@@biremusicit’s usually ppl who enjoy living in sin who likes to take Gods grace for granted be hatyat mewdekena hatyaten eyatatamu menor yeleyayal if u enjoy sinning ur not from God as John predicted keled adelem yefsesew dem
He is not wrong, you can read Hebrews 3,6,10,12 and 2 Peter 2, unbelief can lead to someone forfeiting their salvation. Especially Hebrews 3:7-19 & 6:4-8 shows this. I think he could've said that willful sin can lead to unbelief but he said it mostly correct. Blessings.
Just remember what happened to the People of Israel. God promised them the Promise land. However, they don't listen and obey his words, they ended up in desert. Same analogy applied for z believers, if we don't lived here on earth accordingly, we definitely lost our salivation. Do Not Deceived!! When you doing the sin you are going to be on the list of the sinner unless you repent truly, and never do same sin. Believing in Jesus doesn't mean you have a license to do whatever you like on this earth. You should crucify your body with Christ then you inherit the kingdom of God. Don't decived. Remember God is holy & his kingdom reject unholy being. Careful, do not Deceived brothers and sisters. We have to disciplined and change our heart and life. The HOLYSPIRIT is here to help us in the process. Ask him a grace a power, he will do it, but don't expect to rip what you don't saw. God is Just!!
Please read and study the word of God by taking time. If you try to mention the verses from the Bible with out the context and try to promulgate any doctrine,that may lead people to destruction.
እግዚአብሄር በደህንነት መዝገብ ላይ አንዴ ከፃፈን በኃላ ስርዝ ድልዝ መዝገብ የለውም የሚል ትምህርት ተምሬ ተቀብዬው ነበር። አሁን እንደገባኝ ከሆነ ግን በደህንነታችን ካልፀናን ልንሰረዝ እንችላለን ምክንያቱም በእብራውያን ፀሀፊ እንዲህ ያለውን መዳን ቸል ብንል ወዴት እናመልጣለን ይላል so በአዳነን ጌታ ፀንተን መኖር አለብን። ልጆች ሆይ ማንም አያስታችው አመንዝሮች ቢሆኑ፣ ሌቦች፣ተሳዳቢዋች መንግስቱን አይወርሱም ተብለናል ስለዚህ የጨለመውን አለም ብርሃን ሊያደርግ ወደመጣ ጌታ ተጠግተን እለት እለት ወደሱ ማደግ እንጂ አፈግፍጎ መዳን የለም ጨው አልጫ ቢሆን በምን ይጣፍጣል? እኛ ጨው ካልሆንን ወደ ውጭ መጣላችን አይቀሬ ነው ጌታ ሆይ በድካማችን ታላቁ መንፈስህ ብርታት ስለሚሰጠን ተመስገን ሁሉ ባንተ በሆነው ጌታ ተማምነን እንጓዝ ዘንድ እርዳን ተባረኩ ወንድሞቼ።
እንግዳውስ አንተ በክርስቶስ ደም ላይ እየተራመድክ ነው።
መጀመሪያም በአንተ ፅድቅ አልዳንክም በአንተ ድካምም አትጠፋም።
ዋናው ነገር የእውነት የዳነ ሰው ሀጢያትን ደጋግሞ አይሰራም ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ በውስጡ ስላለ ።
