል፣ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶችና በቀበሌው የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍል በተገኙበት መርሃ-ግብሩ ተካሂዷል።
በተፋሰስ ልማቱ መርሃ-ግብር ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ሲሆኑ በ2017 ዓ.ም የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ በተመለከተ በክልላችን ከ9ሽህ በላይ ተፋሰሶች ላይ ከ366 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በተለያዩ የስነ-አካላዊ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች ለመሸፈን ትልቅ ግብ በማስቀመጥና ይህንኑ ለማሳካት የተለያዩ የቅድመ ዝግጀት ስራዎች ተጠናቀዋል ብለዋል።
በዛሬው እለት በሁሉም የክልላችን አካባቢዎች የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ክልላዊ የማሰጀመርያ መርሃ-ግብሩ በይፋ መጀመሩን ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ተናግረዋል።
በዚህ አመት በተፋሰስ ልማት ተሳታፊ የህብረተሰብ ክፍል በተመለከተ ዕድሜው ለስራ የደረሰና መስራት የሚችል የማህበረሰብ ክፍል ሲሆን ከ4.5 ሚሊዮን ህዝብ በላይ የሚሳተፍበት የተቀናጀ የማህበረሰብ ተፋስስ ልማት ስራም ይሰራል ሲሉ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ተናግረዋል።
እንደ ክልል በአለፉት አመታት በተሰሩ የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራዎች ህብረተሰቡን በማነቃነቅና ሰፊ ርብርብ በማድረግ የአፈር ክለትን በመቀነስ በየዓመቱ እየታጠበ የሚሄደውን አፈር በማስቀረት፣ ለምነቱን መጨመር፣ ደንን
በማልማት የመሬትን ሽፋንንና የጽድቀት መጠን ማሳደግ፣ ማሻሻልና እንዲሁም በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የገፀ ምድርና ከርሰ ምድር ውሃን ማበልፀግ ተችሏል ሲሉ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ገልፀዋል።
ዶ/ር ድረስ ሳህሉ አክለውም ማህበረሰቡ በልማቱ ተጠቃሚ ሁኗል፣ የስራ ዕድል ተፈጥሯል፣ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን በማወቅና በመረዳት ዘላቂነቱንና ልማቱንም እንደ ባህል ተቆጥሮል፣ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል ብለዋል።
የስሜን ወሎ ዞን ግብርና መምርያ ሃላፊ አቶ ተገኘ አበተ የተፈጥሮ ሃብትልማትና ጥበቃ ስራ አመቱን ሙሉ የሚሰራ መሆኑን፣ የተፋሰስ ልማትስራ ማህበረሰቡ እንደባህል ይዞ እየሰራ ነው፣ የቅድመ ዝግጅት ስራ ተጠናቆ ዛሪ በዞናችን በሁሉም ቀበሌዎች የተፋሰስ ልማት በዛሬው እለት በዋድላ ወረዳ የተግባር ማስጀመርያ መርሃ-ግብር ተካሂዶል ሲሉ አቶ ተገኘ አባተ ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- አሻግረው ፈረደ
ካሜራ :- ጌታቸው ታፈረ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ
ድረ-ገጽ
www.amhboard.go...
ቴሌግራም t.me/AmharaBur...
ፌስቡክ www.facebook.c...
ዩትዩብ / @amharaagriculturebure...
ቲክቶክ / amhara.agricultur