I am glad to see you.Thanks God. Alex I don't want to say a lot just may God bless you again and again. Wshing you best rest of your life. You're my favorite singer.
This guy is a living legend , 19 yrs and still strong !!! Ppl if u r in prison for only 2 days u may get crazy ! Alemayehu was sick for 19yrs plus he was in a camp and in prison for doing nothing... his mentality is beyond us !!! DEZDEMONA brother …beyyyyyy marign…endegennnnnaaaa….yenewaaa dezdemona 🫶🏽
ወላሂ የሰይፉ መልካምነት ነው ሁሌም ሚገርመኝ ለተቸገረ ሁሉ ሟች ነው እኛ ብዙ ግዜ interview የተደረገለት ሰው ብቻ ላይ ነው ምናተኩረው የሰይፍሻ መልካምነትና ቅንነት አልተወራለትም ለምታደርገው መልካም ተግባራት ሁሉ አላህ ይስጥህ 🥰🥰
Tekekelellll welahi seyefu melekam sew Allah yitebekh
ጎበዝ በጣም በጣም👏👏👏
Yehea balegeawochen shefan yemiset leba tabiya
በትክክል
Thank you
ስይፉ ትልቅ ነህ።። የተለየ ቅላፄ ባለቤት የሆነው አለማየሁን ማየታችን ደስ ብሎናል
በጣም :: ልዩ የሆነ ነገር አለው:: i hope he tours again
ካዳነው ጌታ ኢየሱስ ወደጨለማው አለም ወደዘፈን መመለሱ ነው ያስደሰታችሁ???
@@TesfaAleke Ay Pente 😂😂😂😂 Wanaw Chifera Enante Gaar Aydel ende Yalew? 😂😂😂😂 Demo Atafrum Eko Sewn Sititechu 😂😂😂😂 Eferu Eshi 👆👆
ሰይፉ ከሰራቸው የቴሌቭዥን ዝግጅቶች ቁጥር አንድ ከአሌክስ ጋር ያረከው ቆይታ ነው !
I agree with you
I agree with you 🎉🎉
Yes
Nooo Abdukiar interview was the best....this is the 2nd best
❤❤🎉👌
ብቻዋን ለፍታ ላሳደገች የልጆቹ እናት ምስጋና ያስፈልጋታል።
ሰይፋ ግን ምን ዓይነት ደግ ሰው ነህ!! ቅንነት ቤቷን የሰራችብህ ። እግዚአብሔር እድሜ ያጥግብህ ጌታ ኢየሱስ ይባርክህ።
ወይኔ ልጁን እንዴት እንደወደድኩት!!! ነፃነቱ፣ በራስ መተማመኑ፣ ጨዋና ጨዋታ አዋቂ እግዚአብሔር ከፍ ያድርግህ!!!
የ90ዋቹ ምርጥ ድምፃዊ❤
@hanna ሀኒቾ፣ ስለ ልጁ እኔ ከምፅፍ የሌላ ሰው ኮሜንት ካየሁ like እገጫለሁ ብዬ scroll ሳረግ ...
አንጀት የሚበላ ልጅ ነዉ ፈጣሪ እንኳን አገናኛቸዉ
እግዚአብሔር ደግ ነው ልጆቹን እንኩዋን እዚደረጃ ደርሠው ማየት ቀላል አይደለም
🥰
ልጁ ለአባቱ ያለውን ፍቅር በደንብ አየነው ተባረክ❤❤❤
ትዝታ ወደ 1994 አሌክሶ የ90ዎቹ ምርጥ ባለህበት ሰላምህ ይብዛ 🙏
የሰይፉ ደስታ ፊቱ ላይ ይነበባል እግዚአብሔር ታላቅ ነው
አሌክሶ እንኳን ለሃገርህ አበቃህ
ድምጻዊ አከማየሁ ሂርጶ በ1993/94 ዓም ተማሪዎች እያለን በጣም ከምንሰማው ሙዚቃ የአንተና የጎሳዬ ተስፋዬን ነበር፣ የምር አሌክስ ስላየሁህ ደስ ብሎኛል፣ ባይተዋር በጣም ደስ የሚለኝ ዘፈን የሚያስለቅሰኝ ነው
እንኳንም ኖርዌይ ቆይተህ ህክምናህን ለመከታተል አበቃህ!!! አግዚአብሄር ምናልባት በስራ አድርጎ ወደዛ የላከህ የሚያጋጥምህን አስቀድሞ ስለሚያውቅ ይሆናል፣ እንኳንም ተረፍክ፣
እግዚአብሄር ረጅም ዕድሜና ጤና ይስጥህ!! አያት ስለሆንክ ደስ ብሎኛል፣
❤
ذكريات الجميله ❤
ሰይፉ በጣም የሚገርም ስብእና ያለው ሰው ነው ሲሰጥ አለሁላችው ሲል ሁሉን ነገር በድብቅ በዚ ገዳይ ልታይ ልታይ የማይል
በጣም.ሰይፉ.ልቡ.ቡቡ.ነው.የዋ.ነው
የአሌክስን ዘፈን ከህፃንነቴ ጀምሮ ግጥሙ ሳይገባኝ አልቅሺ አልቅሺ ይለኝ ነበር። በጣም ያሳዝነኛል ድምፁ። የት ይሆን ያለዉ ብዬ አስብ ነበር። እንኳን ፈጣሪ ለሀገርህ አበቃህ ሌጀንድ!!