@@solomonyiheyis1623 እኔ የዳንኩት በስራዬ ነው የሚል በፍፁም አልፃፍኩም ሰው የዳነው 100% በእየሱስ ክርስቶስ ስራ ብቻ ነው ነገር ግን እምነት ስራ አለው ገላትያ 5 ተመልከት የስጋን ስራ እየሰራህ ድኛለው ብትል እንዴት ይሆናል???
@@sebelleteferaminas9875 ሰብለ እህቴ በውይይት በማመንሽ ደስ ብሎኛል ።
ገላትያ 5 ላይ የሚናገረው ስላልዳኑ ሰወች ነው የሚያወራው ።
ዝቅ ብለሽ ቁጥር 22 ስታነቢው ስለመንፈስ ፍሬ ነው የሚያወራው ስለዳኑ ሰወች ያ ደግሞ እለት እለት በአይምሮ በመታደስ ነው የሚመጣው ምክንያቱም የነፍስ መዳን በሂደት ነው ።
ቆሮንጦስ ላይ ብትሄጂ ያንን ሁሉ ሀጢያት ሲያደርጉ ጳውሎስ በስጋቸው እንደሚያጭዱ አተኩሮ ሲናገራቸው እናያለን እንጂ መዳናችሁን ታጣላችሁ ሲላቸው አናይም።
ይሄን ስልሽ ድኛለሁ ብየ የማያቋርጥ ሀጢያትን ባደርግ እስከሞት የማደርስ ቅጣትን እንደምቀጣ ቃሉ ይናገራል በምድር ያሉ በረከቶችን ጨምሮ በዙ ነገር ላጣ ችላለሁ ቃሉም ህያው ሆኖ አይሰራብኝም።
ግን Please ይሄ ከመዳናችን ጋር አይገናኝም መዳናችን ዋጋው ትልቅ ነው ደም ነው የፈሰሰው ያውም ንፁህ ደም ።
አይደለም በሰማይ በምድር ራሱ መዳኔን ሳስበው ኩራት ይሰማኛል ።ምንግዜም መዳንሽን እንድትጠራጠሪ ከሚያደርጉሽ አገልጋዮች ራቂ። ሻሎም 🙏
እግዚአብሔር ይባርክህ
ጥልሻ !!!❤❤❤
ወንድሜ አገልጋይ ጥላሁን ጌታ ከእነኝህ ሃስተኛ ነብይት ፣ሐዋርያት ፣ ወንድሞች ጌታ በደሙ ይሽፍንህ
የዘመናችን ጵውሎስ ነህ
መስቀሉን ፣ ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ስለምታስተምር በክርስቶስ ፍቅር እወድሃለሁ ብዙ ተጠቅማለሁ
ቀኖቹ ፣ ዘመኑ ክፍ ነው
አንተ ግን በጌታ በርታ
ከሰው. ፣በስው አልተቀበልክም ከራሱ ከክርስቶስ ነው
ምልክቱም ክርስቶስን መስቀሉን ብቻ ስለምታስተምር
በርታ ፅጋው ይብዛልህ
ጥልዬ ዘመንህ ይባረክ
ተባረክ ነብይ ጥሌ በብዙ ይብዛልህ
መንፈስ ይረክሳል ትክክል ነህ
የቱ ጥቅስ ነው ታሽጉል የሚል ግምታቸውን ነው የሚናገሩት
በጣም በብዙ ይብዛልህ ይስፍልህ ባንተ ብዙ ተጠቅሜአለው ።
ሰው ክርስትናን መኖረና ማስተማር ሲያቅተው ነው ስጋና መንፈስን ለያይተው የሚናገሩት እየሱስ ልክ እንዳተ ሰው ቢበራለት እንኮን ሀጥያት ሊሰራ ተሰውቼ እንዳባቶቼ በሄድኩ ነበረ የሚለው ትክክለኛ ወንጌልህ ይብዛልን
ጌታ ይባርክህ ።
አንተ ምርጥ አስተማሪ ነክ በቆምክበት መድረክ ሁሉ ክርስቶስን በሙላት ነው የምትገልጠው ግን ዋና መሠረቱን ጣልክ ሰው በጌታ ኢየሱስ አምኖ ከዳነ በኃላ ደህንነቱ አይወሰድም ምክንያቱም ከማይጠፋ ዘር ተወልዳችኃል ይላልና ይንን መልሶ ማየት መልካም ነው
ጥላሁን ብልጥ ሰባኪ
1. ጥቅስ በትክክል ቢጠቀስ። ፣ ሃሳባችንን እንዲደግፍልን ባንጠመዝዘዉ። ዮሐንስ ያለዉ የወጡቱ መጀመሪያም ከእኛ ወገን አልነበሩም ነዉ።
1ኛ ዮሐንስ 2 : 19፤ ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ።
2. ዝሙት የሰሩና፣ በጌታ እራት በorgy ያላገጡ የቆሮንጦስ አማኞች እንኳ ከዓለም ጋር እንዳይኮነኑ ሆነዉ በጌታ ተገሰጹ (በህመም፣ በድካምና በሞትም ጭምር)፣ እንጂ ድነታቸዉን አልተነጠቁም። 1 ቆሮ 11፡30-32
3. የእግዚአብሄርን መንግስት መዉረስ በሥራ (በማድረግና አለማድረግ) አይደልም። አሊያ በዛዉ አካሄድ ገላትያ 5 ላይ አብሮ የተጠቀሱት ጥልና ክርክርም የእግዚአብሄርን መንግስት እንዳንወርስ ያደርጋሉ ልንል ነዉ።
ክፍሉ በክርስቶስ ስላይደሉ ሰዎች መገለጫ ነዉ የሚያወራዉ እንጂ፣ በክርስቶስ የሆኑቱ ስለሚገጥማቸዉ ድካምና በዛም ምክንያት ድነታቸዉ ስለመጥፋቱ አይናገርም።
ድነታችን የማይጠፋዉ፣ ከማይጠፋዉ ዘር ስለተወለድንና፣ በጉዞ መሃል ድካም ቢኖር እንኳ ክርስቶስ ራሱ የሚታይልን የአዲስ ኪዳን መካከለኛ /ወይም ሊቀ ካህናችን ስለሆነና፣ ጸጋዉ ለፍጻሜ ስለሚያበቃን ነዉ።
እሺ አይጠፋም so what እና ምን ይጠበስ?
