🔴የዛሬው ይለያል😱😱👉ማህሌቱ ደምቋል ❤️እእእእልልልልልልል🔵👉 እንዳያመልጣችሁ 📌😍 ኑ የሰማዕቷን በረከት ተካፈሉ❗️❗️

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 25 гру 2024
  • ታህሳስ 6 በዚህች ቀን ታላቋ ሰማዕት የቅድስት አርሴማ ዓመታዊ በዓሏ ነው፤ ይህም ቅዳሴ ቤቷ የተከበረበት ነው ...በዚህም ቀን ታላላቅ ተአምራቶች ተደርገዋል፤ በተለይም ይህ ቀን በአገረ አርማንያ ልዩ ስፍራ አለው፤ በመዲናችን አዲስ አበባ አስኮ ቃሎ ተራራ ላይ ግሩም ቤተክርስቲያን አላት ታዋቂው ገዳሟ ግን ወሎ ሲሪንቃ ይገኛል። መስከረም 29 በሰማዕትነት ያረፈችበት ነው፤ እነዚህን ሁለቱን ቀናት ቤተክርስቲያን በደማቁ ታከብራቸዋለች፤ሌላው በዛሬው ቀን ታላቁ አባት አብርሃም ሶርያዊው ያረፈበት ቀን ነው፤ ይህ አባት ተራራን ያፈለሰ ነው፤ ታሪኩ ወዲህ ነው አባ አብርሃም የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ በነበረበት ወራት አንድ አይሁዳዊ ወደ ንጉሱ ገብቶ እንዲህ ይለዋል “እነዚህ ክርስቲያኖች የሚገርሙ ናቸው በወንጌላቸው ላይ የሰናፍጭ ቅንጣት እምነት ካላችሁ ይህንን ተራራ ተነቅለህ ወደዚያ ሂድ ብትሉት ይሆንላቹዋል ይላል፤” ይህ የሐሰት ወንጌል ነው፤ከመካከላቸው ይህን የሚያደርግ አንድስ እንኳን የለም ይለዋል” ንጉሱም አባ አብርሃምን አስጠርቶ “በእርግጥ ወንጌላችሁ እንዲህ ይላልን ?” ይለዋል አዋን ንጉስ ሆይ ብሎ ይመልስለታል፤ ታዲያ የክርስቲያኖች ሁሉ አባታቸው አለቃቸው አንተ ነህ እስኪ አድርግና አሳየኝ ይለዋል፤ እሺ ግን 3 ቀን ብቻ ይስጡኝ ብሎ ወጣ፤ ጨነቀው ወደ እምቤታችን ቤተክርስቲያን ገብቶ 3 ቀን 3 ሌሊት እህል ሳይበላ ውኃ ሳይጠጣ አለቀሰ፤ እመቤቴ አታሳፍሪኝ አላት፤ ተገለጸችለት ይህ ላንተ አይሆንም ግን ወደ ከተማ ውጣ በእንስራ ውሃ ተሸክሞ የሚሄድ ሰው ታገኛለህ፤ ስሙ ስምዖን ጫማ ሰፊ ነው፤ አንድ አይና ነው፤ አንዱን አይኑን ያጠፋው የልጄን ትዕዛዝ ለማክበር ብሎ ነው፤ ለእርሱ ይቻለዋል እርሱ የሚልህን አድርግ ትለዋለች፤ እንደተባለውም ስምዖንን ያገኘዋል፤ ነገሩን ሁሉ ይገልጽለታል፤ እሺ ለማንም ስሜንም ስራዬንም እንዳትገልጽቢኝ፤ ህዝቡን ሰብስብ እኔ በተሰወረ ቦታ ሆኜ የማሳይህን እየተመለከትክ አድርግ አንተ የምታደርገውን ደግሞ ህዝቡ ያድርግ አለው፤ ንጉሱም ሰራዊቱም ህዝቡም ይህንን ታአምር ለማየት ተሰበሰበ፤ 41 ጊዜ ኪራላይሶን ብለው ሶስት ጊዜ ሰገዱ፤ ከዚያም አባ አብርሃ ስምዖን የሚያሳየውን እየተከተለ መስቀሉን አውጥቶ ወደ ተራራው አማተበ፤ ተራራው ወደ ላይ ተነሰ፤ ታላቅ ፍርሃት ሆነ፤ ሶስት ጊዜ ተራራው ወደ ላይ እየተነሳ ይቀመጣል በተራራው ስር ከወዲያ ማዶና ከወዲህ ያሉ ሰዎች ይተያዩ ነበር ይላይ፤ ንጉሱም ህዝቡም እጹብ እጹብ አሉ ምስጉን እግዚያብሔርንም አመሰገኑ፤ ንጉሱ ክርስቲያን ሆኖ ተጠምቋል ብዙ አብያተክርስቲያናትንም አንጿል። አባ እብርሃምም ተፈርቶና ተከብሮ በቅድስናም ኖሮ በዛሬዋ እለት አርፏል። ከቅድስት አርሴማ፤ ከአባ አብርሃምና ከስምዖን ጫማ ሰፊ በረከታቸውን ያድለን !!! አሜን
    🔵👉🔴ቻናላች Subscribe , like , share ማድረግ እንዳትረሱ ❗️
    ይቆየን ።

КОМЕНТАРІ •