@@desstadessta አታቀርቅሪ ቀን ያልፋል
ሰይፉ አሌክስን ስላቀረብከው ሰለረዳኸው በጣም ደስ ብሎኛል ነገርግን እባክህ መዝፈን ካልፈገ አትገፋፉት:: ካላመነበት ይጨነቃል:: ከተጨነቀ ደግሞ በሽታው ሊያገረሽበት ይችላል አና እባክህ እራሱ ልቡ የፈቀደውን ነገር እንዲያደርግ ብቻ እርዱት:: ጎሮሮውን ለመዝፈን ብቻ ሳይሆን እሱ ከህይወት የተማራቸውን ብዙ ነገሮች ለወጣቶች እያስተማረ ህይወት መቀየር ይችላል::
ሃይማኖት ቀይሮዋል ለዛ ነው
አለማየሁ ዉድ የኢትዮጲያ ልጅ የፅንቁ ድምፅ ባለቤት እንኳን ደህና መጣህልን ዉድ ነህ አሌክስ ።
ወጭውን ያውም በአሁኑ የኢትዮጵያ ኑሮ ሙሉው ከነህክምናው ቸርች ከቻለለት ፒስ ካልሆነ ግን ጥግሽን ከነ ተከታዮችሽ ያዥ
ወይ ሰይፋ የተባረክ ይሄው በልጆች አንበሸበሸህ ፈጣሪ የልጅ ልጅ ለማየት ያብቃህ ለቁም ነገር ያድርስልህ ልጆችህን ለሰው እንደምትደርስ ፈጣሪ ይድረስልህ 🙏አሌክስዬ እንኳን ለአገርህ አበቃህ ፈጣሪ ጨርሶ ይማርህ ለንስሀ ለቁርባን ያብቃህ ለዘፈን ሳይሆን ለምን እድለኛ ነህ ከሞት መመለስህ ስለዚህ አንተ ፈጣሪህን የምታመሰግንበት ጊዜ ነው እነጂ ዘፈኑ ይብቃህ ልጆችህን ይጠብቅልህ🙏🙏🙏🙏
አሜን
😢😢😢በእባ ጨረሰኩ እውነት መልካምና ደግ መሆን ከአሌክስ ተማሩ ያመልካምነቱ ጥሎ አልጣለውም ፈጣሪ ይጠብቅህ የኛ ትዝታ ነህ አሌክስየ❤❤❤
ሰይፉ በጣም ደስ የሚል ሹው እንባ እየተናነቀኝ ነው ያየውት አሌክስ እንኳን ለሀገርህ አበቃህ እንደልጆችህ ነው ደስ ያለኝ ስይፉ በመጨረሻ ክሰህናል 2017 እንደጀምርክ በዚሁ ምልክ አስጨርሰን። አተ ዘፈን ብቻ አይደለም ለካ በ90ዎቹ የሚባለው ጪዌውስ ቢሆንስ ያኔ አይደል እንዴ የቀረው። መልካሙ ሁሉ ይገጠምህ ጋሽ አሌክስ ።ያለሽ እያንዳንድሽ ስጭ እና ያየናፈቀን ድምፅ እንስማው። ብቻ በጣም ነው የተደሰትኩ አይ ቢኖርኝ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
ዘፈን ሀጢያት ነው።
Alex በጣም real ሰው ነው ማስመሰል የሚባል ነገር አላየሁበትም ይገርማል
Betam❤
የ90 ዓ.ም ትውልድ የሆናችሁ እንደ እኔ አይኑን ሳይነቅል ይህን ሾው ዘመኑን እያስታወሰ በተመስጥኦ በማየት የጨረሰ!!
Ena. thank God. my young. age still I'm in Manchester. I will be back soon
እኔም ዘመኔን እያሰብኩ ነው ያየሁት
✌👌
እኔ
አለን✌️የአሌክስን ሙዚቃዎች ሁሌም እንደ አዲስ ነው የምሰማቸው ❤❤❤
ወይ ሰው መሆን...... 😢። እንኳን ብቻ ልጆችህን በአካል ደግመህ ለማየት አበቃህ ወንድሜ። ሌላው ከንቱ የከንቱም ከንቱ ነው ። አምላክ ጤና እና እድሜን ይስጥህ።
አልአዛር በእዉነት የልጅ ልክ ነህ!!!አባትህን የምትወድበት ልክ የምተገልፅበት ልክ በስመአብ በእዉነት ተባረክ🙏🙏🙏 አለማየሁ ሂርጶ እግዚአብሔር ፍፁም ጤና ይስጥህ በቀረዉ ዘመንህ የረዳህን እግዚአብሔርን የምትጠጋበት ዘመን ይሁንልህ🙏🙏🙏 ሰይፉ በእዉነት መልካም ሰዉ ነህ 🙌
OMG Alex, በጣም ምርጥ ሠው። ከአብዬት እስከ ወሎ ሠፈር ራዝማታዝ ሲሠራ በደንብ ነበር የምንግባባው። በጣም በነገሠበት ሠአት ወጥቶ በመቅረቱ በጣም ይገሮመኝ ነበር ለካንስ ወዳጄ ብዙ አይተሀል። እንኳንም ለሀገርህ ለወገንህ ለቤተሠብህ በሠላም አገናኘህ።
አሌክስ ያልተወራለት አዘፋፈኑ ለየት ያለ ምርጥ ድምፃዊ🥰❤️
Yes❤❤❤❤
ሰይፍዬ በጣም ነው የምወድህ የማደንቅህ ሙያዊ ግዴታህን በትክክል ነው የተወጣኽው። በርታ ሰላምህ ይብዛ 🙏
ውይ አሌክስ እኔ ኤርትራዊ ነኝ አዲስ ተወልጄ ስላደግሁ ሁሌም ስለአሌክስ በጣም ስለምወደው ሁሌም ስለሱ እጠይቅ ነበር ይገርማል በመሸረሻ ታስረህ በጣን አሰብኩ ላገኝህ ፋልጌ አልቻልኩም ሚገርመው ጀግና ነህ 19አመት ካምፕ መኖር በጣም በጣም አይታሰብም ሳስብው ግን ጀግና ነህ በምቾት እዚህ አውርፓ ጥሩ ቦታ እተኖርን አንተ ግን ያን ሁሉ አመት አይታሰብም፣፣ወይ ዘፋነህ በጣም ስሰማው ያማል ግን አይዞህ ስልክህን ተውልን አምንችለውን እናግዛለን።
Bless you
ሰይፍሻ ላንተ ቃላት የለኝም እግዚአብሔር በልጆችህ ይካስህ ዘርህይለምልም አሌክስዬ እንኩዋንም ለሀገርህ አበቃህ።
ሰይፉን እናመሰግናለን ማለት አለብን በህይወትእያለ!