እኔ ሚገርመኝ እኮ ይሄ የሚናገረው እራሱንም እንደሚመለከት አለማስተዋሉ ነው ፡ሰው ሀጥያት ስለሰራ ከህይወት መፅሃፍ የሚሰረዝ ከሆነ መጀመሪያ የሚሰረዘው ይሄ ሰውዬ ነው ምክንያቱም እሱም ሀጢያት ስለሚያደርግ።አይ እኔ ሀጥያት የለብኝም ካለ ደሞ እራሱን ያስታል።ብዙ የኢትዮጵያ አገልጋዮች ላይ የሚታየው ትልቁ ችግር ጥቅስን ያለ አውዱ የመጥቀስ ችግር ነው። እንዲህ አይነት ሰዎች ያልገባቸው ነገር የዳነ ሰው ከህይወት መፅሃፍ ላይ እንደማይሰረዝ ብቻ ሳይሆን እንደው ቢሰረዝ እንኳን ተመልሶ አይፃፍም ምክንያቱም የተፃፈው አንዴ በተደረገ መስዋት ነው ።ሰለዚህ እንደገና ለመፃፍ ክርስቶስ እንደገና መሰቀል አለበት ይህ ደግሞ አይሆንም። ያባቱን ሚስት ያገባው ሰውዬ እንኳን ነብሱ በጌታ ቀን ድናለች።ምክኒያቱም መጀመሪይም የዳነው በእምነት እንጂ በስራ ስላልሆነ።1 Corinthians 5 (አማ) - 1 ቆሮንቶስ
1: በአጭር ቃል በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ይወራል የዚያም ዓይነት ዝሙት በአሕዛብስ እንኳ የማይገኝ ነው፥ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው ይኖራልና።
2: እናንተም ታብያችኋል፤ ይልቅስ እንድታዝኑ አይገባችሁምን? ይህን ሥራ የሠራው ከመካከላችሁ ይወገድ።
3-4: እኔ ምንም እንኳ በሥጋ ከእናንተ ጋር ባልሆን፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፥ ከእናንተም ጋር እንዳለሁ ሆኜ ይህን እንደዚህ በሠራው ላይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሁን ፈርጄበታለሁ፤ እናንተና መንፈሴም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ጋር ተሰብስበን፥
5: መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው።
@@biremusicit’s usually ppl who enjoy living in sin who likes to take Gods grace for granted be hatyat mewdekena hatyaten eyatatamu menor yeleyayal if u enjoy sinning ur not from God as John predicted keled adelem yefsesew dem
4 አውቄዋለሁ የሚል ትእዛዛቱንም የማይጠብቅ ውሸተኛ ነው እውነትም በእርሱ ውስጥ የለም።
5 ቃሉን ግን የሚጠብቅ ሁሉ በእርሱ የእግዚአብሔር ፍቅር በእውነት ተፈጽሞአል። በእርሱ እንዳለን በዚህ እናውቃለን፤
6 በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደ ተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል።
5 ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት፡- እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።
6 ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም፤
ይህ ሰው በጣም ትክክል ነው
You're blessed,!
አዳም ህያው ነብስ ነው ፤ እየሱስ ህይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው ፤
ጌታ ይባርክህ
ነብይ ጥሌ እግዚአብሔር ዘመንህን ይበክህ ስው እንድምውዳ ግን ያቃዋል እንዴ ወንጌልን ስስብክ ሁለም አድስ እሆነለው ድገግሜው እስመ ነበር በአንቴ ክርስቶስን አያሁብ
ግሩም ማብራርያ ነው የተወደድክ ጥሌ የሠው ሁለንተናን የገለጥክበት መንገድ
የሰው ሁለንተና
1መንፈስ
2 ነብስ
3 ስጋ
ነው።
በዘመናችን ላለው የነብያት አገልጋዮች
ነብይነት
የእግዚአብሔርን ቃል በግልጠት ከማወቅ ይጀምራል።
ቃል የሌለው ትንቢት ወሬ ነው
የሰውን ስም ስልክ ቁጥር በመጥራት ሰው ነብይ ሊባል አይችልም።
የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ።
በጣም ያሳዝናል ስለ እየሱስ ክርስቶስ በዚህ ልክ ከሚያስተምር ሰው የማይጠበቅ ነገር ነው የተናገርከው ነብይ ጥሌ የደሙን ጉልበት እና የመስዋዕቱን አቅም ምን ያክል እንደሆነ ሳትረዳ ነው ማለት ነው ያንን ሁሉ ትምህርት ያስተማርከው? መፅሐፍ ቅዱስ እኛ እንደፈለግነው የምንተረጉመው መፅሐፍ ሳይሆን በተፃፈበት አውድ መሰረት ልንተረጉመው የሚገባን መፅሀፍ ነው። የዘላለም ህይወት የሀጥያታችን ስርየት ሲሆን ሊገኝም የሚችለው በበጉ ደም ብቻ ነው ምክንያቱም ደም ሳይፈስ ስርየት የለምና። ህግን በመጠበቅ ሊፀድቅ የሚችል እኮ ማንም ስለሌለ መሰለኝ ክርስቶስ የመጣው(የማይጠፋ ዘር) የተባለው ታድያ ከማይጠፋው ዘር ተወልደናል ብለህ ስታበቃ በዛው አፍህ ዝሙት ከሰራሁ እጠፋለሁ።? ከፈለክ እኮ መጥፋት ትችላለህ የንፁሁን በግ የክርስቶስ እየሱስን ዋጋ አታቅልልብን መስዋዕቱ ትልቅ ነው አንተ የእየሱስን ደም ከዝሙት እኩል ብታሰልፈውም ደግነቱ አብ በመስዋዕቱ አንዴ ረክቶአል ከእንግዲህ ለሀጥያት የሚቀርብ ምንም መስዋዕት የለም !!!!!!!!!!!!
“አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና።”
- ዕብራውያን 10፥14
@@ArtistBiniyamTadesse ወዳጄ የልቤን ተነፈስክልኝ ። ሰውየው ስለ እየሱስ ብዙ ይናገራል ግን መልሶ ኔጌቲቭ አስገባው ያሳዝናል በጣም።
Mathew's 7 :21 gelatia 5:20 and 6:7 qolasias 3:13
Ynebeb
የዕብራውያን መልእክት ወደኃላ የመመለስ ውጤት የማስጠንቀቂያ ደወል ነው።
Geta yebarkachehu
ጥሌ ይሄን የቤተክርስቲያን አፍራሽ የሰይጣን ትምህርት አፍርሰው።ጌታ ይባርክህ።
እንግዲህ ፀጋ እንዲበዛ በሀጢያት ፀንተን እንኖርን ይላል ሮሜ 6:1ስለዚህ በሀጢያት ፀንቶ መኖር ይቻላልን?
