ያ ደቀ መዝሙር - ዲያቆን ማኑሄ ዳዊት
Вставка
- Опубліковано 1 січ 2025
- ያ ደቀ መዝሙር
የኤፌሶን ዓምደ ወርቅ የፍጥሞ ብርሃን
ክቡር ወንጌላዊ ምክሃ ቅዱሳን
ፈለገ ሃይማኖት መብረቀ ስብሐት
የጥበባት ባሕር ዮሐንስ ማኅቶት
ታማኝነት ጌጡ ትህትና ነው ልብሱ
ትዕግስት መገለጫው ፍቅር ነው ስብከቱ
የቁርጥ ቀን ወዳጅ የአምላክ ደቀ መዝሙር
ሰባኪ ዜናሁ ለወልደ አምላክ ክቡር
ያ ደቀ መዝሙር ወልደ ነጎድጓድ ነው
ቃልም ሥጋ ሆነ ብሎ የሰበከው
አዝ= = = = =
በመስቀል ስር ያለው ብቸኛ ሐዋርያ
ልዩ ነው ዮሐንስ የሌለው አምሳያ
ጌታ ይወደዋል ከሁሉም በላይ
ስራው ስላበራ በምድር በሰማይ
ያ ደቀ መዝሙር ፍቁረ እግዚእ ነው
በዚያ የስቃይ ቀን ጌታን ያልተለየው
አዝ= = = = =
በእብነ በረድ ላይ ስቅለቱን ቢስለው
አንደበት አውጥቶ ስዕሉ አናገረው
በዕንባ ተሞልቶ አቅፎ ቢሳለመው
ወዳጄ አገልጋዬ ዮሐንስ ሆይ አለው
ያ ደቀ መዝሙር ቁጹረ ገጽ ነው
ሰባ ዘመናትን ሲያነባ የኖረው
አዝ= = = = =
ፍጥሞ በምትባል በአንዲት ደሴት ላይ
ሰባት መቅረዝ ታየው ተከፍቶለት ሰማይ
የአዲስ ኪዳን ነቢይ ባለ ራዕይ እሱ ነው
የዓለሙን ፍጻሜ ክርስቶስ ያሳየው
ያ ደቀ መዝሙር አቡቀለምሲስ ነው
ከሐዋርያቱ ራእይ የጻፈው
ዲያቆን ማኑሄ ዳዊት