ለድሀ ደራሽ የብዙሰዎችን ህይወት ያቀና ሰዉ ነዉ።💚💛💖💚💛💖💚💖💛💖
እኔም ይህንን እያሠብኩ ነበር!!እዉነት ግን የሰይፍሻ አይነት ስንት ሰዉ ይሆን ያለን??
ትክክል በእጅ የያዙት ወርቅ ነው ሰይፉ አላስተዋልነውም
@@mamebekele4484 ረዥም እድሜና ጤና ይስጠዉ
Amen 🙏 and
አሌክስ እንኳን ጌታ እረዳህ ፤እንዳልከው እድሜ የጨመረልህ እግዚያብሔር ይባረክ!! ታዲያ ወንድሜ ያ በመከራህ ጊዜ ካንተ ጋር ለነበረ፤ ከሞት መንጋጋ ለታደገህ፤ ልጆችህን በሰላም ጠብቆ ፍሬያቸውን ላሳየህ፡እግዚያብሔር ውለታው በሰጠህ ድምፅ ምስጋናና ዝማሬ ነው እንጂ ዘፈን አይደለም፡፡ እባክህ አሌክስ ከተዘጋጀልህ አለማዊ ወጥመድ ራስህን አድን ፡፡ ሰውን መፍራት ወጥመድ ነው እግዚያብሔር መፍራት ግን ጥበብ እና ቅዱስ የሆነውን ማወቅ ነው፤ደግሞም በሰው ከመታመን በእግዚያብሔር መታመን ይሻላል ይላል ቃሉ፡ስለዚህ ወንድሜ ትላንትናህን(ምድረበዳህን) ያሻገረህ እግዚያብሔር ለነገ ለሚያሠጋህ ለጎደለህ በማን ሊሞላ ይችላል ላልከው ነገር ሁሉ ታማኝ ነው፤ እሱ የሚረዳህ ካንተ ምንም ሳይፈልግ ነው፡፡ ሰው ግን እንዲህ አይደለም ፤
እግዚያብሔር የሠጠህን ዕድል በማስተዋል እንድትጠቀምበት ፤ የደከመን የሚያበረታና አፅንቶ የሚያቆም የእግዚያብሔር የፀጋው ሀይል እንዲለቀቅልህ ፀሎቴ ነው
ተባኖባችሗል - ምቀኞች - አስመሳዮች - የጥበብ ጠላቶች ። የሙሉቀን አይበቃችሁም - የነካችሁት ሁሉ ...
ከአስራ አራት ህሙማን መካከል እግዚአብሔር እድል ስለሰጠህ አምላክህን በዝማሬ አመስግን ደግሞም መንፈስህ ያን ይመስላል እንኳን ደስ ያለህ about the second chance❤
“ከግብፅም ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለ ክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ባለ ጠግነት እንዲሆን አስቦአልና ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ፤ ብድራቱን ትኵር ብሎ ተመልክቶአልና።”
- ዕብራውያን 11፥25-26
ጎበዝ ልጅ በእግዚአብሔር ትልቅነት ያምናል እግዚአብሔር ይመስገን
ስካንዲኒቪያን ሀገሮች ለመኖር በጣም ከባድ ነው የአየር ፀባዩ በተለይ ዲፕረሸን ያስይዛል እኔም ከ13 አመት በፊት ስዊድን ነበርኩ 11 ወር ተቀምጬ መኖር አቃተኝ ወደ ሀገሬ መጣሁ ሰው ካላየ አያምንም ስደት ከባድ ነው
የሰይፍሻ ደስታን ግን ፊቱ ላይ እያያችሁት ነው ግን ❤❤❤❤❤ አሌክሶ እንኳን ለሀገርህ በሰላም ውድ ሀገርህ ወደ ኢትዮጵያ መጣህ ሀገር ምንም ግዜ ሀገር ናት ❤❤❤❤❤❤
አይ ሰይፍሻ ለዚህ ለዚህ ማን ብሎህ ተባረክ እግዚያብሄር እንኳን ለሀገርህ አበቃህ
ለሀገር ወገኖች መብቃትህ እግዚአብሔር ይመስገን። ወንድሜ ጌታ ዘመን የጨመረልህ ለራሱ ነው ዘፋኝ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርስም ዘምር አመስግነው ጌታ ኢየሱስ ይሻልሀል
በጣም የሚያስተምር የሚያጽናና የእግዚአብሔርንም መልካምነት የሚያሳይ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ሰይፉ ቀልደኛ ብቻ ሳትሆን ቅን ልብ ያለህ ሰው መሆንህንም አይቻለሁ በርታ አሌክስም እንኳን ለሀገርህ አበቃህ
በጣም ነው ያሳዘነኝ ያሳለፋቸውን ነገሮች ሳስበው አልቅሼ ነው የጨረስኩት ፕሮግራሙን እንኳን ለሀገርክ አበቃህ አሌክስ
I am glad to see you.Thanks God. Alex I don't want to say a lot just may God bless you again and again. Wshing you best rest of your life. You're my favorite singer.