ነብይ ጥላሁን ንስሀ ግባ ....አንዴ የዳነ ሰው ደህንነቱን አያጣም በራሱ አንደበት *ክርስቶስን ካልካደ በቀር * ሰው በድካሙ በምድር ላይ ይቀጣል እነጂ ድነቱን አያጣም ምክንያቱም መጀመሪያም በርሱ ፅድቅ ስላልዳነ።
ዘፍጥረት 1:26 ላይ እግዚአብሔር በራሱ መልክ የፈጠረዉ ሰዉ እሱ አዳም ነዉ ትላለህ? ያ ሰዉ ነዉ መንፈስ። ይህም ኋላ በአዳም አፍንጫ እፍ በተደረገ በፈጣሪዉ ትንፋሽ ህያዉ ነፍስ ያለዉ ሰዉ እንደሆነ በምዕራፍ 2:7 ተገልጿል። በአንደበተ ርቱዕ የቋንቋ ዕዉቀትና ከተሜነት በመጠቀም የቃሉን መገለጥ መሰወር አይገባም። በዚህች ዓለም የለቀምነዉ ለአእምሮ የሚሆን መረጃ ተጠቅሞ ቃሉን ይበልጥ መግለጽ የሚገባ ይመስለኛል። እኔ ግን በስብከት ሞኝነት ብቻ ሳይሆን በእዉነተኛ የእግዚአብሔር ቃል መገለጥ የማምነዉ መንፈስ መሆኔን ነዉ።
ወንጌል ለነፍሳት መዳን እና ለመከናወን ይሁን።
እኔ ሚገርመኝ እኮ ይሄ የሚናገረው እራሱንም እንደሚመለከት አለማስተዋሉ ነው ፡ሰው ሀጥያት ስለሰራ ከህይወት መፅሃፍ የሚሰረዝ ከሆነ መጀመሪያ የሚሰረዘው ይሄ ሰውዬ ነው ምክንያቱም እሱም ሀጢያት ስለሚያደርግ።አይ እኔ ሀጥያት የለብኝም ካለ ደሞ እራሱን ያስታል።ብዙ የኢትዮጵያ አገልጋዮች ላይ የሚታየው ትልቁ ችግር ጥቅስን ያለ አውዱ የመጥቀስ ችግር ነው። እንዲህ አይነት ሰዎች ያልገባቸው ነገር የዳነ ሰው ከህይወት መፅሃፍ ላይ እንደማይሰረዝ ብቻ ሳይሆን እንደው ቢሰረዝ እንኳን ተመልሶ እንደማይፃፍ ነው ምክንያቱም የተፃፈው አንዴ በተደረገ መስዋት ነው ።ሰለዚህ እንደገና ለመፃፍ ክርስቶስ እንደገና መሰቀል አለበት ይህ ደግሞ አይሆንም። ያባቱን ሚስት ያገባው ሰውዬ እንኳን ነብሱ በጌታ ቀን ድናለች።ምክኒያቱም መጀመሪይም የዳነው በእምነት እንጂ በስራ ስላልሆነ።1 Corinthians 5 (አማ) - 1 ቆሮንቶስ
1: በአጭር ቃል በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ይወራል የዚያም ዓይነት ዝሙት በአሕዛብስ እንኳ የማይገኝ ነው፥ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው ይኖራልና።
2: እናንተም ታብያችኋል፤ ይልቅስ እንድታዝኑ አይገባችሁምን? ይህን ሥራ የሠራው ከመካከላችሁ ይወገድ።
3-4: እኔ ምንም እንኳ በሥጋ ከእናንተ ጋር ባልሆን፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፥ ከእናንተም ጋር እንዳለሁ ሆኜ ይህን እንደዚህ በሠራው ላይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሁን ፈርጄበታለሁ፤ እናንተና መንፈሴም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ጋር ተሰብስበን፥
5: መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው።
እኔ እንደሚመስለኝ መዳን እንደዜግነት ነው ዜግነትን ለመነጠቅ በሃገር መክዳት ወንጀል መሳተፍን ይጠይቃል መዳንን ለማጣትም መንፈስ ቅዱስን የሰደበ ሰው ብቻ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ ይኸውም ኢየሱስን አለመቀበል ማለት ነው ጌታ ይህንን ያለው አጋንንትን የሚያስወጣው በቡኤልዜቡል ነው ስላሉት ነው ይህንን የሚል ደሞ መጀመሪያም ድንአል ማለት አይቻልም ያንድ ሃገር ዜጎች ዜግነትን የማያስነጥቅ ብዙ ወንጀሎች ይፈፅማሉ እንደወንጀላቸውም ይቀጣሉ ሰማያዊ ዜግነት የተሰጠንም እኛ በተመሳሳይ የተለያዩ ሃጢያቶች ሰርተን እንገኛለን ሂሳብም እናወራርዳለን እኔ እራሴ ለሃያ ምናምን አመት ከአምልኮ እርቄ ያሻኝንሳደርግ ቆይቼ ሂሳቤን አወራርጄ ተመልሻለሁ