ሰይፉ ፋንታሁን ረጅም እድሜና ጤና ከ እነ መላዉ ቤተሰብህ እንኳን አደረሳችሁ ስለምታደርጋቼዉ መልካም ነገሮች ሁሉ ፈጣሪን እጅግ አብዝቶ ይባርክህ
🇺🇸 እኛም ልባችን ኢትዮጵያ ነው
ሀገራችንን እግዚአብሔር ሰላም ያድርግልን 🙏
“ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።”
- ዮሐንስ 10፥10
እውነት ነው ሰይጣን ለመግደል ለማዋረድ የገንዘብ ,የእውቅናና ዝና ያዘጋጃል ጌታ እየሱስ ጌታ ነው ለዘላለም ከእጁ መዳፍ ማንም አያወጣት በደሙ የታተመች ነፋስ።
በፀሎት እንደግፈው።😇😇🙏🙏
ሰይፉዬ አላህ ይጨምርልህ ገናለብዙዎች ምትተርፍ ቅን ኢትዮጲያዊ ነህ እድሜ ይስጥህ
አሌክስ የ90ዎቹ ምርጥ ድምፃሚ ነበር ዜማዎቹና ድምፁ ለየት ያሉና ደስ የሚሉ ናቸው
የሰው ልጅ ተስፋ ካለው ፈጣሪ ከረዳው ሁሉም ያልፋል😢😢❤❤
በመጀመሪያ ሰይፉ ፋንታሁንን በጣም ማመስገን ይገባል። ሁሌም የተቸገረን ሰው ለመርዳት ያለው ፍላጎት በጣም ይደንቃል። አሌክስ እንኳን ለሃገር በሰላም አበቃህ። ስደት አይኑ ይጥፋ። ስንቱ አይምሮውን ስቶ በሰው ሀገር የሚንከራተት አለ። አንተ በጤና አገርህ በመግባትህ እ/ር የተመሰገነ ይሁን። የለሊት ስራ ጨርሼ ወደ ቤት እየሄድኩ ነው post የተደረገውን ያየሁት። የእንቅልፍ ሰዐቴን ቀንሼ ነው ሙሉ Interview ያየሁት። በጣም ስለምወድህና ስለማከብርህ። መልካም አዲስ አመት ከነመላ ቤተሰቦችህ ይሁንላችሁ።
በእውነት የተቀላቀለ ስሜት ነው የተሰማኝ።ሰይፉ ላይ ቀርቦ አሁን ያወረውን(ምስክርነት) በሙሉ ከአሥራ ምናምን አመት በፊት በሆነ መጽሔት ላይ አንብቤአለሁ።እናም በዚያቃለመጠይቅ ላይ የማስታውሰው ኢየሱስ ደሜን በደሙ ቀየረው አነጻው እያለ የተቆረጠን ተስፋ እንዴት እንደቀጠለለትና እድሜ እንደጨመረለት ነበር ሲመሠክር ያነበብኩት።እናም በሙሉ አቅሙ ያገለገላት አለም አንቅራው ተፍታው ማንም አጠገቡ በሌለበት ብቻውን ያስታመመውንና ያዳነውን ጌታ በብዙ ምስጋና ሲያከብረው ተመልክቻለሁ ።እናም ለካ ዓለም ዛሬም ድረስ ልቡ ውስጥ እንደከተመች ነው ያየሁት።በተቀጠጠለለት ዕድሜ ያዳነውን ጌታ እንደማገልገል ጀርባውን ላዳነው ጌታ ሰጥቶ ዓለምን ለማገልገል እየተሟሟቀ እንደሆነ ሳይ ልቤ በጣም አዘነ።በእርግጥ እግዚአብሔር ከሳበው በስተቀር ወደ ጌታ ሊመጣ የሚችል እንደሌለ ሳይ ደግሞ እግዚአብሔር የልቡን ዓይን ከፍቶለት አለምን አንቅሮ ተፍቶ ጌታን እንዲከተልና እንዲያገለግል ከልቤ ተመኘሁ።
ሰይፍሻ ግን ክብር ይገባሀል🙏🏾ብዙ ያልተነገረልህ ሩህሩህ ለተቸገረ ደራሽ ለከፋው አፅናኝ ለታመመ ደራሽ የሆንክ ጥሩ ወንድም ነህ:: ተባረክ🙏🏾ልጆችህ ይደጉልህ ደግነት ለራስ ነው::
ከዘላለም ባርነት ያንድ ቀን ነፃነት አለ መንግሱቱ ሀይለማራም
ይሄንን ሁሉ ያደረገው የክብሩ ባለቤት ልዑል እግዚአብሔር ስሙ በፍጥረታት አንደበት ሁሉ የተመሰገነ ፣ የተወደደ ፣ የከበረ ፣ የተቀደሰ ለዘለዓለም ይሁን ! እንኳን ለቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ በሰላም አበቃህ ወንድማችን ።
የጻፍከው ምስጋና ልክ ነው። ግን "ቅድስት ሀገር" ያልከው ስህተት ነው። ሀገሬን እወዳታለሁ ግን "ቅድስት" ብዬ አልዋሻትም። ሀገር ህዝብ ነው።
እንሰሳ@@TesfaAleke
@@tarikueshetu1464 ይኸው መሠከርክ እንዳንተ/ች አይነቶች ሚሊዮን ተሳዳቢዎች : ነፍሰገዳዮች: አመንዝሮች የበዙበት ሀገር እንዴት "ቅድስት " አልካት????
ምስጋናው ልክ ነው ቅድስት ሚለው ግን ከባድ ውሸት ነው
@@TesfaAleke ቢመርህም ዎጠው አንተ ተቀበልክ አልተቀበልክ ምን እዳይመጣ? ወደድክም ጠላህም ኢትዮጲያ ቅድስት ሀገር ነች። ታድለህ አንተም እንኳን ኢትዮጲያዊ ተብለክ ተፈጠርክ የሆንክ ሰነፍ
አሌክሶ ያራዳ ልጅ መገናኛ ቤት ስታሰራ እኛ ነበርን አፈር ያነሳነው ምርጥ ለጋስ የገባህ ኑርልን
እባካችሁ ፀበል ቢጠመቅ ካለበት ድብርት ይወጣል
😂 I remember እንደ ጎረቤት
@@እኔምአምናለሁአድነኝብየ 😆😆😆😆😂
@@yohanneswoldu4658 ልክ ነው
አሌክስ በጣም የተረጋጋ ሲናገር ተደማጭ በሳል ሰው ነው በጣም ነው የወደድኩት። ሰይፉ በጣም ትልቅ ሰው ነህ እስካሁን ካየዃቸው ፕሮግራሞች ለኔ ቁጥር 1 ነው።
ሰይፋ በሂወትህ ዘመን ከሰረህው ሁለ ዝገጅት አሌክስን የጠየቅበት ቀን ነው፣
ህይወት እኛ እንዳሰብነው አይደለም እኔ 2007 አዲስ አመት የመን ድንበር ነበርኩ አሁን 2017 ተባለ ሳኡዲ የምር ደከመኝ መረረኝ ግን አይሞላም እስኪ ሀብታሞች የእውነት ማንኛውንም ስራ እሰራለሁ ሀገር አስገቡን በስደት ምንም አዲስ ነገር አላገኜሁ😢😢
@@hamahyy7178 💞💞💞💞💞💞
Faxari al
ንስሀ ገብቶ በጌታው ፊት ምህረት ያገኘን የቀድሞ ዘፋኝ ወይንም ሰይጣን አወዳሽ የነበረን ሰው ተመልሶ እንዲዘፍን ማስጨነቅ ምን የሚሉት ነው ሰይፉ እባክህ ከዘፈን ደላላነት ውጣና እ/ርን በእየሱስ አማካኝነት አምልክ ይብቃህ በዘፈን የሚገኝ ጥቅም ሞት የዘላለም ሞት ነው
@@hamahyy7178
Dear Sister hama , do not lose hope ok. I am from Eritrea and I have such a difficult time , thanks to God I am in Switzerland now.
ለአሌክሰ መሬት ይሰጠው ግን አባቱ ነው ትንሰኤ ልጅ ነው ይመሳሰላሉ
ትንሳኤ ጎበና በየወሩ እንግዳ ይሁን የምትሉ። ጨዋታው አይጠገብምኮ❤
@@EliasBekele-s1m betammmm
እግዚዐብሄር እድል ሲሰጥ ወደ ቤተክርስትያን ወደ ቤቱ ነዉ ተመልሰህ ወደ ሀጥያት ባትመለስ መልካም ነዉ❤
እኔ የማንንም ቃለመጠየቅ በዚህ ደረጃ ፈዝዤ አይቼ አላውቅም የምር እንኳን ለሀገርህ ከልጆችህ ከመላው ቤተሰብህ አገናኘህ በጣም ነው ደስ ያለኝ እኖድሀለን ረጅም ያኑርህ
በእውነት ሰይፍሻ አሌክስን ስላየሁት ቃላትም የለኝም።በጣም ከሚናፍቁኝ ሰዎች ዋናው አሌክሶ ነበር እግዚአብሔር ምን ይሳነዋል።እንኳን በእድሜና በጤና አየንህ እንዴት ደስ እንዳለኝ አልገልጸውም።ሰይፍሻ መልካም ሰው ክፉ አይንካህ።የልጅ ክፋት አያሳይህ።ምን አይነት ወርቅና ደግ ዘመን አለፈ።ጎስሽንም አብረህ ታቀርበው ነበርኮ ሰይፍሻ፡ በልዩ ገጠመኝና ትዝታ ያጅቡት ነበር።ብቻ ደስ ብሎኛል።ተው ሰይፍሻን አንድ ቀን ቀመን እናክብረው።የክብር ዶክትሬት ይሰጠው ይታሰብበት።እውነት ሰይፍሻ የሚገርም ሰው ነው የሰራውን መልካም ነገር ልትነግረው ልታመሰግነው ስትጀምር ለበስበስ ያደርጋታል አቦ በሰማይ ቤት ይመዝገብልህ።
አሌክስዬ እንዴት ደስ እንዳለኝ ሳይክ አንተም በሂወት እያለህ እኛም በህይወት እያለን እንኳን አየንህ🙏🏽ብዙ የልጅነት ትዝታዎች አሉኝ ባንተ ሙዚቃ ያንተን ሙዚቃዎች ከማዳመጤ ብዛት አካባቢዬያሉ ሰዎች ሁሉ ያዳምጡታል ከዛም በላይ ይወዱታል ሁሌም ስሰማው ሙዚቃህን ወደ ልጅነት ግዜዬ ይመልሰኛል ለማንኛውም እጅግ በጣም ተወዳጅ ሰው ነክ❤️ አሁንም እድሜ ጨምሮ ጨማምሮ ይስጥህ ተወዳጁ አለማየሁ ሂርፖ❤️
ድሮም እወድህ ይበልጥ ወደድኩህ በስብእናህ እና በግልፅነትህ ።ምርጥ የአራዳ ልጅ
This guy is a living legend , 19 yrs and still strong !!! Ppl if u r in prison for only 2 days u may get crazy ! Alemayehu was sick for 19yrs plus he was in a camp and in prison for doing nothing... his mentality is beyond us !!! DEZDEMONA brother …beyyyyyy marign…endegennnnnaaaa….yenewaaa dezdemona 🫶🏽