@@biremusic ትክክል ...ባለማወቅም ይሁን በአጉል ኩፈሳ በክርስቶስ ደም ላይ ነው የቀለደው ያሳዝናል
ከዳንን በኃላ ፍሬ ይጠበቃል እራሳችንን እያታለልን ሲኦል እንዳንገባ እንጠንቀቅ::ከስራ የተለየ እምነት የሞተ ነውም ይላል ቃሉ:: እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎቼ ናችው:: ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል እነሱም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉአቸዋል ብሎአል ጌታ እራሱ:: ስለዚ ፍሬ የማናፈራ ከሆነ ሺ ጊዜ ለምን አናምንም እንቆረጣለን ከሕይወትም መፀሐፍ እንደመሰሳለን:: ስለዚ ማመን ብቻ አያድንም:: አሁን አሁን መስመሩን የሳተ ፍሬ አልባነትን የሚያበረታታ ና የሚያዘናጋ ትምህርተ ተስፋፍቶአል:: እንዳንስት ይህ ለሰው ስጋ ምቾት የተዘጋጀ ነፍስን ግን የሚያጠፋ ትምህርተ ነው::100% ከሕይወት መፀሐፍ ላይ ስማችን ይደመሰሳል እንደ ቃሉ የማንኖር ከሆነ:: በውሸት ተስፋ የሚሞሉ ና ከቃሉ ውጪ የሚያስተምሩ እራሳቸው ገደል ገብተው ሌላውንም ይዘው ገደል የሚገቡ ስለሆኑ ከእንደዚ አይነቶቹ እንጠበቅ:: ቃሉ እውነት ነው አይሻርም::
ጌታ ይርዳህ
እንደው ምን አለበት የወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን አገልጋዮች ኢንተርቪው በሚዲያ በአደባባይ መካሰስ የቤተክርስቲያንን ድክመት ማውራት መሳለቂያ መሆን ቢቀር ሌሎቹ ሃይማኖቶች ጉድለት ስህተት የለም ? ሺ ጉድለት አለ ግን አያወሩም ጴንጤ ግን መካሰስ ብቻ ማስተዋልን ይስጣችሁ 🖤
medanachin yetemeseretew eyesus lay nw esu sileyazen nw medanachin maywesedew bro..... ye eyesusin sira atakalu
ዳግም መወለድ፣ ከእግዚአብሔር መወለድ ማለት ነው። በዚህ ከተስማማን 1ዮሐ 4:9-10 ላይ፦ "ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኀጢአትን አያደርግም" ይልና ምክንያቱን "በውስጡ ዘሩ ይኖራልና" ይላል። እዚህ ላይ ከእግዚአብሔር የተወለዱ ሁሉ የሚለው ቃል ዳግም የተወለዱ ሁሉ ኀጢአትን አይሠሩም ብሎ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ዘር ዳግም በተወለዱት ሁሉ እንደሆነ ያብራራል። ኀጢአት አይሠሩም ማለት ከናካቴው ኀጢአትን አይፈጽሙም ማለት ያይደለ ኀጢአትን የሕይወት ዘይቤ አናደርግም ማለት ነው። እናማ ዳግም የተወለደ ሰው የፈለገው ኀጢአት እየፈጸመ ድነቱ አይነጠቅም የሚለውን ትተን፣ ደግም የተወለዱ ሁሉ ግን ዘሩ በውስጣቸው ስለሚኖር ኀጢአትን እንደ የሕይወት ስልት አድርገው ስለማይወስዱ የዘላለም ድነታቸው አይነጠቁም። ዳግም ሳይወለዱ ነገር ግን ዳግም ተወልደናል የሚሉት ግን፣ ሲጀምር ወገን ስላልነበሩ ወገን እንዳይደሉ ይገለጥ ዘንድ ዳግም ከተወለዱት ሕብረትና ጉባኤ ይወጣሉ። በዚህ ላይ ምልከታችሁ ፈታ አድርጋችሁ ብታቀርቡስ!!
then መፅሐፍ ፊል ላይ የራሳቹን መዳን ፈፁሙ ይላል ካንተ አመለካከት ጋር እንዴት ልታስኬደው ነው?