You're right. Kudos to him
U Are fight👍
ሰይፉ መድሀኒያለመ ጨምሮ ጨማምሮ ይስጥህ ሰው እክባሪ ነህ እድሜ ከጤና ጋር ከነመላው ቤተሰብህ ይስጥህ ❤️❤️❤️❤️❤️🙏🏽🙏🏽🙏🏽
Alex ስላየሁህ ደስ ብሎኛል የድሜህን ቀናት የጨመረልህን አምላክ አምልከዉ
ሰይፉ ትለያለህ
ላዳነህ ለደረሰልህ እድሜን እድልን ሊሰጥህ በብቸኝነትህ በቡስቁልናህ ጊዜ ደርሶ ላፅናናህ ላገዘህ ስሙን ጠርተህ ለባረከው ጌታ ኢየሱስ ለመዘመር ያብቃህ ሳይረፍድብህ አለም ከንቱ ናት አባቴ
ሠይፍየ የዋህ እኮ ነህ አሌክሥን ሥታየው ደሥታህ ፊትህ ላይ አለ በአሌክሥ ዘፈን 16ገጽ የፍቅር ደብዳቤ ፅፌ ነበር።ያነበበችው አልመሠለኝም ፈተና ሠአት ነበር።እንኳን ለሀገር አበቃ
❤❤❤❤❤❤
አንባባው ከሆነ ለመውደቋ ተጠያቂ ነህ@@abyssiniawit1736
😂😂😂antes asfetagh nberk yemchik asakegh
😂😂😂😂😂😂😂
😂😂😂😂
ሠይፍየ ሚሥኪንኮ ነህ ወላሂ አላህ አንተነም በጤና ያኑርህ አዛኝኮ ነህ አሌክሥየ አላህ እንኳን ለሀገርህ አበቃህ አብሽር ከዛ ሁሉ ፈተና ዪወጣህ ጌታህ ያቀውቃል
ሰይፍሻ በጣም ምርጥ ሰው እግዚአብሔር ይባርክህ አሌክስ እንኳን በሰላም ለሀገርክ አበቃክ የኢትዮጵያ ህዝብ ደግ ነው አይዞክ❤❤❤
እግዚአብሔር ቢዘገይም የሚቀድመው የለም እድሜና ጤና ይስጥህ አለማዬሁ❤❤❤❤🎉
ሰይፉ በጣምምም ሚገርም ከሰው ስተት የሚማር መልካም ልብ ያለው ሰው ነው ግን የሚገባውን ቦታ አላገኘም.. አስቡት አስኪ አንድ ቀን ማለፉ ቢሰማስ አንዴት አንደምንፀፀት 😢😢ሚዲያ ጭር ነው ሚያረገው የኛ ድምቀት በጣም ወድሃለሁ 😘
በጣም ትክክል ሰይፉ መልካም ሰው ነውቀና ነው ግን አልተነገረለትም
@@aby605 እድሜይስጥልን
ህይወት ማለት ይቺ ናት እንደ ቀልድ 19 አመት አሌክሥን ሣሥብ ኢቫንጋዲ ከአዕምሮዬ አይጣፋም አሌክሥዬ እንኳን ለሐገርህ በሠላም አደረሰህ ሁሉም ይሥተካከላል አይክፋህ ወንድምዬ ቀሪ ዘመንህ ይባረክ
ሰይፉ ከልብ መልካም ሰው ነህ ።ፈጣሪ እድሜ ከጤና እና በረከት ያድልህ።...አንተ በማስተዋል እና በብልጠት አምልጠሀል።ከተሳሳተ ጋብቻ የዘገየ ይሻላል...
ሁሌ ጥሩ ስራህ ለክፉ ቀን ስንቅ ነዉ እግዚያብሄር ለሀገርህ ከቤተሰቦችህ ከወዳጆችህ ጋር በሰላም አገናኘናኘህ አምላክህን እገልግል አመስግን ቀሪዉ ዘመንህ ይባረክ ደጉ ዘመንን አስታወስከን ለሀገራችን ሰላሙን ፍቅሩን ይስጠን🙏🏾
ዋዉ አባትና ልጅ እንዴት ደስ ትላላችሁ:: እንክዋንም በህይወት ተገናኛችሁ🙏🏾
ሰይፉሻ ቲክቶከርሮችን እና ሌሎች ቁምነገር የሌላቸውን የሶሻል ሚዲያ ሰዎች ከምታቀርብ እንደዚህ አይነት እንቁ የሆኑ እንግዶችን ብታቀርብ የተሻለ ነው በርታ
እንኩዋን እግዚአብሔር በሰላም እና በጤና ለእናት አገርህ አበቃህ በጣም ደስ ይላል ❤️❤️❤️❤️የሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ፈውስ እንዳደረገልህ ስትናገር ሰምቻለሁ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን ቀሪ ዘመንህን ለታደገህ ጌታ እየዘመርክለት በቤቱ ዘመንህን ጨርስ🥰🥰🥰🥰
በጣም ከገረመኝ ነገር በጣም በጣም ኩሩ ነው ወደድኩት አቦ ነገ የሱ ነው እየዞረ በኢትዮጵያ ላይ መርዳቱን ይቀጥላል ቶሎ ማረፊያውን አስቀድሙለት ፡፡
እያለቀስኩ ነው የሰማሁት 😢😢😢ስደት አይኑ ይጥፋ እንኳን እግዚአብሔር እረዳህ እንኳን ጌታ ኢየሱስ ፈወሰህ አነሳህ ሁሉ ለበጎ ነው እንኳን አየከው የእግዚአብሔር እጅ ደግመህ ግን እንዳትዘፍን እድሜ ለሰጠህ ጌታ ዘምርለት ❤❤❤❤ ከቤትህ ደስታ አይጥፋ በኢየሱስ ሰም
ሰይፍ ያልተነገረለት መልካም ሰው ነው አሊክስ ግን እግዚአብሔር እንኳን ለሀገሩ አበቃክ🙏🙏
I’m so pleased to see you again Alex. እንኩአን አላህ ለሀገርህ አበቃ
ወንድሜ አለማየሁ እግዚአብሔር እንኳን ለሃገርህ አበቃህ! ግን እግዚአብሔር በተቀጠልህ አድሜ እርሱ የሚከብርበትን እና ደስ የሚሰኝበትን ነገር አድርጎ ማለፍ ይሁንልህ
ክብር ሁሉ ለእግዛብሔር ይሁን! ኣሜን። እንኳን ለዚህ አበቃህ አሌክስ !!