አዎ ድኛለሁ ድነት እንዲሁ በቀላሉ ይጠፋል ከሚሉት ወገን አይደለሁም አብ ለእቃቃ ጨዋታ አንድያ ልጁን አይገድለውም ነበር። እግዚአብሔር የሰጠን ነገር በሙሉ ከሃላፊነት ጋር ነው አገልግሎት ቢሆን እድሜ ጤና እውቀት ሁሉ የሰጠኝ እንዳተርፍበት ነው ከሃላፊነት ጋር ድነትም ለኔ እንደዚሁ ነው ሃላፊነት ሰጥቶናል አውቃለሁ በዚች ሚጢጢ ማንነትህ እንዴት ነው የድነትን ሃላፊነት ምትወስደው እንደዛ ከሆነ ለምን ክርስቶስ ሞተ የሚል ጥያቄን ያስነሳል ሁሉም የሱ ነው ፀጋውም ምህረቱም የሱ ነው ከኔ ሚጠበቀው submission ብቻ አይደል
የተወደድክ Naal: ባቀረብከው መልእክት ተንተርሼ ጥቂት ምልከታየን እሰነዝር ዘንድ ወደድኩ። "አንዴ የዳነ ሰው ሊጠፋ ይችላል ወይም አይችልም?" በሚል አርእስት ዙሪያ በርካታ የቃሉ ተማሪዎች ያነጋገረ፣ ነገር ግን በኛ በአበሾቹ ዘንድ ብዙ ስፍራ የማይሰጠው ጠቃሚ ነገረ መለኮታዊ ጉዳይ ነው። እንዲህ ዓይነቱ ጠሊቅና ሰፊ ጉዳይ በጨበጣና በቆሮጣ ከስነ አውዳዊ አፈታቱ ባፈነገጠ አንድ ጥቅስ መመለስና መግባባት የሚቻል ከቶ አይደለም። ይልቅስ ሁሉም ገንቢና አናጺ ምክር ያቀፈውን ሙሉእ በኩሉሄ "Self Sufficient" ወደ ሆነው ሕያው ቃሉ በማዘንበልና በማትኮር ስለ ጉዳዩ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የተነገሩትንና የተፃፉትን በስርዓት ቀራርሞና ዳስሶ ማቅረብና መመርመር የሚሻ sensitive ጉዳይ ነው። ከአሥር ዓመታት በፊት በመፅሐፍ ቅዱስ ከወገኖች ጋር በዚህ ርእስ ዙሪያ በጥቂቱ ጨበጣ በሚመስል መልኩ ከተሟጎትን በኋላ፣ ምልከታየን ፈታ አድርጌ ለማቅረብ ወደ 28 ገፅ የያዘ፣ ከ 200 በላይ ጥቅሶች ያለበት ፅሑፍ በ email ልኬላቸው ነበር። ይህ ፅሑፍ የዳነ ሰው አይጠፋም የሚለውን የሚያሣይ ብቻ ያይደለ፤ ሊጠፋ ይችላል ሊያስብሉ የሚችሉት ቁጥሮችም ያካተተ ነው። ከእነዚህ አንዱ ጳውሎስ "Work out your salvstion " በማለት የመከረውና አንተ በጥያቄ መልክ የሰነዘርከው ነው። መልካም ፈቃድህ ከሆነ በ email ያልኩህ ፅሁፍ ልልክልህ እችላሉሁ። ካነበብከው በኋላም ሰከንና ረጋ ብለን በጥልቀት ልንነጋገርበት እንችላለን። ለጊዜው ግን የሚከተሉት ሦስት ጥያቄዎች መፅሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጌ በትህትና ልጠይቅህ። 1)በእውነት ከጌታ ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኀጢአትን እንደማያደርግና ለዚህም ጠንቁ የእግዚአብሔር ዘር በውስጡ ማለትም የአባቱ ዘር ስለሚኖር እንደ ሆነ ሐዋሪያውና ወንጌላዊው ዮሐንስ በ 1ዮሐ 3:9-10 በማያሻማ መልኩ ፅፏል። እዚህ ላይ "ሁሉ" የተሰኘው ቃል ቢሰመርበት በጎ ነው። አንዳንዶቹ ከጌታ የተወለዱት ብቻ ያይደሉ፣ ኀጢአትን የማያደርጉት ከእግዚአብሔር የተወለዱት ሁሉ ናቸው። እዚህ ላይ የዳነ ወይም ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ፣ ኀጢአትን እንደ የሕይወቱ ዘዬ አድርጎ አይወስድም፣ ኀጢአትን እንዳሻው እየተንቦጫረቀበት ድኖ የሚጠፉ ሳይሆን ከመነሻው ከእግዚአብሔር ያልተወለደ የነበረ ነው። በ 3:9-10 ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኀጢአት የማያደርግ ከሆነ፣ለምን ታድያ ይኮነናል ለምንስ ይጠፋል? ይህች ሳታቅማማ እየጎመዘዘችህም ብትጎነጫትት በጎ ነው። በዮሐ 6:37:39 ታላቁና ታማኙ እረኛችን ጌታችን ኢየሱስ "ኣብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፣ ወደ እኔ የሚመጣውንም ወደ ውጭ አላወጣውም፤ ከሰማይ የወረድሁት የራሴን ፈቃድ ለማድረግ ሳይሆን ፣የላከኝን የእርሱ ፈቃድ ለመፈጸም ነውና፣ የላከኝም ፈቃድ፣ ከሰጠኝ ሁሉ አንድ እንኳ ሳይጠፋብኝ በመጨረሻው ቀን እንዳስነሣ ነው።" . አየህ ወዳጄ፤ አብ ካልሰጠው በቀር ወደ ወልድ በራሱ ተነሣሽነት ማንም ሊመጣ እንደማይችል ልብ እንበል፣ ደግሞም ወልድ የመጣው የአባቱ ፈቃድ ያም አባቱ ለእርሱ የሰጠውን ለመቀበል እንደ ሆነም እናስተውል። አብ ለወልድ የሰጣቸው ሁሉ የዳኑና፣ የተቀበላቸውን ሁሉ በመጨረሻዋ ቀን እንደሚያስነሣቸው እናስምርበት። በቀላል ቋንቋ አብ ለወልድ ከሰጠው ማለትም ከዳነው አንድ እንኳ ሳይጠፋ በመጨረሻዋ ቀን፣ ማለትም በሙታን ትንሣኤ እንደሚያነሣ ወልድ ይነግረናል። ታድያ አንዱ በአብ ለወልድ ተሰጥቶቶ በመጨረሻው ቀን እንዳይነሣና ድነቱ እንዲነጠቅ የምታደርገዋ ቀዳዳ የቷ ትሆን? መድረኩ ጠባብ ስለሆነ፣ ሦስተኛው ማለትም በሮሜ 8:38-30 ወርቃማዎቹ የድነት ሰንሰለቶችን "The Golden Chains of salvation" ለማቅረብ ኡልቻልኩም። የጌታ ፀጋና ሰላም ከአንተ ጋር ይሁን! አሜንና አሜን!!!
ዮሐ 1:13 እንዴት አያችሁት ብታብራሩልኝ
ወንድሜ ስለ ክርስቶስ መከራ ስቃይ፥ በኢትዮጵያ ውስጥ ስላሉት ሀሰተኛ ነብያቶች ለምትናገረው ሁሉ ልክ ነው ።ነገር ግን ዋናህን ጥለሀል! እርሱም የዘላለም ህይወት (ደህንነት) ላይ ያለህ አስተምሮ ፈጽሞ አደገኛና ኢ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው። እርሱን በሚመለከት የጠቀሳቸው ጥቅሶች በሙሉ ስህተት ናቸው ያለ አዉድ (context) ነው የጠቀስካቸው። በተለይ ቆላስያስ ምራፍ3 ላይ" የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርሱም" ብለህ የተናገርከው ጨርሶኑ የለም።
እና ወንድሜ ጥሩ ነገር አለህ ነገር ግን ስለ ደህንነት እና የዘላለም ሂወት ቁጭ ብለህ መማር ያለብህ ይመስለኛል።
He is not wrong, you can read Hebrews 3,6,10,12 and 2 Peter 2, unbelief can lead to someone forfeiting their salvation. Especially Hebrews 3:7-19 & 6:4-8 shows this. I think he could've said that willful sin can lead to unbelief but he said it mostly correct. Blessings.
አረ በጌታ ግብዞች አትሁኑ ኢየሱስ የከፈለው ውድ ነው።
1peter1:21_23
የዳነ እግዚአብሔር ልጄ ያለው እንዴት ልጅነቱ ይወስዳል?
Bednb yewosedal be fetu betikikl kaltemelasek lemsale 10 denagel 5 yebertu neber 5 senefoch neberu yilal kezam behuala yeberetuti 5 kegeta Gare sehedu 5 senefoch alawkachihum ke wodet endehonachihu alachew gin 10rum kirstos teketaye neberu
ሰላም ለናንተ መጠየቅ የሚፈልገው ነገር ethiopia ቸርች ላይሆን ያለው ነገር ትክክል ነው ብሎ ያምናል
ሕያው ነፍስ ሆነ አይልም "ሕያው ነፍስ ያለው" “እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።”
- ዘፍጥረት 2፥7
“እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ከምድር ዐፈር ወስዶ ሰውን አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ሆነ።”
ዘፍጥረት 2:7 NASV
እኔም አልተሳሳትኩም። አበጀዉ የሚለዉ hardware አካሉን ነዉ። የሰዉ መንፈስ አስቀድሞ በዘፍጥረት 1:27 ተፈጥሯል። ይህን ታምናለህ ወዳጄ?
ቆላስይስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ እንግዲህ በምድር ያሉቱን ብልቶቻችሁን ግደሉ፥ እነዚህም ዝሙትና ርኵሰት ፍትወትም ክፉ ምኞትም ጣኦትንም ማምለክ የሆነ መጎምጀት ነው፤
⁶ በእነዚህም ጠንቅ የእግዚአብሔር ቍጣ በማይታዘዙ ልጆች ላይ ይመጣል፤
⁷ እናንተም ደግሞ ትኖሩባቸው በነበራችሁ ጊዜ፥ በፊት በእነዚህ ተመላለሳችሁ።
የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርስም የሚለው የታለ ።
የዳነ ሰው ለሚሰራው ሀጢአት በስጋው ይቀጣል ከመዳን ጋር ግን አይገናኝም ።
በኛ አገር ክርስትና አስተሰብ ልክ ነህ ጥልዬ መጀመርያ የተፋጠራዉ መን መሆኑን አልገለጥክም ይህንን አልገለጥክም ማለት ሙሉ ስህተት አስተማር ሆንክ ማለት ነዉ አንድ መጨመር አንድ መቀነስ አትችልም ለምሰሌ ዘፍ 1÷26 27 ይህን መሰረተዉ የመጽሐፍ ቅዱስ እዉነት አጠመምክ ማለት ከፍርድ ስር ወድቀሃል ተጠንቀቅ በኔ በኩል ሻሎም
ሰላም ላንተ ይሁን ነብ ይጥላሁንን ማግኘት እንዴት ይቻላ?
John 3:6
ስለክርስቶስ መከራ መቀበል እራሱን የቻለ ጉዳይ ነው ነገር ግን ስው በተለያየ እጅግ ከባድ ስቃይ ውስጥ በልጅ ህመም ብዙስቃይ ውስጥ ሲያልፍ የእግዚአብሔር የፀጋ ስጦታ አላቸው ብሎ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይፀጋው ስጦታ አላቸው ብሎ ቢሄድ ለምን እንደስተተኛ ይቆጠራል? የእግዚአብሔርን ምህረትና ቸርነት መፈለግ ስተትም አይደለም ሰዎች ን መኮነን ጥሩ አይደለም ይህ ስዉ ጥሩ አስተማሪ ነው ሆኖም አንድ አንድ ነገሮች --
Ere voice aysemam bedenb
Thank you for your comment we will correct it
Just remember what happened to the People of Israel. God promised them the Promise land. However, they don't listen and obey his words, they ended up in desert. Same analogy applied for z believers, if we don't lived here on earth accordingly, we definitely lost our salivation. Do Not Deceived!! When you doing the sin you are going to be on the list of the sinner unless you repent truly, and never do same sin. Believing in Jesus doesn't mean you have a license to do whatever you like on this earth. You should crucify your body with Christ then you inherit the kingdom of God. Don't decived. Remember God is holy & his kingdom reject unholy being. Careful, do not Deceived brothers and sisters. We have to disciplined and change our heart and life. The HOLYSPIRIT is here to help us in the process. Ask him a grace a power, he will do it, but don't expect to rip what you don't saw. God is Just!!