ሰይፋ ተባረክ አሌክስ እንኳን ደህና መጣህ በጣም ነው የምወድህ
ይገርማል የነዚህ ምርጥ ሙዚቃወች ባለቤቱ አልሞተም መሻአላህ ወላሂ ማን እደሆነ አላቅም ነበር ግን እወዳቸዋለሁ ብዙ እጠብቃለን ጋሸ ከአንተ
አሌክስ ልዩ ተሰጥኦ ያለው ድንቅ ድምፃዊ ነው። እግዚአብሔር ይመስገን እንኳንም በህይወት ተርፎ አይኑን ለማየት አበቃን።
የኢትዮጲያ አርቲስቶች ግን መቼ ነው ለሰይፉ ትልቅ ምስጋና የምታቀርቡት ? የምስጋና ፕሮግራም ማዘጋጀት አለባችሁ ። እኔ የሚመስለኝ የሰይፉ በጎነት በቀልድ ተሸፍኗል !!! ሰይፉ ከነቤተሰቦችህ ፈጣሪ ይጠብቅህ
❤
I have never seen seifu being emotionally original like this. I saw the morality of Alex on seifu eyes. Astounding friendship.
ሰይፉ ፈጣሪን እናመስግን።
አላህ ለሀገሩ ስለበቃው ምስጋና ይገባዋል ትልቅ ምስጋና።
ሰይፋ እግዚአብሔር ይባርክህ 😢😢😢 ዘመንህ ይለምልም❤ ከድንኳንህ ከቤትህ ደሰታ አይጥፋ ስደትን ያየው ያውቀዋል 😢😢 በልጆችህ አግኘው ይህን ስፅፍ እያለቀስኩ ነው አሰብኩት ያሳለፈውን ምጥ ሆድ ይፍጀው ብሎ እንጂ 😢😢😢 ጌታ ለክብሩ ያቁመው ❤❤❤
በመጀመሪያ የአሌክስንና ጎሳየን ሙዚቃዎች እና የ90ችን ስሰማ በጣም ትዝታ ውስጥ ነው የምገባው ሲቀጥል አልክስ 19 ዓመታትን ያሳለፍቸው ቸግሮች በጣም ያሳዝናል ፈጣሪ እንኳን ከዚህ ሁሉ አወጣክ EBStv ለምትሰሩት መልካም ስራ ፈጣሪ ይስጣቹ ሰይፉም እግዚአብሄር ይስጥህ፡፡ ነገር ግና አሌክስ እንዳለው እግዚአብሄር ሁለተኛ እድል ሰቶኛል እንዳልክ የሰጠህ እድል እግዚአብሄርን ለማገልገል ሊሆን ይችላልና ደግመህ ወደ ዘፈን ባትገባ ደስ ይለኛል ሰይፉም እትወስወሰው እንዲዘፍን መዝሙር ወይም ሌላ ነገር ቢሰራ ደስ ይለኛል፡፡
እሌክሶ እንኳን እግዚአብሔር ለሀገርህ አበቃህ እኩያየሆነ ልጅ አድርስሀል ልጆችህ የልጅ ልጆችህ ይባረኩልህ ቀሪ ዘመንህ ይባረክ 🙏🏾❤️በጣም ደግ ስው ነህ ሀገርህን ስለምትወድ እኛም እንወድሀለን❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
የማይረሳ አሁንም ቢሰማ የማይሰለች አሌክሰ እንወድሀለን እድሜ ጨምሮ ይሰጥህ እንኳን ሀገርህ ገባህ እሰይ
ፀበል ብትሄድ በጣም ጥሩ ነው ከእግዚአብሔር ጋር መምጣትህ በጣም ደስ ይላል
እንኳን ወደ ሀገርህ በሰላም መጣህ!! በጣም ነው ሙዚቃዎችህን የምወዳች❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉
አሌክሶ እንኳን ደህና መጣህ።
ኢቫንጋዲ ከምንጊዜም ምርጡ አልበሞች አንዱ ሳልሰማው አልውልም።
አሌክሶ እንወድሃለን !