በአምሳሉ ከተፈጠረ እግዚአብሔር እኛን ካልመሰለ እኛ እርሱን ከመሰለን እንግዲህ ምን ከባድ አይደለም ሰው መንፈሰ ነው ። መንፈስ ማለት እኮ አካል የለውም ማለት አይደለም
Yonas Embiale ተባረክ። በአምሳሉ ለተፈጠርንበት ጉዳይ የጌታ መልክ ምን እንደሚመስል ዮሐንስ 4:24 " እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል" ይላል። በመልኩ የፈጠረንን እንመስላለን።
መንፈስነታቹ ተገልጦ እስክናይ አናምንም ና አናግረኝ 😂😂
ጥሌ ዘመንሕ ይባረክ ፀጋ ይብዛልህ
በማብራራት ብዛት እውነትን መደበቅ አይቻልም።
ጌታ እየሱስ አብዝቶ ይባርክህ
2 nd qorontos chapter 3 ewneten lemeketel yemiwedu hulu ysededalu haseteghoche gn eyesatuna eyasatu yqexlalu jhon 22 tha dikum yetsidek erkusum yerkes leyehulum endyesraw ekefle zend wagaw beeje new bloal eyesus
Yhe sewye mlu konfidens yalow ymeslal bible gn bedemb yeteredaw aymeslegnm. 1yohans 3: 6
ድምፅ ?
You don't even care about the sound quality. You are too quiet and hard to listen. Make sure you sound check first going into recording or to air.
If i can lose my salvation I will lose it
ጥሌ እየሱስን በማቆላመጥ እየገለፅከው የዳነ ድነቱ ይወሰዳል ?
Dink show 👍👍👍
DAWIT FASIL ይቅረብልን
??????
Please read and study the word of God by taking time. If you try to mention the verses from the Bible with out the context and try to promulgate any doctrine,that may lead people to destruction.
Geta iysus yerdahale
በነገራችን ላይ one saved forever saved ታላላቅ ስኮላሮችም የሚያምኑበት ትምህርት ነው ጆን ማካርተር ጆን ፓይፐር ጨምሮ ድነት አይጠፋም ሲሉ ያስተምራሉ ያው ጥሌ ኢየሱስን ቢያወራ ያምርበታል ከዛ ውጪ የተፋቀ ውሸት ነው ሚሆነው የሚያነሳው ሀሳብ በራሱ ስነመሎኮታዊ አመክንዮ የለውም።
@elkadoshministry905i know
ደምጽ አይሰማም
በጣም እሚገርመው ግን 99% ፔንጤዎች አንዴ ድነናል በሚል ሲመፃደቁ ነው የምናየው
አሁንም ቢሆን በስራችን አይደለም የዳንነው። የዳንነው ክርስቶስ በሰራው ስራ ነው።ስለዳንን ነው የመዳንን ፍሬ የምናፈራው ወይም በቅድስና የምንኖረው እንጂ ለመዳን አይደለም የምንለፋው! ኑሮአችን የመደናችን ነፀብራቅ ነው። ምን አልባት አንቺ ወይም አንተ በስራ እንደሚድን ሰው ነው የምትለፉት። እዚ ውይይት ላይ ያለው ሃሳብ ይከብድሻልና ተይው!!!
ድምጻችው አይሰማም
አጭበርባሪ ነብያቶች እየሄድክ ታበረታታለህ ገንዘብ ስለሚሰጡኽ ነው። ለምን ኢመጽሐፍ ቅዱስ ልምምድ ያደረጉ ዝም ትላለህ ?
የሰውን የአፈጣጠር ታሪክን በቅርበት ስንመለከት ስጋውን ከምድር አፈር አበጀው ከአፉ በወጣው እስትንፋስ ደግሞ ነፍስን ሰጠው ይለናል፡፡ በዚሀ ቀመር ከሄድን ሶስተኛው አካል የሆነው መንፈስ የቱ ጋር ነው ሲፈጠር የምናየው፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ካየነው ሰው ሲሞት ስጋው ወደ አፈር እንደሚሄድ ነፍስ ደግሞ ወደፈጣሪዋ እንደምትሄድ እንጂ ነፍስና መንፈስ እንደሚሄዱ አልተነገረንም፡፡ ኢየሱስም ሲሞት ነፍሴን በእጅህ አሳልፌ እሰጣለሁ አለ እንጂ ነፍስና መንፈሴን አላለም፡፡ ከዚህ አንጻር የሰውን ሁለንተና በሶስት (ትራይኮቶሚ) ማስቀመጥ እንዴት እንችላለን፡፡
1 korontos 6_ 15 MN telwaleh Lela demo uehi mekaber emgbaw segachn aynesam endi ?