በጣም የምወደው ዘፋኝ አለማየሁ ሂርዾ ❤ ለምን እንደሆነ አላውቅም ዘፈኖቹ ልቤ ውስጥ ዘልቀው ይገባሉ ዘፈን መስማት አአልፈልግም ግን የሱን ዘፈኖች still እሰማለው ለእኔ አንደኛ ነው🫶እና በሰላም ሀገርህ ስለገባህ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል🙏
ኖሮውይ እና ሲዊዘርላንደ ብዙ ኢትዬጵያዊያን ያለ መኖሪያ ፍቃደ ይኖራሉ።እኔም እግዚአብሄር እረደቶኝ በ9 አመቴ ወረቀት ባገኝም።በዚህ ዘመን ያሳለፍኩት ቸግር እግዚአብሄር ብቻ ነዉ የሚያዉቀዉ።
ሰደት አይኑ ይጥፋ።
@@negussiebekele4138 እውነት ነው ስድት አይኖ ይጥፋ
እኳንም አላህ እረዳህ😢😢😢😢😢😢😢
የእውነት በሳቅ እና በእንባ ነው ያዳመጥኩህ በጣም ነው ያሳዘንከኝ የ90ዎቹ ምርጥ ድምጻዊ አሌክስዬ 1995 የክርስቶስ ፍቅር ያልገባኝ ግዜ እና በጣም ልጅ የነበርኩበት እድሜ ስለነበረ እኔም ሙዚቃዎችህን በፍቅር አዳምጣቸው ነበር እና ባጭሩ ማለት የምፈልገው እግዚአብሔር በድጋሚ እንድትኖር እድል የሰጠህ ለእራሱ አላማ ፈልጎህ ነውየአለም ጭብጨባ እና የአለም አድናቆት ብዛት እንድትኖር እድል ከሰጠህ ከእግዜአብሄር ጋር ሊያለያይህ መሆኑ በጣም አዛዝኖኛል አሌክስዬ አለም ትበቃሀለች ጓደኛችህን ከሞት እና ከሲኦል አላዳነቻቸውም እግዚአብሔር ማስተዋልን ይስጥህ እግዚአብሔር ወደ እራሱ ሀሳብ ይመልስህ አለም ልትገድልህ ልታጠፋህ አሸብርቃ አሰፍስፋ እየጠበቀችህ ነው እግዚአብሔር ማስተዋልን ይስጥህ ።ወዳጆችህም በህይወት እግዚአብሔር ስላተረፈህ እድሜን ለጨመረልህ ፈጣሪ የቀረህን ዘመን እርሱን አገልግል ከማለት ይልቅ አለም ላይ የዲያቢሎስ አገልጋይ እንድትሆን እያበረታቱህ ነው እግዚአብሔር ይጠብቅህ ዝናም አለምም ገንዘብም ሁሉም ጠፊ ነው ከማይጠፋ ከእግዚአብሄር መንግስት እንዳትጎድል እርሱ እግዚአብሄር ማስተዋልን ይስጥህ አሌክስዬ❤
አልዬ የምር የደስታን እንባ አነባሁ ስላየሁህ ድምፅህ ዘፈኖችህ ለረጂም ግዜ ነገሮቼን እረሳባቸዋለሁ ደሞም ሁሉ ነገሮችህ አወራርህ መልክህ አባቴን ቁጭ ድንግልን ብቻ እንኳን ለሀገርህ ለወገንህ ለልጆችህ አበቃህ መልካምነትህን ደግነትህን ብዙ ወዳጅ ጓደኞችህ አልፈው በህይወት ከብዙ መከራ መትረፍህ ምስክር ነው የኔ አባት እድምዬን ቀንሶ ለአንተ ይስጥህ 1000 አመት ያኑርህ የኔ ደግ ሰው።
አጎቴ ድሮ ስደት ስድነት ነው ጠንክረህ ተማሪ እያለ ይመክረኛል ራሽያ ለአብራሪነት ሥልጠና ለ5 ዓሜት ከ7ወር ተምሬ ስመረቅ ብዙ ሀገሮች መሄድ ይችል ነበር ግን ስደት ስድነ ነው ብዬ እምብ ብዬ ሀገረን በአየር ኃይል አብራርነት እያገለገልኩ ነው ማን እንደ ኢትዮጵያ
❤ man ede hager wedajae
Hero❤
አዎ ማን እንዳገር ሀገር🙏🥰
ጀግና
አሁን ስንት ንፁሃን አማራ ገድለሃል?
እንኳን ለ ዚህ አበቃህ ወንድሜ! አስራዘጠኝ አመት በመከራህ ዉስጥ አብሮህ ከሞት መንጋጋ አውጥቶህ ያልተለየህን የብፅእት፣የቅድስት ድንግል ማርያምን ልጅ ቸሩ መድሃኒአለምን አትለየዉ ዘፈን ሃጢያት ነዉ። ሞትን ይዘህ ከ አገርህ ተሰደድክ ሞትን አራግፈህ በክርስቶስ ፀድተህ ስትመለስ ሞትንተመልሰህ አትጣጨብጣት ወንድሜ!አስራ ዘጠኝ አመት ሙሉ ዘፈን አላኖረህም ወይሞ ጓደኛ
ተባኖባችሗል - ምቀኞች - አስመሳዮች - የጥበብ ጠላቶች ። የሙሉቀን አይበቃችሁም - የነካችሁት ሁሉ ...
አሌክስ እንክዋን ለ ሀገርህ አብቃህ
ግን ደግሞ የ ኅዋላህን እየረሳህ ወደ ፊት መዘርጋት አለብህ ❤️ ያ ጌታ ከ ሙታን መሃል ያነሳህን እድሜ የጨመረልህን ይሄን ጌታ ትተህ ዳግመኝያ ወደ ቀድም ህይወት እንድትመለስ ዲያብሎስ በ ደጅህ እያደባ ነዉ ፈጥነህ ንቃ እንቢ በል ከ ሙታን መንደር ያወጣህ ጌታ አየሱስ ነዉ በ ዙርያህ ተሰብስበው ወደ ቀድሞ ህይወትህ ሊከቱህ እያየህ ነው ወዳጄ ሂወት ይሻልሃል ❤ ሰው አልምን ሁሉ ቢያተርፍ ነብሱን ግን ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል ይላል የ እግዚአብሔር ቃል
ማንንም አትስማ ከ ጌታ በቀር መች በ ፈርድ ቀን በጌታ ፊት እንደምትቆም አታቅም ተዘጋጅተህ ቁም እወድሃለው ጌታ እየሱስ ይርዳህ 🙏🙏🙏
እግዚአብሔር ይመስገን እድለኛ ነህ አንተስ ስምና ዝና ስላለህ ጥሩ ተቀበሉህ እደለኛ ነህ ስቱ በወጣበት ቀረ ስቱ አሁንም ምን ይዤ ልመለስ እያለ ቢመለሱም መግቢያ የለለው ስቱ ቀረ አሌክስዬ አንተ በጣም እድለኛ ነህ እንኳን ላገርህ አበቃህ
እውነት እግዜአብሔር ይመስገን የኔ ጌታ መልካም አባት ነው በስደት የምትሰቃዩ እግዜአብሔር ለሀገራቹ ያብቃቹ እግዜአብሔር ተስፋ እናድርግ ሁላችንም አያሳፍረንም ክብሩ ይስፋ!!!